“… በብዙ ድካምና ትግል ደርግን አሸንፈናል፣ አዲስ አበባን ተቆጣጥረናል፤ … አዲስ አበባን ስንቆጣጠር ደስ ያለንን ያህል እናንተም ደስ እናዳላችሁ ገልፃችሁልናል … ደርግን ጣልን እንጂ የደርግን ቢሮክራሲ (ዉጣ ዉረድ)መጣልና ማስወገድ አልቻልንም፡፡ … እናንተ ናችሁ ይህንን ማድረግ የምትችሉት ፤ … ያሰቀመጥንላችሁ የመንግስት ሹመኛ አይደለም፡፡ ከእናንተ መካከል የወጣ እናንተኑ ለማገልገል የተመረጠ አገልጋያችሁ ነዉ፤ … የሚሰራ ከሆነ ይቀጥላል፣ የማይሰራ ከሆነ አባሩት፣ እናባርረዋለን፣ …” ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ(የቀድሞ)
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEgO0fyiScvOHewdG8XhJi24JyQehFvRkGv6g264btswKDpC8xcFLJMNySxFp3E1cQtmduLARoAyhL1APW5z-2YFGYed6ChWxxNkw8UjwFgZaZoRzEIJE6O24cW4eGZ8rn5Qy61VV1y3iVQ/s320/P.M.meles.jpg)
እንደ አገር ኢትዮጵያንና ግዛቶቿን በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ገዥዎች (መሪዎች) ገዝተዋታል መርተዋታልም፡፡ ለዚህ ትዉልድ ለዚያዉም በወጣቱ ትዉልድ አዕምሮ ዉስጥ ሰርፀዉ የገቡና አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሪ የቀድሞዉ የኤፌርሪ ፕሬዘዳንትና ጠቅላይ ሚኒስተር በመሆን ለ21 ዓመታት አገሪቱን የዕድሜያቸዉን 3/4ኛ ሊያሰብል በሚችል መልኩ ድርጅታቸዉ ህወኣት(ኢህአዴግን) የመሩ ታላቅ ሰዉ ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ናቸዉ፡፡
ኢትዮጵያን ባለፉት ብዙ አስርት ዓመታት ከድህነት ወለል በታች በመዉረድ እና በዉስጥና በዉጭ ጠላቶች በጦርነት ስትታመስ፣በርሃብ፣ በእርዛት እና በጦርነት የምትታወቅ ሆና ነበር፤ ህዝቦቿም ከሚላስና ከሚቀመስ እጦት ባሻገር የሰላም እጦት ተተኪ ትዉልዷን ርሐብና ጦርነት ቀጥፏቸዋል፡፡
“ጠብ ሲል ስደፍን” እናደለችዉ ሴትዮዋ አንዱን ሰትል አንዱ ብቅ ሲልባት ከንጉሱ ጀምሮ እንዃን ሶስት ሥርአቶችን አስተናግዳለች፡፡እናት አገራችን ኢትዮጵያ እነዚህን አሰቃቂ ዘመናት እንድታሰተናግድ ግድ ያላት አብይ ምክንያት በኢኮኖሚ ያለማደጓ (የድህነቷ) ምክንያት ነዉ፡፡ለዚህ ነዉ በጋራ እና በተናጠል አቅሟን ያሳነሳት፡፡
የሆነዉ ሆኖ ባለፋት ሁለት አሥርት ዓመታት የኢህአዴግ ምንግሥት ሥልጣኑን ከወታደራዊ የደርግ መንግስት በድል አድራጊነት ከተቆጣጠረ ወዲህ ይህንን ያህል ለህዝቡ በኪሱ ጠብ ያለለት ነገር ባይኖርም ቅሉ የአገሪቱ ዕድገት (ኢኮኖሚ) በመንግሥት ሪፖርት መሰረት ከዘጠኝ በማያንሱ ዓመታት በሁለት ድጅት እያደገ መጥቷል፡፡ በተጨባጭብም በመጠኑም ቢሆን የሥራ አጥነት ቀንሷል፣የመኖሪያ ቤት ችግር መፍትሔ እያገኘ ነዉ፣የጤና ተቋማት ተገንብተዋል፣ የእናቶች ሞት ቀንሷል፣ የወጣቶች እንደ እሳት እራት ወደጦር ሜዳ መማገድ አቁሟል፣ የዩኒቨርስቲዎች ቁጥር ከእጥፍ በላይ ጨምሯል፣ አስፋልት በሽ በሽ ነዉ፣የዉስጥ ለዉስጥ መንገድም ዋና ዋና ከተሞች ላይ ያልደረሰበት ቢኖር በእቅድ የተያዘ ካልሆነ ያላተሰራ የለም፣የመደራጀት መብት ተሰጥቷል፣ … በአጭሩ ፍጥነቱ አዝጋሚ ቢሆንም የዲሞክራሲ ጭላንጭል ጨለማዉን እየገፈፈ ይገኛል፡፡ “ሊነጋ ሲል ይጨልማል” እንደሚባለዉ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ “ሊነጋ” ነዉ መሰል ብዙ ችግሮች እንደጥላ አጥልቶበታል፡፡ለምሳሌ፡-
.መልካም አስተዳደር እጦት እንደ ነቀርሳ ሥር ሰዷል፣
.በሃብት እኩል(ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ) አለማደግ፣(ምንም እንዃን አደጉ በሚባሉትም አገሮች የሐብት ክፍፍሉ እኩል ባይሆንም ቅሉ የአገራችን ግን ክፍተቱ የትጠለሌ ሆኗል/ በጠግቦ አዳሪና በተርቦ አዳሪዉ መካከል/)
.ሙስና፣ (የግለሰብንም ሆነ የድርጅቶችን ሥራ ለማከናወን መማለጃ መቀበል ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሷል)
.የመብት አለመተግበር ፣(በህገ መንግሥቱ ተደንግገዉ ለሰፊዉ ህዝብ ጥቅም ሲባል በትጥቅ ትግሉ ብቻ ሳይሆን በደምና በነፍስ መስዋዕትነት የተገኙት መብቶች በህግ ከለላ፣ በህግ ክፍተት፣ እንዲሁም በማን አለብኝነት እየተጣሱ ይገኛሉ፤ )
.ጥራትን መሰረት ያደረጉ ሥራዎች አለመሰራት፣ ( የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ዋና ዋና መንገዶች፣ የትምህርት ፖሊሲዎች፣ የሥልጣን ክፍፈሎች፣ ዕቅድና ክንዉኖች፣ የልማት ተቋማት፣ …)
.ሥራን ወቅቱን ጠብቆ አለማጠናቀቅ፣( ፕሮጀክቶች እና በጀት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙ ግራ እስኪያጋባ ድረስ በጣም መዘግየትና ጊዜን ማባከን፤)
.የአገሪቱንና የማህበረሰብን ዕጣ ፈንታ በጥቂት ሰዎች እጅ መጣል፣( በአንድ ሰዉ ራዕይ ብቻ አገርን መምራት ወይም ትዉልድን ማኮላሽት፣ ተስፋ ቢስ መሆን፣ ተተኪ አለማፍርት፣ …)
.የአገርን ሀብት ለግል ጥቅም ማዋል፣(በአንድም ሆነ በሌላ ለህብረተሰቡ መዋል ያለበትን ጥሬ ሃብት ተሰርቶም ሆነ በዕርዳታ መልክ የተገኘዉን ለግል ጥቅም ማዋል፣ ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ ሃብቶችን በራስና በቤተሰብ ስም ማዘዋወር እና መጠቀም፣/ከቀበሌ ቤት አንስቶ እስከ ጥሬ ገንዘብ/)
.ህግን ለራስ ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል መደንገግም ሆነ መሻር፣ (የሽብርተኛ ህግ በአብይነት የሚጠቀስ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማስነጠስ እንዃን እንደማሸበር የሚተረጎምበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤)
.ትዉልድን ማምከን፣(ከህጉ መላላትና ተጠያቂነት ማጣት/አለመኖር/ የተነሳ ይልቁንም የወጣቶች መዋያ ማዕከላት ባለመኖር ምክንያት ትዉልዱ መዋያዉን መጠጥ ቤት፣ሽሻና ጫት ቤት፣… መዋል ዋና ሥራዉ አድርጓል፤ በዚህም ምክንያት ትዉልዱ በኣላስፈላጊ ሱስ በመገደዱ አመንዝራ፣አስገድዶ ደፋሪና ቀምቶ አዳሪ ሆኗል፡፡ የራሱን እጣ ፈንታ መወሰን ተስኖታል፤ )
.የማስፈፀም ብቃት ማነስ ወይም ቸልተኝነት፣(መንገዶችን፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን፣ቢ.ፒ.ር.፣ ትራንስፎርሜሽኑን፣ … ለአገርና ለህብረትሰብ ጥቅም ሲባል ይጀመራሉ የመንግስት አስፈፀሚ አካላት አቅም ማነስ የተነሳ በታቀደለት ጊዜና ወጪ አይጠናቀቅም፤)
.ሐብትን በአግባብ አለመጠቀም፣(ከላይ በዘረዘርናቸዉ እና በሌሎች ምክንያት ሃብት የትም ሲባክንና የማንም መጠቀሚያ ሲሆን እናየዋለን፤)
.መከፋፈል፣(በድርጅት ዉስጥ ርስበርስ አለመስማማት፣ በዘር፣ በሃይማኖት፣በቋንቋ፣ … መከፋፈል የአገሪቱ ራስ ምታት እንዲሆን አድርጓል፤)
.ጣልቃ ገብነት፣(የሃይማኖት ነፃነት በመግፈፍ ጣልቃ በመግባት ማተራመስ /እዝህ ጋር ያየን እንደሆነ መንግሥት ለማረጋጋትና በተለያየ ሰበብ ሲገባ ሌሎች ደግሞ ድርጅቱ(ኢህአዴግን) ሽፋን በማድርግ ሃያማኖቶችን የሚያናክሱ እና የሚያራክሱ አወቅሽ አወቀሽ ሲሏት እንደ ሚባለዉ በተለያዩ ህዝባዊ ሚድያዎች የሚዘልፉ ጥቂቶች አልታጡም)እንደ አገር ኢትዮጵያንና ግዛቶቿን በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ገዥዎች (መሪዎች) ገዝተዋታል መርተዋታልም፡፡ ለዚህ ትዉልድ ለዚያዉም በወጣቱ ትዉልድ አዕምሮ ዉስጥ ሰርፀዉ የገቡና አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ መሪ የቀድሞዉ የኤፌርሪ ፕሬዘዳንትና ጠቅላይ ሚኒስተር በመሆን ለ21 ዓመታት አገሪቱን የዕድሜያቸዉን 3/4ኛ ሊያሰብል በሚችል መልኩ ድርጅታቸዉ ህወኣት(ኢህአዴግን) የመሩ ታላቅ ሰዉ ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ናቸዉ፡፡
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEj3EP-mhyphenhyphen58nyZWNUD2owMHnV_Kc2TbvHDVhyphenhyphennFHHxZBKf_HiY3gjiLXRJoXrSplvk3wDhcyAHTp2LVPMLug01m85Is5BXud9K5IKteHECEohoT2sPz3foidPJXOigajgRhqpssPoOReXg/s320/p.m.jpg)
እነዚህ ነገሮችን ዘረዘርን ማለት ልማት የለም ማለታችን እንዳልሆነ አንባቢ ልብ ሊለዉ ይገባል ያስተዛዝባልና፤ ለማ ብለንም ዝም አንልም ኢህአዴግ መንግሥት እንደ መሆኑ መጠን ብዙ እንጠብቅበታለንና አንድም የክቡር የአቶ መለስ ዜናዊን ሌጋሲ የምናቀጥልበት ሰዓት ላይ ነልናም፡፡ አንድም ወቅቱ የምርጫ ወቅት እንደ መሆኑ መጠን የመረጥንህ የገባኸዉን ቃል እንድትፈፅማቸዉ ነዉ ብለን እናሳስባለን፣ሥህተቶቹንም እንጠቁማለን፡፡
አንዳንድ ማህበራዊ ድህረ ገፆች ጥላቻቸዉን እንደሚገልጡበትም አየረነት መንገድ በመጠቀም ብዕራችንን አናጎድፍም፣ “በሬ ወለደ” አይነት ዉሸትና “ወልድ ፍጡር ነዉ” አይነት ክህደት አንክድም፤ ልማት፣ዲሞክራሲ፣ዕድገት፣ …ወዘተ አለ በማለትም ዝም አንልም፡፡ አንዳንዶችም ለማደር ሲሉ ጥቂቱን ሥራ በማግዘፍ ዘወትር እንደሚያወሩትም የልማት መንግሥት ነኝ ብሎ ለልማት የተነሳዉን በወሬ መንገድ አንዘጋበትም፡፡መንግሥትም ይስራ የሚሰራ ዘወትር እንደተሳሳተ ነዉ እኛም እያየን እንጠቁማለን ተያይዘን በታቀደዉ ጊዜ አገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ አገሮች ተርታ እናሰልፋታለን፡፡
ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ እንዳሉት መንግሥት የተመሰረተዉ ለህዝብ ጥቅም እንደመሆኑ መጠን ማረም ያለበት ነገር ሲኖር እንዲህ በአደባባይ እንነግረዋለን፣ በጓዳ እያማነዉ በአደባባይ እያመሰገንን ለዉድቀት አናበቃዉም፤ እምቢኝ አሻፈረኝ ሥልጣኑ የራሴ ነዉ ህዝብ ምን አገባዉ ብሎ ካለና አልሰማ ብሎ ጆሮዉን ሲነፍገን በምርጫ ካርዳችን ሥልጣንን እንቀማዋለን በአመፅ ሳይሆን፡፡ከዚህ ሲዘል በምስራቅ አፍሪካ እንዳየነዉ ከዚያ ይሰዉረንና የሚያምፅ እንዳለ የሚዘነጋዉ አይመስለኝም ብሶት የወለደዉ ጀግና አምፆ ጫካ የገባና ሰላምና ዲሞክራሲን ያመጣ ነዉና፡፡
በስተመጨረሻም ላሰምርበት የምፈልገዉ ዓብይ ነገር “… ያሰቀመጥንላችሁ የመንግስት ሹመና አይደለም፡፡ ከእናነተዉ መሃል የወጣ እናንተኑ ለማገልገል የተመረጠ ነዉ፤ … የሚሰራ ከሆነ ይቀጥላል ፣ የማይሰራ ከሆነ አባሩት፣ እኛም እናባርረዋለን፣ ….” በ1984 ዓ.ም. አቶ መለስ ዜናዊ የተናገሩት ነበር፤ እኝህን ታላቅ ሰዉ ካጣናቸዉ ድፍን ሰባት ወራት አለፈዉ መጋቢት 28 ቀን 2005 ዓ.ም. በይፋ በስማቸዉ ፋዉንዴሽን ተመስርቷል ትልቅ ሰዉ፣ መሪ፣አባት፣ታጋይ፣ … ናቸዉና እኝህ ታላቅ ሰዉ እንዳሉት ደርግን ከጣሉት ማግስት የደርግን ቢሮክራሲ መጣል ቀላል አልሆነላቸዉም እነሆ ዛሬም ድረስ ተረፈ ደርግ የሆኑ በኢህአዴግ ጉያ በኢህአዴግ ልክ የተሰሩ ደርጋዊያን አሉ ስርአቱን የሚያበላሹ ህዝቡን የሚያስለቅሱ መብላት እንጂ መስራት የማይሆንላቸዉ በክፍ ባህሪያቸዉ ከመጣዉ ጋር በማደር እንደ ተባይ ከደሃዉ ትከሻ ላይ የማወርዱ ብዙዎች ናቸዉ፤ ለደርግ ዉድቀት የኢህአዴግ የራስ ምታቶች አላማ የለሾች፣…. እናዳሉት ተሿሚዎች ለህዝብና ለህዝብ ብቻ እንዲሰሩ እግዚአብሔር ይርዳልን፤ ካልሆነ ግን እንደፈለገን ስንፍልጋቸዉ የምንሾምበትን ሳንፈልጋቸዉ የምናወርድበትን ሞገስና ዲሞክራሲ እግዚአብሔር ያድለን፡፡ እንዲህ እያደረግን እርሳቸዉ የተናገሩትን፣ ያቀዱትን፣ የጀመሩትን ሌጋሲ ለአገራችንና ለህብረተሰባችን ስንል እናስቀጥላለን፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ