እምነት የሚጣልባቸው አዋቂዎች እና እድገትን የሚያፋጥኑ ግንኙነቶች
ሰው
በችሎታው ብቻ አያድግም። ከሚያስተምሩት፣ ከሚያርሙት፣ ከሚያበረታቱት፣ ከሚገዳደሩት እና ከሚከፍቱለት ዕድሎች ጋር በሚገነባው ግንኙነትም
ይወሰናል።
አንድ
መሪ በዙሪያው ያሉትን ሰዎች ሳይመርጥ ከተጓዘ፣ የራሱን አቅም ሊገድብ ይችላል። በተቃራኒው፣ በጥበብ የተመረጡ ግንኙነቶች የእውቀት፣
የእድል፣ የምክር፣ የተጠያቂነት እና የጥበቃ ምንጭ ይሆናሉ።
1.
ሁሉም ግንኙነት አንድ ዓይነት አይደለም
ብዙ
ሰዎች የሚያውቁህ መሆናቸው ብዙ ጠቃሚ ግንኙነቶች አሉህ ማለት አይደለም።
·
አንዳንድ ግንኙነቶች ጊዜህን
ብቻ ይወስዳሉ።
·
አንዳንዶቹ ኃይልህን ያሳንሳሉ።
·
አንዳንዶቹ ወደ ኋላ ይጎትቱሃል።
·
አንዳንዶቹ ግን እንድታስብ፣
እንድትማር፣ እንድትደፍር እና እንድታድግ ያደርጉሃል። ስለዚህ ጥያቄው “ስንት ሰዎችን አውቃለሁ?” አይደለም። ጥያቄው፦
“በዙሪያዬ
ያሉት ሰዎች እኔን ወደ ምን እንድጓዝ እያደረጉኝ ነው?”
2.
አዋቂ ሰዎችን መፈለግ