በክፍል አንድ “ፍቅር በFace book” በሚለው እውነተኛ ታሪክ ላይ መሰረት ያደረገ ክፍል
ማቅረባችንን ሳሙኤል በFace book ላይ የተዋወቃትንና ሳይስቡት ፍቅር ውስጥ ገብተው በኃላም ሕይወትን የመጀመር አዝማሚያ አሳይተው
ከትውልድ ቀዬው ከአዲስ አበባ ተነስቶ የፍቅረኛው ልታገኘው እንደልፈልገች እንዳፌዘችበት፣ ደግሞ የህይወቱን ቁስል እንዳደማችበት
ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ በብዙ ልመና ሆስፒታል በር ላይ ሰላም ብሏት እንዳተመለሰና ተስፋ ቆርጦ እንደነበር ተመልክተናል ቀጣዩ የሳሙኤል
ገጠመኝ ምን ይመስላል? አብረን የምናየው ጉዳይ ይሆናል፡፡
‹‹ሴት ልጅን ያመነ ጉም የዘገነ አንድ
ነው›› ስልህ እንዲሁ ከመሬት ተነስቼ አይደለም ወይንም ለሴቶች ጥላቻ ኖሮኝ በዚህ ተነስቼ አይደለም ወይንም ለሴቶች ጥላቻ ኖሮን
በዚህ መንገድ ለመግለጽ ፈልጌ አይደለም ከሴቶች ተሽዬ ለመገኘት የጥላቻ ሰው ሳይሆን የፍቅር ሰው ሆኜ መገኘት እንዳለብኝ ከልቤ
አምናለሁ ይህንን ስልህ የተቀደሱ ንዑዳን ክቡራን ናቸውና ፍቅር ይገባቸዋል እያልኩህ አይደለም፡፡ ይገርምሃል ከረጅም አመታት በፊት
ለሴቶች ልዩ ክብርና ፍቅር ….ነበረኝ አሁንም ቢሆን ተረቶች ሁሉ ከብዙ ሰው ጋር ያጋጩን ነበር፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር በራስህ
እስካልደረሰ በስተቀር ስሜቱ አይገባህም ቁስሉ አይጠዘጥዝህም … አሁን ለአንተ የምነግርህን ነገር ለአስር ሰው ባወራላቸው በእርግጠኝነት
ሁሉመን ‹‹የአንተ በምን ይለያል በሰው ከደረሰው የተለየ ምን ደረሰብህ? ይኼ ደግሞ ሰው ሆነህ ስትኖር የሚያጋጥም ነገር ነው
….›› እያሉ እንደሚያረክሱብኝ ይገባኛል፤ እኔኮ ከህመሜ ፈውሱን ተበድያለሁና ካሳ ክፈሉኝ ወይም ፍረዱልኝ እያልኩ አይደለም ቢያንስ
ጭንቀቴን ስሙኝ ነው እያልኩ ያለሁት እግዚአብሔር ከዚህ ይሰውርህና አንተ ግን እየሰማኸኝ ውስጤን ተንፍሼልሃለሁ አንተም ልብ ብልህ
ትማርበታልህ ከበተራታህም ሎሎችን ታስተምርበታለህ፡፡
‹‹ምን ሆኖ ነው ገና ለገና ያፈቀርኳት
ልጅ ላገኝህ አልፈልግም ስላለች ወይም ስለጠላችው ወይም ስለከዳችው እንደዚህ የሚሆነው?›› ትል ይሆናል በለኝ ግዴለም እኔ ግን
ያጋጠሙኝን ገጠመኞች ላጫውትህ ገና አሥራ ስምንት አመት ሳይሞላኝ አንዲት የሶስት ልጆች እናት ትዳሯን እስከ ልጆቿ በትና ጎረምሳ
ተከተትላ ስትሄድና ለአስታራቂ ሽማግሌ ስታስቸግር አውቃለሁ እንዲሁ ይህ ከሆነ ከሁለት ዓመት በኋላ የመጀመሪያ ፍቅሯን አጣጥማ ሳትጨርስ
አንድ ልጅ ወዳው በፍቅር ላይ ፍቅር እያስጨነቃቸው ጮቤ እየረገጡ ሳለ ምንም ሳይጎድልባት ጨዋ ቤተሰብ አሳድጓት የተማረ ሁሉ የሞላው
ይህ ጉደለው የማይባል ከልቧ የምታፈቅረውን አግብታ ከሌላ ወንድ ጋር ተኝታ ተያዘች ባልም ፍቅርን እንደሻማ ያልብሳችሁ ብሎ መርቆ
ፈታት በተከበረበት አገር አንገቱን አስደፋችሁ ገና ለጋ ፍቅሩን ቀነጠሰችበት የጋለውን ሥሜቱን ቀዝቃዛ ውሃ ደፋችበት ሌላናዋ ደግሞ
እንዲሁ ከት/ት ቤት ጀምሮ ፍቅረኛዋ የነበረውን አገር ምድሩ እንደባልና ሚስት ሲመለከታቸው በነበረበት በትውልድ አገራቸው በክብር
በስነ ሥርዓት ተጋብተው ልጅ ለመውለድ አርግዛ ሳለች ይጋጫሉ እርሱም ከርቀት ከሚሰራበት ቦታ ይቅርታ ለመጠየቅ ለዕርቅ ደከመኝ ሰለቸን
ሳይል ይመጣል ይታረቃሉ ይሄዳል ደግመው ይጣላሉ ደግሞ ይመጣል ይሄዳል ተሰቃየ ጉልበቱ በመንገድ አለቀ ግን ምንም ለውጥ የላትም
ከትዳር በኋላ ፍቅራቸው ያልተዳፈነ እሳት ሆነ ቢጭሩት የማይቀጣጠል በስተመጨረሻ በፍርድ ቤት ከሰሰችሁ በመሃል ልጅም ተወለደ የፍቺ
ደብዳቤም ደረሰው ፍርድ ቤት ጊዜ ሰጣቸው ልጁንም እያሳደገ ተቆራጭ እያደረገ ፍቅሩን ደጅ እየጠና ቆየ ያሰበው ግን አልተሳካም ተፋቱ
ልጄን ልውሰድና ላሳድግ ብሎ ሲጠይቅ ያንተ አይደለም ተባለ እናስ የማነው ተብሎ ሲጠየቅ የሁለቱም ጓደኛ የነበረ ቤተኛ የሆነ ይህን
ያደረጋል ተብሎ የማይጠበቅ በጫጉላቸው ጊዜ እንኳን እንደ ወንድም እንደ ወዳጅ አብሮ ሲጫወት አብሮ ሲበላ ሲጠጣ እያደረ እየሰነበተ
ትዳርን ያላመደ ባልንጃራቸው ልጅ እንዳሆነ መጨረሻም ፊርማቸውን እንኳን ሳይቀዱ አብራው መኖር ጀመረች ባለቤት ተብዬ ጓደኛዬም ልቡ
ተሰበረ ሥሜቱ ተነካ ክብሩን ተነካ ይኼ የምንግርህ ጥቂቱ ነው ምናልባት አዲስ ነገር ነው ወይ? ወንዱስ ቢሆን? ልትለኝ ትችላለህ፤
ወደ እኔ እንምጣ ደግሞ የልጅነት ፍቅረኛዬ ሠንቄ ከነበረው ከሕይወት ዓላማዬ አደናቅፋ የፍቅርን ፊደል አስቆጥራ የፍቅርን ጽዋ አስጎንጭታን
እያጣጣምኩት እያለሁ ልትለየኝ ልትጠላኝ ምላ ተገዝታ ያጋጠማትን የአሜሪካ ኑሮ ዕድል ተጠቅማ ከሄደች በኋላ ከወራት በኋላ የውሃ
ሽታ የሆነችብኝ ምን ባደረኳት ነው? ቃሏን ለምን አጠፈች? እኔኮ የዶላር ችግር የለብኝም የፍቅር እንጂ፣ እኔኮ አሜሪካ እንድታኖረኝ
አይደለም ህልሜ በልቧ እንድታኖረኝ በልቤ እንድትነግስ እንጂ ፡፡ ዛሬ ደግሞ ፍቅርን እንደምፈራ እየነገርኳት ህመም አለብኝ ቁስሌ
እንዳያገረሽብኝ እያልኳት ከተማፅኖ ጭምር እያፈቀርኳት እንዲህ ማድረግ ምን ይሉታል? ምን በደልኳት? ታዲያ ‹‹ሴት ያመነ ብል ይፈረድብኛል?
እስኪ ፍረደኝ! በል እስቲ ህሊናህ ያለህን ፍርድ በይንብኝ በል እባክህ ጥፋቱ ያንተ ነው ብለህ ጥፋቴን ቦታውን ጠቁመኝ እያለ ሲቃ
እየተናነቀው ራሱን መቆጣጠር አቅቶት ድምጹ ሌሎችን እስኪረብሽ ድረስ ከፍ በማድረግ ትናንት ያገኘሁት ሣይሆን የጥንት ጓደኛው ያህል
ስሜቱን መቆጣጠር እስኪሳነው ህመሙን ጭንቀቱን ተነፈሰልኝ፡፡
ይኸውልህ ደረሰ ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስብው
የርሷ የባህሪ ለወጥ የጀመረው አንድ ቀን ድንገት ይሁን አስባበት አላውቅም ‹‹ታገባኛለህ? አለችኝ እውነቴን ለመናገር እርሷን ማግባት
የኔ ሥራ እንጂ የርሷ ጭንቀት አልነበረም ምክንያቱም ወድጃታለሁና፡፡ ነገር ግን መዋሸት አልፈልግምና ሁሉን ነገር ዘርዝሬ ነገርኳት
ደሞዜ ስንት እንደሆነ ከዚያ ላይ የተጣራ የሚደርሰኝን ለቤተሰብ የቤት ወጪ ሥንት እንደምሰጥ የዓባይ ግድብ የቦንድ ግዢ……. ተቆራርጦ ሥንት እንደሚቀረኝ ነገርኳት ከተወሰነ ወራት
በኋላ የዓባይም እንደሚያልቅ ነገሮችም ሲስተካከል እንደምንነጋገር ሆኖም
ግን የኔና የርሷ መጨረሻ አብሮ በትዳር እንደሆነና ዛሬ ግን ልዋሻት እንደማልፈልግ አጉል ቃል እንደማልገባ ነገሮችን
አስተካክዬ እኔ ራሴ ልታገባኝ እንደምትፈልግ እንደምጠይቃት ነገርኳት የተወሰነ ቅሬታ አነበብኩባት ከኔ ጭንቀትና እውነት ውሸትና
ቅሬታ ሽንገላ በሥሜት ‹‹አዎ አገባሻለሁ›› እንድላት ፈለገች ይሁን እንጂ የከፋ ነገር በመካከላችን አልነበረው የሆዷን እግዜር
ይወቀው እንጂ እንዲያውም ብር ልላክልህ ትለኝ ሁሉ ነበር፡፡
የኔ ፍቅር ከቀን ወደቀን እየጨመረ ሲመጣ
በመካከላችንም የነበረው እንቅፋት የፍቅር ችግር ሳይሆን በኢኮኖሚ ራስን አለመቻል ስለነበር ወደያው አንድ ነገር ወሰንኩ ስራ ማፈላለግና
የተሻለ ደመወዝ ተከፋይ መሆን እንዳለብኝ ምክንያቱም ጥሩ የስራ ልምደና የት/ት ደረጃ አለኝና የሚገርመው በወራት ውስጥ የምፈልገውን
ሥራ ከእጥፍ በላይ በሆነ ወርኃዊ ደመወዝ ተቀጠርኩ ወደ ድሬደዋ የፍቅር አገር የመጣሁት ስራ ከመጀመሬ በፊት ይህንን የምስራች ለፍቅሬ
ልነግራት ታገቢኛለሽ ወይ ብዬም የትዳር ጥያቄ ላቀርብላት፣ እመጣለሁ ብዬ ቃል የገባሁትንም ቃልኪዳኔን ለመፈጸም ለድርብ ድርብርብ
ደስታ ነበር ጉዞዬ ከአ.አበባ ድሬደዋ ነገር ግን በድሬደዋ ሙቀት ውስ ፍቅራችን ለፍሬ እንደ ደረሰ ሰብል ታጭዶ ተወቅቶ ወደ ጎተራ
ሳይገባ ውርጭ መታውና ልቤን ደግሞ የፍቅር ጦር አደማው ላይሻለኝ ላይጠገን ልቤ ተሰበረ ‹‹ ጉም ጨበጥኩልህ ሥቅሥቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ ግራ መጋባት በሚታይብኝ ሁኔታ ‹‹አይዞህ›› እያልኩ ለማጽናናት
እንዳያለቅስም ‹‹አታልቅስ›› በማለት አባበልኩት፡፡
ደረሰ ተወኝ እባክህ ለምን አላላቅስ ለምንስ
አላነባ ምን ቀረኝ ፣ጌታዬኮ አብሬያት እንድኖር ከግራ ጎኔ አጥንት ከፍሎ የሰጠኝ ሴትን ነው፡ ታዲያ ሴቶች እንዲዘህ እንደጉም አልጨበጥ
ካሉ ወንድ ላግባ እንዴ?! ምን ለማለት ነው አታልቅስ የምትለኝ እያፅናናኽኝ
እያበረታኸኝ ነው? ወይስ በቁስሌ ላይ እንጨት እየቆሰቆስክበት ነው?
እምባ ተናነቀኝ የወንድ ልጅ ሐዘን እና ጉዳት አሳዘነኝ እኔም የራሱን ጥያቄ መልሼ ራሴን ግን ለምን?
አልኩት፤ታዲያ አሁን ምን እያደረክ ነው? በማት በጥያቄ መልክ ጨዋታ ለመቀየር ሞከርኩ ከሐዘኑ የማስወጣበትን መንገድ እየፈለኩ፡፡
‹‹አሁን ምን አደርጋለሁ እቅዴን ምኞቴን
ተስፋዬን ውሃ ባለው መነሻዬን ራስ ሆቴል አድርጌ ዳቻቱ ሰፈር፣ መጋላ፣ ኮኔል ድልድይ፣ ከዚራ፣ ለገሃር፣ ሃምበር ዋን፣ ሃራር መውጫ፣
ታይዋን፣ ሳቢያን፣...ወዘተ እያልኩ ላይ ታች ሥል ውዬ ዛሬ ደግሞ ራስ ሆቴል አርፋለሁ፤ የከፋው (ግራ የገባው) ቱሪስቱ ታውቃለህ
እንደዚያ ሆኛለሁ፡፡
አይዞህ ታሪክ ይቀየራል ራስህን አትጉዳ
በትዕግስት ነገሮችን በሙሉ መርምራቸው ደግ ሴቶች በሙሉ አንድ አይደለሙ ወላድ በድባብ ትሂድ እዛው አዲስ አበባ የአገርህን ልጅ
ታፈቅራለህ አይዞህ!
“ምን አልክ ፍቅር?! ፍቅር እንደገና ! ሴት ልጅን እንደገና ላምናት? ይገርምሃል አንድ ጓደኛዬ በሆነ
ወቅት ስለ ሴት ልጅ ያለውን መጥፎ አመለካከት ተመልክቼ እንዲራራ መልካም አመለካከት እንዲኖረው ብዙ ጥረት አደርግ ነበርና ስለሴት
እናትነት፡ እህትነት፡ሚስትነት፡ ወዘተ እያነሳሁ ብዙ ብዙ ነገር እለው ነበር ዛሬም አንተ ለምን እንደዚህ እንደምትለኝ ይገባኛል፡፡
አዎ የምትለውን በሙሉ ነች አምናለሁ ነገር ግን ያ! ጓደኛዬ እንዳለኝ ሴቶች የሚመቻቸው ከርህራሄ ይል ጭካኔ፣ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ፣
ከመግባባት ይልቅ ፀብና ክርክር፣ አብሮ ከመኖር መለያየት ይመቻቸዋል።ይኸም የመጣዉ ከጥቅም ፈላጊነታቸውና ራሳቸውን አብዝተው ከመውደዳቸው
የሚመነጭ ይመስለኛል። ዛሬ ዛሬ እንደውም ከወንድ በተቃራኒ በሆኑ ቁጥር የሚወደዱና የሚፈለጉ እየመሰላቸው ሲሞላቀቁ ይታያል፡ እውነታው
ግን ይህ አይደለም በተቃራኒው ነው ስለዚህ አያስፈልጉኝም፡፡››
‹‹እስኪ የመለያየታችሁ፡ ይቅርታ የመቀያየማችሁ ዓብይ ጉዳይ ምንድን ነው ብለህ ታስባለህ?
‹‹ግልፅ ነውኮ ያኔ ነገሮች ባልተስተካከሉበት ወቅት ለርሷ ወቅታዊ ላልሆነ አጣዳፊ ጥያቄ አገባሻለሁ
የሚል የውሸት ተስፋ ስላልሰጠኋት ነው፤ እስኪ ተመልከታት ይህቺን ሴት እኔ ያኔ ብዋሻት ዛሬ ድረስ ከኔ ጋር ነች፡ አሁን ሥመጣ
በደስታ ትቀበለኛለች አዲስ አበባም ትመጣ ነበር ያፈለገንንም ነገር እናደርጋለን ደግሞ ስለ መጋባት አናነሳም በቃ! ምናልባት ‹ቆይተን
መቼ ነው ታዲያ የሰርጋችን ቀን?› ትለኝ ይሆናል፡፡››
እሷም ጥያቄዋ ስህተት ያለበት አይመስለኝም እውነትዋን ነው የማታገባት ከሆነ ለምን ጊዜዋን ታባክናለች?
‹‹እኔስ ምንድን ነኝ ዝም ብዬ ጊዜዬን የማባክነው የወንድ ልጅ ዕድሜ እና የዕባብ ዕድሜ አንድ ነው
ያለው ማን ነው? የኛም ዕድሜ ይሄዳልኮ እንደ ሴቶቹ ባይሆንም፤ እኔ ደግሞ ራሴን እፈልገዋለሁ ዝም ብዬ አልንዘላዘልም፡፡ የማላገባትን
የእኔ ያልሆነችዋን ሴት አልፈልጋትም ወንድ አዳሪ አይደለሁምኮ፡፡
ቀጣይ ጊዜህን ታድያ እንዴት ታሳልፋለህ
ያለሴት መኖር ይከብዳል፡ ለምን አላስታርቃችሁም?
አመስግናልሁ፡ግን አሁን የማሰቢያ ጊዜ
ነዉ የምፈልገዉ ዳግም የምሳሳትበት ጊዜ አልፈልግም፡፡…ለወንዱም ለሴቱም መልካም ዘመን እና ጣፋጭ የፍቅር ጊዜ እመኝላቸዋለሁ። እነሆ
ላንተም መልካም መዝናኛ፡፡
አሜን ብዬ ምርቃት ከተቀበልኩ በሁላ ይጠቅም
ይሄናል በማለት እንዲህ አስፍራለሁ፡፡
(ገጠመን የምትሉትን ፍቅር በfacebook
ላኩልኝ እኔም እንዲህ ለሰፊዉ ህዝብ ጥቅም በምስጢር አቀርበዋለሁ።)
ክፍል 3 በእኛዉ ገጠመኝ እና ታሪክ ፈጣሪ ካደረሰን እናንተም ከላካችሁልኝ እንገናኛለን፡ቸር
ይግጠመን።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ