ሐሙስ 26 ፌብሩዋሪ 2026

እንዴት ልጆችን በሁለንተናዊ መስክ እናሳድግ? ክፍል 2

 

ባለፈዉ በክፍል አንድ በይደር እንዳቆየነዉ ክፍል ሁለትን እነሆ ብለናል፤ ክፍል አንድን ያላነበባችሁ ወደዚህኛዉ ንባብ ከመሸጋገራችሁ በፊት ክፍል አንድን እንድታነቡት ይመከራል፡፡

ልጆችን እንዴት እናስተምር/ምንስ እናስተምራቸዉ?

1.     ልጆች እንደመሆናቸዉ እና በተለያየ እድሜ ክልል እንደመሆናቸዉ ቅርበት ይፈልጋሉና በቅርበት ሆነን ልናስተምራቸዉ ይገባናል፤ (የሙሴ እናት በግብፅ ምድር ለልጇ ሞግዚት ሆና ስታሳድገዉ ስለ ሕዝቧ እና ስለ አምላኳ ስታስተምሩ በቅርበት ሆና ነበር፤ እኛም በሥጋ ላልወለድናቸዉ ልጆች የመንፈሳዊ እዉቀት ወላጆች እንደመሆናችን ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ስለእስራኤል አምላክ ልንነግራቸዉ ይገባል፡፡ (የሙሴ እናት ይህንን ብቻ አይደለም ያደረገችዉ በግብጽ ጣኦት አምልኮ እንዳይወሰድ አድርጋም ታስተምረዉ ነበር፡፡ እኛም ስለ ተዋህዶ ትክክለኝነት ስለ ሌሎችም ስህተት ልናስተምራቸዉ ልዩነቶችንም በእድሜያቸዉ መጥነን ልናስተምራቸዉ ይገባል፡፡)

2.     መንፈሳዊ ተግባራትን በማለማመድ ልናስተምራቸዉ ይገባል፤ (ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብን፣ ገድላትን፣ ስንክሳርን፣ የቅዱሳንን ነገር፣ ወዘተ )

3.     ስብእናን በማሳደግ፤ ልብ፡- በጎ መዝገብን የሚያወጣ ራሱን የሚገዛ፣ የማይቆጣ እንዲሆን ማለማመድ አለብን፡፡

ü  ምኞት፡- በጎ የሆኑትን ከክፉ መለየት እንዲችል ማሳወቅ፡፡

ü  አመክንዮ፡- የዚህን ዓለም ብልጭልጭ ነገሮችን ሳይሆን አስቀድሞ ጽድቁንና መንግስቱን እንዲሻ ማድረግ (ዮቶር ሙሴን መክሮ እንዳሳደገ እኛም መጥነን እንዳይሰለቹ በማድረግ ልናስተምራቸዉ ይገባል)

4.     እዉቀትን በመስጠት፡- በአስኳላዉ የሚሰጠዉን፣ በዓለም ያለዉን የሚያዩትን የሚሰሙትን በማንሳት/በመጥቀስ ልናስተምራቸዉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

በትዳር ውስጥ መወያየት ለምን ከባድ ይሆናል?

  በትዳር ውስጥ መወያየት ለምን ከባድ እንደሚሆንባቸው ጥንዶች በርካታ የስነ - ልቦና እና የማህበራዊ ምክንያቶች አሉ። በተለይም አብሮ መኖር በጀመሩበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበረው “ የ...