ማክሰኞ 22 ኤፕሪል 2014

እኔ ወድሻለሁ!


እንዲያ እየጠላሽኝ
እንዲህ እየወደድኩሽ
እንዲህ እየባተትኩ
አንቺን ካልመሰለሽ
እንዲያ እያልኩ … ደፋ ቀና
አንቺን ከመሰለሽ በህይወቴ የምዝናና፣
.
.
.
አንቺ እንዲህ ከሆንሽ
እንዲህ ካሳሰበሽ
ሰላሙን ከነሳሽ
እንዲህ  ካናገረሽ
እኔን ምን አለፋኝ
ምንስ አደከመኝ?
የተደፋ ዉሃ ዳግም ላይቀና፤
.
.
.
እቴ ሙሽራዬ
ዉዴ የኔ ፍቅር
የኔ ተናፋቂ
ሽቅርቅሯ እመቤት
ስሚኝ ልማልልሽ
በሙሉ ዕድሜዬ
በሙሉ ጤናዬ
በሙሉ ህይወቴ
…. እኔ ወድሻለሁ!
ጥላችን ተወግዶ ፍቅራችን እንዲፀና፡፡
፡፡
፡፡
፡፡
እኔ ልሙትልሽ
ዉዴ ልማልልሽ
በጣሙን መሮኛል
ቁርጥሽን ልንገርሽ
ነፍሴ ተጨንቃለች
እጅግም መሯታል
እንዴ! …..
ግን ይህ ሁሉ ለምን?
ለምን የኔ እናት?
.
.
.
.
ብረር….ብረር….
ሂድ ጥፋ ይለኛል
ነጉደህ ….ነጉደህ…..ነጉደህ
ካንድ ጥግ እረፍ …….
ብሎ ይመክረኛል
…    ….  …
ግን፡ … … ግን እኔ ወድሻለሁ!
ዓይኖችሽ ጥላቻ ሁሌ ሲያመነጩ
ፍቅሮችሽ እንደ ሆምጣጤ …
እንደ ሬት ሲመሩ፡
ፊትሽም እንደሾክ ጥንቱን ይዋጋሉ
እንደ እሳት ወላፈን እጅግ ያጋረፋሉ፤
.
.
.
ዉዴ ልጠፋ ነዉ
ኧረ ምን ያሻላል?
አንቺ ብጠይኝም
አንቺ ባታምኚኝም…..
እኔኮ ላንቺ….
እንደ አንቺ ሃሳብ
… ሌባ ነኝ
… ዉሸታም ነኝ
… ቃላባይ ነኝ
ቤቱን የማለወድ ነኝ
የዉጭ አልጋ የቤት ዉስጥ ቀጋ
ግን ለምን……?
እንግዲህ ሌባ መባሌ ካልቀረ
….. ብዬ አልልሽም!
አንቺ ካለወደድሽኝ
…. ብዬ አልልሽም!
.
.
.
ግና!
እኔ እንደወደድኩሽ
እኔ እንዳፈቀርኩሽ
ፍቅር …
ዘወትር አይፀናም!
አንድ ቀን ሊላላ
አንድ ቀን ሊሰበር
አንድ ቀን … …
……. ……. …
አንድ ቀን፣
ዳግም ልቤ ሽፍቶ
ከስፍራዉ ተናግቶ
ልቤ እንደወደደሽ
ሊጠላሽ ከቃጣዉ
አንቺን አያድርገኝ
ሊጠላሽ ይችላል!
ሊርቅሽ ይችላል
ሆዴ!
ሊከፋኝ እንደሚችል
እቴ ተገንዘቢ
ዉዴ ልብ አድርጊ
እኔን ምን ቸገረኝ
እኔን ምን ገዶኝ …
መባባሉ ቀርቶ
መኖሩ ይሻላል
በፍቅር ተደራጅቶ፡፡
ካልሆነ ግን ….
ዉዴ ቆርጫለሁ…
ፍቅሬን ጨራሻለሁ….
መገፋቴ ካለቀረ….
እንዳሞራ በራለሁ፤
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta



ደረሰ ረታ!    30/12/2005

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...