ሰኞ 29 ኤፕሪል 2013

ቃለ መጠይቅ


የሰዉ ልጅ መሰረታዊ የተባሉትን አስፈላጊ ነገሮችም ሆነ የቅንጦት ነገሮች ለማሟላት ገንዘብ አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን ሥራን መስራት ግድ ይላል፤
ሥራ ስንል የቀን ስራ ፣ የመንግስት ስራ፣ የግል ድርጅት ስራ፣ የዓለም አቀፍ መስሪያ ቤቶች ስራ፣ ተደራጅቶ የሚሰራ ስራ፣በግል የሚሰራ ስራ፣ … ወዘተ ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡
እነዚህን ስራ ለመስራት መቀጠር ቀዳሚ ተግባር እንደሆነ የታመነ ነዉ፤ ለመቀጠር ደግሞ ሊያሟሉ የሚገባዎት መሰረታዊ ነገሮች እንዳለ ሆነዉ ዘመድ ወይም ቃለመጠይቅ ከነርሱ ዉስጥ የሚጠቀስ ነዉ፡፡ ለዛሬዉ ቃለመጠይቁን እንመለከታለን፡፡
(ለቃለመጠይቅ ፈተና እድሉን ያገኙ ተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝራቸዉ ተለጥፈዋል ሁሉም ለጀማሪ ሰራተኝነት ሳይሆን ለዉስጥ ዕድገት የሚወዳደሩ ይመስላሉ አለባበሳቸዉን ለተመለከተ ሴተም አጭር ቀሚስ ረጅም መጫሚያ ወንዱም ሙሉ ልብሱን ከነከረቫቱ ለብሷል )
(ለቃለመጠይቁ በፈታኝነት የተመደቡት ቦታ ቦታቸዉን ይዘዉ ፈተናዉን ጀምረዋል ተፈታኞችም አንድ በአንድ እየገቡ ደቂቃዎችን እያሳለፉ ሲወጡ ሲገረፉ የቆዩ ፣አቧራቸዉ ቡን ብሎ፣ላብ በላብ ሆነዉ፣ጠቋቁረዉ ይወጣሉ፤ አንዱ ተረኛ ገባ … )
ተጠያቂ፡- ገብቶ ከፈታኞች ፊት ለፊት ቆመ
ጠያቂ 1 ፡- እንካን ደህና መጣህ
ተጠያቂ፡- እንካን ደህና ቆያችሁኝ
ጠያቂ 2 ፡- ቁጭ በል
ተጠያቂ፡-አመሰግናለሁ( በማለት ወነበሩ ላይ ተቀመጠ)
ጠያቂ 1፡-ለምን መጣህ
ተጠያቂ፡- ድርጅታችሁ ባወጣዉ ማስታወቅያ መሰረት (የማስታወቅያ ቁጥሩን፣ የወጣበት ክፍል፣የሰዉ ብዛት፣ … ወዘተ ጠቅሶ) የፅሁፍ ፈተና በማለፌ ዛሬ ደግሞ ለቃለ መጠይቅ ተጋብዤ ነዉ የመጣሁት፤
ጠያቂ 1፡-(እንዳኮረፈ ሰዉ በመሆን) እስኪ ካሪኩለም ቪቴህን( CV ) አብራራልን
ተጠያቂ፡-እድሉን ስለሰጣችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ፤ ሥሜ፡-(ሙሉ ስሙን ተናገረ)፣የትዉልድ ዘመን፡-(የተወለደበትን ዘመን ተናገረ)፣ትምህርት መቼ እንደጀመረ፣ የት እንደተማረ፣ የትምህርት ደረጃዉን በደንብ አስረዳ … …
ጠያቂ 2 ፡- በቃህ (ድምፃቸዉ የቁጣ ነበር )
ጠያቂ 3 ፡-የምትቀጠርበትን የስራ ክፍል ሥራ ተናገር
ተጠያቂ ፡- ገና አዲስ ምሩቅ እንደመሆኔ መጠን ምንም ዓይነት የስራ ልምድ ሥለሌለኝ በአሁኑ ሰዓት ሥለማላዉቀዉ ክፍል መናገር ይከብደኛል፤
ጠያቂ 1፡-ታድያ ምን ልትሰራልን ነዉ?(የቁጣ ፊታቸዉ ምንም አልተቀየረም )
ተጠያቂ ፡- ማስታወቂያ የወጣዉ በዜሮ የስራ ልምድ ስለሆነ (ብሎ እየተናገረ እያለ )
ጠያቂ 4፡-ስለርሱ አትነግረንም አሁን ይልቅስ ስለፕላኒንግ (Planning) የምታዉቀዉን ንገረን፤
ተጠያቂ ፡-የማኔጅመንት የማዕረግ ተመራቂ እንደመሆኑ መጠን በግልፅ እንግሊዝኛ አብጠርጥሮ ተናገረ፤
ጠያቂ 1፡- የት አገር ነዉ plan (ዕቅድ) እንዲህ አይነት ትርጉም ወይም ትንታኔ የኖረዉ?
ተጠያቂ ፡- (እየሆነ ያለዉ ነገር ከቁጥጥር ዉጭ ሆነበትና እርሱም ቆጣ በማለት) Planning & Plan has a big difference በማለት የሁለቱን ልዩነት ወደ ማስረዳት ገባ (አሁንም ጠያቂ 2 አቋረጡት)
ጠያቂ 3፡-እስኪ ስለ ሪፖርት ንገረን?
ተጠያቂ ፡- ያለማቋረጥ ለአምስት ደቂቃ ይክል ከተናገረ በኋላ በአጭሩ ይህን ይመስላል (ሁሉም ጠያቂዎች በጣም ተደመሙ ይህንን ሰዉ እንዴት ይጣሉት የሚፈለገዉ የሰዉ ብዛት አንድ ነዉ ማስታወቂያዉ ሲወጣ ሊቀጠር የታሰበ ሠዉ ግን ተዘጋጅቶበታል በጣም ተጨነቁ )
ጠያቂ 4፡-ጥያቄያችንን አጠናቀናል በመጨረሻ ከአንድ ደቂቃ ባለሰ የምትለን ነገር ካለ ተናገር፤
ተጠያቂ ፡- የምለዉ ነገር የለኝም ሁለት ጥያቄ ግን አለኝ፡ 1ኛ. የኛ ባልሆነ ቋንቋ ይህንን ያህል ሰዓት ፈጅተን በራሳችን የመግባብያ ቋንቋ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ምን ማለት ይቻላል?
2ኛ. የአገራችን የሥራ ቋንቋ አማርኛ (የአፍ መፍቻችን ነዉ) ወይንስ እንግሊዝኛ ነዉ? ጨርሻለሁ!

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...