ማህበራዊ ጉዳይ

  ሰው

ሐምሌ 11 ቀን 2003 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡27 መነሻ ቦታ ሚኒሊክ አደባባይ ሚኒሊክን ለማያውቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይህንን ላላወቀ መነሻዬን ልንገራችሁ 59 ቁጥር አንበሳ አውቶብስ መነሻ ሐሳብ የኛ ሰው መድረሻ ቦታ አዲሱ ገበያ መድረሻ ሐሳብ እኔም አላውቀውም፡፡
ለጽሑፌ መግቢያም መውጫም እንደባለሞያ የለኝም በቃ የኛ ሰው ብዬ ጀመርኩ መብቴ ነው ማን የሰጠህ ካላችሁ የናንተም የመጠየቅ መብት ይከበራል መልሱን የሚሰጠውን እኔም እናንተም ባታውቁት ይሻለናል፡፡
የኛ ሰው የሚለውን እንዳነበባችሁ ሲፈልጋችሁ “የኛ ሰው በአሜሪካን ” ወይም የኛ ሰው በ… ያስታውሳችሁ ማስታወስ የማትፈልጉትም፣ ማስታወስ የማትችሉትም መብታችሁ ነው ፡፡
የኛ ሰው የሚለውን ሐሳብ የወሬ ቋንጧ ሳላደረገው የወሬ
የፆም ሰዓትም ሳይገባ በትኩሱ ለጆሮአችሁ ላሰማችሁ የአንበሳ አውቶቡሱ ከብዙ ሱባኤ ከብዙ ምህላ በኋላ ከቺሊ ምድር ሥር ለብዙ ቀናት እንደሰነበቱት ማዕድን አውጪ ዎች በነርሱ ምድር ተከድናባቸው በኛ ላይ ደግሞ የአንበሳው ደጃፍ ተዘግቶብን ከቆየንበት ሥፍራ ተንቀሳቅሰን መንገድ ጀመርን ለምን የሚሉ ጥያቄዎች ያላችሁ መልሱን ራሱ ነገር ይመልሰዋል ጆሮአችሁን እያከካችሁ ቆዩን አለበሊዚያም ጉርርር በሉት ለጆሮአችሁ ወይም እንደየምነታችሁ በስመአብ - ቢስሚላኂ -በየሱስ ስም… ወዘተ ማለት ትችላላችሁ፡፡
ልክ እሳት አደጋ ዋና መስሪያ ቤት ጋር እንደደረሰን የሆነ ነገር አየሁየኛ ሰውመነሻ ሐሳብ የሆነውን የኛ ሰው ነገር ምን ተዳዳሪ እንደሚባሉ አላውቅም ወይም ምን ልላቸው ወይም ምን ዓይነት ሥም ላወጣላቸው እንደምችልና የትኛው ሥም እንደሚመጥናቸው አላውቅም አንድ ነገር ግን አውቃለሁ በታችኛው የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ሠዎች ፍላጐት በየጐዳናው እየተዘዋወሩ እንደሚያሟሉ እኔን ጨምሮ ብዙ እቃ ገዝቼአቸዋለሁ ሲሸጡልኝ ዋስትና አለው ብለው  አልዘላበዱልኝም የማጣሪያሽያጭ ብለው አይኒን አላጭበረበሩኝም  አንዳንዴ ጆሮዩን አደናቆሩት እንጂ እየተንጫጩ እነዚህየኮንትሮባንድ ዕቃ ሻጮች እነዚህህገወጥ ነጋዴዎችእነዚህየቤት ኪራይ ወጪ፣ የመንግሥት ግብር፣ የሠራተኛ ደመወዝ ወጪ የሌለባቸውወዘተዎች ፤እነዚህ ምኑ እንዳተነካ የንብ መንጋ ብትን አሉ አቅማቸው ግር ማለት ሳይሆን ብትን፣ ብን ማለት ነውና ያሳደዳቸውን ወይንም ያባራራቸውን አላውቅም ወይም አላየሁም የሚያባርራቸው እንደሆነ የለም እነርሱም የሚያያቸውን በንስር ዓይናቸው አዩት የሚያስድዳቸውን ሸሹት ነገረኛን መፍትሔው  መሸሽ ነውና የተቻለኝን ያህል የሚያሳድዳቸውን ለማየት በዚያች ቅጽበት አማተርኩ ፖሊስ ወይም ደንብ አስከባሪ ፍለጋ አላየሁም ምናልባት ቀይ ለባሽ ወይም ነጭ ለባሽ አለበዚያም ሌላ መልክ የለበሰ አዲስ አሰዳጁ መጥቶባቸው ይሆናል እነርሱም መሰደዳቸው አሳዳጁም ማሳደዱን ሳያቆም እኔ እይታዬን አቁሜ መንገዴን ቀጠልኩ ማየቴን ማቆም ፈልጌ ሣይሆን የነበርኩበት 59 ቁጥር አውቶቡስ እንደኔ በዚህ እይታውስጥ ሳይሆን ጐዳናውን  እየቃኘ ስለነበረ ይዞኝ ነጐደ እኔም ከዚህ መነሻነት የኛን ሰው ማየት ጀመርኩ በዕዝነ ምናምኔ ዘልዬወደ ሰማሁት አንድ ነገር ሄድኩ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች ዓለማት ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ ህይወት ያላቸው ልምድ እየዞሩ በየጐዳናው መሸጥ ወይም የሚያሳድዷቸው ማስቸገር ነው መሰለኝ እንዲሁ ነው ሲሯሯጡ ሲኳትኑ የሚውሉት አሉ የሚያሳድዷቸውም ህግ ተሰርቶ ይሁን በኛ አገር ሠርታችሁ አለፈላችሁ ብለው ቀንተው ይሁን አይታወቅም ያሳድዷቸዋል ይዘርፋቸዋል ይገሉዋቸዋል….ወዘተ አሉ ለነገሩ ምን ይገርማል እንኳንስ ባዕዱ በሰው አገር ወገኑ ራሱ በአገሩ ያስድደው የለ አንድ ነገር አስታወስኩ አንድ ጊዜ በጆሮዬ ጥልቅ ያለችውን አዳምን ከገነት አምላኩ ሲያባርረው ጥረህ ግረህ ብላ የሚለው አባባል ወይም ታሪክ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ) ታዲያ ኢትዮጵያዊ ተሳደህ ተሰዳደህ (አንዱ አንዱን አሳዶ) ኑር ተብሎ ተፈርዶበት በታሪክ አልተነገረ በመጽሐፍ አልተፃፈ ይሆን ይኸውላችሁ የኛ ሰው ዕጣ ክፍሉ አንዱ አንዱን ማሳደድ አንዱ በአንዱ ላይ መቅናት አንዱ በሌላው የላብ ውጤት ንብረት ላይ መነሳት ማሳደድ ሆነ እላችኋለሁ፡፡
ይኸንን ነው እንግዲህ የኛን ሰው በደቡብ አፍሪካ የኛን ሰው በገናናዋ አገር በአሜሪካ የኛን ሰው በአገሩ በመንደሩ በቀዬው የታዘብኩትን በዚህች የሰው ጉዳይ በማይለው ጭንቅላቴ ምን አገባኝ ብዬ ትቼው መለከ ከማለት አንድ የኛ ሰው ጉዳይ በዓይኔ በብረቱ ጥልቅ አለ ምን በሉኝ መከታተላችሁን ከኔ ጋር መሆናችሁን እንዳውቅ… ድሮ የኔታ እግር ስር ሆነን ሥንማር ሲያስነጥሳቸው …
የኔታን ይማርልን እንዳልነው ከኔ ጋር ሁኑ ብዙ ነገር ስለ የኛ ሰው የምነግራችሁ አለ ከአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ቅድም ሚኒሊክ አደባባይ ጋር ለሁለት ተሰልፈን እንደዳቦ ቤት ዳጁ ደጅ ስንጠና መግቢያ ቲኬቱን ለመቁረጥ ስንጠባበቅ ከፈለጋችሁ ‘ቪዛ’ በሉት እንደሆነ የኛ አገር ትራንስፖርት አሜሪካ መግቢያ ቪዛ ያህል ችግሩ ጠንክሯል እንደሆነ ተሰልፈን እያለ ወረፋ አለመጠበቅ በዘመድ መስተናገድ ለሚያውቁት ሰው ቁረጥልኝ ብሎ ሐቀኛውን ወደ ኋላ ማስቀረት የአውቶቡስ ተራ አሪፍነት እንደሆነ ተጠቃሚዎችና የደረሰባችሁ እርር ብላችሁ ለማንም መተንፈስ አቅቷችሁ አይታችሁ ታዝባችሁ በደሉ ተፈፅሞባችሁ ዝም ብላችሁ የሄዳችሁ ታውቃላችሁ፡፡
ከዚያ በኋላ ተሰልፈን እያለ አንዲት ሴት ፈጠን ብላ መጥታ ገንዘብ የምተሰበሰበዋን አንድ ብር ይዛ ቀራበቻት በቃ ሰው ዓይን አወጣ መከባበር ተራ መጠበቅ ቀረ ይቺ የህግ ኩሬ የሆነች አገር ላይ ህግ የሚያውቅ እንጂ የሚያከብር ጠፋ ብዬ በውስጤ ሳጉተመትም ቆርጣ ለመግባት እግሯን ስታነሳ ሳያት እርጉዝ ነበረች በሆዴ ላወራሁት በሆዴ በሆዷ ያለው ምን እንደሆነ ስላላወኩ ገና ለገና ነገን ፈርቼው በሆዷ ያለውን ይቅርታ ጠየኩት እርሷም ገባች እኔም ገባሁ እርሷም ቆማለች እኔም ቆምኩ እርሱንም አርግዘሻል አንተም ተበሳጭተሃል ብሎ ተቀመጡ ያለን አልነበረም ሰው ‘ሼም’ አያውቅማ የተጨካከነም መሰለኝ እኔ ግነ የኛ ሰው ዝም ቢላትም‘ሼም ቆነጠጠኝና’ አንድ ሰው አስነስቸ አስነስቼ ሁለት ሰው የሚያስቀምጠው ላይ ለሶስት እንዲቀመጡ አደረኩ  በእናቴ ሆድ ውስጥ እያለሁ የማይመቹ ነገሮችን ቀስሜ ነው መሰለኝ እንዳለተመቻት ገባኝ እንደማይመች አርግዞ መማር አይጠይቅም እድሜ ለቴክኖሎጂ ‘በአልትራሳውንድ’ ማወቅ ይቻላል ከቴክኖሎጂ (ዘመን አማጣሹ) ጋር መግባባት ካልቻላችሁ ልጁ  (ልጁቱ) ተፅዕኖ እንዳላሳድር በፆታ ላይ ሁለቱንም ተጠቅሜአለሁ ጊዜው የዕኩልነት ነውና እንዳልተመቻቸው አፍ አውጥተው ከሆነ ይነግሯችኋል አፍ ካለውጡ ጊዜው ቢያልፋም የምታምኑት እንደየምነታችሁ መጠን ማታ በህልም ይግለጡላችሁ እርጉዟ የጠረጠርኩት እውነት ሆኖ የተቀመጠችበት አልተመቻትም ለማስነሳት የኛን ሰው ፀባይ ጠንቅቃ ታውቃለችና እንዲነሱላት አስባ ለመነሳት ተግደረደረች አይገርማችሁም የኛ ሰው መጨካከን የጀመረው መቼና እንዴት በማን አማካኝነት እንደሆነ ባይታወቅም ተጨካክኗል የተግደረደረችውን ጨክና አደረገችው ተነሰታ ቆመች የገረመኝ ነገር ወንዱ ልጅ ገና ጐረምሳው አርግዞ ወይ አስረግዞ የማያውቀው ነፍሱ ሹክ ብላው አውቆ ነው መሰል ሲነሳ አጠገቧ የነበሩት ሲያጣብቧትና ሲያስነሳት የነበሩት ሴት ለዚያውም ሴት ወይዘሮ ስንት ጊዜ አርግዘው ያማጡ ዕርግዝና የልጅ ልጅ ባይኖረውም የልጅ ልጁን የሚያውቁት ሴትዮ ጨከኑባት ፍቅራቸውንም ፀባቸውንም ባላውቀውም አይዋደዱም የሚባለውን ስሞታ ሳይሆን አይቀርም ለማለት ደዳኝ እንዳላምን ግን አፍራሽ ነገር አጋጠመኝ ምን በሉ እንጂ አድማጭ አንባቢዎች ተረት ተረት ስንባል የመሰረት ስንል እንቅልፍ እየወሰደን እንዳደግነው መድረሻችን እስኪለየን፡፡
እንደእኔ ያለው ፈሪ በሆዱ ሲረግማቸው ግማሹ ሲገላምጣቸው ጨኻኝ ሲላቸው መቼስ የኛ ሰው ብዙ መልክ አይደል ያለው አዎ በሉ ከበስተኋለው የነበሩ ሰዎች ተመካክረው ነው መሰል እንጃ ሁለቱ ተነስተው አንዱ በዕድሜ የገፋ በሽበት የበለፀጉ እናትን ጨምረው ለሁለት አመቻችተው አሰቀመጧት አቤት የኛ ሰው ሥንት አይነት አለመሰላችሁ የኛ ሰው በሰው አገር የኛ ሰው በአገራችን…
በነገር እንዳያዝኳችሁ አውቶብስ እየሄደ እየሄደ ሰሜን ሆቴልን ተሻግሮ ቆመ በየመቆምያው መቆምና ሰው ማውረድ ብቻ ሣይሆን ሰው መጫንም ግድ ይለዋልና እንደእኛ የአንበሳ አውቶቡስን በየፌርማታው ዓይኑን ለማየት የልባቸውን ፈቃድ ለመፈፀም ወደ መደራሻቸው ለመድረስ ዓይናቸውን ስቅለው የሚጠብቁት ብን ብለው ሳይሆን ግር ብለው ወደ ትኬት ቆራጫ ተመሙ ውስጥ ካለነው አብዛኛው የቅድሙን የራሱን የዓይን ናፍቆት ገብቶ ተወጣውና ነገሩን ሁሉ ረሳውና ሾፌሩን በቃ በሩን አትክፈት ሞልቷል የት ለማስገባት ነው እያለ ማጉረምረም ጀመረ ለራሱ ቢሆን መሙላት አይደለም ቢተርፍ አይደለም አውቶብሱ ውስጥ አንበሳው ጫንቃ ላይ ተቀምጦ መሄድ የሚናፈቀው ወገኑን ተጨናንቆ ገብቶ ወደቤቱ እንዳይገባ አሳደደው በልቡ ከአንበሳው ደጅ አሳዳዳቸው አይገርምም የኛ ሰው ነገር የኔስ ነገር ብትሉ መንገዴ መንጐድ ትቼ የትዝብት ምች እንደመታው ሰው ምን አስታዘበኝ እኔንጃ ይግራማችሁና አንድ የገረመኝን ነገር ልንገራችሁ የኛ ሰው ክፋቱ እንደደግነቱ ሁሉ ወደር የለውምና የዘዋሪው/የሹፌሩ/ የትኬት ቆራጩ አሰማሪ/ሥምሪት ክፍል/ናት አሉ በዚህ ዋሉ በዚህ ውጡ በዚህ ግቡ ብላ የምታስጨንቃቸው ያ ሁሉ ምድረ ሰው ከአፋ እስከ ገደፍ ሞልቶ አንበሳውን አላስፈሳ አላስገሣ ያለውን ህዝብ ማን ጫን አለህ አውርድ ብላ ማንቁርቱን ያዘችው አሉ ዘዋሪውን ዓይኔን ወደዳጅ ጣል ሣደርግ ለተቀማጭ ሠማይ ቅርቡ አይደል ርዝመቱ ምን ያህል እንደሆነ ባታይወቅም ታታክረዋለች እርሱ ሊያስረዳት ይሞክራል ትኬት ቀንጣሿ ቶሎ ደርሰን እንመጣለን ብላ ትማፀናለች ከጐኔ የነበሩት መሄድ ያማራቸው ተጓዥች “ይኼ ሁሉ ህዝብ ቆርጦ ሲገባ የት ነበረች አለቃነቷን ይህ ሁሉ ሰው ይወቅልኝ ብላ ነው?”:‘የሴት ነገር ድሮም’…ወዘተ ይላሉ ፍርዱ ለመስጠት አንቀፅ ለመጥቀስ፣ቀነ ቀጠሮ ፣ምስክር፣ክርክር ፣ ግርግር ፣ ውዥንብር  ወዘተ … ስለሚያስፈልግ እኔ በድምፅ ተአቅቦ አልፌዋለሁ የኛን ሰው ግን ታዘቡልኝ፡፡
መቼስ ጥፊም ይደገም የለ አንድ ልድገማችሁ ጥፊ ቢደገም ያማል የኔ ደግሞ ትዝብት ይጨምራል ከመግቢያው እስከ መውጫው ጢም ያለው ሰው ለመግባት እንዳልቸኮለ ለመውጣት ያረገዘችው ሳያምጣት ምጥ የያዘቸው ዘዋሪውን አሰጨነቁት ኃላፊዋን በምልጃ ተሳፋሪውን የሆነ ጥግ ፈልጐ በውረጃ ተገላገላቸው የኛ ሰው ግን አይገርምም? ይገርማል ፡፡
የኛ ሰው መቼስ የማይለው የለም 59 ቁጥር ወይራ ሠፈር /ቤቴል/ መሄዷን ትታ ባህር ዛፍ ሠፈር ወደ አዲሱ ገበያ ምን ትሠራለች ሳትሉ አትቀሩምና ሾፌሩና ትኬት ቀንጣሿ መዘወር ያማራቸው ሳይሆኑ ሰው የመርዳት ፍቅር ያደራባቸው ነበሩና ተራቸው /ሰዓታቸው/ እስኪደርስ እንደ አፈር የፈሰሰውን ህዝብ ወደየቀየው ለመበተን ለአሰሪ መስሪያ ቤታችውም የማይነጥፍ ኪሳችውን ለማሰብ ነበር ፡፡
የኛ ሰው በኛ አገርም የኛ ሰው በሰው አገርም ቢወራለት ጉንጭ አልፋ ነውና እናንተ በቃ ባታውቁም እኔ ትዝብቴን በዚህ ላብቃ ሌላ ጊዜ እንዲሁ ሃሳቤን ካልሸወራረው የኛን ሰው እታዘባለሁ፡፡
የሆነ ቀን ነው አሉ ማን እንደሆነ ባላውቅም ስለ የኛ ሰው አስተያየት ለመጠየቅ እግዚአብሔር ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያለ ሰውን ጨምሮ ሃያሁለቱን ፍጥረት ሰብስቦ የታዘባቸሁትን ንገሩኝ አስተያየታችሁንም ስጡኝ ቢል ቀበሮ ቀድማ ተነስታ የኛን ሰው ታዝባ ታዝባ ሰው ምን እንዳረጋት ብትጠየቅ ብዙ የምትለው ቢኖራትም ‘ለሰው ሞት አነሰው’ ብላ ተቀመጠች አሉ እናንተስ ስለሰው መቸስ “ስለሰው ስለሰው ቀድጄ  ልልበሰው” እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ የኛን ሰው ገና እንታዘባለን፡፡
ሐምሌ 11 ቀን 2003 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡27 መነሻ ቦታ ሚኒሊክ አደባባይ ሚኒሊክን ለማያውቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይህንን ላላወቀ መነሻዬን ልንገራችሁ 59 ቁጥር አንበሳ አውቶብስ መነሻ ሐሳብ የኛ ሰው መድረሻ ቦታ አዲሱ ገበያ መድረሻ ሐሳብ እኔም አላውቀውም፡፡
ለጽሑፌ መግቢያም መውጫም እንደባለሞያ የለኝም በቃ የኛ ሰው ብዬ ጀመርኩ መብቴ ነው ማን የሰጠህ ካላችሁ የናንተም የመጠየቅ መብት ይከበራል መልሱን የሚሰጠውን እኔም እናንተም ባታውቁት ይሻለናል፡፡
የኛ ሰው የሚለውን እንዳነበባችሁ ሲፈልጋችሁ “የኛ ሰው በአሜሪካን ” ወይም የኛ ሰው በ… ያስታውሳችሁ ማስታወስ የማትፈልጉትም፣ ማስታወስ የማትችሉትም መብታችሁ ነው ፡፡
የኛ ሰው የሚለውን ሐሳብ የወሬ ቋንጧ ሳላደረገው የወሬ የፆም ሰዓትም ሳይገባ በትኩሱ ለጆሮአችሁ ላሰማችሁ የአንበሳ አውቶቡሱ ከብዙ ሱባኤ ከብዙ ምህላ በኋላ ከቺሊ ምድር ሥር ለብዙ ቀናት እንደሰነበቱት ማዕድን አውጪ ዎች በነርሱ ምድር ተከድናባቸው በኛ ላይ ደግሞ የአንበሳው ደጃፍ ተዘግቶብን ከቆየንበት ሥፍራ ተንቀሳቅሰን መንገድ ጀመርን ለምን የሚሉ ጥያቄዎች ያላችሁ መልሱን ራሱ ነገር ይመልሰዋል ጆሮአችሁን እያከካችሁ ቆዩን አለበሊዚያም ጉርርር በሉት ለጆሮአችሁ ወይም እንደየምነታችሁ በስመአብ - ቢስሚላኂ -በየሱስ ስም… ወዘተ ማለት ትችላላችሁ፡፡
ልክ እሳት አደጋ ዋና መስሪያ ቤት ጋር እንደደረሰን የሆነ ነገር አየሁየኛ ሰውመነሻ ሐሳብ የሆነውን የኛ ሰው ነገር ምን ተዳዳሪ እንደሚባሉ አላውቅም ወይም ምን ልላቸው ወይም ምን ዓይነት ሥም ላወጣላቸው እንደምችልና የትኛው ሥም እንደሚመጥናቸው አላውቅም አንድ ነገር ግን አውቃለሁ በታችኛው የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ሠዎች ፍላጐት በየጐዳናው እየተዘዋወሩ እንደሚያሟሉ እኔን ጨምሮ ብዙ እቃ ገዝቼአቸዋለሁ ሲሸጡልኝ ዋስትና አለው ብለው  አልዘላበዱልኝም የማጣሪያሽያጭ ብለው አይኒን አላጭበረበ
ሩኝም  አንዳንዴ ጆሮዩን አደናቆሩት እንጂ እየተንጫጩ እነዚህየኮንትሮባንድ ዕቃ ሻጮች እነዚህህገወጥ ነጋዴዎችእነዚህ  ‘የቤት ኪራይ ወጪ፣ የመንግሥት ግብር፣ የሠራተኛ ደመወዝ ወጪ የሌለባቸውወዘተዎች ፤እነዚህ ምኑ እንዳተነካ የንብ መንጋ ብትን አሉ አቅማቸው ግር ማለት ሳይሆን ብትን፣ ብን ማለት ነውና ያሳደዳቸውን ወይንም ያባራራቸውን አላውቅም ወይም አላየሁም የሚያባርራቸው እንደሆነ የለም እነርሱም የሚያያቸውን በንስር ዓይናቸው አዩት የሚያስድዳቸውን ሸሹት ነገረኛን መፍትሔው  መሸሽ ነውና የተቻለኝን ያህል የሚያሳድዳቸውን ለማየት በዚያች ቅጽበት አማተርኩ ፖሊስ ወይም ደንብ አስከባሪ ፍለጋ አላየሁም ምናልባት ቀይ ለባሽ ወይም ነጭ ለባሽ አለበዚያም ሌላ መልክ የለበሰ አዲስ አሰዳጁ መጥቶባቸው ይሆናል እነርሱም መሰደዳቸው አሳዳጁም ማሳደዱን ሳያቆም እኔ እይታዬን አቁሜ መንገዴን ቀጠልኩ ማየቴን ማቆም ፈልጌ ሣይሆን የነበርኩበት 59 ቁጥር አውቶቡስ እንደኔ በዚህ እይታውስጥ ሳይሆን ጐዳናውን  እየቃኘ ስለነበረ ይዞኝ ነጐደ እኔም ከዚህ መነሻነት የኛን ሰው ማየት ጀመርኩ በዕዝነ ምናምኔ ዘልዬወደ ሰማሁት አንድ ነገር ሄድኩ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች ዓለማት ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ ህይወት ያላቸው ልምድ እየዞሩ በየጐዳናው መሸጥ ወይም የሚያሳድዷቸው ማስቸገር ነው መሰለኝ እንዲሁ ነው ሲሯሯጡ ሲኳትኑ የሚውሉት አሉ የሚያሳድዷቸውም ህግ ተሰርቶ ይሁን በኛ አገር ሠርታችሁ አለፈላችሁ ብለው ቀንተው ይሁን አይታወቅም ያሳድዷቸዋል ይዘርፋቸዋል ይገሉዋቸዋል….ወዘተ አሉ ለነገሩ ምን ይገርማል እንኳንስ ባዕዱ በሰው አገር ወገኑ ራሱ በአገሩ ያስድደው የለ አንድ ነገር አስታወስኩ አንድ ጊዜ በጆሮዬ ጥልቅ ያለችውን አዳምን ከገነት አምላኩ ሲያባርረው ጥረህ ግረህ ብላ የሚለው አባባል ወይም ታሪክ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ) ታዲያ ኢትዮጵያዊ ተሳደህ ተሰዳደህ (አንዱ አንዱን አሳዶ) ኑር ተብሎ ተፈርዶበት በታሪክ አልተነገረ በመጽሐፍ አልተፃፈ ይሆን ይኸውላችሁ የኛ ሰው ዕጣ ክፍሉ አንዱ አንዱን ማሳደድ አንዱ በአንዱ ላይ መቅናት አንዱ በሌላው የላብ ውጤት ንብረት ላይ መነሳት ማሳደድ ሆነ እላችኋለሁ፡፡
ይኸንን ነው እንግዲህ የኛን ሰው በደቡብ አፍሪካ የኛን ሰው በገናናዋ አገር በአሜሪካ የኛን ሰው በአገሩ በመንደሩ በቀዬው የታዘብኩትን በዚህች የሰው ጉዳይ በማይለው ጭንቅላቴ ምን አገባኝ ብዬ ትቼው መለከ ከማለት አንድ የኛ ሰው ጉዳይ በዓይኔ በብረቱ ጥልቅ አለ ምን በሉኝ መከታተላችሁን ከኔ ጋር መሆናችሁን እንዳውቅ… ድሮ የኔታ እግር ስር ሆነን ሥንማር ሲያስነጥሳቸው … የኔታን ይማርልን እንዳልነው ከኔ ጋር ሁኑ ብዙ ነገር ስለ የኛ ሰው የምነግራችሁ አለ ከአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ቅድም ሚኒሊክ አደባባይ ጋር ለሁለት ተሰልፈን እንደዳቦ ቤት ዳጁ ደጅ ስንጠና መግቢያ ቲኬቱን ለመቁረጥ ስንጠባበቅ ከፈለጋችሁ ‘ቪዛ’ በሉት እንደሆነ የኛ አገር ትራንስፖርት አሜሪካ መግቢያ ቪዛ ያህል ችግሩ ጠንክሯል እንደሆነ ተሰልፈን እያለ ወረፋ አለመጠበቅ በዘመድ መስተናገድ ለሚያውቁት ሰው ቁረጥልኝ ብሎ ሐቀኛውን ወደ ኋላ ማስቀረት የአውቶቡስ ተራ አሪፍነት እንደሆነ ተጠቃሚዎችና የደረሰባችሁ እርር ብላችሁ ለማንም መተንፈስ አቅቷችሁ አይታችሁ ታዝባችሁ በደሉ ተፈፅሞባችሁ ዝም ብላችሁ የሄዳችሁ ታውቃላችሁ፡፡
ከዚያ በኋላ ተሰልፈን እያለ አንዲት ሴት ፈጠን ብላ መጥታ ገንዘብ የምተሰበሰበዋን አንድ ብር ይዛ ቀራበቻት በቃ ሰው ዓይን አወጣ መከባበር ተራ መጠበቅ ቀረ ይቺ የህግ ኩሬ የሆነች አገር ላይ ህግ የሚያውቅ እንጂ የሚያከብር ጠፋ ብዬ በውስጤ ሳጉተመትም ቆርጣ ለመግባት እግሯን ስታነሳ ሳያት እርጉዝ ነበረች በሆዴ ላወራሁት በሆዴ በሆዷ ያለው ምን እንደሆነ ስላላወኩ ገና ለገና ነገን ፈርቼው በሆዷ ያለውን ይቅርታ ጠየኩት እርሷም ገባች እኔም ገባሁ እርሷም ቆማለች እኔም ቆምኩ እርሱንም አርግዘሻል አንተም ተበሳጭተሃል ብሎ ተቀመጡ ያለን አልነበረም ሰው ‘ሼም’ አያውቅማ የተጨካከነም መሰለኝ እኔ ግነ የኛ ሰው ዝም ቢላትም‘ሼም ቆነጠጠኝና’ አንድ ሰው አስነስቸ አስነስቼ ሁለት ሰው የሚያስቀምጠው ላይ ለሶስት እንዲቀመጡ አደረኩ  በእናቴ ሆድ ውስጥ እያለሁ የማይመቹ ነገሮችን ቀስሜ ነው መሰለኝ እንዳለተመቻት ገባኝ እንደማይመች አርግዞ መማር አይጠይቅም እድሜ ለቴክኖሎጂ ‘በአልትራሳውንድ’ ማወቅ ይቻላል ከቴክኖሎጂ (ዘመን አማጣሹ) ጋር መግባባት ካልቻላችሁ ልጁ  (ልጁቱ) ተፅዕኖ እንዳላሳድር በፆታ ላይ ሁለቱንም ተጠቅሜአለሁ ጊዜው የዕኩልነት ነውና እንዳልተመቻቸው አፍ አውጥተው ከሆነ ይነግሯችኋል አፍ ካለውጡ ጊዜው ቢያልፋም የምታምኑት እንደየምነታችሁ መጠን ማታ በህልም ይግለጡላችሁ እርጉዟ የጠረጠርኩት እውነት ሆኖ የተቀመጠችበት አልተመቻትም ለማስነሳት የኛን ሰው ፀባይ ጠንቅቃ ታውቃለችና እንዲነሱላት አስባ ለመነሳት ተግደረደረች አይገርማችሁም የኛ ሰው መጨካከን የጀመረው መቼና እንዴት በማን አማካኝነት እንደሆነ ባይታወቅም ተጨካክኗል የተግደረደረችውን ጨክና አደረገችው ተነሰታ ቆመች የገረመኝ ነገር ወንዱ ልጅ ገና ጐረምሳው አርግዞ ወይ አስረግዞ የማያውቀው ነፍሱ ሹክ ብላው አውቆ ነው መሰል ሲነሳ አጠገቧ የነበሩት ሲያጣብቧትና ሲያስነሳት የነበሩት ሴት ለዚያውም ሴት ወይዘሮ ስንት ጊዜ አርግዘው ያማጡ ዕርግዝና የልጅ ልጅ ባይኖረውም የልጅ ልጁን የሚያውቁት ሴትዮ ጨከኑባት ፍቅራቸውንም ፀባቸውንም ባላውቀውም አይዋደዱም የሚባለውን ስሞታ ሳይሆን አይቀርም ለማለት ደዳኝ እንዳላምን ግን አፍራሽ ነገር አጋጠመኝ ምን በሉ እንጂ አድማጭ አንባቢዎች ተረት ተረት ስንባል የመሰረት ስንል እንቅልፍ እየወሰደን እንዳደግነው መድረሻችን እስኪለየን፡፡
እንደእኔ ያለው ፈሪ በሆዱ ሲረግማቸው ግማሹ ሲገላምጣቸው ጨኻኝ ሲላቸው መቼስ የኛ ሰው ብዙ መልክ አይደል ያለው አዎ በሉ ከበስተኋለው የነበሩ ሰዎች ተመካክረው ነው መሰል እንጃ ሁለቱ ተነስተው አንዱ በዕድሜ የገፋ በሽበት የበለፀጉ እናትን ጨምረው ለሁለት አመቻችተው አሰቀመጧት አቤት የኛ ሰው ሥንት አይነት አለመሰላችሁ የኛ ሰው በሰው አገር የኛ ሰው በአገራችን…
በነገር እንዳያዝኳችሁ አውቶብስ እየሄደ እየሄደ ሰሜን ሆቴልን ተሻግሮ ቆመ በየመቆምያው መቆምና ሰው ማውረድ ብቻ ሣይሆን ሰው መጫንም ግድ ይለዋልና እንደእኛ የአንበሳ አውቶቡስን በየፌርማታው ዓይኑን ለማየት የልባቸውን ፈቃድ ለመፈፀም ወደ መደራሻቸው ለመድረስ ዓይናቸውን ስቅለው የሚጠብቁት ብን ብለው ሳይሆን ግር ብለው ወደ ትኬት ቆራጫ ተመሙ ውስጥ ካለነው አብዛኛው የቅድሙን የራሱን የዓይን ናፍቆት ገብቶ ተወጣውና ነገሩን ሁሉ ረሳውና ሾፌሩን በቃ በሩን አትክፈት ሞልቷል የት ለማስገባት ነው እያለ ማጉረምረም ጀመረ ለራሱ ቢሆን መሙላት አይደለም ቢተርፍ አይደለም አውቶብሱ ውስጥ አንበሳው ጫንቃ ላይ ተቀምጦ መሄድ የሚናፈቀው ወገኑን ተጨናንቆ ገብቶ ወደቤቱ እንዳይገባ አሳደደው በልቡ ከአንበሳው ደጅ አሳዳዳቸው አይገርምም የኛ ሰው ነገር የኔስ ነገር ብትሉ መንገዴ መንጐድ ትቼ የትዝብት ምች እንደመታው ሰው ምን አስታዘበኝ እኔንጃ ይግራማችሁና አንድ የገረመኝን ነገር ልንገራችሁ የኛ ሰው ክፋቱ እንደደግነቱ ሁሉ ወደር የለውምና የዘዋሪው/የሹፌሩ/ የትኬት ቆራጩ አሰማሪ/ሥምሪት ክፍል/ናት አሉ በዚህ ዋሉ በዚህ ውጡ በዚህ ግቡ ብላ የምታስጨንቃቸው ያ ሁሉ ምድረ ሰው ከአፋ እስከ ገደፍ ሞልቶ አንበሳውን አላስፈሳ አላስገሣ ያለውን ህዝብ ማን ጫን አለህ አውርድ ብላ ማንቁርቱን ያዘችው አሉ ዘዋሪውን ዓይኔን ወደዳጅ ጣል ሣደርግ ለተቀማጭ ሠማይ ቅርቡ አይደል ርዝመቱ ምን ያህል እንደሆነ ባታይወቅም ታታክረዋለች እርሱ ሊያስረዳት ይሞክራል ትኬት ቀንጣሿ ቶሎ ደርሰን እንመጣለን ብላ ትማፀናለች ከጐኔ የነበሩት መሄድ ያማራቸው ተጓዥች “ይኼ ሁሉ ህዝብ ቆርጦ ሲገባ የት ነበረች አለቃነቷን ይህ ሁሉ ሰው ይወቅልኝ ብላ ነው?”:‘የሴት ነገር ድሮም’…ወዘተ ይላሉ ፍርዱ ለመስጠት አንቀፅ ለመጥቀስ፣ቀነ ቀጠሮ ፣ምስክር፣ክርክር ፣ ግርግር ፣ ውዥንብር  ወዘተ … ስለሚያስፈልግ እኔ በድምፅ ተአቅቦ አልፌዋለሁ የኛን ሰው ግን ታዘቡልኝ፡፡
መቼስ ጥፊም ይደገም የለ አንድ ልድገማችሁ ጥፊ ቢደገም ያማል የኔ ደግሞ ትዝብት ይጨምራል ከመግቢያው እስከ መውጫው ጢም ያለው ሰው ለመግባት እንዳልቸኮለ ለመውጣት ያረገዘችው ሳያምጣት ምጥ የያዘቸው ዘዋሪውን አሰጨነቁት ኃላፊዋን በምልጃ ተሳፋሪውን የሆነ ጥግ ፈልጐ በውረጃ ተገላገላቸው የኛ ሰው ግን አይገርምም? ይገርማል ፡፡
የኛ ሰው መቼስ የማይለው የለም 59 ቁጥር ወይራ ሠፈር /ቤቴል/ መሄዷን ትታ ባህር ዛፍ ሠፈር ወደ አዲሱ ገበያ ምን ትሠራለች ሳትሉ አትቀሩምና ሾፌሩና ትኬት ቀንጣሿ መዘወር ያማራቸው ሳይሆኑ ሰው የመርዳት ፍቅር ያደራባቸው ነበሩና ተራቸው /ሰዓታቸው/ እስኪደርስ እንደ አፈር የፈሰሰውን ህዝብ ወደየቀየው ለመበተን ለአሰሪ መስሪያ ቤታችውም የማይነጥፍ ኪሳችውን ለማሰብ ነበር ፡፡
የኛ ሰው በኛ አገርም የኛ ሰው በሰው አገርም ቢወራለት ጉንጭ አልፋ ነውና እናንተ በቃ ባታውቁም እኔ ትዝብቴን በዚህ ላብቃ ሌላ ጊዜ እንዲሁ ሃሳቤን ካልሸወራረው የኛን ሰው እታዘባለሁ፡፡
የሆነ ቀን ነው አሉ ማን እንደሆነ ባላውቅም ስለ የኛ ሰው አስተያየት ለመጠየቅ እግዚአብሔር ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያለ ሰውን ጨምሮ ሃያሁለቱን ፍጥረት ሰብስቦ የታዘባቸሁትን ንገሩኝ አስተያየታችሁንም ስጡኝ ቢል ቀበሮ ቀድማ ተነስታ የኛን ሰው ታዝባ ታዝባ ሰው ምን እንዳረጋት ብትጠየቅ ብዙ የምትለው ቢኖራትም ‘ለሰው ሞት አነሰው’ ብላ ተቀመጠች አሉ እናንተስ ስለሰው መቸስ “ስለሰው ስለሰው ቀድጄ  ልልበሰው” እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ የኛን ሰው ገና እንታዘባለን፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...