‹ንግድ› የሚለውን ቃል ስንመለከት ሐሳባችን ወደብዙ አቅጣጫ ሳይበታተን አልቀረንም ወደ ብዙ ቦታም ሳንደርስ አልተቀመጥንም ከአነስተኛ ሱቅ እስከ ታላላቅ መደብሮች ወይም ጉምሩክ ድረስ ከጉልትም አንስተን እስከ ወደብ ላይ የሚለዋወጡት የንግድ ሥራዎች ሳንቃኝ አልቀረንም አልያም ደግሞ በብሉይ ኪዳን የነበረውን የከሊዳውያን ዑር፣ የግብፅ ጢሮስና ሲዶና እስራኤልን እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ዘመን ለእስራኤል ሃገር በሮሚና በኢጣልያ የሚደረገው ታላላቅ የንግድ ሥራ በአይነ ሕሊናችን ሳንቃኝ አልቀረንም፡፡ በአጭር ቃል ከነዚህ ሁሉ እንደምንገነዘበውና እኛም እንደምናከናውነው አንድን ነገር በአንድ ነገር መለወጥ ወይም አንድ ነገር በብር መሸጥ ማለት ንግድ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ንግድ የሚለው ቃል በብዙ አይነት መንገድ ስያሜውን ሊያገኝ ይችላል፡፡
ለምሳሌ አንድ ሰው የአንድን ድርጅት ዕቃ እንቅስቃሴ … በማስተዋወቅ ጥበቡ ቢያስተዋውቅና ለገበያ ቢያቀርብለት ያ ሰው ንግድ ነገደ ማለት ነው፡፡ እንዲሁም አንድ የንግድ ፈቃድ ያለው ሰው ንግድ ፈቃዱን ለሌላ ሰው በማከራየት ሥራውን እንዲሰራበት ቢያደርግ ያ ሰው ንግድ ነግዷል ማለት ነው፡፡ በሌላ መልኩም በዚህን ሰሞን ተንሰራፍቶ እንደምናየው ፎቶግራፎቻቸውን ለማስታወቂያነት የሚሸጡ ሴቶች እህቶቻችን እና ወንዶች ወንድሞቻችን እንደሚያደርጉት ይህ በተዘዋዋሪ ንግድ የሚለውን ስያሜ ሊሰጠን ይችላል ስለንግዱ በዚህ አናብቃና ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ ‹‹ስመ አምላክ ነጋድያን ይታቀቡ›› እንድል ያሰኘኝ ዋናው ጉዳይ ዛሬም እንደ ጥንቱ እስራኤላውያንን እግዚአብሔር በቤተመቅደስ ውስጥ ሲሸጡና ሲለውጡ አይቶ ‹‹ቤቴ የፀሎት ቤት እንጂ የሌቦች ዋሻ አይደለም›› ብሎ እንደገሰፃቸው ለተግሣፅ ነው፡፡
በቤተክርስቲያን ዙሪያ ስንቃኝ ኢማንያን ያልሆኑ ግን ስመ አምላክ ነጋድያንን በተለያየ መልኩ እናገኛቸዋለን፡፡ ‹‹መስሎ ከመታየት ደርሶ ከመመለስ አምላክ አበዊነ ያድነን›› ይላሉ የዋልድባ አባቶች እኛንም ይሰውረንና በአለባበሳችን በአነጋገራችን በአካሄዳችን ብቻ መስሎ ከመታየት እንደ በጎች መሐል ተኩላ ከመመስል እግዚአብሔር ያድነን፡፡ እንደገናም ከክብር ከማዕረግ ከፀጋ እግዚአብሔር ደርሶ ከመዋረድ አምላክ ያድነን፡፡
• ተምሮ አምኖ ንሰሐ ገብቶ ለሥጋ ወደሙ አለመብቃት
• አርብ ረቡዕ ሲፆሙ ከርሞ ፍልሰታ ድረስ ደርሶ አስቀድሶ ፁሞ አዲስ አመት ሲመጣ ወደ ቀደመ ግብር መመለስ /አለመፅናት/
• ኩዳዴን ሲፆሙ ከርሞ ከበዓለ ሃምሣ በኋላ መዘናጋት . . . ወዘተ ደርሶ መመለስ ነውና ከዚህ ይሰውረን የነዚህ ገጠመኞች ውጤት ስመ አምላክ ነጋድያን ያደርገናልና፡፡
ስመ አምላክ ነጋድያንን በሰንበት ት/ቤት በእናቶች በአባቶች በወንድሞች በእህቶች በሕብረተሰቡ ዘንድ ስንመለከት ዓለም በአጠቃላይ ስመ አምላክ ነጋድያን ነን ማለት ነው፡፡
ሰንበት ት/ቤትን ስንመለከት ከአባላት አንስቶ እስከ አመራር አካላቱ ድረስ ከተወሰኑት በስተቀር ነጠላውን አጣፍቶ አለባበሱን አካሄዱን አነጋገሩን አሳምሮ ፍሬ አልባ ነው በመዘመር ከበሮ በመምታት በመስበክ በኮሚቴነት በመስራት ብቻ የሚኖር ለንሰሐ ለሥጋ ወደሙ ያልበቃ ኑሮው ሕይወቱ ከማስተማሩ ይልቅ የሚያሰናክል ከሚያስመሰግን ይልቅ የሚያስነቅፍ ስመ አምላክ ነጋድያን ይበዙበታል፡፡
እናቶችንም በቤተክርስቲያን ዙሪያ ስንመለከታቸው በአንደበታቸው ስመ አምላክን ሲጠሩ ፈጣሪንና ቅዱሣንን ሲመሰግኑ ደስ ብለው ነጠላቸውን አጣፍተው ቤተክርስቲያን ሲሄዱ ማኅበር ሰንበቴ ሲጠጡ ደስ አሰኝተው ነገር ግን ከእናቶችም ጠዋት ቤተክርስቲያን ማታ ቤተ ጣኦት የሚሄዱና እግዚአብሔርን የሚያሳዝኑ ስመ አምላክ ነጋድያን እናቶች አልታጡም፡፡
አባቶችንም ስንቃኛቸው ከብዙሐኑ ጥቂቶቹ እንዲያውም ከጥቂቶቹ በስተቀር አብዛኛውን ስንመለከት ባህታዊ ሳይሆኑ ባህታዊ ነን፣ መነኩሴ ሳይሆኑ መነኩሴ ነን … የሚሉ እዚሁ የተሰራ ነገር ግን ማዳን የሚቻለውን መስቀል በመዋሸት ከግሸን ነው የመጣው ከኢየሩሳሌም ነው የመጣው ግዙ፤ አፈሩን ፀበሉን /አንዳንዴም ውሃ ቀድተው/ በሆነ ነገር በማሸግ ከኢየሩሳሌም የመጣ ፀበል እምነት ለበረከት ግዙ ወዘተ… በማለት የሚነግዱ ሐሰተኞች ሞልተዋል አንዳንዶችም እውነተኞች አባቶች ሆነው ፀጋ እግዚአብሔርን አገራንንት ማውጣት ድውያንን መፈወስን … በገንዘብ ካልሆነ በቀር ንክች የማያደርጉ ‹ስምኦኖች› አልታጡም እንደገናም ወደ ወላጆቻችን ስንመለስ አገር በማቅናት ቤተክርስቲያን በማሰራት የተጣለ በማስታረቅ የሚታወቁ ሆነው ዕለተ ሰንበትን እና ለንግስ በዓላት ለስብሰባ ወይም ለእድር ሰዓት ካልሆነ ቤተክርስቲያን የማይደርሱ ስመ አምላክ ነጋድያን አባቶችም ሞልተውናል፤
እኛም እነዚህን መሳይ አባቶችና እናቶች ይዘን መጥፎውን ከጥሩው ሳንለይ እምነታችን ባህላችንን ከአባቶች ነው የወረስነው በማለት ‹‹የመጥረቢያ ልጅ መዘለፊያ›› እንዲሉ በእምነታችን ስመ አምላክ ነጋድያን ሆነን ቀርተናል፡፡
ወንድሞችንም ስንመለከት ልበ አምላክ ዳዊት እንዳለው ‹‹ወንድሞች በሕብረት ቢቀመጡ መልካም ነው›› እንደተባለ ሕብረታችን መልካም ሆኖ ሳለ ምግባራችን መክፋቱ እምነታችንና ሥራችን አብሮ አለመሄዱ ከአብዛኞች መካከል የጥቂቶቻችን በሕብረት መቀመጥ ለዱለታ መሆኑ ስመ አምላክ ነጋድያን ሳያሰኘን አልቀረም እህቶችም ብንሆን ከአለባበሳችን ጀምሮ ስንመለከት ውጪያችን ክርስቲያን አስመስሎን አኗኗራችን የሚያስነቅፈን ክርስትናችንን ሰንበት ተማሪነታችንን ዘማሪነታችንን መሸፈኛ ተገን በማድረግ ውሎአችን ግን የሚያስነቅፈን ከስመ አምላክ ነጋድያን እንደመደባለን ማለት ነው፡፡
ወደሰፊው ሕብረተሰብ ስንመለስ ደግሞ ከእያንዳንዱ ግለሰብ እስከ መንግስታዊ የሆኑና መንግስታዊ ልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የመንግስት አካል ድረስ ስመ አምላክ ነጋድያን የሚያሰኛቸውና ሊታቀቡ የሚገባቸው ብዙ ነገሮች አሉ ጥቂቱን እንደምሳሌ አድርጌ አነሳለሁ፡፡
- በየበአላቱ በየአዲስ ዘመናቱ ከሽያጮች አንስተን እስከ መዝናኛ ፕሮግራሞች ስንመለከት ማስታወቂያዎችን ስንመለከት በአምላክ ስም የምንነግድ ያሰኙናል፡፡ ለእድገት መሳሳቱ መሯሯጡ በጣም ደስ የሚያሰኝ ሆኖ ሳለ ነገር ግን 0.05 ሣንቲም ሳይቀነስ ‹‹የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ›› ‹‹የመስቀልን የልደትን የጥምቀትን በዓል ምክንያት በማድረግ ታላቅ የገበያ ቅናሽ›› እግዚአብሔር የማይፈቅደውን ኃጢያት የሆነውን ነገር በእግዚአብሔር ሥም በመነገድ ‹‹አዲሱን አመት የገናን /ልደት/ በዓል ምክንያት በማድረግ የሙዚቃና የዳንስ ምሽት …›› በማለት ማስተዋወቅ ስመ አምላክ ነጋድያን ያሰኘናል አስተዋዋቂውን አስተናጋጁን አዘጋጁን ብቻ ሳይሆን በትንሳኤ በልደት በጥምቀት በመስቀል … የት መዋል እንዳለብን እያወቅን ሌላ ቦታ የምንውለውን እያንዳንዳችን ከነቀፋው አናመልጥም በሌላ መልኩም የእጅ እና የግድግዳ ሰዓት የጆሮ ጉትቻው ከኒተራው የቁልፍ መያዣ በተለያዩ እቃዎች ላይ የእግዚአብሔርንና የቅዱሣንን ምስል መነገጃ ማድረጉ ስመ አምላክ ነጋድያን የሚያሰኘን ሥራ ነውና በሕግ እንታቀብ ከላይ እንደጠቀስነው ይህ አሳዛኝና አስከፊ ሥራ መስለው የሚታዩትና ደርሰው የተመለሱ የቤተክርስቲን የነበሩ ልጆች የሥራ ውጤት ነውና እግዚአብሔር መስሎ ከመታየት ደርሶ ከመመለስ ይጠብቀን አሜን፡፡ ይቆየን፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ