ከላይ ባለ ገጽታቸው እጽዋት መስለው እጽዋት ናቸው ብለው ነፍሳት ሲጠጓቸው/ሲቀርቧቸው በውስጣዊ ማንነታቸው ሥጋ በል እጽዋት ናቸው።
ሰወችም ዘመድ እጽዋት ናቸው ሥንል ሥጋ ዘመድ፣ ልጅ፣ እህት፣ ሚስት፣ አዛውንት፣ መነኮሳት፣ የሚበሉ የሚደፍሩ ሥጋ በል እጽዋት አመንዝራና ቅንዝራም ናቸው።
በአለም ላይ በወረርሽኝ የተከሰተው COVID19 ባስከተለው በቤት መቀመጥ #stayhome ብዙዎች የውሻ ባህሪ ያላቸው ወንዶች ወንድም፣ አባት፣ አጎት፣ ዘመድ መስለው የዋሃን ሴቶችን ያለ እድሜ ገደብ በመድፈር ከክብር አነውረዋቸዋል።
ሰው ስንላቸው እንስሳ እየሆኑ ጨቅላ ሴቶችን የበሉ እንስሳ ወንዶች ተበራክተዋል፤ በየሚዲያው ከሰማናቸው ከመቶ በላይ ሴቶች በዚህ ጥቃት የስነልቦና ስብራት፣ የሞራል ውድቀት፣ የሥጋ ጉዳት ቤት ይቁጠራቸው።
ይህ ክስተት እየተነሳን ማውገዝ የከፋ ነገር ባይሆንም ችግሩ በዚህ ብቻ አይፈታም።ልጆቻችንን ወንድሞቻችንን በቤት ስናሳድግ ሴቶችን አክባሪ፣ ወንጀልን የሚከላከል፣ ዝሙትን የሚጸየፍ አድርገን ልንቀርጻቸው ይገባል።
ሴቶቻችንም እያንዳንዷ ድርጊታችሁን ዝሙትን ቀስቃሽ ከሆነ ተግባራት ልትጠበቁ፣ ልጆቻችሁን እና እህቶቻችሁን ከዚህ ተግባር ልትገድቡ ይገባል።
መንግሥትም አገርንና ትውልድን አንገት የሚያስደፋ ተግባራትን በሚያከነረውኑት ላይ ከሌሎች አገራት ህግ ተሞክሮ በመውሰድ ጠንካራ ህግ በማውጣት የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የሴቶችን የመኖር መብት ከሥጋ በል እጽዋት ወንዶች ሥጋት ነጻ ሊያደርግ ይገባል።
ደፋሪዎችን አወግዛለሁ፤ ከተጎዱ ሴቶች ጉን እቆማለሁ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ