Believe
That Success Is Your Birth Right
የስኬት
ህጎች
መጀመሪያ
ሊያዉቋቸዉ የሚገባዎትን ጠንቅቀዉ ሳያዉቁ ስኬታማ ለመሆን አስበዉ ያዉቃሉ?
ስለስኬት ህጎች ሳያዉቁ ስኬታማነትን ማሰብ ፡- ስለማሽከርከር ህግ ሳያዉቁ እና የመንገድ ደህንነት ህጎችን ሳይረዱ መኪና እንደማሽከርከር ይቆጠራል፡፡
ሆኖም ስኬት የምርጫ ጉዳይ እንጂ በሌላ ሰዉ የሚጫኑት አይደለም፡፡
የስኬትን
ህግ ካወቁና ከተገበሩ ስኬታማነትን ባይፈልጉ እንኳን የተሳካለት ሰዉ ነዎት፡፡ የተለያዩ የሰዉን ልጅ ለስኬት የሚያበቁ ክንዉኖች
አሉ የእርስዎ ስኬት የትኛዉ እንዲሆን ይፈልጋሉ?
Ø
ሃብት ፡- የገንዘብ
ብዛት ከአስተሳስብ ድኅነት አያድንምና የእርስዎ ሃብት ምን እንዲሆን ይሻሉ?
Ø
ዕዉቀት፡- ወደ ተግባር
የማይለወጥ ዕዉቀት የጋን ዉስጥ መብራት ነዉና የእርስዎ እዉቀት ለርስዎ እና በዙሪያዎ ላለዉ ምንድን አደረገ?
Ø
ጥበብ፡- ጥበብን
መፈለግ እንቁን ከመፈለግ በእጥፍ ይሻላል እርስዎ ጥበብን ለመፈለግ ምን ያህል ዋጋ ይከፍላሉ?
Ø
ትዳር/ቤተሰብ፡-
ቤተሰብ የአገር መሰረት ነዉና ትዳሮትን ምንድን ላይ ነዉ የመሰረቱት አለት ላይ ወይንስ አሸዋ ላይ?
Ø
ስራ፡- ዕለት ተዕለት
ጥሮ ግሮ የሰዉ ልጅ ህይወቱን እንዲመራ የአምላክ ትዕዛዝ ነዉ እርስዎ ስራዎን ሲሰሩ ዉጤታማ ለመሆን ነዉ ስራዎን ለማጠናቀቅ ብቻ
ነዉ የሚሰሩት …
Ø
ወዘተ …
1.
የመፈለግ ህግ
"አንድን ነገር እጅግ ጠንካራ በሆነ ፍላጎት ከፈለጉት እንደሚያገኙት
አይጠራጠሩ ፤"
Ø ጠንካራ ፍላጎት የስኬት መነሻ ሲሆን እንዲሁም ግብን ያሳያል አንድ ሰዉ ጠንካራ ፍላጎት
ካለዉ በልቡ የሞላዉን ፍላጎቱን ለማሳካት ይጥራል፤ ያሳካዋልም፡፡
Ø ጠንካራ ፍላጎት ነገሮችን በድል ለመስራት ትልቅ ሃይል ነዉ፤ (እኤአ 2000 ላይ ኃይሌ
ገብረ ስላሴ በሲዲኒ ኦሎምፒክ ህመሙን ታግሶ አንደኛ በመዉጣት ያሸነፈዉ ፖልቴርጋት ቀሽም ስለሆነ ወይንም ተወዳዳሪ ስላልነበረ ሳይሆን
ኃይሌ የማሸነፍ ጠንካራ ፍላጎት ስለነበረዉ ነዉ፡፡ለኃይሌ
መሸነፍ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ አማራጭ አልነበረም / አይደለምም) ፤ ለጊዜዉ ስሙን የማላስታዉሰው የጦር ጀነራል የነበረ አንድ ሰዉም የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ተልዕኮዉን ለመወጣት
ሰራዊቶቹን ይዞ ባህር አቋርጦ በሄደ ጊዜ የተሻገረበትን መርከብ በማቃጠል እና ድልድዩን በመስበር ነበር ጦርነቱን የጀመረዉ ምክንያቱም
ጠላትን ድል ሳያደርግ የሃገርን ዳር ድንበር ሳያስከብር ወደ ኋላ የመመለስ ህልም አልነበረዉምና፤ ጠንካራ ፍላጎቱ ድል እንጂ ወደ
ኋላ መሸሽ/መመለስ አልነበረምና ነዉ፡፡ መርከቡ እና መሸጋገሪያዉ ድልድይ ቢኖር ፈሪዎች ወደ ኋላ መመለስን እንደ አማራጭ ይጠቀሙበት
ነበርና ነዉ፡፡ ስለዚህ እኛም ወደ ኋላ የሚመልሱንን ከስኬት ከተሻለ ለዉጥ ወደ ኋላ የሚያሰቀሩ መንገዶችን ልናቃጥል አዉጥተን ልንጥል
ይገባናል፡፡
መፈለግ፡- ማግኘት የሚፈልጉትን ነገር እስከሚያገኙ ድረስ አንዳች ሃይል እንዳያስቆምዎት ያስችላል፡፡
ሁል
ጊዜም ስለግብዎ ያስቡ፡-
መጀመሪያ ግብ አለዎት?
ግብዎት ምንድን ነዉ?
ግብዎን ምን ያህል ለማሳካት ይፈልጋሉ?
ግብዎን ለማሳካት ምን ያህል ዋጋ ይከፍላሉ?
በምን ዓይነት ሁኔታ ዉስጥ ነዉ ተስፋ ቆርጠዉ እጅዎን
የሚሰጡት?
ይልቅስ
አንድን ነገር አጥብቀዉ ከፈለጉ የፈለጉትን ነገር መተዉ አማራጭ እንደሆነ በፍፁም እንዳያስቡ ….
ü የሚሳካበትን መንገድ ብቻ ይፈልጉ፣
ü መክፈል የሚገባዎትን ዋጋ ሁሉ ይክፈሉ፤
ü ሁሌም ግብዎን ከምንም በፊት ያስቀድሙ፡፡
ፅኑ ፍላጎትዎ ለስኬትዎ ዋና ሞተር ነዉ፤
ፍላጎትዎ ጠንካራ ካልሆነ እና ወደሚፈልጉት ስኬት ሊያደርስዎት
ካልቻለ፡-
ü
በማስታወሻዎ ላይ ማሳካት የሚፈልጉትን
ነገር ለምን ማሳካት እንደፈለጉ ምክንያትዎን ይዘርዝሩ፣
ü
ማሳካት ከሚፈልጉት ጉዳይ የሚያገኙትን
ትርፍ/ጥቅም/ ይዘርዝሩ፣ የሚፈልጉት ነገር እየበዛ በሄደ ቁጥር እያደር ጠንካራ የመሆን ዕድልዎ እየጨመረ ይሄዳልና፤
ü
የስኬት ፍላጎት መዘርዝርንም
ዘወትር ጠዋት ማንበብ እና ስለርሱ ማሰላሰልዎን አይዘንጉት፡፡
መልመጃ፡-
i.
በህይወትዎ ዉስጥ ያለዎትን ግብ ይፃፉ አያይዘዉም ለምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ጭምር ይጥቀሱ
ii.
አቅም እንዲሆንዎ አሁን ያሉበት የሥራ መደብ ሰራተኛ በመሆንዎ ያገኙትን ጥቅም ይዘርዝሩ
2.
የማመን ህግ
"ማንኛዉም እዉነት ነዉ ብለዉ ያመኑት ነገር ወደ እዉነታነት
/የገሃዱ ዓለም/ይቀየራል" ይህ ማለት
ü
ይሳካል ብለዉ ካመኑ ይሳካል
ü
አይሳካም ብለዉ ካመኑ የሚሳካ
ነገር እንኳን ቢሆን ለእርስዎ አይሳካም፤ ቢሳካልዎ እንኳን ጥቅሙ አይታይዎትም፡፡
1)
ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ ማመን ካልቻሉ ምንም እንኳን
ጠንካራ ሰራተኛ ቢሆኑ ስኬትን አያዩትም፡፡
2)
ስኬታማ ለመሆን ከምንም በፊት ማመን ይጠበቅብዎታል፡፡
Ø የሥነ-አዕምሮ ጠበብቶች አዕምሮአችን በህልማችን እና በገሃዱ ዓለም መካከል ያለዉን ልዩነት
እንደማያዉቅ ይናገራሉ፡፡ ዘወትር የምናስበዉ ነገር ወደፊት ለምናሳካዉ ነገር ሃይል/ጉልበት/ ይሆነናል፡፡በተዘዋዋሪ የዛሬዉ እምነታችን
የነገ ፍሬአችን/ዉጤታችን ነዉ ማለት ይቻላል፡፡
Ø ሊያሳኩ ባሰቡት /ባቀዱት ነገር ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ከሆኑ/እምነቱ ካለዎት እንዳያሳኩት
የሚያግድዎት ነገር የለም፡፡ (ይህ ማለት ተግዳሮቶች የለም ማለት አይደለም ማሳካት ስለሚፈልጉት ነገር ማሸነፍዎ እንደማይቀር በማመን
ጭምር እንጂ)
መልመጃ፡-
1)
አሁን ያቀዱትን ነገር ማሳካት እንደሚችሉ ማሰብ ችለዋል?
2)
እስኪ ሁለት ዓይንዎን ይጨፍኑና እራስዎን ይመልከቱ/ያቀዱትን
እንዳሳኩ ይስቡ/
ምን ተሰማዎት?
ደስታዎ ምን ያህል ነዉ?
ያቀዱትን ነገር
እንደማያሳኩት ይሰማዎታል? እንግዲያዉስ፡-
1.
ዘወትር ማታ ከመተኛትዎ በፊት
ለጥቂት ደቂቃዎች ማሳካት የሚፈልጉትን ነገር ያሰላስሉት
2.
ዘና በማለት ዓይንዎን ይጨፍኑ
እና ማሳካት ስለሚፈልጉት ነገር ግልፅ የሆነ ምስል ወደ አዕምሮዎ ያምጡ ፤ ይህን ምስል በትክክል እንደተሳካልዎት በማሰብ ደስታዉን
ያጣጥሙት፡፡ የሚታይዎት ምስል ነፍስ ይዝሩበት እየተጠቀሙበት እንደሆነ ያስቡ፡፡
3.
ይህንን ነገር በራስ መተማመንዎን
እስኪያዳብሩ ድረስ እና ህልምዎት/ግብዎን እስኪያሳኩት ይለማመዱት፡፡
ማሳሰቢያ፡-
የሥራ ባልደረባዎ /ቤተሰብዎ/የቅርብ አለቃዎ/ጓደኛዎ … ሊያደናቅፍዎት ስለሚችሉ ህልምዎን አጋርዎ
ካልሆነ ሰዉ ዘንድ ያርቁት፡፡
መልመጃ፡-
ሁለት
ደቂቃ ይዉሰዱና ዓይንዎን በመጨፈን በቀጣይ ጊዜዎት ሊያስመዘግቡ ስለሚፈልጉት ዉጤት ፣ ሊኖርዎት ስለሚፈልጉ ቤት እና መኪና፣ ሊያስተዳድሩት
ስለሚፈልጉት ቤተሰብ እና ሰራተኛ፣ ሊሰሩበት ስለሚፈልጉበት የመስሪያ ከባቢ፣ … ወዘተ ስለህልምዎ ያሰላስሉ፡፡
3. የአዎንታዊ አመለካከት ህግ
"የምናስብበት ሁኔታ የምናሳካበት/የምንተገብርበት መንገድ
ነዉ"
ü አመለካከትዎ ሁለነገርዎ ነዉ፤
ü ስለዙሪያ ገባዎ የሚመለከቱበት እይታዎ ከሚያጋጥምዎ ነገር ጋር የሚደራደሩበት መንገድ ነዉ፡፡ስለህይወትዎ
የሚያስቡት ከዚያ አከባቢ የራቀ አይደለም፡፡(ከባድ መስሎ የሚታይዎት ነገር በዘመድ/በገንዘብ/ … በስተቀር የማይሆን/የማይሳካ መስሎ
የሚታይዎ ከሆነ ከዚያ ዉጭ አማራጭ አይታይዎትም፡፡)
ü እራስዎን በደንብ ያድምጡ ፡- የሚሰማዎት " ፈጣሪ ሆይ ህይወት በጣም ከባድ ነዉ… መቼም ቢሆን አይሳካልኝም … ነገሮች ሁሉ በእኔ ላይ ጠመዋል … ሰዉ ሁሉ ይጠላኛል
… " ከሆነ በትክክል ችግር አለብዎት፡፡
"መሰናክሎችን መቆጣጠር አንችል ይሆናል ነገር ግን አመለካከታችንን መቆጣጠር እንችላለን፤"
ü ቀና አመለካከት እና መልካም ነገርን የመጠበቅ አዝማሚያ ስኬትን ለማምጣት እንደ ማግኔት
ናቸዉ፡፡
ü ቀና አመለካከት ላለዉ ሰዉ ከዉድቀት እንኳን ብዙ ወደ ስኬት ሊቀየሩ የሚችሉ መልካም አጋጣሚዎች
አሉት፡፡
ü በመሰረቱ ስኬት የሚገኘዉ ከብዙ ዉጣ ዉረድ /ሙከራ/በኋላ ስለሆነ እያንዳንዱ ሙከራ ወደ
ስኬት አንድ እርምጃ ያቀርቡናል፡፡
ቀና አመለካከት እንዲኖርዎ ፡-
I.
ራስዎን
ያዳምጡ፡- (አሉታዊ ነገሮች ሲያጋጥመንም ሆነ በማንኛዉም ጊዜ እራስን
ማዳመጫ ለማንኛዉም ሰዉ አስፈላጊ ነዉ)
II.
በቂ
እንቅልፍ ይተኙ፡- (በቀን ቢያንስ ለስምንት ሰዓት የእንቅልፍ ጊዜ
ያስፈልጋል)
III.
የነገሮችን
ትክክለኛ ገፅታ ያስቀምጡ፡- (ለማስተባበል /ለማስመሰል ስንል እዉነታዉን
መደበቅ እራስን መዋሸት እንጂ ለዉጥ የለዉም)
IV.
በበቂ
ሁኔታ እረፍት ይዉሰዱ፡- (ለሰዉ ልጅ የስራ ሰዓት እንዳለዉ ሁሉ
የእረፍት ሰዓት ያሰፈልገዋል፤ እረፍት የሌለዉ ሰዉ ምርታማነቱ እየቀነሰ ከመሄዱም ባሻገር የጤና መታወክ ሊያጋጥመዉ ይችላል)
በምንም
ዓይነት አጋጣሚ ዉስጥ ሆነዉ ቀና ነገርን ማሰብ ህይወትዎን ደስተኛ ከማድረጉም ባሻገር ወደ ሚያስቡት ስኬት ያቀርብዎታል፡፡
መልመጃ፡-
- ü በህይወት ዘመንዎ ያጋጠመዎ አንድ መሰናክል ይፃፉ፤
- ü በህይወት ዘመንዎ ስለ አጋጠመዎ ሁለት መልካም አጋጣሚ ይጥቀሱ፡፡
- Ø በህይወት ዘመኔ አጋጥሞኛል ስለሚሉት አንድ ዉድቀት ይፃፉ፤
- Ø በህይወት ዘመንዎ ከአጋጠመዎት እና ከዚህ ዉድቀት ልምድ ያገኙትን ለዉጥ አምስቱን ይዘርዝሩ፡፡
- v ከትናንት ዉድቀት መማር ካልቻሉ አሁንም ለመዉደቅ ዝግጅት ላይ ነዉ ያሉትና ላለመዉደቅ ይጠንቀቁ፡፡
4.
የፅናት ህግ
"ሙከራዎትን ካስቀጠሉ ያቀዱትን ማሳካት ይችላሉ"
o
የፅናት ችሎታ ሰዎች ለስኬት
የሚያደርጉት ተግባር ነዉ፤
o
ከመጀመሪያ ዉድቀት በኋላ ስንት
ጊዜ ለማቋረጥ ሞክረዋል?
o
ስኬት ከመጀመሪያዉ ሙከራ በኋላ
ተከትሎ በፍፁም አይመጣም፤ እጅግ ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ህይወት በብዙ ድካም የተገኘ እንደሆነ ይጠቁመናልና፡፡
o
ግብዎ የፈለገዉ ነገር ቢሆን
መሰናክል አያጣዉም፤ መሰናክል የስኬት የህይወት አካል ነዉና፡፡ ሁል ጊዜ መሰናክልን ይጠብዉት፣ ይማሩበት፣ ራስዎን ከመሰናክል ጋር
ያለማምዱት፣ …
v የዓላማ ፅናት ከሌለዎት
ህልምዎን እንዳያሳኩ በዙሪያዎ ላሉ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ፈጣሪዎች በቀላሉ ይጋለጣሉ፡፡ እነዚህም፡-
1)
ጓደኛ፡- ሰዉ ባለንጀራዉን ይመስላልና ባለንጀሮቻችንን
እንጠንቀቅ
2)
ዘመድ፡- ክፉ የማይመስሉ ሃሳቦችን በማምጣት
ከዓላማችን ይነጥሉናል፤
3)
ክፉ አሳቢዎች/አድራጊዎች፡- መጽሐፍ
ከክፉዎች ራቅ እንዲል ከክፉዎች መራቅ ይገባናል፤
4)
ማህበረሰብ፡- አንድ
ህፃን ይዞ የሚመጣዉ ብሩህ አመለካከት ሲሆን በአከባቢዉ ካለዉ ማህበረሰብ ከሚደርስበት የሥነ-ልቡና ጉዳት ወይም መጥፎ ገጠመኝ የተነሳ
ብሩህ አመለካከትን ለማጣት ይገደዳል፡፡ ዓለማዉንም ይስታል፡፡
5)
አጥፊዎች
6)
ፍርሃት
ለዓላማቸዉ
በመፅናት ብዙ ሰዎች ከብዙ ዉጣ ዉረድ በኋላ ለስኬት በቅተዋል፤
1.
ቶማስ ሂድሰን ከ10ሺህ ጊዜ ሙከራ በኋላ እንዲሳካለት ያስቻለዉ ጽናቱ
ነበር
2.
3.
4.
5.
የኔ
የሚሏቸዉ የተሳካላቸዉን በመዘርዘር እነርሱን ለመምሰል ይጣሩ፡፡
ያለዉድቀት
ልምድ/ተሞክሮ/ለዉጥ በፍፁም አይገኝም፡፡ ዉድቀት የህይወት መጨረሻ ሳይሆን የስኬት መጀመሪያ ነዉ፡፡
5.
ግብን የመቅረፅ ህግ
"ግብን ያላስቀደመ ስኬት በፍፁም የለም"
ግብን
መቅረፅ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችል ጉልበት ያለዉ መሳሪያ ነዉ፡፡
የግብ መኖር፡-
v ትኩረታችንን ይስባል፣
v መነቃቃትን ይፈጥራል፣
v ቀስ በቀስ ለስኬታችን የሚያቀርበንን ተግባር እንድናከናዉን ይረዳናል፤
ያለበቂ እና ትክክለኛ ግብ ህልማችን ህልም ብቻ/ቅዥት ሆኖ ይቀራል፡፡
ግብን መቅረፅ ዉጠየታችን ላይ ተፅዕኖ ማሳረፍ ይችላል፡፡
1) ምርጫ፡- ግብ እይታችንን /አመለካከታችንን በቀጥታ ጠቃሚ ወደሆነ ነገር ብቻ እንዲሆን ያደርጋል፤
2) ጉልበት፡- ግብ ዘወትር የምናወጣዉን ጉልበት ልናሳካዉ ወደምንችለዉ (ወደአቀድነዉ) ነገር የበለጠ
እንድንጠቀም ይረዳናል፡፡
3) ፅናት፡-
4) ግንዛቤ፡- ግብ የእያንዳንዳችን ባህሪ እንድናዳብር ይረዳናል፡፡
የምንቀርፀዉ ግብ SMART መሆን አለበት
1)
S Specific የተወሰነ/የተመጠነ
መሆን አለበት፡- ም/ለምን/እንዴት? የሚሉትን ጥያቄ የሚመልስ መሆን አለበት፤
2)
M Measurable
መለካት የሚችል መሆን አለበት፤
3)
A Attainable
ሊተገበር የሚችል መሆን አለበት (ያልተለጠጠ /ያልተወሳሰበ/በቂ ጊዜ(ዕዉቀት/ገንዘብ/ችሎታ …))ያለዉ መሆን ይኖርበታል፤
4)
R Relevant አግባብነት
ያለዉ/ዉጤት ያለዉ መሆን አለበት፤
5)
T Time bound በጊዜ ገደብ የታጠረ መሆን አለበት፤
ስኬትዎ ያለዉ ራስዎ ዉስጥ ነዉ፡፡ እርስዎ
ዉስጥ የሚገኝ ችሎታ፣ የተጠራቀመ ጉልበት ያልተነካ ጥንካሬ፣ ያልተጠቀሙበት ስኬት፣ የተደበቀ ክህሎት፣ ድል የማድረግ ብቃት አለ፡፡
ስለዚህ ይጠቀሙበት፡፡ አሜሪካዊዉ የሥነ-ልቡና ሊቅ ዊልያም ጂምስ መሆን ካለብን ጋር ሲነጻጸር አሁን ሆነን
የምገኝበት ሁኔታ በግማሽ እንደመንቃት ነዉ የሚቆጠረዉ ይለናልና እንንቃ፡፡ የተሻለ ዶሮ መሆን ይቻላል ነገር ግን እርስዎ
አሞራ/ንስር ነዎት፡፡ መመሳሰልዎና መጠነኛ ስኬት ማግኘትዎ የርስዎ አይደለምና እንደ ንስር በከፍታ ላይ በስልጣንና በሃይል ይብረሩ/ነገሮችን
በጥልቀት ይመርምሩ፡፡ከእርስዎ ዉስጥ ወደዱም ጠሉም ለሰዉ ዘር ሁሉ የሚበቃ ብርሃን አለ፤ ሃይል አለ፤ ስኬት አለ፡፡
ስለስኬት
ማወቅ ያለብዎት
የስኬታማ
ሰዎች ልምዶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች
የስኬታማ
ህይወት ትርጉም ከሰዉ ሰዉ ቢለያይም የሁላችንም ጥረት በተሰማራንበት የስራና የኑሮ መስክ ዉጤታማ በመሆን ደስተኛ ህይወት መኖር
ነዉ፡፡ የስኬት
ጉዞ የሚጀምረዉ ከምናስቀምጣቸዉ ግቦች እና ራዕይ ነዉ፡፡ ሁላችንም እንደየአቅማችን እንጥራለን፤ ነገር ግን ወደ ስኬት
የሚደርሱት ጥቂቶች ናቸዉ፡፡የሚገርመዉ ደግሞ በአብዛኛዉ ስኬታማ የሚባሉ ሰዎች ስኬታማ መሆን የቻሉት የተለየ ተሰጥኦ ወይም ከሌላዉ
ሰዉ የተለየ የተመቻቹ ሁኔታ ላይ ስለነበሩ አይደለም፡፡
ታድያ ስኬታማ ሰዎች ከሌሎች የሚለዩት በምንድን
ነዉ?
ዕድለኛ
ስለሆኑ ነዉ የሚሳካላቸዉ? አይደለም፤ይልቁንም ዕድልን ወደስኬት መቀየር ስለቻሉ እንጂ፡፡ (ሁላችንም ዕድሉ ተሰጥቶናል በዕድሉ የመጠቀም
ያለመጠቀም ጉዳይ እንጂ)
እነርሱን
ልዩ የሚያደርጋቸዉ የሚከተሉዋቸዉ ልምዶች እና የአኗኗር ዘዴዎችን አዉቀን ለራሳችን ህይወት በሚመቸን መልኩ በማዋዛት የተሻለ ስኬታማ
ህይወት መፍጠር እንችላለን፡፡
አስር ስኬታማ ለመሆን የሚጠቅሙ ዋና ዋና
ልምዶች እና የአኗኗር ዘይቤዎች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
1. ግብ መቅረፅ፡- የስኬታማ ሰዎች መለያ ባህሪ ነዉ፤ከየት ተነስተዉ የት እንደሚደርሱ ይወስናሉ፡፡በነፈሰበት
ከመንፈስ ይልቅ ዓላማን አንግበዉ ህይወታቸዉን ይመራሉ፡፡
2. ዕለታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፡-
ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም/እንዳይባክን ይረዳናል፤ጉዳያችንን
በቅደም ተከተል እንድናከናዉን ይረዳናል፡፡ከስህተታችንም ወዲያዉ እንድንማር ይረዳናል፤ …
3. ዓላማን አለመሳትና
አለመዘንጋት፡- መዘናጋት የብዙዎች መሰረታዊ ችግር ነዉ፤ ቀናችንን
በእቅድ መጀመር እንዳንዘናጋ ይረዳናል፡፡የበለጠ ደግሞ የሚያዘናጉንን ነገሮች መለየት እና ከእነርሱ መራቅ ትልቅ መፍትሔ ነዉ፡፡
4. ሳያቋርጡ መሞከር ፣ተስፋ
አለመቁረጥ፡- ቶማስ ኤድሰን አምፑልን
ለመፍጠር 1000 ጊዜ ሞክሯል፣
አብርሃም ሊንከን የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ከመሆኑ በፊት ብዙ ዉድቀት አጋጥሞታል፣
ኢትዮጵያዊዉ ቅዱስ ያሬድ ዛሬ
እንዲህ በዓለም ከመታወቁ በፊት 7 ጊዜ መዉደቅ አጋጥሞታል፤
የነዚህ ህይወት የሚያስተምረን ነገር ሳያቋርጡ መሞከር ለስኬት እንደሚያበቃ ነዉ፡፡ የስኬት ጉዞ በዉጣ ዉረድ
የተሞላ መንገድ ነዉ፤ ስኬታማ ሰዎች ሁሌም ዉድቀት በዙሪያቸዉ እንዳለ ያምናሉ፡፡ለስኬታማ ሰዎች መዉደቅ የስኬት
ዋዜማ ነዉ፤ ተስፋ እየሰነቁ ወደፊት ይጓዛሉና፡፡
5. እራስን ማወቅ ፡-
ስኬታማ ሰዎች እራሳቸዉን ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ፡፡ማን እንደሆኑ፣
ምን እንዳላቸዉና ምን እንደሚጎላቸዉ በደንብ ያዉቃሉ፡፡ግባቸዉን በጥንካሬያቸዉ እና በችሎታቸዉ ዙሪያ ይቀርፃሉ፡፡ስኬታማ ሰዎች የማይችሉትን
እችላለሁ አይሉም፤ ከሌሎች ለመማር ይጥራሉ እንጂ፡፡ በእያንዳንዱ ሰዉ ዉስጥ ሊኖር ከሚችለዉ ከተከማቸ ሳይንሳዊ ግኝቶች ነገር ግን
ካልተንጸባረቁት እና ካልተጻፉት አስደናቂ ድርሰቶች/ያልተሳሉ ዉብ ስዕሎች/ያልተቀመሩ ሙዚቃዎች/የማስተዳደር ብቃቶች/ … ከፊሉ እርሶ
ዉስጥ ነዉና በደንብ እራስዎትን ይወቁ፡፡
6. መወሰን መቻል፣ በፍጥነት
ማሰብ፡- በፍጥነት ማሰብንና የመወሰን ችሎታን በአንድነት አጣምሮ
በመጠቀም ለስኬት መብቃት አንዱ እና ዋነኛዉ ነዉ፤ ስኬታማ ለመሆን ዉሳኔ የመስጠት አቅም ላይ መድረስ ይኖርብናል፡፡ ፈጥኖ መወሰን
የማይችል ሰዉ ህይወቱ በፀፀት የተሞላ ነዉ፡፡
7. ለጋስ መሆን፣ ሰዉን
መርዳት፡- በመስጠት ድሃ የሆነ የለምና ስኬታማ ሰዎች ዋና
መገለጫቸዉ ለጋስነት ነዉ፤ የሌሎች ስኬት የእነርሱን ስኬት እንደሚደግፍ በደንብ ይገነዘባሉ፡፡
8. ኪሳራን አለመፍራት
(Risk Takers) ፡- ስኬታማ ሰዎች ኪሳራን አይፈሩም፤ ይልቁንም ስኬትን በማሰብ
ሌሎች የማይደፍሩትን ሃሳብ ይደፍራሉ፡፡ ኪሳራን የሚፈሩ ሰዎች ደግሞ በአንፃሩ ከቆሙበት ፈቀቅ ሳይሉ እዚያዉ ቆመዉ ዘመናት ያልፋሉ፡፡ኪሳራን
አለመፍራት ግን ግልብ የሆነ ዉሳኔ በመወሰን ኪሳራ ዉስጥ መግባትን አያካትትም፡፡
9. ዕዉቀትን መሻት ፡-
ዕዉቀትን ለመጨመር ዘወትር ማንበብ ሁል ጊዜ ሙሉ ሆኖ እንደመንቀሳቀስ ይቆጠራል፡፡
10. ጤናችንን መጠበቅ፡-
ስኬታማ ሰዎች ጤናቸዉን ለመጠበቅ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣
የሰዉነት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ በቂ እንቅልፍን እረፍት በማድረግ … ይታወቃሉ፡፡ስኬት እና ጤና ተነጣጥለዉ የሚታዩ ነገሮች አይደሉም፡፡
ግብን
ለማሳካት የሚረዱ 10 ወሳኝ ነጥቦች
1.
ግብ የመቅረፅ አስፈላጊነት፡- ግብን መቅረፅ ሂደቶችን ለመከታተል እና ስራ ለነገ የማለት አባዜያችንን ለማስወገድ ብሎም የተግባር ሰዉ ለመሆን ያግዘናል፡፡
2. የሚያነቃቃ፣ የሚያነሳሳ
ግብ መቅረፅ፡- መሃል ላይ አልያም መጨረሻ ላይ ድካም አልያም
አስቸጋሪ ፈተና ቢያጋጥመን የዉጤቱን አስፈላጊነት እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደ ፊት መገስገስ እንድንችል ያደርገናል፡፡
3. የተመጠነ (Specific)
ግብ መቅረፅ፡- የተመጠነ ስንል ዉጤቱ በትክክል የታወቀ እና
በማያሻማ መልኩ ሊገለጽ የሚችል ፣ ያልተንዛዛ እና ሊደረስበት የሚችል ማለት ነዉ፤ የተመጠነ ግብ በምን፣የት፣መቼ፣ለምን እና እንዴት
የተፈለገዉን ዉጤት ማሳካት እንደምንችል በግልጽ ይመራናል፡፡
4.
የሚለካና የሚደረስበት ግብ መቅረፅ፡- ይህንን ያህል ሊባል የሚችል እና በአቅማችን ሊደረስበት/ልናሳካዉ የምንችል ግብ ማስቀመጥ
ይኖርብናል፡፡
5.
የማሰላሰል (Imagination) ችሎታችንን መጠቀም፡- ግባችንን እንደተሳካ አድርጎ ማሰላሰል ከፍተኛ መነቃቃትና መነሳሳት ይፈጥራል፤ ከዚህም
ባሻገር ንቁ ላልሆነ የአዕምሮ ክፍል (subconscious mind) የምንፈልገዉን እየነገርን ነዉ፡፡
6.
የተግባር ሰዉ መሆን -ግቦች ያለተግባር ረብ የለሽ ይሆናሉና፡- አንዳንዶች እጅግ በጣም ጥሩ ግብ ይቀርጹና ተግባር ላይ ባዶ ይሆናሉ ይህ
ደግሞ የትም አያደርስም፤
7.
አሉታዊ ሀሳቦችን ማስወገድ፡- ግብ ከቀረጽን በኋላ መትጋት ያለብን ግቡ የሚሳካበት ጉዳይ ላይ እንጂ አፍራሽ ጉዳዮችን ልንመለከት አይገባም፤ እንደዚህ
አይነት አመለካከትም ካላቸዉ ዘንድ እንራቅ፡፡
8. ትኩረት ለሚጠቅሙና
ወሳኝ ጉዳዮች ፡- በዙሪያችን ትኩረትን የሚስቡ እጅግ ብዙ
ነገሮች ይኖራሉ ግባችንን ለማሳካት ማድረግ የሚኖርብን ትኩረታችን ጠቃሚ ነገሮች ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
9.
ጊዜና ገንዘባችንን አናባክን፡- ሁለቱም ግባችንን ለማሳካት ሃብት ስለሆኑ እንዚህን ሃባታት ከብክነት በመጠበቅ በአግባቡ
ልንጠቀምባቸዉ ይገባል፡፡
10. እንቅፋቶችን (ተግዳሮቶችን)
ወደ መልካም አጋጣሚ መቀየር፡- በስኬት ጎዳና ላይ ለመረመድ
ተግዳሮቶችን ማለፍ ግድ ይለናል ስለዚህ በሚገጥሙን ባለመሸነፍ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር ለስኬት ልንበቃ ይገባናል፡፡
ግቦችን ለማሳካት የሚረዱ ተግባራዊ ነጥቦች
አንዳንዶቻችን
የሆነ ግብ ይኖረንና እንዴት ወደ ተግባር መቀየር እንዳለብን ግራ ተጋብተን ግባችንን በአእምሯችን እያመላለስን ተቀምጠን ይሆናል፡፡
ሌሎቻችን ደግሞ ዓላማችን ከግብ እንዲደርስ የተሳሳቱ ሙከራዎች አድርገን ስኬት እርቆን እየኖርን ይሆናል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በመቀጠል
ግቦችን ለመተግበር የሚረዱ ጠቃሚ ነጥቦች፣ ምክሮች እንዳስሳለን፡፡
እነዚህ
ቀጥሎ የምንዘረዝራቸዉ 10 ነጥቦች ግብን ለማሳካት እንደሚረዱ በስነ-አዕምሮ ተመራማሪዎች፣ ራስን ማሻሻል ላይ በሚሰሩ ጠበብት የተመሰከረላቸዉ
ናቸዉ፡፡ነጥቦቹ በተግባር ተፈትነዉ ዉጤታማ የሆኑም ናቸዉ፡፡
ወደ ስኬት
የሚያደርሱ ዘጠኝ ደረጃዎች
1.
በህይወት ዉስጥ ዓላማን ጠንቅቆ ማወቅ፡- ወደምንሄድበት/ ወደምንደርስበት መዳረሻ ጉዞ ከመጀመራችን በፊት ጠንቅቀን ልናዉቀዉ የሚፈባ
ነገር አለ፤ እሱም ዓላማ ነዉ፡፡ " ወደየት እንደምትሄድ የማታዉቅ መርከብ ንፋሱም አያግዛትም " እንደሚባለዉ ሁሉ እኛም ዓላማችንን ጠንቅቀን ማወቅ ቁልፍ ነገር ነዉ፡፡
2.
የራስ የሆነ የህይወት ፍልስፍና/መመሪያን/መያዝ፡- ከፈረሱ ጋሪዉ እንዲሉ እንዳይሆንብን ስለስኬት ከማብሰልሰላችን በፊት ስለራሳችን የህይወት
ፍልስፍና ማወቅ ትልቅ ሚና አለዉ፤
3.
የቅርብ ፣የመካከለኛ እና የወደፊት/የሩቅ/ ጊዜ ዕቅድ ማዉጣት፡- የሰዉ ልጅ ሁሉን ነገር በአንድ ጊዜ ማከናወን አይችልም እንደደረሰበት እድገት ደረጃ
መጠን እና ክህሎቱ ይወሰናል፡፡ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ መጠን ቅደም ተከተል በመስጠት ሊከናወን በሚችል መልኩ ዕቅድ ማዉጣት
ይገባል፡፡
4.
ለእያንዳንዱ ዕቅድ /ድርጊት/ግልፅና ሊደረስበት የሚችል ግብ ማስፈር፡- በጥናት የተደገፉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የዓለማችን አስር በመቶዉ ያህሉ ግልፅ የሆነ
ግብ ሲኖራቸዉ ያንኑ ለመተግበር ደፋ ቀና ሲሉ ቀሪዉ የዓለማችን ዘጠና በመቶ አቅጣጫ
የሌለዉና ዝም ብሎ ወጥቶ የሚገባ ነዉ ማለት ነዉ፡፡ እንግዲህ ዓለማችን እየተመራች ያለችዉ በእነዚህ ጥቂት ሰዎች ዓለማ/ግብ
(ጥረት/ተስፋ) / አለበለዚያም ከመነሻዉ የላቀ መዳረሻ ነዉ ማለት ነዉ፡፡
5.
ዉጤቱን ለማሳካትም የጋለ ስሜትን ማዳበር፡- ከሁሉም በላይ ስኬታማ ለመሆን የማከናወን እና ስራን በስኬት ለማጠናቀቅ የጋለ ስሜት
አስፈላጊ ነዉ፡፡
6.
ግቦችን ለማሳካት የጊዜ መርሃግብር መንደፍ፡- ተፈጥሮ እንኳን ቀን እና ሌሊት ፣ክረምት እና በጋ፣ ጠዋት እና ከሰዓት … በሚል የተከፈለ
ነዉ ይህ የየራሱ መተግበሪያ አለዉ፤ እንዲሁ የሰዉ ልጅ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ግቦቹን ለማሳካት መርሃግብር መንደፍ ይጠበቅበታል፡፡ኣመትን
ለአስራሁለት ወራት መክፈል፣ በስድስት ወር ለሁለት በመክፈል፣ በሶስት ወር ለአራት በመክፈል መርሃግብር መንደፍ፡፡ ሳምንትን ቀናትን
ሰዓታትን በመከፋፈል መርሃግብር መንደፍ ይኖርብናል፡፡ መርሃግብር መንደፍ የራሱ የሆነ ጥቅም አለዉ (ለምሳሌ ከጭንቀት ራስን መጠበቅ)
7.
ለማከናወን በተነሱት ድርጊት የማይናወፅ እምነት እና በራስ መተማመን ማጎልበት፡- እዚህ ጋር ከአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት አብርሃም ሊንከን የህይት ተሞክሮ ብዙ ነገር እንማራለን፤
አብርሃም ሊንከን ለአገሩ ህይወቱን ለመስጠት የወሰነዉ በወጣትነቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ካጋጠመዉ መዉደቅ መነሳት አንፃር አገሩ አፍ
አዉጥታ የአንተን ግልጋሎት አልፈልግም ያለችዉ እስኪመስል ድረስ ተፈትኗል፡፡ለህግ አዉጪነት / አርቃቂነት ተወዳድሮ ነበር አላለፈም፣
ወደ ኮንገረንስ ዉስጥ ለመግባት ሞከረ አልተሳካለትም፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ዉስጥም ለመግባት ያደረገዉ ሙከራ አልተሳካም ፣ ሁለት
ጊዜ በአሜሪካ ሴኔት ዉስጥ ለመግባት ሞክሮ የተለየ ነገር አልገጠመዉም፣ ለፕሬዘዳንትነት ባደረገዉ እጩነት ፉክክር የመጀመሪያዉ አልተሳካለትም፤
በመጨረሻ ግን ትግሉንና ሙከራዉን ሳያቋርጥና ተስፋ ሳይቆር በራስ መተማመኑ እንዳለ ሙከራዉን ቀጠለ የአሜሪካ ህዝብም መሪያችን ሁን
ብሎ መረጠዉ፡፡ እርሱም ተወዳጅ መሪያቸዉ ለመሆን በቃ፡፡
8.
ምንጊዜም አዎንታዊ ዉጤትን መጠበቅ፡- ይህ ድርጊት ቀላል ነገር ባይሆንም ከዚህ የተሻለ አማራጭ የለንም፤አንዲት የበርክሌይ
ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ በትምህርት ዘርፍ ላይ ባደረገችዉ ጥናት ያገኘችዉ ዉጤት የሚያሳየዉ ከመቶ
ተማሪ ዉስጥ ሰማንያ ስድስት በመቶ ያህሉ አሉታዊ/አፍራሽ የሆኑ ነገሮችን ሲሰሙና ሲቀበሉ አስራስድስት በመቶ ያህሉ ብቻ አወንታዊ/ገንቢ
ነገሮችን ይቀበላሉ፡፡ እኛስ ከየትኛዉ ነን?
የትኛዉንም
ስኬታማ ነዉ የሚባል መንገድ እንከተል አመለካከት ካልቀየረ ስኬታማ ነዉ የተባለዉ መንገድ እኛ ላይ ዉጤት አያመጣም፡፡ሰዉ ከተስተካከለ
ዓለሙም ይስተካከላልና፡፡የተስተካከለ አመለካከት ስንይዝ የጠሩ ግቦችን እንነድፋለን፤ የጠራ ራዕይም ይኖረናል፡፡ የምናስባቸዉ ነገሮች
በተደጋጋሚ የማይፈፀሙልን ከሆነ ቀዉሱ ያለዉ በእኛ ስነ ልቡና ዉስጥ ነዉ፡፡ ስለዚህ ልናርመዉ የምንችለዉ እራሳችን እንጂ ዉጫዊ
ሃይል የለም፡፡
9.
ቀድሞ በአይነ ህሊና ዉጤቱን በመመልከት ደስታን መግለፅ፡- ነጭ ሆኖ የተፈጠረ ሰዉ ጥቁር ለመሆን አይችልም፤ ሆኖም ግን የወደፊት ህይወቱን መቀየር፣
ታላቅነትንና ደስታን ለማግኘት የሚያስችሉ ነገሮችን መቀዳጅት ይችላል፡፡ ስለዚህ ነገ መሆን የሚፈልገዉን/ ሊደርስበት ያቀደዉን ነገር
ከወዲሁ በአዎንታዊ በመመልከት እና የሚጠበቅበትን በማከናወን ወደዛዉ መጓዝ ይኖርበታል፡፡
የስኬታማ ሰዎች መለያ ባህሪያት
(ልማድ)
እንደ
ግለሰብ ስኬታማ የምንላቸዉ ሰዎች ሁሌም የተነቃቁ ፣ጀግኖች፣ቃላቸዉን የሚጠብቁ፣ሁሌ ዝግጁ የሆኑ፣ለመማር ፈቃደኞችና ዝግጅት ያላቸዉ፣ሃላፊነትን
መሸከም የሚችሉ እና ኃላፊነትን የሚወስዱ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን አንድ ሰዉ ብቻዉን ቢሮጥ ይቀደማል፣ ቢጠነክር ይዝላል፣ … ስለዚህ
ድር ቢያብር ነዉና ቢሂሉም ከአንድ ሁለት ስለሚሻል በቡድን ሆነን የምሰራቸዉ ተግባራት መለያ ሊኖራቸዉ ይገባል ይህም የስኬታማነት
ባህሪ/ልማድ ሊሆን ይገባል፡፡
በሶስት ከፍለን ማየት እንችላለን፤ነገር ግን
ሰባት ናቸዉ፡፡
1. ግለሰባዊ ድል
i.
ተነሳሽነት መዉሰድ (proactivity)
ii.
የመጨረሻዉን በአእምሮአችን
አስቀምጠን መጀመር
iii.
ቀዳሚ ነገሮችን ማስቀደም
2. ህዝባዊ /ማኅበረሰባዊ/የብዙሃን ድል
i.
ሁለቱም ወገን አሸናፊ ስለሚሆኑበት
ማሰብ
ii.
ቅድሚያ ሌሎች እንዲረዱዎት
ሳይሆን ሌሎችን ስለመርዳት ማሰብ (ራስን በሌሎች ቦታ አድርጎ የመመልከት ግንኙነት)
iii.
ቅንጅት መፍጠር (የፈጠራ ክህሎት
የታከለበት ትብብር)
3. ተሃድሶ
i.
መጋዙን መሳል (አካላዊ/መንፈሳዊ/አዕምሮአዊ
እና ማኅበረሰባዊ)
ተነሳሽነት
መዉሰድ (PROACTIVITY)
ዉጤታማ
ለሆነ ሰዉ የመጀመሪያ ሊባል የሚችለዉ ልማድ ለህይወታችን እና ለድርጊታችን ኃላፊነት መዉሰድ (proactivity) ነዉ፡፡
v Proactivity የቃሉ ትርጉምም ተነሳሽነትን ከመዉሰድ ትንሽ ጠለቅና ከበድ ያለ
ነዉ፡፡
እንደ
ሰዉነታችን ለሕይወታችን ኃላፊነት አለብን ማለት ነዉ፡፡ባህሪያችን የዉሳኔያችን እንጂ የሁኔታችን መገለጫ አይደለም፡፡ ነገሮችን እንዲከዉን
ለማድረግ ተነሳሽነቱም ኃላፊነቱም አሉን፡፡
ኃላፊነት
ስንል በእንግሊዝኛዉ Responsibility የሚለዉ ቃል ይተካዋል፡፡ ይህ
ቃል ሁለት ቦታ ሊሰነጠቅ የሚችል ነዉ፤ Response እና Ability ይህ ማለት አፀፋ እና ችሎታ እንደማለት ነዉ፡፡ በዚህም
መሰረት Responsibility የሚለዉ ቃል አፀፋ ለመመለስ ያለን
ችሎታ ተብሎ ይተረጎማል ማለት ነዉ፡፡
በእኛ
በስራችንም ሆነ በሕወታችን አፀፋ የመስጠት ችሎታችን ምን ይመስላል?
በከፍተኛ
ደረጃ Proactive ናቸዉ የምንላቸዉ ሰዎች ያንን ኃላፊነት ይገነዘቡታል፤
ለባህሪያቸዉ
ሁኔታዎችን ተጠያቂ አያደርጉም ራሳቸዉ ኃላፊነት ይወሰወዳሉ እንጂ፤ (ከዚህ በተቃራኒዉ ያሉት እና ከባቢያቸዉ በእነርሱ ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጥር ቀድሞዉኑ ስለፈቀዱ Responsibility
ከሚሰማቸዉ ይልቅ Reactive /አጸፋ-መላሽ/ ይሆናሉ፡፡)
እነዚህ
ሰዎች አየሩ ሸጋ ሲሆን ደስ የሚል ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ሲዳምን ወይንም ሲያካፋ አለበለዚያም ካፍያዉ ወደ ዶፍ ሲለወጥ ግን ባሕሪያቸዉም
አፈፃፀማቸዉም አብሮ ይጠቁራል፡፡
እኛስ
በቅርብ አለቆቻችን፣በሥራ ጫናዎች፣በምናስመዘግባቸዉ ዉጤቶች፣ … ላይ ጥገኞች በመሆን አንቀያየርም ወይንስ እንዴት ነን? ራሳችንን
የመፈተሸ ሥራ እንስራ፡፡
v ተነሳሽነትን (ኃላፊነትን) የመዉሰድ ባህል እያዳበርን ስንሄድ በመቀጠል ደግሞ የግምት
(Imagination) እና ነፃ ፈቃድ (Independent will) በመጠቀም በዚያ እዉቀታችን ላይ ስናክል … ማለትም እንደ ቃል
መግባት፣ ግልፅ የሆኑ ዓላማዎች ማስቀመጥ፣ ለእነዚህ እዉነታዎች ታማኝ መሆን … የባህሪ ጥንካሬ እንገነባለን፡፡
ቃል መግባት
|
መጠበቅ፣
|
ግብ ማስቀመጥ
|
ለማሳካት መስራት፣
|
ዉሥጣዊ
የሆነ የሃቀኝነት ስሜትን እናጠናክራለን፡፡
ከዚህ
በተጨማሪ ደግሞ ለራሳችን ሕይወት የበለጠ ኃላፊነት ለመሸከም የሚያስችል ጥንካሬ እናገኛለን፡፡ በመቀጠልም ትንሽ በትንሽ ቀስ በቀስ
የክብር ስሜታችን ከሙዳችን እየበለጠ ይመጣል፡፡በስተመጨረሻ መሰረታዊ የሆኑትን የዉጤታማነት ልማዶች ምሰሶ ባለቤት እንሆናለን፡፡እነርሱም
(ዕዉቀት፣ክህሎት እና መሻት) ናቸዉ፡፡
መልመጃ፡-
ተነሳሽነትን
(ኃላፊነትን) መዉሰድን በቀጣይ በ30 ቀናት ዉስጥ በተፅዕኖ ንፍቀ ክበብ (circle of influence) ላይ ብቻ በመወሰን
እንዳትሰሩት በአደራ ጭምር መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡
ትንንሽ
ቃሎችን (promise) ለራሳችሁ በመግባት ጠብቋቸዉ፡፡ ሞዴል (ምሳሌ/አርአያ) ለመሆን እንጂ ፍርድ ለመስጠት አይቸኩሉ፤ ትችትም
አያስፈልግም፡፡ የችግሩ ሳይሆን የመፍትሔዉ አካል ይሁኑ፡፡ ስህተት ሲሰሩ ስህተትዎን በማወቅ ያርሙት እና እርስዎም ይማሩበት የሌሎችን
ድክመት በሃዘኔታ ስሜት ይመልከቱ እንጂ ክስ በማቅረብ አይመልከቱ፡፡
እኛ
ለራሳችን ደስታ ሳይሆን ዉጤታማነት ነዉ ኃላፊነት ያለብን … ከዚያም ለበርካቶች የምንገኝባቸዉ ሁኔታዎች ናቸዉ፡፡ በ30 ቀናት ዉስጥ
ሊተገበሩ ከሚገባዉ ዉስጥ ለማስገባት በመጀመሪያ ከሥራም ሆነ ከግል ህይወትዎ የሚያበሳጭዎትን /ይህ ደካማ ነገሬ ነዉ/ አንድ ተሞክሮ
ይዉሰዱ፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊቆጣጠሩት የሚችሉት አለበለዚያም በፍፁም የማይቆጣጠሩት መሆኑን ጊዜ ወስደዉ ያስቡ፡፡በመቀጠልም
በተፅዕኖ ንፍቀ ክበብ (circle of influence) ሊወሰዱ ስለሚችሉት የመጀመሪያ እርምጃ ያስቡ፡፡
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ