የክፍል ሶስት መጠናቀቅ
ብዙም ቀጣዩን ክፍል እንድንጓጓለት ባያደርገንም አንድ ነገር ይዞ እንደሚመጣ ግን ተስፋ እናደርጋለን፤ ከፊሎች ደግሞ በጉጉት ጠብቀዉታል
ይህ አጋጣሚ መጨረሻዉ ምን ይሆን? እያሉ ለሁላችሁም ክፍል አራትን እነሆ እላለሁ፡፡ መልካም ንባብ ! የማነበብ ባህላችንን እናዳብር፡፡
‹‹ በልቼ ዕቃ ሳላጥብ ማዋልና ማሳደር አልወድም ንጽህና የሌላትንም ሴት እንደዛዉ አልወድም ፣
ማንንም ቢሆን …. አላደረገችዉም እንጂ እናቴም ብትሆን
ይቅርታ አጥቤ እስክመጣ አልበም ነገር ልስጥሽ እንድትደበሪበት?››
ይቅርታ አጥቤ እስክመጣ አልበም ነገር ልስጥሽ እንድትደበሪበት?››
ቆይ ሴት እያለማ ወንድ ልጅ ምንም ቢሆን ዕቃ አያጥብም ባይሆን የእስካሁኑ
እንግድነት ይብቃኝና እኔ ልጠብ (የሴትና የቄስ እንግዳ የለዉም ሲባል ስለምሰማ) አልኩት የዉሸቴን ዉስጤ ግን የሚፈልገዉ በአልበሙ ገጾች ላይ ከተሰደሩት መካከል አንድ ጉብል አንገቱ ላይ ተጠምጥማ፣
እሱ ደግሞ እንደ ዘንዶ ወገቧን አለቅ ብሎ ‹‹ችቦ አይሞላም ወገቧ›› እያለ ሲያወድሳት ያለበትን ፎቶግራፍ አይቼ ልቤ እንዲያርፍ
ፈለኩ ምንም እንኳን እሱን ፎቶ ለማየት የዉስጥ ጥንካሬ ባይኖረኝም፤
‹‹ በፍፁም አይደረግም እስካሁን ያደከምኩሽ አንሶ በዛ ላይ …. የማይታሰብ
ነዉ፤ ባይሆን ….››
ምን አደከምከኝ መብላት ያደክማል እንዴ? ያወራነዉ ሁለታችን ምን የተለየ
ነገር አደረኩና ነዉ ያደከምከኝ? …. ‹‹ ባይሆን›› ያልከዉ ምኑ ነዉ?
‹‹ ባይሆን ሌላ ጊዜ ማለቴ ነዉ፤ ››
ልላ ጊዜ መቼ? ልቤ ከቅድም ይልቅ አሁን የባሰ መምታት ጀመረ፤ ደስስስ …. …ስ አለኝ በቃ ዳግም በዚህ ቤት እንደምስተናገድ ተስፋ ሰነኩ፡፡
‹‹ የእስካሁኑ ይሁን ብለናል አሁን ለምን ፍራሹ ላይ አትቀመጭም
… … እኔ ሳህኖቹንና ድስቱን ልጠብ የተዝረከረከ ቤቴን ላጽዳ ድንገት እንግዳ እንኳን ቢመጣ፤ ››
እንዴ የሚመጣ ሰዉ አለ እንዴ? … በማለት ፍራሹ ላይ ልቀመጥ ጫማዬን
ላወልቅ የነበረችዉ ሴትዮ ‹‹ ባለህበት ቁም ›› የሚል ወታደራዊ ትዕዛዝ እንደደረሰዉ ሰዉ በንቃት ባለበት ቆምኩ፤
‹‹ ኧረ ስቀልድሽ ነዉ እንኳን ሌላ ሰዉ ቤቴ እኔንም በስራ ቀን ቤቴ
እንዲህ በብርሃን ያገኘችኝም ዛሬ ነዉ ››
አብረን ተገኘና፤ … ታድዬ አልኩ ሳላዉቀዉ አልሰማኝም ነበርና መልስ
አልሰጠኝም
ስለብቸኝነቱ ሲያወራኝ ደስታ ይሰማኛል ነፍሴ ሃሴት ታደርጋለች የዛሬዉን
አያድርገዉና ከቤ እንዲህ ቁጭ ብለን ሲያወራኝ እኔ ብቻ በልቡ እንዳለሁ፣ እኔ ብቻ የሱ እንደሆኑኩ፣ እሱ የኔ ብቻ እንደሆነ፣ ሴት
የሚለዉን ነገር ከፆታነት ባሻገር ያለዉን በእኔ እንዳወቀ ሲነግረኝ፣ ‹‹ፍቅር ማለት ምን ማለት ነዉ? ተብዬ ብጠየቅ አንቺ ነሽ
ብዬ እናገራለሁ ›› እያለ በጆሮዬ ሲነግረኝ፣… የዚህች ዓለም ንግስት የሆኑኩ ያህል ትልቅ ክብርና ኩራት ይሰማኛል፤ እነዚህን የመሳሰሉ
ወሬዎች ስሰማ ዓለምን የጨበትኩት ያህል ክብር፣ ኒሻን የተሸለምኩ ያህል ጀግንነት ልቤን ይሞላዋል፡፡ገበያ መሃል እንደዋለች ቅቤ
ቀልጠሸ እለቂ እለቂ ይለኛል … …
በህይወቴ ዘመን ወንድ ልጅን በሌላ ሴት የተቀደምኩት አንድ ጊዜ ብቻ
ነዉ፤ እሱም ቢሆን የሚሰጠኝ ፍቅርና ክብር የመጀመሪያዉ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ ለፍቅር የዉጭ ዜጋ እያልን የምንቋምጠዉን አምሮቴን
እንደኩፍኝ ነበር ነቅሎ ከዉስጤ ያወጣልኝ ሆቴል ስንገባ ወንበር ስቦ እስቀምጦኝ፣ ስንወጣም ስንገባም የሆቴል በር ስቦ ከፍቶ የሚያስወጣኝና
የሚያስገባኝ ነበር፡፡ ምን ይሄ ብቻ መኪና እንደ አንባሳደር ከፍቶ አስገብቶ ከፍቶ ነበር የሚያስወርደኝ፤ መኪናዉ ተበላሽታም ሆነ
ለቼክአፕ ጋራዥ የገባች እንደሆነ እንኳን ታክሲ ይዤ እንድመጣ እድሉን አይሰጠኝም ሰፈር ድረስ መጥቶ በኮንትራት ታክሲ ይዞኝ ሄዶ
ይመልሰኝ ነበር፡፡
ያበሻ ወንድ አያዝልቅልህ ተብሎ የተረገመ ይመስል እንደዛ ከቤን በማጣት
የተጎዳ ልቤን እንዳልጠገነዉ ፍቅሩ ሲያልቅበት አጠገቡ እያለሁ ሌላ ሲፈልግ እኔ ሁሉን ነገር ሳልነፍገዉ ሌላ ሴት ጋር ሄዶ አገኘነዉ
ቢሉኝ እንደ ፍቅረኛ ሳይሆን እንደ ጓደኛ ተመለስ ይቅርብህ ብዬ ብመክረዉ ‹‹ በፍፁም የምትይዉን ነገር አላደረኩም ›› ብሎ ካደኝ፤
እሺ አላደረክም ሰወች በፍቅራችን ቀንተዉ ስለሆነ ሃሳቡም አይኑርህ ችግራችንን በመነጋገር ለመፍታት ጓደኛ፤ ለዘላቂ ኑሮአችን ደግሞ
ፍቅረኛሞች ሆነን እንዝለቅ ብለዉ ከሰዉ የሰማሁትን በዓይኔ አይቼ ብመክረዉም እምቢ አለ፡፡ እሷ ያላትን ነዉ እኔም ያለኝ በማለት
በእርሷ ላይ ወደ አንተ አልመጣም ብዬ ተለየሁት፡፡ ፈጣሪዬንም ምናለበት በሰላም የቆመዉን የአክሱም ሐዉልት ጣሊያኖች ቆርጠዉ ከሚወስዱብን
የወንዶቹን ብልት ቆርጠዉ በወሰዱት ብዬ አማረርኩት፡፡
ደስተኛነቴን እንጂ ሃዘኔን አይቼ የማላዉቀዉ ሴትዮ በወንዶች ባህሪ
ጨጓራ በሽተኛ ሆኔ ጸበል ሄድኩኝ እድሜ ለኩክ የለሽ ማርያም፣ እድሜ ለጻድቃኔዋ ማርያም ተፈዉሼ ስመጣ ይኸዉ ፈጣሪ ምን ይሳነዋል
ለሐዋርያት በተዘጋ ቤት ዉስጥ ተገኝቶ ያጽናናቸዉ መንፈስ ቅዱስ አጽናኝ አድርጎ የላከ አምላክ ለኔም በተዘጋ ቤት ዉስጥ ይህን የመሰለ
ለግላጋ ወጣት ሰጥቶ ሊያጽናናኝ ይሆናል በማለት ፍራሽ ላይ ቁጭ ብዬ እመኛለሁ፡፡ብዙዎች እንዳልተመኙኝ እና እንዳለገኙኝ ይኸዉ በሰዉ
ቤት ወንድ እመኛለሁ፡፡
‹‹ ተጫወች እንጂ … ከደበረሽ ደግሞ …. ምን ያህል እንደምትወጂ
ባለዉቅም ሙዚቃ ልከፍትልሽ እችላለሁ … ›› በማለት የሙዚቃ ሲዲ ወደ ማጫወቻዉ አስገብቶ ከፍቶ ሄደ እንዳጋጣሚ የተከፈተዉ ሙዚቃ
የግርማ ተፈራ ካሳ ነበር ‹‹ ታድያለሁ … ›› እያለ ማቀንቀኑን
ቀጠለ፤ ልቤ ተረበሸ ‹‹ የኔ ቆንጆ … ፍቅር ተመግቤ›› የሚሉት ስሰማ እሱ እኔን ያለኝ ያህል ልቤ በድብቅ ፍቅር ቀለጠ፡፡
‹‹ በአፍላነት ዘመን ሳገኝሽ ስጦታዬ አንቺዉ ነሽ›› እበጂ እበጂ አለኝ የሚያደርገኝን አሳጣኝ፤ ዉስጤ ደግሞ ያለሽዉ ሰዉ ቤት
ነዉ ለዚያዉም ኩሩ ወንድ ቤት አርፈሽ ተቀመጭ! እራስሽን ትዝብት ዉስጥ እንዳትከቺ ላንቺ ያለዉንም ግምት እንዲወርድብሺ አታድርጊ
ብሎ ሸብቦ አስቀረኝ እንጂ እንደራሴ ቤት ጮክ እያልኩ ከግርማ ጋር ባቀነቅን የሚወጣልኝ መስሎ ተሰማኝ አጉል ባህላችን ግን ባህል
በሚባል ሽባ ገመድ ጠፍሮ ከፍራሹ ላይ እንድቀመጥ ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈልኝ፡፡ ዘፈኑን በዉስጤ ጓዳ ቆልፌበት እኔ በሃሳብ ፈረስ
ሌላ ዓለም ዉስጥ ገባሁ፡፡
በተዘጋ ቤት ዉስጥ መኝታ ቤቴ ገብቻ ‹‹ አንተ ልጅ … ›› የሚለዉን
ዘፈን ለከቤ እንዳልዘፈንኩ ገልብጬ ለሱ ዘፈንኩለት
‹‹
ሴቶች ተገለባባጮች ናችሁ ›› የሚለዉን ሃሜት ነዉ ብዬ ጆሮዬን ደፍኜ እንዳልነበር ዛሬ ለራሴ እዉነት መሆኑን አረጋገጥኩ ግልብጥ
ብዬ ዛሬ ለዚህኛዉም ስዘፍን፤ መሆን የነበረበት ግን እንደ እሳት ተዳፍኖ ላለዉ ለከቤ ፍቅር ነበር ሴት አይደለሁ ግን ተገለባበጥኩ
ከመጣዉ ጋር አዳሪ፡፡
‹‹ ሸማመተዉ ይሄ ሰዉ ሸማመተዉ፣
ሸማመተዉ ይሄ ልጅ ሸማመተዉ፤…. ››
የሚለዉን
የመኪያ የፍቅር ዘፈን ስንኞቹን አለማወቄ አበሳጨኝ፡፡ ስለ ዉበቱ፣ቁመናዉ፣ጨወታዉ …ለማድነቅ ፈልጌ ስንኝ አጣሁለት
‹‹ሸማመተዉ ሸማመተዉ ሸማመ….ተ…..ዉ…. ቁንጅናን …ቁመናን….ሸማመተዉ….ጨወታን
….ሸማመተዉ…..ሸማመተዉ….››
‹‹ ትኩስ ነገር ቡና ወይስ ሻይ ምን ትፈልጊያለሽ?›› ከምኞት ፈረሴ
ላይ አዉርዶ ፈጠፈጠኝ፤
አ…..ይ ምንም በቃ…እ…. ጠ….ጠጥቻለሁ! ተደነባበርኩ ዋሸሁት ‹‹
ጠጥቻለሁ ›› በማለት፡፡
‹‹ ለስላሳ ምን ይምጣልሽ?››
ምንም
…ምንም አልፈልግም፤ ለምን ቁጭ ብለህ አታጫዉተኝም
በቃ አሁን ልቀመጥ ነዉ የመጨረሻ መስተንግዶዬ ነዉ ከዛ ቁጭ ብዬ ቻት
እናደርጋለን ካካካካ (ሞቅ ያለ ሳቅ ሳቅን) በፌስ ቡክ የምናደርገዉን ቻት ለጨወታ ማድመቂያ ጣል እንዳደረጋት ገባኝና እኔም አብሬ
ሳኩኝ
የላስቲኩን ሚሪንዳ ቀድቶልኝ ሞቅ ወዳለ ጫወታችን ተንደርድረን ገባን፤
*******/////******//////******
ቤትህ የሴተላጤ እንጂ የወንደላጤ ቤት አይመስልም፤ … ነገሬን ጀመርኩ
እንግዲህ የኮቴ ከፍዬ ኤንባሲ የገባሁና ቪዛ ካልተመታልኝ እንደሚቆጨኝ ያህል ተሰማኝ የሆነ ነገር ስለሱ ሳልሰማ ከቤቱ ከወጣሁ
‹‹ ለምንድን ነዉ ሁል ጊዜ ቆንጆ ቆንጆዉን ጥሩ ጥሩን የራሳችሁ የምታደርጉት
በጣም ብዙ ሴቶችን የታዘብኩት ነገር ንጹህ ነገር ሁሉ የእናንተ፣ የዓለም ጠበብት የሆናችሁ ያህል ስታወሩ ሰማለሁ… አናቃችሁም ሽንኩርት
እንኳን የሚያርባችሁ አይደላችሁም እንዴ፤ ወንድን መያዝ ሳትችሉ እንዴት ነዉ?… ለምን ታናግሪኛለሽ? እስኪ እንተወዉ ስናዉቀዉ አለች
አሉ ››
እንዴ ብዙ ሴት ታዉቃለህ ማለት ነዉ? በድንጋጤ እና ተስፋ በመቁረጥ
ነበር ይህን ጥያቄ የሰነዘርኩለት
‹‹ ማለት? አልገባኝም ማን አለሽ?››
እንዴ አሁን ራስህ ብዙ ሴቶች አዉቃለሁ ስትል አልነበር እንዴ ነዉ
ወይስ ጆሮዬ ነዉ ብዬ ተጠራጠርኩ
‹‹ እንደዛ ያልኩት እንደዚህ ስለሴት ሙያ አዳምቀዉ የሚያወሩ ለማለት
ነዉ እንጂ እንደዚህ ቤቴ መጥታ ፍራሼ ላይ ተቀምጣ ያወራችኝ ለማለት ፈልጌ አይደለም፤››
ቆይ
ግን እንደዚህ ቤትህ መጥታ ፍራሽህ ላይ ተጋድማ ከጉያህ ተሸጉጣ ያወራችህ ያወራሃቸዉ ስንት ናቸዉ? ብዬ ለመጠየቅ ፈለኩና በልቤ
አሳደርኩት፡፡
‹‹ ጠጭ …›› ብሎ ብርጭቆዉን አቀበለኝ
ያፈረ እንግዳ ባለቤቱን ይጋብዛል እንዲባል አንተም ብርጭቆ አምጣና
ቀድተህ ጠጣ እነጂ ብዬ ጋበዝኩት
‹‹ የነበረኝ ብርጭቆ ሶስት ነበር ሁለቱን ሰበርኳቸዉ አሁን የቀረዉ
ይሄ ብቻ ነዉ ስለዚህ አንቺ እስክትጠጪ ወረፋ መጠበቅ አለብኝ›› ብሎ ሙዚቃ የሚመስለዉን ሳቁን ለቀቀዉ፡፡
አብረን መጠጣት እንችላለን፤ ካልኩ በኃላ እፍረት ተሰማኝ
‹‹ ተመርምረሸል?››
ድርቅ የሚያደርግ ድንጋጤ ደነገጥኩ፤ ምኔን?
‹‹ አብረን እንድንጠጣ አፍሽን ነዋ በአንድ ብርጭቆ ለመጠጣት የአፍ
ምርመራ እንጂ ሌላ ምን ያስፈልጋል? ››
በምርመራ በኩል ችግር የለብኝም አንተ ለመጠጣት ዝግጁ ከሆንክ እንኳን
የአፍ ምርመራ የኤች.አይ.ቪ. ምርመራ ያረኩት በቅርቡ ነዉ፤ ከፈለክ ደግሞ አብረን ማድረግ እንችላለን፡፡ ቅብጥርጥር ማለቴ ታወቀኝ
ምን አገናኝቶት ነዉ ስለ ኤች.አይ.ቪ የማወራዉ? ነዉ ወይስ ንፁህ ነኝ እያልኩ ማመልከቻ ነዉ?
‹‹ በቅርቡ ኤች.አይ.ቪ. ምርመራ ያረግሽዉ በሰላም ነዉ ወይስ የምትጠራጠሪዉ
ነገር ነበር? ይቅርታ ግን፤››
ምንም ችግር የለዉም እንዳልኩህ ጻድቃኔ ከመሄዴ በፊት ለመመርመር ብዬ
በጣም ፈራሁ ከዛ ስመለስ ወኔዬ ጨመረ መሰለኝ ለመመርመር ድፍረት ሳገኝ ተመረመርኩ እንደፋራሁት ሳይሆን ነጻ ነሽ ተባልኩ፤
‹‹ ምን የሚያስፈራ ነገር ነበር?›› በተመስጦ ሆኖ ነበር እንደጋዜጠኛ
የሚጠይቀኝ፤ እኔም ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ ሁሉንም ነገሬን ዘርዝሬ ነገርኩት፡፡
‹‹ ኦ በጣም ደስ ይላል!›› ብሎ ዝም አለኝ አንተስ? ለማለት ግን
ድፍረት አጣሁ፤
‹‹ ተጫወች ›› ብሎኝ በመስኮት በኩል ሃይለኛ ነፋስ እየገባ ስለነበር
መስኮቱን ሊዘጋ ተነሳ፤ ሲመለስ ተመልሶ ዱካዉ ላይ ሊቀመጥ ሲል በጣም የተራራቅን ስለመሰለኝ አጠገቤ ፍራሹ ላይ እንዲቀመጥ ግድ
አልኩት፡፡ አልዋሽም በጣም ወድጄዋለሁ፤ እሱ ካልተጃጃለ መዉደዴ በደንብ ያስታዉቃል ዘና ብዬ ነዉ የተቀመጥኩት የለበስኩት ልብስ
ስላልተመቸኝ የሱሪዬን ቁልፉንም ዚፑንም ከፍቼ ነበር የተቀመጥኩት …. ቢሆንም ፍርሃትም ሆነ እፍረት አልተሰማኝም፡፡እንዲመቸኝ ትራስ
እንድደገፍ አቀበለኝ ችግር የለም ይበቃል፣ ተመችቶኛል፣ … በሚሉ ተልካሸ ምክንያቶች እንደመግደርደር አልኩ፡፡
‹‹ ቆሎ ትወጃለሽ?››
ጥሬ እና ቆንጆ የማይወድ ማን አለ? መልሶቼ ሁላ የሚገርሙ ናቸዉ መዘባረቄ
በዛ የማይገናኝ ነገር አወራ ጀመር፤
‹‹ መልሱ አዎ ነዉ! ተረት ባለዉቅም ቆንጆ እና እሸት መሰለኝ የሚባለዉ››
አዎ! ወዳለሁ አምጣልኝ፤
*************///////////*****//////****/////*******************
ቤቲ ደጋግማ ብትደዉልም ማንሳት አልቻለኩም ባነሳ የምታወራኝ ስለሱ
ነዉ ምን ብዬ መልሳለሁ? በዚሁ ከቀጠልኩ ደግሞ ምን ትለኛለች? አጣብቂኝ ዉስጥ ገባሁ፡፡
‹‹ምስጢር ከሆነ ወጣ ልበልልሽ እንድታወሪ?›› ተጨንቆ ነበር የጠየቀኝ
ጓደኛዬ ናት ምንም ምስጢር የለዉም
‹‹የወንድ ጓደኛሽም ቢሆን ችግር የለዉም ቤቱ ዲሞክራሲ የሰፈነበት
ነዉ ሰዉ የራሱን ዕድል በራሱ መወሰን የሚችልበት ነዉ የሰዉን መብት እስካልነካ ድረስ፤››
ምን ማለት ነዉ ቅድም ነግሬህ የለ ከጓደኛዬ ጋር ከተጣላን ቆየ ብዬ
… ተንተባተብኩ፤ ስናደድ እንተባተባለሁ የምለዉ ነገር ሁሉ ይጠፋኛል፡፡ ቆይ ከእሱ ጋር ብሆን አንተ ቤት ምን እሰራለሁ? ተቆጣሁ
አይገልጸዉም፤ እንደ ብራቅ ነበር የምጮኸዉ .. አነጋገሬ ደግሞ ቅጥ ያጣ ስለነበር ተሸማቀኩ ግልጽ ያለ ፍላጎቴን የሚያሳብቅ ነበር፡፡
ቤቲ ድጋሜ ደወለች እንዲያዉም ደስ ይበልህ አንስቼ አወራታለሁ፡፡
ሃሎ ቤቲዬ
‹‹ሃሎ ምነዉ የፍቅር መቀስ ሆንኩ እንዴ?››
ምን ማለት ነዉ?
‹‹ ምንም ግልጽ አይደለም እንዴ? ከፈረንጅ ጋር ነሽ?››
እንዴት እንደዛ ልትይ ቻልሽ … እንደምጠላ እያወቅሽ?
‹‹ የሚፈልጉትን ሲያጡ ያጡትን ይቀላዉጡ ሲባል አልሰማሽም?፤ እንደዛ
ደግሞ ያልኩሽ ጥያቄ ስታበዢ አማርኛ ጠፍቶብሽ ከሆነ ብዬ ነዉ፡፡››
ለማንኛዉም ያልሽዉ ግምት ሁሉ የተሳሳተ ነዉ …..እ… በኃላ ደዉልልሻለሁ
አሁን ቁምነገር እያወራን ነዉ፤ …. ቻዉ እሺ ቤቲዬ …. እ… በቃ…. ቻዉ ወድሻለሁ፡፡ ስልኩን ቀድሜ ዘጋሁት … አሁንስ ደስ አለህ
አመንከኝ፤
‹‹ እንዴ ምን ሆነሻል ስቀልድኮ ነዉ›› በማለት ለማባበል እቅፍ አረገኝ
አጋጣሚዋን ሳገኝ ዘርግቶ የነበረዉ እግሩ ላይ ገደም በማለት የናፈቁኝ ፊቱን ከስሬ እንዳይነሳ ይዤ ወደላይ ያለማቋረጥ አየዉ ጀመር፤
እሱ ሲያየኝ አይኔን ሰብራለሁ እሱ ዞር ሲል እኔ እንደ ሰጎን ትክ ብዬ አየዋለሁ፡፡
ጨዋታዉ እየደራ ሲመጣ መላመዳችን ሲጠነክር ፂሞቹን መደባበስ፣ ቅንድቦቹን
መነካካት፣ ከንፈሮቹን ፍጥጥ እያሉ ማየት ተደጋጋሚ ስራዬ ሆነ፡፡
‹‹እንዴት ነዉ ቆሎዉ ይጣፍጣል አይባልም እንዴ ዝም ብለሽ ፈጀሽዉኮ?››
አንተ አልቆላኸዉ ምን አስባለኝ? እዉነትም ዝም ብዬ በላለሁ ሃሳብ
የሚያዘወትር ሰዉ የምግብ ፍጆታዉ ስንት ይሆን አልኩ በልቤ የማያሳስብ ነገር ሲያሳስበኝ፡፡
‹‹ ቆንጆ ቆሎ መርጦ መግዛትም ያስመሰግናል ይህን አታዉቂም እንዴ?››
ቆንጆ ሴትስ መምረጥ ትችልበታለህ አልኩኝ በልቤ በዚህ መካከል ስልኩ
ጠራ
‹‹ ሃሎ እንዴት ነሽ?››
እንዴት ነሽ የሚለዉን ስሰማ ንዴቴ ቀንድ አወጣ! የማደርገዉ የምጨብጠዉ
ጠፋብኝ፡፡
ሴቶች የፍቅራችሁ መግለጫ ቅናት ይሁን ብሎ እግዜር የረገመን እስኪመስል
ድረስ መገለጫችን ሆኗል ካልቀናን ወንዶቹም የምንወዳቸዉ አይመስላቸዉም፤ የፍቅራቸዉም ጥግ እኛን በቅናት እስከማብገን ድረስ ነዉ፡፡
እንዲያዉም አንዳንዴ እናቴ በአባታችን ስትበሳጭ ‹‹ ቅና ያለዉ …. … ›› ስትል እሰማት ነበር ምን እንደሆነ ባይገባኝም፡፡
****************፡፡**፡፡**፡፡**፡፡********************
ንዴቴ ሲበርድልኝ የቅናት ዛሬ ምሱን ሲያኝ ቸር ያሰንብተን እና በቀጣይ
ክፍል በክፍል አምስት ያገኛኘን!
for more information join my telegram channel
@t.me/deressereta
የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta'S Views : ክፍል አራት ….. ….. አጋጣሚ >>>>> Download Now
ምላሽ ይስጡሰርዝ>>>>> Download Full
የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta'S Views : ክፍል አራት ….. ….. አጋጣሚ >>>>> Download LINK
>>>>> Download Now
የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta'S Views : ክፍል አራት ….. ….. አጋጣሚ >>>>> Download Full
>>>>> Download LINK