ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ተስፋዬ ማን /ምንድን/ ነው? ከወደየትስ ነው?
እንደምን አደርክ እንደምን ዋልክ እንዳልልህ ባህሪህን መመራመር አይቻለኝም ስለጤንነቴም እንዳልነግርህ ሁሉን የምታውቅ ቸር አምላክ ነህ እንዳላምንህ ሁሉን ነገር ሳይጠይቁህ በልግስና አውቀህ የምትሰጥ ነህ ስላደረክልኝ ዋጋ እንዳልከፍልህ እንደምድራዊ ነገስታትና መኳንንት እጅ መንሻን የምትሻ አይደለህምና ብቻ የባህርይ ገንዘብህ የሆነውን ምስጋና ብቻ ላቅርብልህ ዘወትር ከኔ ሳትርቅና ሳትለየኝ የረድኤት እጅህ ሳይታጠፍብኝ የምህረት አይንህ ከእኔ ሳይነቀል እንዲሁ የምትናፍቀኝ ከውኃ ጥማት ከእንጀራ ረሃብ ሁሉ የምትብስብኝ መለኪያ መጠን የሌለው ፍቅርህ የሚስበኝ አምላኬ ሆይ አስቀድመህ ሰማይና ምድርን ፣ በምድርም ላይ የሚመላለሱ በእግር የሚሽከረከሩ በልባቸው የሚሳቡ በክንፋቸው የሚበሩ በሰማይና በምድር ለኔ ፈጠርክ፣ እፅዋትንም ሳይቀር ከአዝርዕት ጋር እመገባቸው እገለገልባቸው ዘንድ ለእኔ አዘጋጀህ /አደረግህ/ ከዚያን ባሻገርም ከሁሉ በላይ ራስህን በማዕከለ ምድር በቀራንዮ አደባባይ አይሁድ ምራቃቸውን እየተፉብህ እንደብርሃን የሚያበራ ፊትክን በጥፊ ተፀፋህ ቸርና ለጋስ እጆችህን የወንጀለኞች መቅጫ በነበረው አሁን ግን ትምክህታችን በሆነው መስቀል ቀኝና ግራ እጆችህን ቸነከሩህ ደረትክን በጦር ተወጋህ ደምህን አፍስሰህ ሥጋህን ቆርሰህ ለኔ ተሰዋህ፤
ለእውራን ብርሃን ለአንካሶች መሄጃቸው ጤና ላጡ ጤናቸው ሰላም ላጡ ሰላማቸው የሆንክ ደግ አምላክ ሆይ ለእንደኔ አይነቱ ደካማ ፍጡር ብርታት የሆንክ አምላኬ ሆይ ባህሪህን ካላስቆጣሁና ካላስከፋሁህ አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ እባክህ አምላኬ ሆይ ተስፋዬ ምንድን ነው? ማንስ ነው? ከወደየትስ ነው? ብዬ ጥያቄ ሳቀርብልህ ዘወትር የማይለኝን አፅናኝ መልስህን ከምድር በማንጋጠጥ የምጠይቅህ የዘወትር ጠያቂህ /ለማኝህ/ ምዕመን ነኝ፡፡
ተፃፈ ለልዑል አምላክ
በአንድም በሌላም እንናገራለን:ጆሮ ያለዉ ይስማ:ልብ ያለዉ ልብ ይበል፡፡ የታዘብነዉን የምንናገርበት፣ የምናዉቀዉን ለትምህርት እና ለእርምት የምናዉልበት ከወገንተኝነት ነፃ የሆነ መድረክ ነዉ፤ …ሁሌም ቢሆን አስተያየቶችን እና መልዕክቶችን ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡
ማክሰኞ 2 ኤፕሪል 2013
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!
መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡
-
ያለው ዕለት ለንጋቱ ቦታውን ለመልቀቅ መሰናዶውን ያጠናቀቀ ይመስላል በቤቴ መስኮት ቀዳዳ የሚገባው የንጋት ብርሃን “ ነግቷል ተነስ” የ ሚል ሰው ያህል ከፊት ለፊት በቀዳዳው እየገባ ...
-
እናቴ አትሙቺ ልሙትልሽ እኔ ከጎኔኮ ሳጣሽ ይባክናል ዐይኔ ዛሬ ዛሬ የነ ሻኪራ፡ የነ ቢዮንሴ፡ ቱፓክ፡ሮናልዶ፡ ሜሲ፡ … እና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች ፎቶ ገበያዉንና ቤታችንን ከማጨናነቁ በፊት፡ ከከተማዉም አል...
-
የስኬት ሚስጢር ምንድን ነው ? የስኬት ሚስጥር ለአንዱ የሚሰራው ለሌላው ሊለይ ቢችልም፣ በአብዛኛው ስኬታማ ሰዎች ህይወት ውስጥ የሚታዩ ዋና ዋና ምሰሶዎች አሉ። ስኬት በአንድ ጀምበ...
ስለአንተ ሁል ጊዜ ተገድለናል
ከሁለት አስርት አመታት በፊት ከፍቶኝ እንዲህ በማለት ስንኝ ቋጥሬ ነበር ለመግቢያ ያህል እንጠቀመዉ፡፡ ምንድን ነዉ ዝምታዉ ጠይቁት ይናገር፤ ዝም ያለዉ ለምንነዉ ከፍቶት ነወይ ምድር፡፡ በኢትዮጵያ አማኞች እና ...
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ