ባለፈዉ በክፍል አንድ በይደር እንዳቆየነዉ ክፍል ሁለትን እነሆ ብለናል፤ ክፍል አንድን ያላነበባችሁ ወደዚህኛዉ ንባብ ከመሸጋገራችሁ በፊት ክፍል አንድን እንድታነቡት ይመከራል፡፡
ልጆችን እንዴት እናስተምር/ምንስ እናስተምራቸዉ?
1. ልጆች እንደመሆናቸዉ እና በተለያየ እድሜ ክልል እንደመሆናቸዉ ቅርበት ይፈልጋሉና በቅርበት ሆነን ልናስተምራቸዉ ይገባናል፤ (የሙሴ እናት በግብፅ ምድር ለልጇ ሞግዚት ሆና ስታሳድገዉ ስለ ሕዝቧ እና ስለ አምላኳ ስታስተምሩ በቅርበት ሆና ነበር፤ እኛም በሥጋ ላልወለድናቸዉ ልጆች የመንፈሳዊ እዉቀት ወላጆች እንደመሆናችን ስለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ስለእስራኤል አምላክ ልንነግራቸዉ ይገባል፡፡ (የሙሴ እናት ይህንን ብቻ አይደለም ያደረገችዉ በግብጽ ጣኦት አምልኮ እንዳይወሰድ አድርጋም ታስተምረዉ ነበር፡፡ እኛም ስለ ተዋህዶ ትክክለኝነት ስለ ሌሎችም ስህተት ልናስተምራቸዉ ልዩነቶችንም በእድሜያቸዉ መጥነን ልናስተምራቸዉ ይገባል፡፡)
2. መንፈሳዊ ተግባራትን በማለማመድ ልናስተምራቸዉ ይገባል፤ (ጸሎትን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብን፣ ገድላትን፣ ስንክሳርን፣ የቅዱሳንን ነገር፣ ወዘተ )
3. ስብእናን በማሳደግ፤ ልብ፡- በጎ መዝገብን የሚያወጣ ራሱን የሚገዛ፣ የማይቆጣ እንዲሆን ማለማመድ አለብን፡፡
ü ምኞት፡- በጎ የሆኑትን ከክፉ መለየት እንዲችል ማሳወቅ፡፡
ü አመክንዮ፡- የዚህን ዓለም ብልጭልጭ ነገሮችን ሳይሆን አስቀድሞ ጽድቁንና መንግስቱን እንዲሻ ማድረግ (ዮቶር ሙሴን መክሮ እንዳሳደገ እኛም መጥነን እንዳይሰለቹ በማድረግ ልናስተምራቸዉ ይገባል)
4. እዉቀትን በመስጠት፡- በአስኳላዉ የሚሰጠዉን፣ በዓለም ያለዉን የሚያዩትን የሚሰሙትን በማንሳት/በመጥቀስ ልናስተምራቸዉ ከክፉዉ እንዲሸሹ ከበጎዉ እንዲጣበቁ አድርገን ልናሳድጋቸዉ ይገባል፡፡ (የመረጃ ቴክኖሎጂዉን (በቴሌቭዥን እና ኢንተርኔት የሚተላለፉ መልዕክቶች) ልጆች እንዴት መጠቀም/መከልከል እንዳለባቸዉ በመንገር) /ልጆች 13 ዓመት እስኪሞላቸዉ ድረስ ማኅበራዊ ድረገጾችን መጠቀም እንደሌለባቸዉ ጥናቶች ያስረዳሉ/
ü ከትምህርት እንደሚያዘናጋቸዉ፣
ü ከእንቅልፍና ከማኅበራዊ መስተጋብር ያራርቃቸዋል፣
ü ቁምነገር እንዳይሰሩ ያዘናጋቸዋል፣ ….
የቴክኖሎጂ ዉጤቶች የምንላቸዉ፡-
o የቪዲዮ ጌም መጫወት
o ፊልም ማየት፣
o ዘፈን ማዳመጥ፣
o የቴሌቭዥን መርሐግብሮች፣
o ወዘተ …
የኢንተርኔት እና ቴሌቭዥን ዉጤቶች ለልጆች ያለዉ ጉዳት
ü ባህልና እና ሃይማኖት ያላገናዘቡ መሆናቸዉ
ü ለሳይበር አባላጊዎች የተጋለጡ መሆን
ü በማየመች አካሄድ ከተጠለፉ በኋላ መንታፊዎች እነዚያን መረጃዎች እንደማስፈራሪያነት በመጠቀም ለአስገዳጅ ነገር መጋበዝ (ከዚህ የተነሳ ልጆች ራሳቸዉን እስከማጥፋት፣ ለጭንቀት እስከመዳረግ፣ ለአደንዛዥ ዕፅ መጋለጥ)
ü በሳይበር ዝሙት እስከ መፈጸም መድረስ (ሱሰኛ መሆን)
ü ያለ አቅማቸዉ የተለያዩ ነገሮችን መግዛት
ü አላስፈላጊ ፋይሎችን ቫይረሶችን ወደ መጠቀሚያቸዉ (ስልክ፣ ታብሌት፣ ኮምፒዩተር) ሊያወርዱ ይችላሉ፡፡
በጥናት የተረጋገጡ አብዛኛዉን ጊዜ በኢንተርኔት እና ቴሌቭዥን መርሐግብራትን የሚከታተሉ ልጆች ያጋጥሟቸዋል የተባሉ ነገሮች፡-
ይቀጥላል …
በክፍል 3 እንገናኝ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ