እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች አሉት
ተፈጥሮ በኡደት (Process) የተመላች ናት፡፡ ዘመናትን በጊዜ ቀመር አስልታ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላኛው ታሻግራለች፡፡ የኡደት ስሌትዋ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትናንሽ ወደ ትላልቅ የሚያመራ ነው፡፡
የሰው ልጅ የዕድገት ለውጥ ዓላማ በተፈጥሮ የወረሰውን እምቅ ኃይል ከከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው፡፡ ኤልሳቤጥ ሃርሎክ የተባለች የሳይኮሎጂ ምሁር እንደገለጸችው ሰዎች በአእምሮ ፤ በአካል ከሌሎች የተሻሉ ሆነው ለመገኘት የሚያደርጉት ጥረት ወደ ዕድገት ለውጥ ግብ ለመድረስ የሚደርጉት ጥረት ስለሆነ እነዚህን ጥረቶቻቸውን እውን ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ሰዎች እራሳቸውን ለማሻሻል እምቅ አቅምና ችሎታ ካላቸው ከወዴት ነው የሚጀሚሩት የሚለው ነው፡፡ ብዙዎቻችን በስራችንና በህይወታችን የምንፈልገውንና የምንሻውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻልነው ዕቅዶቻችንንና ስኬቶቻችንን ከታች ከትንንሽ ነገሮች ስለማንጀምራቸው ነው፡፡ ቀድሞ የሚታየን ትልቁ ስዕል እንጂ ወደ ትልቁ የስኬት ጎዳና ለመድረስ ከትንሽ ነገር መጀመር እንዳለብን አንገነዘብም፡፡ ከዚህ በታች ከትንንሽ ነገር ተነስተን ወደ ትልቁ ስኬት ለመጓዝ የሚረዱንን ነጥቦች እንመለከታለን፡፡
1.ትምህርት
የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያለቻው ሰዎች ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑት ዕውቀትንና ዕቅድን መሰረት አድርገው ነው፡፡ በስራዎቻቸው ላይ ወሳኝ ጉዳዮችን በደንብ ስለሚያውቁ ከሌላው ሰው በተሻለ ሃሳብና መረጃ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ ዕውቀቶቻቸውን በመመንዘርና ማኅበራሰባቸውን በማገልገል የተሻለና የተሳካ ህይወት (ገቢንም ጨምሮ) መኖር ይችላሉ፡፡ ዕውቀት በጨመረ ቁጥር የሰው አስተሳሰብ አድማሱ ስለሚሰፋ ምን ሰርቶ ምን ማግኘትና የት እንደሚደርስ አቅጣጫን ይጠቁማል፡፡ ትምህርት ስንል በአንድ የትምህርት መስክ የምናገኛውን የሰርተፍኬት ብዛት ብቻ ሳይሆን በህይወት ልምድና ተሞክሮ ያገኘነውን ዕውቀት ትርጉም ባለው ስራ ላይ ማዋልና በትንሽ በትንሹ በመደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ ትምህርት ታግዘን ህይወትን ለማሸነፍ የምንሄድበትን የህይወት ጉዞን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡
2. ክህሎት
በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን ክህሎት የምናስመዘግበውን ውጤት ብዛትና ጥራት ይወስናል፡፡ የምንሰራውን ስራ በደንብ ካወቅነው በስራችን ቅልጥፍና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ በብቃት መሸጋገር እንችላለን፡፡ ከማናውቀው ነገር አንድ ብለን ከመጀመር የምናውቀውን ነገር አሻሽሎ በመስራትና ክህሎትን በማዳበር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
3. ግንኑነትን ማስፋት
በምንሰራው ስራ ላይ ብዙ ሰዎችን ለማወቅ ከጣርን ግንኙነታችንን በማጠናከር አማራጮችን ማስፋት እንችላለን፡፡ ስለዚህ የግንኙነት አድማስን ለማስፋት ዘውትር ማኅበራዊ ገመዶቻችንን በረጅሙ መዘርጋት አለብን፡፡
4. ጥሩ የስራ ልምድ
ጥሩ የስራ ልምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስራዎችን እንድንሰራ ይረዳናል፡፡ ይህን ለማድረግ ስራዎቻችንን በዕቅድ መስራት አለብን፡፡ ጥሩ የስራ ልምድ አንድን ነገር ከማከናወናችን በፊት አስቀድመን እንድናስብበት ስለሚያስችለን ከስራው በኋላ የሚከሰቱትን ማንኛውንም አወንታዊና አሉታዊ ውጤቶችን አስቀድሞ መገመት ስለሚያስችል ኪሳራን ለመቀነስ ይረዳል፡፡
6. አወንታዊ አመለካከት
የምንሰራው ስራ እኛነታችንን ስለሚገልጸው በስራችን ላይ አወንታዊ አመለካከት ፤ በእራስ መተማመን ፡ ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር ጥሩ መስተጋብር ካለን ሁሌም መልካም ነገር እንድናስብ ስለሚረዳን ወደ ምንፈልግበት ደረጃ እንድንደርስ አወንታዊ አመለካከት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
7. ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ይኑረን
ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ወይም ምልከታ መያዝ የምንፈልገውንና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡ ሰዎች በውጫዊ ገጽታችን ሊገምቱንና ሊፈርጁን ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውጫዊ ምልከታ የእኛንም ሆነ የሌላውን ስለማይገልጽ ስለእራሳችንም ሆነ ስለሌሎች ሰዎች ጥሩና የተቃና አመለካከት ሊኖረን ይገባል፡፡
8. ፈጠራ
ፈጠራ አንድን ነገር ዘውትር በተሻለ ፍጥነት፤ ቅልጥፍና ፤ በቀላል አኳሃን እንድንተገብረው ይረዳናል፡፡ ፈጠራ አዲስ ነገር ፈጥሮ ወይም ሰርቶ ማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገሮችን ከዚህ ቀደም ከምናያቸው ዕይታና ግንዛቤ በአዲስ መልኩና በሌላ አቅጣጫ ማየትንም የሚያካትት ነው፡፡
9. ማንነት
እራስን መግራትና ግልጽነት ብዙ የስኬት በሮችን እንድንከፍት ይረዳናል፡፡ መተማመን የግንኙነት ሁሉ መሰረት ነው፡፡ ሰዎች የሚያውቁን በድርጊታችንና በቃላችን የምንታመን ከሆነ ነገሮችን በፍጥነት በቀላልና በታማኝነት በእኛ በኩል እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡ ይህም ብርታትና በራስ መተማመንን ስለሚፈጥርልን ወደምንፈልገው ደረጃ ለመድረስ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡
ዕቅድህ 15ኪሎ ክብደት መቀነስ ከሆነ በቀላሉ እንቅስቃሴ ማድረግና አመጋገብህን በማስተካከል ከትንሹ መጀመር ትችላለህ፡፡ ከዚያ ወደ ምትፈልገው ደረጃ ስትደርስ እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች እንዳሉት ትገነዘባለህ፡፡ ሻሎም
አንቶኒዮ ሙላቱ

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ