ባለፈዉ በ " ክፍል አንድ " የአንዲትን ወጣት የህይወት አጋጣሚ በራሷ አንደበት ስትተርክልን
እንደነበረ ክፍል አንድን የተከታተለ የሚያስታዉሰዉ ነገር ነዉ፤ዛሬም ቀጣዩን የህይወቷን አጋጣሚ እንዲህ በአንደበቷ ታጫዉተናለች፡፡
መልካም ንባብ!
እንግዲህ የአጋጣሚ ነገር የት እንደሚጥል አይታወቅም አሁን ሳወራህ በህይወቴ ያሳለፍኳቸዉ ነገሮች ሁሉ ህልም ነዉ
የሚመስሉኝ፤
በዕድሜዬ ሁለት አስርት ዓመታትን ሳስቆጥር በሰፈርና በሃይስኩል እንዲሁም ብዙ የፍቅርም የጥላቻም የሃዘንም ገጠመኞች
አሉኝ፡፡ እንደ ፍቅር ግን ሬት የለም ሬት! እዉነቴን ነዉ የምልህ ፍቅር ሬት ነዉ! ሰወች የት አባታቸዉ አይተዉ ስለጣፋጭነቱ እንደሚያወሩኝ
አላወቅም፤ ምናልባት የፍቅር ህይወታቸዉን በተገላቢጦሽ የኖሩ ሰወች እዉነት መስሏቸዉ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰወች ስንባል ይልቁንም ሴቶች
የሌላኛዉን የወንዱን ማለቴ ነዉ ህይወት ስለማንኖርለት፣ ህመሙን ስለማንታመምለት፣ ስቃዩን ስለማንሰቃይ ነዉ እንጂ አጋራችን/ፍቅረኛችን
እኮ በኛ በሴቶች የተነሳ ሙት ነዉ! የለምኮ ሞቷል! በድኑኮ ነዉ አጠገባችን የቆመዉ…. … ፤ ለሞቱ ደግሞ ተጠያቂዎቹ እኛዉ ነን፡፡
የአሻራ ምርመራ የለም እንጂ በነፍሱ ዉስጥ፣ በደሙ ዉስጥ፣ በስራስሮቹ ፣ ከኪሱና በዋሌቱ ዉስጥ ተጣብቀን ደሙን የመጠጥን
እኛ ነን፤ ሴቶች …. … ግን የዋሁ ወንድ ነገር ተገላብጦበት ህይወት አደንዝዛዉ ያለእኛ መኖር እንደማይችል በበድን ምላሱ ለሃጩን
እያዝረበረበ ይነግረናል፤ እኛም ሰምተን እንዳልሰማ ይህ ደምፅ የሙት ነዉ ብለን ሳንቃወም ስጋዊና ደማዊ ሰዉነታችን በሙቀት ይቀልጣል፡፡
ዉዴ! ነፍሴ! ማሬ! ሃኒ!.... በሚሉ ጉንጫልፋ ቃላት እያንቆለጳጰሰን እኛን ሲያጣ መኖር እንደማይችል፣ ነፍሱ እንደምትወጣ
ያለመጠራጠር ያወራል…. የሞተዉኮ ገና ከሴት እንደተገናኘ ነዉ…. አላወቀም እንጂ ሞትኮ ወደ ገነት ዘዉ ብሎ የገባዉ …. አዳምን
ጠርንፎ ከገነት ያስወጣዉ …. ቁልቁል ተዘቅዝቆ ሱባኤ የገባዉ … ወንድነቱን ሁሉ ረስቶ እንደ ሴት ለነገሩ ያኔ ሴት አልነበረችም የማያዉቀዉን ማንባት የተለማመደዉ ሔዋን ከመጣች በኃላ ነዉ፡፡
… … …
የድሮ ልጆችኮ እየተባለ ይደሰኮራል እንጂ ድሮኮ ነበር ገና ተማሪ ቤት ሲከፈት በእንቁጣጣሽ ጭፈራ ያገኘናትን ድቃቂ
ሳንቲም በመያዝ አይናችን የገባዉን ጠጠር ከረሜላ፣ የጉንፋን ከረሜላ እና ድቡልቡሏን ማስቲካ በመግዛት ወንዶችን ስናማልል የነበረዉ፤
ማን አለ አሁን ይህን ዘመን በክፉ የሚያነሳ? ማንም! … ታዉረን ስለነበረ ነዉ ምክንያቱ! እና ግን ከዛን ጊዜ ጀምሮ በዛ ጨቅላ
አዕምሮ ነበር ወንዶችን የምናጠምደዉ …. … ካካካ ….(ደማቅ ሳቅ)
ይሄኔኮ እየሰማኸኝ ሳይሆን ያጠመዱህን ሴቶች ቁጥር እያሰላህ ነዉ ብላኝ ትረካዋን ቀጠለች
ከቤ ይባላል ከበደ! የኛን ቤት አልፎ ነበር ወደ ትምህርት ቤት የሚሄደዉ በዛን አመት አዲስ ትምህርት ቤት የቀየርኩበትና
ወደ ሰባተኛ ክፍል ሚኒስትሪ አልፌ የተዛወርኩበት አዲስ የመስከረም ወር ነበርና ገና እግሬ የትምህርት ቤቱን ግቢ ከመርገጤ እንደ
ሰንበሌጥ ሳር ልቤ ቀጥ አለች ፤ ምክንያቱ ምንም አልነበረም ከቤን በማየቴ እንጂ …. ….
ከቤ ሰፈር ዉስጥ እዚህ ግባ የማይሉት ምንም የተለየ ነገር የማይታይበት ልጅ ነዉ ከዚህ ቀደም ስለሱ ሆን ብዬ ክትትል
ያረኩበት ነገር አልነበረም፤ … … በቃ አየዋለሁ ምናልባት ያየኛል …. ከዚህ የዘለለ ነገር የለንም ባሳለፍነዉ ክረምት ግን አላየሁት
ዘግይቶ በደረሰኝ ዜና ግን ክረምቱን ማትሪክ ስለተፈተነ ተብሎ አዲስ አበባ ዘመዶቹ ጋር ሄዶ እንደመጣ ሰማሁኝ… … ፡፡
ያዲሳባ ዉሃ እንዲህ ፊት ያጠራል እንዴ? ጠራ አይገልፀዉም የምንጭ ዉሃ ይመስል ኩልል አለ! ወንዱን እንዲህ ካደረገ
ሴቱንማ እግዜር ይወቀዉ እንዴት እንደሚያደርጋት? ማን ያዉቃል ይሄኔ የወረት ዓይንም ይሆናል እንዲህ ቆንጆ ያስመሰለብኝ፤ ለነገሩ
አፍላ ዕድሜ ላይ መሆናችን ልባችንን ደፍኖ ዓይናችንን ብቻ የገለጠ እስኪመስል ከባልንጀሮቼ ጋር የምናወራሁ ሁሉ ስላየነዉ ከሆነ
ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ከቤትም በነፃነት የወጣንበትም ወቅት ቢኖር ይህ አዲስ ዘመን ነዉ ምናልባት ክረምቱን ብዙም ባይሆን ፍስለታን
ብቻችንን ቅዳሴ ጓደኛሞች ተሰብስበን ሄደናል፤ ያኔም ከአስቀዳሹ ጀምሮ ዲያቆናቱ ድረስ ዓይናችን ሲቀላዉጥ ነበር፡፡ ለካስ እህቴ
እንዲህ የምትከታተለኝ ይህን ዕድሜ ስላለፈችበት በደንብ ስለምታዉቀዉ ነዉ ቁጥጥሯ ጠበቅ ያለዉ፡፡ … … …
…. ….. …..
አዲስ ጫማ፣ አዲስ ልብስ፣ አዲስ የደብተር መያዣ የጀርባ ቦርሳ (በገጠር ከተማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል በሚያስችል
መልኩ እሱ ያዘዉ) ተሸክሞ …. በር….ቀት አየሁት ሲጀመር ማንነቱን ባለየሁበት ሁኔታ ነበር በመረቤ የገባዉ፤ ጓደኞቼን መረቤን
እንደዘረጋሁ አሳዉቄያቸዉ ወደርሱ እንድንነቃነቅ ቀጭን ትዕዛዝ ያስተላለፍኩት፡፡ … … ስንደርስ ከቤ ነዉ ትላንት የምናዉቀዉ ዛሬ
ግን በመጠነኛ እድሳት አይናችን ላይ ከፍተኛ ለዉጥ ያመጣዉ … … ይሁን እንጂ በቃ እይታችንን ማርኮታልና በአፍላ ፍቅር ነደፈን
ኧረ ነደፈኝ እንጂ … … መጠመድ ነበረበትና ተከተልነዉ … … አጠመድኩት! …. ነፍሱ በእጄ ላይ እስክትዝል ድረስ ተንፈራገጠች፤
በዉዳሴ ማንነቱን ይልቁንም የወንድነት ወኔዉን አኮላሸሁት (ወንድ ልጅ ከተቀደመ ማንነቱ ይኮላሻል በኔ ስሌት )
ከቢሻ … … ከቤ ሸበላዉ …. ከቡዬ …. እንዴት ነህ? የት ሄደህ ነዉ እንዲህ የጠፋኸዉ? ሞቅ ከማድረግም አልፈን
ቀወጥነዉ ትንፋሽ የሚወስድበት ጊዜም አልሰጥህ አልነዉ! በቃ በአጭሩ ተቀባበልነዉ ተኩላዎች መሃል ጠቦት በግ አስመሰልነዉ፡፡ (ምናልባት
ይህ አባባሌ እንኳንስ እሱን እኔንም የሚያሳፍር ነዉ መቼስ አንዴ የተጠናወተኝ ቆንጆ ነገር አድናቂነቴ አሸንፎኝ እንጂ) ፤ ከቤ
በጨዋ ስርዓት ፈገግ ከማለት ያለፈ ምንም ምላሽ ሊሰጠኝ አልቻለም፡፡ ደፋሯ ግን ተጠምጥሜ ሰላም አልኩት … ጓደኞቼ የኔ አደን መሆኑን
ቀድሜ ስላሳወኳቸዉ በርቀት ይከታተሉን ነበር፤ ሰላም በላቸዉ እንጂ ከቤ በማለት የትንፋሽ መዉሰጃ ጊዜ ነሳሁት፡፡ ድንብርብር ብሎ
እ….እ.ሺ ብሎ እጁን ዘረጋለት ጫፍ ሲያገኙ የማይቻሉ ጓደኞቼ ግማሹ ጉንጩን፣ ግማሹ ትከሻዉን፣ የተቀሩት እቅፍ አርገዉ መሳም ጀመሩ
ነፍሱ በእጃችን ታጥቦ የተጨመቀ አሮጌ ነጠላ ይመስል የጭንቀት ድምፅ አሰማች … … ዓይናችንን በጨዉ የታጠብን የገጠር አራዶች ነበርን፡፡ እንደ ቅናትም እንደማዘንም
ብዬ ነዉ መሰል ጓደኛዬን አታጨናንቁት የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ሰጠሁ … … ለቀቁት፤ ድንቄም ጓደኛ ቀድሞ ባየ ሆነ እንዴ? አሁን ራሱንም
የሚሰማበት ጊዜ የለዉም እንጂ ቢሰማኝ ወይ ራሱን ይዞ ይጮሃል አለበለዚያም ሆዱን እስኪያመዉ ድረስ ይስቅ ነበር፤ … … ጓደኛዬ……
ሃሃሃሃ…..
ወዲያዉ ዓይኔ በርቀት የቋመጠበትን የደብተር መያዣ ቦርሳ ከጀርባዉ መንትፌ ዚፖቹን መፍታት ጀመርኩ በርቀት ዓይኑን
ሰበር አድርጎ መጨረሻዬን ይከታተላል፡፡ ሁሉንም ከፋፍቼ ስጨርስ ደብተሮቹን መግለጥ ጀመርኩ … ቅብጥብጥ አደረገኝ … የደብተሩን
የላይኛዉን ገጽ እንደገለጥኩ ስሙ በተለጣፊ (ስቲከር) ነገር ላይ ተጽፎ ተለጥፏል ይሄኛዉ ደግሞ ሁለተኛዉ ልዩነት ነበር፡፡ከዉስጥ
ተደብቆ ያላየነዉ … ምናልባትም እኛ ያላየነዉ አዲስ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ….
… … …
ቀጣዩን የትምህርት ወቅት ደብተሬን በርሱ ቦርሳ ከተን ነበር ወደ ትምህርት ቤት የምንሄደዉ፤ ጓደኝነታችን እየፀና፣የሴት
ጓደኞቼ ቁጥር እየተመናመነ፣ እሱንም ወዳልተፈለገ ከኔ ጋር ጊዜ የማባከን ሽግግር፤ … … የቆይታ ጊዜአችን ሶስት ወራት አስቆጠረ፣
….
አዉቄ ቀድሜ ወጣለሁ እስኪመጣ ጠብቀዋለሁ … ትምህርት ቤት ግቢ ቶሎ እንዳንገባ እንዳልገባኝ በመሆን ደብተሬን አወጣና
ጥያቄ ጠይቀዋለሁ፤ እሱም ከልቡ ያስረዳኛል፡፡ እንዲህ ቆም ገተር እያሉ መሄድ ተላምደነዋል እንኳን እኔ ከቤ ራሱ ይህ አይነቱ አካሄድ
ቢቋረጥ የሚወደዉ አይመስለኝም፡፡ የኢትዮጵያን የህዝብ መዝሙር እየዘመርን ሰንደቅዓላማ መስቀል ካቆምን ረጅም ጊዜ ሆኖናል፤ በኔ
ሰንደቅነት ላይ ከቤ እንደ ባንዲራ በልቤ ላይ እየተዉለበለበ እሱን እያዜምኩ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር እሱን ከተካሁት ሰነበትኩኝ፡፡ከኢትዮጵያ
ይልቅ እሱ ቀዳሚዉን ስፍራ ይዟል፤ከኢትዮጵያ ይልቅ እሱ ከማበብ አልፎ ፍሬ አፍርቷል … …
… … …
የአጋጣሚ ክፉ በዓይኔ በኩል የገባዉ የርቀት ፍቅር መሳይ ነገር እንደዘበት ሰዉነቴን ተቆጣተረዉ፣ ቆንጆ ነገር አይቼ
የተወሰወስኩት ባላሰብኩት አጋጣሚ መረቡ እራሴኑ አጠመደ፣ (ጉድጓድ ስትቆፍር አርቀህ አትቆፍር ማን እንደሚገባበት አይታወቅም የሚባለዉ
እዉነት እንደሆነ የገባኝ አሁን አሁን ነዉ) በቆፈርኩት ጉድጓድ ራሴዉ ገባሁ፤ ልታይ ልታይ ማለቴ ደበዘዘ፣ ሰፈሬን የቀየርኩ ይመስል
የምመላለሰዉ እነ ከቤ ሰፈር ሆነ፣ እቤት ሳይቀር የወንድሞቼን ስም ሁሉ ከቤ እያልኩ መጥራት ስራዬ ሆነ እናቴ ምንም እንኳን የመጨረሻ
ልጅነቴን ግንዛቤ ዉስጥ አስገብታ ብታሞላቅቀኝም መበላሼቴን ግን በቸልታ ማለፍ አልፈለገችም፡፡
አንቺ ልጅ ምን እየሆንሽ ነዉ? ወዴት ነዉ እየበረርሽ የምትሄጂዉ? እያለች በነጋ በጠባ ብትወተዉተኝም ስሟን አንዳቸዉም
ሴቶቹም ሆኑ ወንዶች ልጆቿ በክፉ ሳያስጠሩ እኔ በሰፈር ዉስጥ ስሟን አስጠራሁት! በአፍላነት ዕድሜዬ ተስፋዬ በፍቅር ተሽመደመደ!
ፍቅር የጓያ እህል ይመስል ልብን ሽባ ያደርጋል! ይህንን ጉዳይ ስድስት ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ በደንብ ተገንዝቤዋለሁ፡፡
የቀሩትን የትምህርት ዘመን ዓይንሽን ላፈር ተብዬ አጠናቀኩ፤ ከቤ ግን እንደኔ ስሜቱ በአሸዋ ላይ የተመሰረተ አልነበረምና
ተረጋግቶ እኔንም ያረጋጋኝ ነበር፡፡ የሚገርመዉ ምንም እንኳን ከርሱ ጋር ላይ ታች ብል፣ ከርሱ ሳልነጠል ብታይም እሱ ግን በክረምት
ወቅት ያካበተዉን የእንግሊዚኛ ቋንቋ ያስጠናኝ ነበር፡፡ እኔም እንደሱ ባልሆንም የፍቅርን ሀ ሁ… አስቆጥሬዋለሁ! የፍቅርን ፅዋ
አስጎንጭቼዋለሁ! በፍቅር አጋንንት አስለክፌዋለሁ!የኔ ፍቅር የሌሊት መጋኛ የቀን ምች እሲሆንበት ድረስ አስለክፌዋለሁ፡፡
ከዚህ ቀደም የትምህርት ፍቅር ይኑረኝ እንጂ ይህንን ያህል ዉጤታማ አልነበርኩም እናም የትምህርት ዉጤቴ ለማለፍያ ብቻ የሚሆን ነበር፡፡ እንዳንዳንድ ሴቶች በፍቅር
ሲያዙ በትምህርት እንደሚዘቅጡት አላደረገኝም ይልቅ ዉጤቴ በተለየ ሁኔታ እየጨመረ ሄደ እንጂ፡፡ በትምህርቴ ቤተሰቦቼ ሳይሆኑ የሚቆጣጠረኝ
ከቤ ሆነ የትምህርት ፍላጎቴ ላይ ነፍስ ዘራበት! የዕዉቀት ፍሬ ዘርቶ በፍቅር ዝናብ አብቅሎ በፍቅር ፀሐይ አብስሎ በፍቅር ንፋስ
አድርቆ ለመልካም ዉጤት ማዕድ አበቃኝ! ከቤ፡፡የመንዘላዘሌን ያህል ዉጤቴ የወረደ ቢሆን ኖሮ አስተማሪዎቼ ዓይንሽን ላፈር ባሉኝ
ነበር ነገር ግን አንገታቸዉን እየደፉ ዜሮአቸዉን ከሚታቀፉት እኔ አይን አዉጣዋ ተሸዬ ስለተገኘሁ መምህራኖቼም እኔን የሚናገሩት
አንደበት አጡ፡፡ እነሱ አይናገሩኝ እንጂ የከቤ የልጅነት አንደበት ይህን ያህል አቅሌን እንድስት ዕድል አልሰጠኝም ነበር፡፡ ከቤ
ፍቅሬም አለቃዬም የልቤ ንጉሥም ነበር እኔም እንደ ባሪያዉ ስገዛለት እንደ ንግስት በልቡ ነግሳለሁ፤ በፍቅር ያነግሰኛል! አፍታም
ሳይቆይ እንደ ባሪያዉ ይገዛኛል፡፡ ዘጠኝ ወራት እንደዘበት ተጠናቀቁ … … …
ቤተሰቦቼ ግን በሰፈር ሰዉ የተነሳ ስማቸዉን ለማደስ
ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ያልወጡት ዳገት፣ ያልወረዱት ቁልቁለት አልነበረም፤ በምክር ያልተሳተፈ ዘመድና ባዕድ አልነበረም! … … እንደ
ታላቅ እህቴ ለነርሱ ነፍስ ያለዉ ሃሳብ ለኔ ግን መርዛማ ዉጤት ያስመዘገበ አልነበረም! ተሳካላትም፡፡ የሁለተኛዉን መንፈቀ ዓመት
ማጠቃለያ ፈተና እንደተፈተንን ዉጤቴን ሳላይ ከቤን በዚህ ዋል በዚህ እደር ሳልል እንኳን እሱ እኔ ሳላዉቀዉ ወደማላዉቃት አዲስ
አበባ ተሰደድኩ፡፡
እሱ ወዲያ ማዶ እኔ ወዲህ ማዶ አንገናኝም ወይ ገደሉ ተንዶ አሉ ቲቸር ጥላሁን! እኔና ከቤን የሚያገናኝ ያ የዉስጥ
ለዉስጥ መንገድ በገደልነት ተቀየረ! እሱ በተራዉ እዛዉ ገጠር እኔ አዲስ አበባ … ማን ያዉቃል አዲስ አበባም መጥቶ ይሆናል! …
… እሱ የመጣዉ ለእረፍት፣ ለትምህርት … እኔ ግን ለቅጣት ከምወደዉ ሰዉ ተነጥዬ በር ሊዘጋብኝ አይኔን በሻሽ ታስሬ በጨላማ ቤት
ልጣል … …
… … …. …
የአዲስ አበባ ቆይታዬ እጅግ በጣም አሳኝ ከመሆኑ በላይ አስጠሊታ ነበር ፤ ከመቃብር ስፍራ ምንም የሚሻል ነገር አልነበረዉም፡፡ማን
ነበር ይሄ? ስሙ ጠፋብኝ
ድሃ ቤት ጥቅስ ፣
ሃብታም ቤት ጥብስ፤ አይጠፋም ያለዉ፡፡
እያዬ ቤት የነበረዉ ጥቅስ እንኳን የሌለበት ባዶ! ቤት ወና፤ ኤጭ እንዴት እንደሚያስጠላ … … ኑሮ ካሉት መቃብር
ይሞቃል አይደል የሚባለዉ የአዲስ አበባ ሰዉ … …
በተለይ በተለይ ከመኝታ ቤታችን ያለችዉ፡-
ዝናብ ሳለ ዝራ፣
እናትህ ሳለች ኩራ፤
የምትለዋን እዚህ ባገኛት ባሉኝ ዋጋ ነበር የምገዛቸዉ
መቸስ አዲስ አበባ የታዋቂ ሰወች ፎቶ ካልሆነ በቀር ጥቅስ መንገድ ላይ ሲሸጥ ማየት ብርቅ ነዉ፡፡
አንድ ቀን እንኳን ለንግስ አብሬያቸዉ ቤተክርስቲያን ብሄድ አይቼ የመጣሁት ቤተክርስቲያኑ ዙሪያ የንግድ ባዛር እንጂ
መንፈሳዊ ስፍራ አይመስልም፡፡ አዲስ አበባኮ ስሟን ቀይራ ያረጀች አበባ ብትባል ይሻላታል ኧረ እንዲያዉም የረገፍች ብትባልስ? ስም
ብቻ …. ኤዲያ አገሬ እንኳን ቤተክርስቲያን ገበያ ራሱ ክብር አለዉ በእህል መሸጫዉ ምን ቦታ ቢጠፋ ከብት አይቆምበትም አዲስ አበባ
ግን ክብር የሌላት አገር የእግዚአብሔርን ተግሳፅ ተላልፈዉ ዛሬም ቤቱን መነገጃ አርገዉታል፡፡
ለመሆኑ አንተ የአዲስ አበባ ልጅ ነህ? ብላ ድንገት ጫወታዉን አቋርጣ ጥያቄ ሰነዘረችልኝ፤ ለቀድሞዉ የአዲስ አበባ
ልጅነት ኩራት እየመሰለኝ የአዲስ አበባ ልጅነቴን ነበር የማዉጀዉ አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ እዉነት አናገረችኝ .. … …..
"የክፍለ ሃገር ልጅ ነኝ! "አልኳት
አይ የአዲስ አበባ ልጅ ከሆንክ አገርህን እፊትህ እንዳላማብህ ብዬ ነዉ የአዲስ አበባ ልጆች ይቺ ያረጀች አገራቸዉ
ለነሱ ሌላ አገር ስለሌላቸዉ ገነታቸዉ ነች፤ እኛ በተለያየ ምክንያት ግማሹ ለስራ፣ ግማሹ ለከፍተኛ ትምህርት፣ ግማሹ ለኑሮ፣ እንደኔ
አይነቱ ደግሞ ተገፍቶ ለቅጣት የምንሄድበት አለን፡፡ እነሱ ግን ወይ በዲቪ አሜሪካ አለበለዚያ በምሬት ወይ በሆነ ነገር ብቻ አረብ
አገር ከመሄድ ወዲያ ምንም አማራጭ የላቸዉምና፡፡
*** *** ***
የተማሪ ያለህ ከሚባልበት አገር መጥቼ የትምህርት ቤት ያለህ ተብሎ ቢታሰስ ቢታሰስ ትምህርት ቤት የማይገኝበት አገር
ልምጣ?
" ሊገኝ አልቻለም! " አለችኝ እቴቴ
ደስ ነበር ያለኝ፤ ከቤ በዓይኔ ላይ እየሄደ ምግብ በጉሮሮዬ አልወርድም ካለኝ ሰንብቷል፤ ሰራተኛዋ እናቴ ታማለች
ብላ አስፈቅዳ እስከምትሄድበት ቀን ድረስ ያረገዝኩ ሁላ እስኪመስለኝ ድረስ ምግብ ስበላ ወደላይ ሊለኝ የሚከጅለኝ ነገር በጣም ነበር
የሚያሳቅቀኝ፡፡ ምንም እንኳን ሰራተኛዋ በመሄዷ ብዪ አትብይ ከሚል ጭቅጭቅ ተነፈስ ብልም ባለመብላቴ ግን የአቅም ማነስ እየታየብኝ
መጥቶ ነበር፤ግን ያለብኝን ስጋት ከከቤ በስተቀር የሚፈታዉ ማንም ምንም ነገር አልነበረም፡፡
"ትምህርት ቤት አልተገኘም " በሚል ምክንያት ወደ ከቤ የምመለስ መስሎ ይታየኝ የነበረዉ የተስፋ
ጭላንጭል መሟጠጡን እቴቴ ቅዳሜ ከሰዓት ከስራ አቋርጣ ስትበር መጥታ አረዳችኝ፤
"ትምህርት ቤት ስለተገኘልሽ ሰኞ እንሄዳለን…" አለችኝ!
ሰማይ ምድሩ በኔ ላይ ያደሙ ይመስል ተስፋዬን አጨለሙብኝ፤ በቃ ተስፋ ቆረጥኩ … … ፍቅር ጨላማ እንደሚወርሰዉ አራሙቻ እንደሚበቅልበት ዛሬ ተገነዘብኩ፡፡የልቤን
ደጅ ዘግቼ የፍቅር አምላክ ወዴት አለህ አልኩኝ በለሆሳስ ፈጣሪ እኛ ቤት ኮርኒስ ላይ ያለ ይመስል ዓይኔን ወደ ኮርኒሱ እቅንቼ፤
… ፈጣሪም ዝም አለኝ! እኔም አንደበቴ በድንጋጤ ተሸበበ፡፡
እቴቴ … …
"አቤት …."
የሚሳካ ይመስለሻል?
"ምኑ? …"
ያልሽዉ የትምህርት ቤት ጉዳይ ነዋ!
"እህ…. እሱንማ አብረን የምናየዉ ይሆናል እግዜር ይስጣትና አንድ የመስሪያ ቤታችን ገንዘብ ተቀባይኮ ነች
መጨነቄን ሰምታ ምዝግባ እንዳለ የነገረችኝ … እንግዲህ እንሞክራለን፤ … "
እቴቴ ለምን ይህንን ያህል ትደክሚያለሽ … … እ…..እዛ …. ዉ ለምን አልማርም ምን አስጨነቀሽ? ማለቴ… እ…
…. አላጨረሰችኝም፤
"በቃ!" መብረቃዊ ምትሃት ያለዉ በሚመስል ድምፅ ቆሌዬን ገፈፈችኝ፤ እንዳያያዟ ከሆነ እንኳንስ እዛ
ሄጄ መማር ይቅርና እናቴን ለበዓል ሄጄ የማገኛት አይመስልም፡፡
**** **** ****
ሰኞ ዕለት ወደ ትምህርት ቤቱ ሰልስት እንደሚደርስ ሃዘንተኛ በዝምታ ታጅበን እንደ ባላገር ባልና ሚስት ፍትና ኃላ
እያልን ደረስን፤
ፈተና የነበረዉ የሒሳብ ትምህርትና ቋንቋ ነበር (የአገር ጉድለት በሒሳብና በእንግሊዝኛ ይሞላ ይመስል)መቸስ ለአማርኛ
ስለማልታማ ቁጥር ዉስጥ አላስገባዉም፡፡ ከፈተናዉ ከወጣሁ በኃላ አንድ የረሳሁት ነገር ነበር ምን መሰለህ ፈተናዉን ስሰራ ፈተና
ላይ ያለሁ ይመስል ከቤ ባስጠናኝ መሰረት ነበር የሰራሁት ይህ ደግሞ ለማለፌና እዚሁ ለመቅረቴ ዋነኛ ምክንያት ይሆናል ብዬ እጠራጠራለሁ፡፡
የታዘብኩት ሌላ ነገር መቸስ አዲስ አበባ ያመጣኝ ለትዝብት ሳይሆን አይቀርም፤
ለፈተና ከመግባታችን በፊት አይደለም በአማርኛ የሚናገር በአማርኛ የሚሰማ ጆሮ ከኔ በቀር ያለ አይመስልም ነበር፤
ወደ ፈተና ክፍል ገብተን ስንፈተን ግን ያ ሁሉ አፉ ለአፍታ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከማዉራት ያልቦዘነ ሁላ ዓይኑ ወረቀቱን ከማየት
ይልቅ ጣሪያ ጣሪያዉን ከማየት አንዳቸዉ እንኳን የፈተና ወረቁቱን መልስ መስጫ ለማየት የደፈረ አልነበረም፡፡ወንድ የለ ሴት … አይ
አዲስ አበባ!
ወጥቼ እህቴን ምን ሆነዉ ነዉ ብዬ ታሪሁን ሳጫዉታት ከተለያዩ የግል ትምህርት ቤት ደግመዉ የተባረሩ እና እዚህ ደግሞ
እድላቸዉን ለመሞከር የመጡ እንደሆኑ ነገረችኝ፡፡
*** /// **** //// ****
ለዛሬዉ ህይወቴ ከአዲስ አበባ ልጆች የቀሰምኩት ነገር ከንፈሬን ሊፒስቲክ መቀባት፣ ዩኒፎርም መቅደድ፣ ሱሪ መልበስ፣
አስተማሪ ማጭበርበር፣ኩረጃ (ለነገሩ ዕድሜ ለከቤ የትምህርት ዘር በደህና ጊዜ ስለዘራብኝ አስኮርጅ እንደሆነ እንጂ አልኮርጅም ነበር
እሱም ቢሆን በእኛ አገር ባህል በገጠሩ አካባቢ ማስኮረጅም ከነዉርነት አልፎ ሐጥያት ነዉ፡፡)፣በየመንገዱ መብላት፣ ፓሪቲ፣በየምክንያቱ
በየጭፈራ ቤት መገኘት፣ … ወዘተ ነበር፡፡
ባለፈዉ እንዳወራሁህ የፍቅር ጓደኛዬ የነበረዉ ከዚህ ሁሉ አጉል ነገሮች (መጠጥ፣ ጭፈራ ቤት፣ ልታይ ልታይ ማለት…)
የፀዳ ስለነበር ተቀላቅሎብኝ የነበረዉን መንፈሳዊነትና አለማዊነት ምንም እንኳን እንዲህ የለየለት መንፈሳዊ ባይሆንም ጭምት ነበርና
እሱን ለመምሰል፣ እሱ ከሚዉልበት ለመዋል ስል በሚያደርጋቸዉ ጥረቶች ህይወቴን ፈር አስይዞታል፡፡እግዚአብሔር ይመስገን ከቤን ባጣዉም
የከፋ ወንድ ላይ አልጣለኝም ነበር፡፡
ያቺን ቀን አልረሳትም ታኅሳስ 12 ፤ ትልቅ ትዛታ ጥላብኛ ነዉ ያለፈችዉ፡፡
ያ ቀን ነበር ፍቅሩን በልቤ ዉስጥ ያሳደረዉ እሱ እንደማንኛዉም ዕለት ህይወቱን እየመራ ነበር ብቻዉን ከሚኖርበት
ቤቱ አራት ሰዓት ገደማ የደረስኩት፡፡
ይቆየን! በክፍል ሶስት እንዲሁ የአጋጣሚን ነገር እናያለን፤

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ