ይመሻል ይነጋል አንድ ቀንም ሆነ
ብሎ ከሰየመው የቀንን አቆጣጠር
የዘመን መቁጠሪያ ስሌት ሲመነዘር
ፈጣሪ ፍጡሩን ዕድሜ ሊለካለት
ከቀኑ እንዳያልፍ ልጓም
ሲያበጅለት
የኔ እና ያንቺን ፍቅር፣
የኔ እና ያንቺን ትዳር፣
የኔ እና ያንቺን ሰላም፣
የኔ እና ያንቺን ጸጋ፣
ከለካው ፈጣሪ፣
ስንት ዘመን ሆነ?
ስንት ዘመን አለፈ?
እየኖርን ላለመኖር
እየሞትን ላለመሞት
የተሟገትንበት፣ የተታገልንበት
ከዘመን ልንቀድም የተሯሯጥንበት
ከዘመን የበላይ ለመሆን የተላፋንበት
ኧረ ለመሆኑ መኖር ከተጀመረ፣
ዘመን ከተቆጠረ፣
ጊዜው ከባከነ፣
ሥንት ሰዓት ሆነ?
ደረሰ ረታ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ