‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን
አናወርስም’’
ጐበዝ ለካ ታክሲ መያዝም ይከብዳል!(ተራ አስከባሪዎች ባይኖሩና በሰልፍ ባያደርጉት እንጃ ወደየቤታችን መግባታችንን(አደራችሁን ዘይት፣ዳቦ፣ስዃር፣ መብራት፣ ዉሃ እና ኔትዎርክ በሰልፍ ይሁን እንዳትሉ ) ) እውነቴን ነው የምላችሁ እስከዛሬ በነበረኝ “ጥልቅ” ግንዛቤ የገንዘብ እንጂ “የዕውቀት” ችግር ያለ አይመስለኝም ነበር፤ (ብዙ ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ስለተከፈተ አለማወቅ አገር ለቆ ጠፋ ብዬ ነበርና የማምነው) በመሐላ ማረጋገጥ ካለብኝ እምላለሁ፤ ደሞ ለመሐላ መርካቶ በጠቅላላ መሐላ በመሐላ አይደል እንዴ ምን ችግር አለው ሳልምል እመኑኝ፤ በታክሲ ከመሔድ በእግር መሔድ በስንት እጥፍ ይበልጣል መሰላችሁ ሲመሽማ ‘’ወክ’’ በማድረግ ዘግዘቅ ማለት ነው ወደ ሰፈር፡፡
ያኔ አዲስ ዓመት መስከረም ሳይጠባ የነበረብኝን አባዜ ጦሴን ጥንቡሳሴን ብዬ በጳጉሜ ፀበል እና ህክምና ከላዬ ልይ ጥዬ አዲሱን አመት በአዲስ ጤና ለመቀበል ወደ ሆስፒታል አመራሁ የጳጉሜ 3 ፀበል ጥሩ( ለዚያዉም የጳጉሜ 3 የሩፋኤል ዕለት ከሁሉም ይበልጣል እጣ መጣል አያስፈልገውም) ሰፈር እስከ ማወክ ቤቶች እስከ መገለባበጥ በደረሰ ዝናብ ተፀበልኩ ጐበዝ!! አትሉኝም? (ለነገሩ ወረኛ ብትሉኝ ይሻላል ወሬ ከጀመርኩ አንዱን ሳልጨርስ ወደ ሌላ እሱን ትቼ ደግሞ ወደ ሌላ እሄዳለሁና) ሐኪሜ MRI ታየው ብሎኝ ለወገቤ ህመም ‘’ቤቴል ሆስፒታል’’ ላከኝ (አላውቅም ማለት ነውር አይደል?! ቦታው የት ነው? እንኳን ሳልል ተፈትልኬ ወጣሁ) ለነገሩ ምን ላድርግ ብላችሁ ነው ሄጄ እንድታከም ሲልከኝ ማስተባበያ ቃላት ጣል አደረገልኝ ይቅርታ ማከም አቅቶኝ አይደለም እዚያ የምልክህ የተሟላ ነገር እንኳን የለንም ለዚያ ነው ታየኛለህ አይደል ‘’ጓንት’’ እንኳን ሳይኖረኝ በእጄ ሥጠቀም ለዚህ ነው ይቅርታ አለኝ፡፡
በሞትኩት ዋናውን ነገር ዘነጋሁት አይደል፡፡ ተመለስኩ በቃ ከምላሴ ፀጉር ይነቀል ከእንግዲህ ወዲያ ወዲህ አልልም፤……
ቤቴል ወዴት አካባቢ አንደሆነ ጠረጠርኩ፣ ወደ ጦርሃይሎች ምን መጠርጠር ብቻ ኢላማዬ ግቡን መቷል ፡፡ እንደምንም ዳገቷን ወጣሁ በታመመ ወገቤ (ታዲያ እንዴት ነው በእግር መሄድ የሚቻለው አትበሉኝ አደራችሁን በቃ አኔ ካልኩ ይቻላል ችግር እንኳንስ በእግር ማስኬድ «በቅቤ» ያስበላል) ሌላውን ተዉት እኔም በቅጡ አላየሁትም ካርድ ክፍል አካባቢውን ካዩት የመንግሥት ሆስፒታል በምን ዕድሌ ነው የሚሉት (በአራዳዎች ቋንቋ ያጣጥፈዋል) ለነገሩ BPR ገብቶ የለ፤MRI ቁጥር 1 እንጂ እዚህ የለም ተባልኩ ሌላውን ነገር ሆድ ይፍጀው፡፡
እንዴት ነው የኔ ነገር አሁንስ እኔም ራሴን ታዘብኩት ስለ መጪው ትውልድ ማውራትና ስለራስ ማውራት ምን አገናኘው? እኔንጃ! ( በራሴ በጣም ተናደደኩ)
ወደ ዋናው ጉዳይ ገባሁ በቃ ላለፈው አፉ በሉኝ መቸስ የጠቅላይ ሚኒስትራችንን ሞት ያላስደነገጠውና ያላስደነቀው ሰው የለም ‘’አሸባሪዎችንና ፀረ ሰላም ሃይሎችን’’ ካልሆነ በቀር፡፡ እናላችሁ ከሞቱ ማግስት ከተማዋ በእርሳቸው ሞትና ፎቶ ማሸብረቁን ያላየ ካለ ይኸው ነገርኩት በቃ ምን ልበላችሁ ተለጠፈ አይደለም ተሰቀለ አይገልጠውም፡፡ ከተለጠፈው አንዱ ሳይሆን ብዙዎቹ እንዲህ ይላል ‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም’’ ልብ በሉና አንብቡት እኔ እንደ ሰዎቹ አልፃፍኩትም ወይም አላነበብኩትም አንዳንዶች ‘’ፀረ ልማት’’ ሐይሎች ወይም የአቡጊዳ ሽፍቶች (በአራድኛ) ‘’ለመጪው ትውልድ ልመናን እንጂ ልማትን አናወርስም’’ ብለው በፈጣኑ የልማት እደገታችን ላይ ያላግጣሉ ዝም በሏቸው እኛ በዓመት በዓመት እንደ ፍቅረኛችን ቻይና በእድገት ተመንድገን ለአሜሪካ ስናስቸግራት ደግመው እቤታቸው የሰቀሉትን አውርደው ያነቡታል፡፡ «አሽሟጣጮች» በሏቸው ልብ ገዝተው እስኪመለሱ፤
ከዚህ በላይ በአንድ ነገር ላይ መቆየት አልችልም ተመልሼ እመጣለሁ፡፡ ቅድም ምን ነበር ያወራነው? ይቅርታ ያወራሁት?
ከቤቴል ቁጥር 2 ወጣሁ ወደ ቁጥር 1 ለመጓዝ አደራችሁን እንደወጣህ ቅር አትበሉኝ ቢሆንም ወሬ ማቆርፈዴ እንደሚያናድዳችሁ ይገባኛል፡፡
ጦር ሃይሎች ሄጄ ቤቴል የሚል ታክሲ መያዝ እንዳለብኝ ተነገረኝ ግን ምን ዋጋ አለው ጦርሃይሎች ትልቁ የታክሲዎች መናኸሪያ ሲገቡ የትኛው ታክሲ የት እንዳለው ማወቅ ይከብዳል ዕድሜ ለታክሲዎቻችን ቀና ብዬ ‘’ታፔላው’’ ላይ ማንበብ ጀመርኩ (እንደኔ ከሆናችሁ አንድ ምክር ልለግሳችሁ አንጋጣችሁ ታፔላ ሲያነቡ ገንዘብ ካልዎት ኪስዎትን ይጠብቁ) ሁሉም ማለት እስኪቻል ድረስ ወደ አብነት ፣ ሜክስኮ፣……………… ይጠራሉ ‘’መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ’’ አይደል የሚባለው ጠይኩ (እናንተም ጠይቁ) ሆስፒታሉን ማግኘቴን አትጠራጠሩ፡፡
አንድ ነገር ትዝ አለኝ የልማት መሃንዲሳችንን ባለራዕዩ መሪያችንን የጀመሩትን እናስጨርሳለን እያልን ቃል እየገባን በሌላ በኩል ለልማት የሚውለውን ገንዘብ ለቢል ቦርድ፣ ለቲሸርት፣ ለኮፍያ፣……….. ወዘተ ማባከን ምን የሚባል ነው?እርሳቸው እንደሆነ ፎቶ እንዲለጠፍላቸው ቢልቦርድ እንዲስቀልላቸው ሐውልት እንዲቆምላቸው አይፈልጉም የልጅነት ሚስታቸው እንደነገሩን ከሆነ፡፡ ልብ ብላችኃል የጥቅስ አይነት አካበድከው አትበሉኝ እንጂ የተሰቀለው ነገር ብዛት ሰፈሩን ሌላ ሠፈር እስኪመስል ድረስ ጠዋት አገር ሰላም ብለው ከሰፈር እንዳልወጡ ማታ ሲመለሱ ሰፈርዎት ይጠፋዎታል ለመሆኑ በአሥሩም ክፍለ ከተማ የተሰቀለው ቢልቦርድና መፈክር የተለበሰው ቲሸርትና ኮፍያ አገራችን ወጪዋን ብቻዎን ቻለችው ወይስ የቻይና እጅ አለበት? (ቶሎ መልሱልኝ የ100 ብር ጥያቄ ነው) የሆነው ሆኖ የአባይ ነገር እንዴት ሆነ ጐበዝ? የአባይን ነገር እንመለስበታለን ይኸንን ሃሳብ ምንጩን ጠቅሼ ልዝጋው ያስብልዎታል ኧረ ቻይና ብቻዎን አትችልም…..፡፡ ምንጭ አሽማጣጦች፤(ዓባይማ ሁለት ዓመቱን ቅርጥፍ እንዳደረገዉ ኢቲቪ ነገረኝ!)
ጠዋት የወጣሁት በሌሊት ነው ሥራ ለመግባት 1፡30 ሰዓት
(ሆዳችሁን እስኪያማችሁ ሳትስቁ አልቀራችሁ 1.30 ሰዓት ሌሊት በመሆኑ)ይሁን ለኔ ሌሊት ነው፡፡ በዚህ ውድቀት ሌሊት ሰባት ቢበዛ የስምንት አመት ልጅ ከመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሣንቲም ሊሽጥ ሲደረድር አየሁት (ልብ አርጉ ሲሽጥ እንጂ ሲለምን አላልኩም) ገና ከተቀበሩ አመት ሣይሞላቸው ይህን አንድ ፍሬ ልጅ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ሣንቲም ለባለታክሲዎች ሲሸጥ (ሲዘረዝር) ልቤ በደስታ አንድም በሃዘን ቀለጠ ተሰበረም ምነው አትሉኝም ደስታው ራዕያቸው እውን ሲሆን በማየቴ ልመናን እርግፍ አድርጐ ትቶ ለሥራ ሲሰማራ፣ ሃዘኔ ዳግም በዚህ ዕድሜ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባው ለህፃናት መብት ሲሟገቱ የነበሩ የጠቅላይ ሚኒስትራችን ራዕይ የህፃኑ ጉልበት ያለዕድሜው ሲበዘበዝ በማየቴ አንጀቴ እርር ቅጥል አለ ለነገሩ ምን አንጀት አለ ብላችሁ ነው በአሽማጣጮችና ‘’በፀረ ልማት ሃይሎች’’ ታክቲክና ቴክኒክ አርሮ አልቆ፡፡
የአባይን ነገር አንስተን ነበር የኔን ሃሳብ ከሰው ሃሳብ አልቀላቀልም ብዬ የተውኩት ‘’አባይ ይገደባል……..’’ ‘’ልመና ታሪክ ይሆናል፤……..(ግራ እጄን እንዳነሳሁ ልብ አርጉልኝ) መፈክሬን ካሰማሁ ዘንዳ እንዴት እንገድበው? ጥያቄ ቁጥር አንድ መቸስ በልመና እና እርዳታ አናደርገውም ገና ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሞተው ቤተሰባቸው ሣይፅናኑ እሳቸውም የመቃብርን ኑሮ ሣይላመዱማ አይሆንም አይደረግም ‘’ሼም’’ የለም እንዴ?! ለነገሩ ለምደውታል ለረጅም ዓመታት የኖሩበት ቤተመንግሥት ብዙም አይራራቅም እርማችንን ለማውጣት የገባን ጊዜ ያየነው ከሆነ እንዲያውም መቃብሩ ሣይሻል አይቀርም በሴራሚክ ነው የተሰራው ደግሞ አዲስ ነው ይሉና ይከራከራሉ ሞተው የሚያውቁ እንደ መከራከሪያ ነጥብ ሲያቀርቡ (ምን ሆኜ ነው ‘ሞተው የሚያውቁ እላለሁ እንዴ አይባልም አይደል? ይቅርታ አድርጉልኝ ለነገሩ የብዙዎቻችን ኑሮ ከቆሙት በታች ከሞቱት በላይ ስለሆነብኝ ነው) በቃ ልመናን አናደርገውም፤ የተጀመረውም በአንድ ወር ደሞዝ ቦንድ መግዛት የብዙዎችን አስተያየት ስሰማ (ይታረምልኝ ሹክሽክታ) በራሳችን ላይ ራስን ለማጥፋት ቦንብ መግዛት ነው ይላሉ፡፡ የኑሮን መወዳድ፣ የትራንስፖርትን ችግር፣ የቤት አከራዮችን ጨካኝነት ግንዛቤ ውስጥ በመክተት(አደራችሁን ለአከራዮች ቦንድ መግዛታችሁን አትንገሩ ቦንብ የገዛችሁ ያህል ነዉ በአይነቁራኛ የሚያዩአችሁ፣ ኮንደሚንየምማ ከወጣላችሁ ነገር ተበላሸ …)፤ የልጆች ወጪና የተለያዩ የማህበራዊ ጉዳዮች (ማኀበራዊ ምግብ አላልኩም የርሱ ዋጋ የማይቀመስ ስለሆነ) የተለያዩ ወጪዎች ሲደመርበት ብድር አይደለም ስርቆት ቢጨመርበት የሚያዋጣና የሚቋቋሙት ነገር አይደለም ለጊዜው ምንጩን ባላውቅም አባይ ይገደባል፡፡ ቆይ ቆይ የአባይን ግድብ በጀት ለመምታት ግብፅና ሱዳን ተስማሙ ነው ወይስ ለመገደብ በጀት (የገንዘብ ችግሩን የሚፈታ) ምክክር አደረጉ ነው፡የሰማሁት? የዘንድሮ ጆሮና ኑሮ አስቸጋሪ ሆነኮ ሰዎች? ….. ብቻ ከሁለት አንዱን ብለዋል፡፡
የጤና ነገር ከተነሳ አይታመሙ እንጂ ታመው ሐኪም ቤት መሔድ አያስፈልግም መዳን ወይም መፍትሔ አለማግኘት እንዳለ ሆኖ ዋጋውኮ ከመቶ ኪሎ ጤፍ ጋር እኩል ቀለብ ነው የሚመስለው፡፡ አንዴ ከታከሙ ተመልሰው የማይታመሙ ይመስል ሁሉ ነገር ውድ ነው ካርድ ከ100 ብር በታች ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ ይመስላል የመድኃኒቱን አይነትና ውድነት የሚታዘዘው የምርመራ ዓይነት ብዛት ሌላ በሽታ ያመጣበዎታል ላብራቶሪ፣ ራጅ፣ አልትራሳውንድ፣MRI፣cityscan፣ እረ ምኑቅጡ እኔን መዘርዘር ያቅተኝ እንጂ ሐኪሞች መፃፍ አያቅታቸውም ‘’በሠው ቁስል እንጨት ቆስቁስበት’’ ነበር ያለው ቀልደኛው ይሁን ግዴለሽ ይፃፉት ይሁን ግዴለም እኔም ልክፈልና ልመርመር፣ ምናለበት የበሽታውን ቅጡን ባወቁት(ስለማወቅ ካነሳሁ አይቀር አንድ ነገር ላዉጋችሁ፡-ሃኪም ቤት ሄድኩ በደምና በሰገራ ዘጠኝ ዉጤት ላመጣ ተፃፈልኝ፣ ከዚያ የተባልኩትን ሁሉ አድርጌ ዶ/ር ጋር ተመለስኩ እርሱም የመድሃኒት ዝርዝር መፃፍ ሲጀምር አያያዙ አላምር አለኝና ምን ተገኘብኝ? አልኩት፤ ይህን መድሃኒት ስትወስድ ይሻልሃል አለኝ፡፡ በሽታዉ ምንድን ነዉ? አልኩ ድምፄን ከፍ በማድረግ ልትጨቃጨቅ ነዉ ልትታከም ነዉ የመጣኸዉ … ዉጣልኝ ታካሚ አለብኝ፤ ብሎኝ እርፍ አሁን እንዃን እዛ ልታከም ስታድየም ዃስ ለማየት አልሄድም አደራችሁን ለመታከም ስትሄዱ ሃኪም አታበሳጩ፣ በሃኪምም አትበሳጩ፤ ) ለምን ያደክመናል መቸስ ከቤታችን እንጂ ከኤርትራ ወይ ከሱማሌ አልመጣን (ይቅርታ ከሱማሌ አልኩኝ ሰዎች እነዚህ ሱማሌዎች የኛዎቹ ናቸው የነዚያዎቹ በቅጡ ባላውቃቸውም ሲታመሙ ነው እንዴ የሚያድሩት ለነርሱ ብዬ የት ልሒድ መረረኝኮ በየግል ሐኪም ቤቱን እነርሱ ናቸው የሞሉት) ነገርን ነገር ያነሳዋል አሉ ነገረኖች ማን ነበረች ያቺ ስለሴቶችና ህፃናት ሞት ስትሟገት ስትፅፍ፣ ስታፅፍ የነበረችውና እናቶች በወሊድ ምክንያት መሞት የለባቸውም ብላ ሣታበቃ በወሊድ ላይ እያለች የገደሏት? (ይቅርታ የእስክርቢቶ መገንፈል ችግር ነው የገደሏት የሚለውን የሞተችውን ብላችሁ አስትባብሉልኝ) (ይቅርታዬ እንደበዛ ይገባኛል ያው ሰባት ጊዜ ሰባ ድረስ ይቅር ትሉኛለችሁ ብዬ ነው)
እንዲሁ በከንቱ እንዳደከምኳችሁ የገባኝ ሲደክመኝ ነው፣ ለማንኛውም ሥናጠቃልል አደራችሁን ‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም’’ በማለት ባይሰማኝም ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ቃል ግቡልኝ አትፍሩ ቃል መግባት ማንን ገደለ ብዙ ባለሀብቶች የተጀመሩትን ለማስፈፀም ደጋግመው ቃል ገብተው የለ ያስፈፀሙት ባይኖርም፡፡
መጀመሪያዬ ላይ ስለ አዲስ ዓመት አውርቼ ዝም ብዬ ሄድኩ ለማንኛውም አሁንም ቢሆን ‘’እንኳን ለሚመጣዉ አዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፡፡ ግዜዉ ስለሚበር አንብባችሁ እስክጨርሱ አዲስ ዓመት መምጣቱ ስለማይቀር፤ መቸስ ይህ ዘመን ብሩህ ነው አይደል? ብሩህ ዘመን ያድርግላችሁ ዶሮና በግ ረክሰው የገበሬውን ሆድ አራርቶልን ሽንኩርትና ቅቤ እንዲሁ በሽበሽ ሆኖ ለቁርጥ ሥጋ ኪሎ 52 ብር ገብቶ ለመንበሻበሽ ያብቃን (አሜን በሉ ከአሜን ይቀራል ይላሉ የኔ አያቶች) በዚያው ዳግም ጨው የሌለው ነገር ሥለማይጥም ጨው ነጋዴዎችንም መንግሥት ፌዴራሎችን ልኮ አደብ ያሥገዛልን፤ እንግዲህ ከምንም በላይ ጤና ነውና ጤና ይስጣችሁ የጤና ነገር ሲነሳ አሁንም ይቺን ነገር ስቦጫጭርላችሁ እዚያው ሆስፒታል ወረፋ እየጠበኩ ነው (ወረፋ ሲባል የዳቦ ቤት ወረፋ እንዴት ሆኖ ይሆን? እኔ እንደሆነ መቆምም ስለማልችል መግዥያውም ስለጠፋኝ ትቼዋለሁ) እናላችሁ አራት ሰዓት ትንሽ ሰዓት ጠብቅ የተባልኩት 11፡30 ሰዓት ሆኖብኛል ገንዘቡ ኖሮ ልትታከሙ ብትሄዱ ለልማት መዋል ያለበት ጊዜ በወረፋ መጠበቅ ስለሚያልቅ ጊዜውም ችግር ይሆንባችኃል፡፡ የኃኪም ቤት ነገር ከተነሳ ወረፋ ይዞ ከመታከም አንድያውን ……… አልጨርሰውም ይቅርብኝ ፡፡
ታዲያ በዚህ ሁኔታ የትኛዋ እናት ትሆን በወሊድ ከመሞት ተርፋ ልጇን በሰላም ተገላግላ በጤና አድጐላት ልመና ቀርቶ ልማትን የምናወርስው? ፈራሁ! (የምን ፍርሃት ሰው ታሞ እንጂ ፈርቶ አይሞትም) ልማትን እናወርሰዋለን፡፡

የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta'S Views : ‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም’’ >>>>> Download Now
ምላሽ ይስጡሰርዝ>>>>> Download Full
የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta'S Views : ‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም’’ >>>>> Download LINK
>>>>> Download Now
የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta'S Views : ‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም’’ >>>>> Download Full
>>>>> Download LINK