ዛሬ መጋቢት 5 ቀን 2005 ዓ.ም.ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የቆየ በዉይይትና በተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች በአክሱም ሆቴል የዳንኤል ክብረት እይታዎች 3ኛ አመት ተከብሮ ዉሎአል፡፡ በበአሉም ላይ 5 የተለያዩ ሰዎች በሰሩት በጎ ስራዎች በዳንኤል እይታ አንባቢዎች ባገኙት ጥቆማ መሰረት ድምፅ ያገኙ ሲሆን ይህም ሁኔታ በየዓመቱ ቀጣይነት የሚኖረዉ ሲሆን ዋና ዓላማዉም የዛሬዎቹን በጎ አድራጊዎች ካላበረታታን እና እዉቅና ካልሰጠናቸዉ ነገ በጎ መስራት ታሪክ ሆኖ ይቀራል የሚል ስጋት ስላላቸዉ እንደሆነ የዝግጅቱ ባለቤት ዲ.ዳንኤል ክብረት አፅንኦት በመስጠት ተናግረዋል፡፡(እነዚህን ሰዎች ወደ ፊት ከሰፊ ትንታኔ ጋር ይዤ የምቀርብ መሆኔን አለበለዝያም በዳንኤል እይታዎች ላይ ሊቀርብ እንደሚችል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡)
ዳንኤል ማን ነዉ? ሥራዎቹስ? ለዚህ ትዉልድ ምን ፋይዳ ይኖረዋል? ከርሱ ምን እንማራለን? … ወዘተ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደፊት እንዳስሰዉ ይሁናል፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ