የጊዜ አጠቃቀም
መግቢያ
ስኬታማ
የጊዜ አጠቃቀም ያዳበረ ሰራተኛም ሆነ ግለሰብ ጊዜዉን በመርሃግብር እና በዕቅድ ይመራል፤ ይህ ሰዉ ህይወቱን የሚመራዉ በዕድል ሳይሆን ራሱ ነዉ፡፡ ስለዚህ ይህንን ዶክመንት ማዘጋጀት ግድ ሆኗል፡፡
ጊዜ
፡-
በቀን
24 ሰዓት
በሳምንት
7 ቀን
በወር
30 ቀን
በዓመት
52 ሳምንት/
365 ቀናት/ ብለን የምንጠራዉ ማለት ነዉ፤
“ ጊዜ
ከሁሉ ነገር በላይ እጅግ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ በተበላሸ ሁኔታ የምንጠቀምበት ነገር ነዉ፤”
ዊሊያም
ፔን
ዓላማ ፡-
v የተቋማትን
፣አልያም የአገራችንን፣ ከዚያም አልፎ የየራሳችንን፣ ወዘተ … “የተለጠጠ” እቅድ ለማሳካት ዋነኛ ሃብት ጊዜ በመሆኑ ጊዜያችንን በመጠቀም ዉጤትን እንድናመጣ ግብን እንድናሳካ ግንዛቤ ለመፍጠር ነዉ፡፡
የጊዜ አስፈላጊነት (ጥቅም)
Ø ለመዉጣት ለመግባታችን የምንጠቀምበት
Ø በመዉጣት በመግባታችን ዉስጥ የምናከናዉናቸዉን ነገሮች የምንፈፅምበት መሣሪያ
” የአንድ
ዓመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀዉ“
“የአንድን ሰዓት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸዉ”
” የአንድን
ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ አዉቶቡስ ለትንሽ ያመለጠዉን ሰዉ ጠይቀዉ“
v ያለ በቂ ምክንያት፣ ከአቅማችን በታች በሆነ ጉዳይ ከሥራ ላይ የቀረንባቸዉ ቀናት ምን ያህል ግባችን ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠሩ እንመልከት፤
የጊዜ
ባህርያት
ü አንዴ ካለፈ በፍፁም ተመልሶ አይመጣም፣
ü ለሚጠቀምበትም ሆነ ለማይጠቀምበት እኩል ይሰጣል ነገር ግን እኩል ዋጋ የላቸዉም፣
ü በብዙ እድሎች የተሞላ ሃብት ነዉ፣
ü ነፃ ስጦታ እንደመሆኑ መጠን በትርፋማነት ለመጠቀም ግን በደንብ ማሰብንና ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል፣
ü ጊዜ ጨካኝ ነዉ ላልተጠቀሙበት ሰወች ምህረትንና ሁለተኛ ዕድልን አይሰጥም፡፡
ሰወች
ለምን ጊዜአቸዉን በአግባቡ አይጠቀሙም?
ü ግድየለሽ/ቸልተኝነት / ዳተኝነት አመለካከት
ü የሞራል ዉድቀት
ü በህይወታችን ግብ እና አላማ ስለሌለን
ü መዘናጋት/ ራስን መዋሸት/ ያለሰሩትን ሰራሁ፣ ያልጀመሩትን ጨረስኩ፣ጎበዝ ነኝ፣ ወዘተ ችግር ስላለብን
ü የሥራን ትርጉም አለማወቅ / የሰራነዉ በቂ ይመስለናል/
ü ማንነታችን /አስተዳደጋችን/ማህበረሰባችን/ የሥራን ዋጋ እየቀነሰዉ መምጣት/በአቋራጭ መበልፀግ/
ü ለማህበረሰባችን እና ለራሳችን የሚረባን ነገር በመትከል አሻራችንን ትተን ለማለፍ ዝግጅት ማጣት
ü ሥራን ለነገ ማሳደር እንደምንችል ማወቃችን (መጥፎ ባህል)
ü ሥራን በዋናነት የእኔ ነዉ ብሎ አምኖ አለመቀበል
ጊዜአችን
እንዴት እና በምን ያልፋል?
ጥናቶች
እንደሚሉት (ጥናቱ የሁሉንም አዋዋል እንደማይወክል ግምት ዉስጥ ይግባ)
ü 8.5 ሰዓታት በእንቅልፍ
ü 1 ሰዓት ራስን በመንከባከብ
ü 2.5 ሰዓታት እንደ ፅዳት ዓይነት የቤት ዉስጥ ሥራን በመስራት
ü 8.5 ሰዓታትን በሥራ ወይም በትምህርት ቤት
ü 3 ሰዓታትን ለወዳጆቻቸዉ እንክብካቤን በመስጠት
እኛስ?
የጊዜን
አያያዝ ጥበብ ለመገንዘብ ከመሞከራችን በፊት ምን እናድርግ?
ü ራሳችንን የመገንዘብ ጉዞ መጀመር አለብን
v ማን ነኝ
v የት ነዉ ያለሁት
v ምን ማድረግ ነዉ የምፈልገዉ
v ይህንን ለማከናወን የፈለኩት ነገር ለመፈፀም ምን ያህል ጊዜ አለኝ
v ሁኔታዉን ለማድረግ ምን ማድረግ አለብኝ
v ከየት ልጀምር
v ብዙም ሳይቆይ ጊዜዬን እንዴት ልጠቀም
ወደሚለዉ
ቁልፍ ጥያቄ መድረሳችን የማይቀር ነዉ፡፡
እነዚህ
ጥያቄዎች መጀመር ያለብንን ነገር እንድንለይ ልባችንን ያነቃቃል፤
ü ጊዜን ከየት ማምጣት እንዳለብን መገንዘብ
ጊዜ
ለማግኘት የትኛዉን ተግባሬን በማቆም ለአስፈላጊዉ ነገር ጊዜ ልፍጠርለት (ቁልፍ ነገር ነዉ) በሥራ ሰዓት ጡል እያልን የምንሄድባቸዉን መቀነስ
ጊዜአችንን
እንዴት እንጠቀም?
ü በአግባቡ (ያለ አግባብ መጠቀም ችግር ስላለዉ)/ከአግባብ በላይ/ከአግባብ በታች
ü ከአግባብ በላይ መጠቀም ጭንቀት ፣ ድካም፣ የጤና ችግር፣ … ያመጣል
ü ከአግባብ በታች መጠቀም ያስቀመጥነዉ ግብ እና ዓላማ እንዳናሳካ ያደርገናል
ü የጊዜን መጠን በማወቅ ”በጀት“ ማዉጣት ፣መቆጣጠር እና መጠቀም
ü ጊዜዬን በሚገባ እንዳልጠቀም ያደረገኝን የግሌን ችግር መለየት
ሰወች
ጊዜአቸዉን እንዴት ነዉ እየተጠቀሙ ያሉት?
1) እንደ አደጋ ጊዜ ተጠሪ (ምላሽ ብቻ መስጠት)
ü አደጋዎች እዚህ እና እዚያ ሲፈጠሩ ምላሽ የሚሰጡ ነገር ግን ቁጭ ብሎ ጊዜዉን በሚገባ ለመጠቀም የሚረዳዉን ዕቅድ ለማዉጣት ”ጊዜ“ የሌላቸዉ
2) ለማስደሰት የሚሰሩ
ü ”እምቢ“ ለማለት ያለመቻል ችግር የተበተባቸዉ ለጠየቃቸዉ ሁሉ ”እሺ“ በማለት ቃል የሚገቡ፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰዉ ተጠይቆ እምቢ ከሚል መደበቁን ይመርጣል፡፡
3) ጊዜ እንዳላቸዉ የሚያስቡ
ü ሁሉንም ነገር የሚደርስበት መስሎ የሚታየዉ
ü እዉቅና ሊያሰጠዉ ለሚችል ሥራ ብቻ ጊዜዉን የሚሰጥ
ü ሲመቸዉ ወይም ”ሙዱን” ሲያገኝ ብቻ የሚሰራ
ü የጀመረዉን ነገር ለሌሎች ለማስተላለፍም ሆነ ለማቋረጥ ትንሽ ” እንቅፋት“ የሚበቃዉ
ü ህይወቱ በመላምት የተሞላ /ሊሆን ይችላል፣ መሰለኝ፣ ሳይሆን አይቀርም፣ …/ የሚያበዛ እርግጠኛ ያልሆነ ሰዉ፤
4) ማህበረሰብ ተኮር
ü ከሰዉ ጋር ሰፊ እና ፈጣን ተግባቦት ያላቸዉ
ü የንግግር እና የመግባባት ችሎታ ያላቸዉ
ü ሁሉም ቦታ ላይ ያሉ
ü አንድ የሥራ ጊዜ በማህበራዊ ነክ ጉዳዮች ማሳለፍን እንደ ችግር የማያይ ዋና የሥራዉ አካል መስሎ የሚታየዉ
ü ይህንን ዓይነት ሰወች አንዳንድ አለቆች /አሰሪዎች/ ወይም የሥራ ባልደረቦች ከዚህ እዚያ ሲል መዋሉን እንደ ታታሪ ሰራተኛ ይቆጥሩለታል፡፡
5) የሰዎችን የሥራ ሰዓት የሚቆጣጠሩ
እኛስ?
ü ራሳችንን በየትኛዉ ቦታ ላይ አገኘነዉ
ü ካላገኘነዉ ራሳችንን በምን ዓይነት ሁኔታ አገኘነዉ
ü ጊዜ አጠቃቀማችንን ሙሉ እና ስኬታማ ነዉ ብለን እናስበዋለን
ጊዜን
በአግባቡ/በጥበብ/ መጠቀም ያለዉ ጥቅም
ü የስኬታማነታችንን ሁኔታ ይወስናል
ü ጊዜን በቁጥጥር ስር ስታደርገዉ ስኬትን የሚያስቀሩ/የሚያርቁ ሁኔታዎችን ታስወግዳለህ
ü በጊዜ ባላለቁ የተጠራቀሙ ሥራዎች የሚመጣ ዉጥረትና ጭንቀትን መቀነስ
ü የአዕምሮ ሰላምና የመከናወን ስሜት
ü የጉልበት መጨመር (የጉልበት እና የጊዜ ነፃነት ማግኘት)
ü ጥራት ያለዉ እና ጠንካራ የቤተሰብ ትስስር (የጊዜ አጠቃቀማችን ችግር ካለበት ተግባሮችህን በጊዜዉ ስለማትጨርሳቸዉ ከቤተሰብ ጋር ሊኖርህ የሚገባዉን ጊዜ የመንካት ባህሪ ይኖረዋል፡፡/ሥራ ቦታ ማምሸት፣ ሥራን ወደ ቤት ይዞ መሄድ፣ቅዳሜ እና ዕሁድ እረፍት ማጣት፣ በእንቅልፍ ሰዓት ፣ በጭንቅት መቃዠት፣ )
ü የተሻለ ጤንነት /ጊዜህን በአግባቡ ተጠቅመህ ተግባራትህን ካጠናቀቅህ በቀሪዉ ጊዜህን ጤንነትህን መንከባከብ የሚያስችል አቅም ይኖርሃል/
v ጥናቶች እንደሚያመለክተዉ በአግባቡ የዓመት ፈቃዳቸዉን ወስደዉ የሚያርፉበት ሰወች ከሌሎች ሰራተኞች 20 በመቶ የልብ በሽታን ይቀንሳል፡፡
ጊዜን
በጥበብ ያለመጠቀም ጉዳቶች
ü የባከነ ህይወት ( “ የባከነ ሃብት በሥራ ይተካል፣ የባከነ ዕዉቀት በጥናት ይተካል፣ የጠፋ ጤንነት በመድሃኒት ይመለሳል፣ የባከነ ጊዜ ግን ለዘለዓለም ጠፍቷልና መተኪያ የለዉም” ሳሙኤል ስማይልስ)
ü የድካም ህይወት
ü የማይረካ ህይወት
ü ተፈላጊነት የሌለዉ ህይወት
ü በግዳጅ ዉስጥ የሚኖር ህይወት
ü ዕቅድ የለሽ ህይወት
ü መዘዘኛ ህይወት
የጊዜ አጠቃቀም እንቅፋቶች
ሙያ ነክ እንቅፋቶች
|
ዉጫዊ እንቅፋቶች
|
ስነ ልቦናዊ እንቅፋቶች
|
ü የተግባር ዝርዝር አለማዉጣት
|
ü የድካም እና የህመም ስሜት
|
ü ግልፅ ያልሆነ ግብ እና የሥራ ቅደም ተከተል
|
ü ለሥራ ቀጠሮን እና የጊዜ ገደብን አለመመደብ
|
ü የኑሮ ሁኔታ መለወጥ
|
ü ፍርሃት
|
ü ለሥራዉ የማይስማማ ሰዓት መመደብ
|
ü ግርግር የሞላበት አከባቢ /ምቹ ያልሆነ የሥራ አካባቢ/
|
ü ”የድብርት”
ሥጋት
|
ü ለሥራዉ በቂ ጊዜ አለመመደብ
|
ü የሰዎች ተፅዕኖ
|
ü ለሰወች መኖር
|
ü
ለሥራዉ የማይመጥን ማንነት
|
ü
ፍፁማዊነት
|
|
ü
የአሰራር ሂደት ጉድለት
|
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ