ማንኛችንም ወንድማችን ተርቦ ዳቦ ሲለምነን ረሃቡን ያስታግስበት ዘንድ
በዳቦ ፋንታ ድንጋይ የሚሰጠዉ ማንም የለም፡፡ በዚህ ምድር ላይ ተፈጥሮ በድሎትም ሆነ በስቃይ ዉስጥ የሚመላለስ ማንኛዉም ፍጥረት
በክርስቶስ ኢየሱስ ወንድማችን ነዉ፡፡ ወንድማችን እስከሆነ ድረስ ደግሞ በወንድሙ የሚጨክን ሰዉ ነፍሰ ገዳይ ነዉ፤(አትግደል እንደተባለ
ሰምታችኃል እኔ ደግሞ ወንድማችሁን በዳቦ እጦት እንዳትገድሉት አስታዉሳችኃለሁ ሃይማኖቱ፣ዜግነቱ፣ብሔሩ …ምንም ይሁን ምንም፤ሰዉየዉ
ምንም ይሁን ማንም) ነፍሱን ማቆያ ዳቦ እንሰጠዋለን፡፡ ምግብ በዋናነት የሚያገለግለዉ ለቁመተሥጋ ነዉና አንድም ሥጋችን ተደግፋ
ያለችዉ በምግብ ላይ ነዉና ወንድማችንን ሲርበዉ ቁራሽ ምግብ ስንከለክለዉ ሥጋዉ ከነፍሱ እንድትለይ ፈቅደናልና ነፍሰ ገዳይ ነን፡፡
በቅዱሳት መፃህፍት ላይ ተጽፈዉ የሃይማኖት መመሪያዎች ከሆኑት መካከል አንዱ ሕግ ‹‹አትግደል›› የሚል ነዉና በአንድም ሆነ በሌላ
መንገድ ሕግ ሽረናል፤ አንድም ደግሞ ይህ ሕግ ሲፃፍ ለዚህኛዉ እምነት ተከታይ፣ ለዚያኛዉ ብሔር፣ ለዚህኛዉ ጎሣ፣ ወይም ዘርና ቀለም
አይልም ስለሆነም ሲራብ አለማብላታችንና ዝምታችን በቀላሉ ከምናየዉ ‹አለማብላት› በዘለለ ነፍሰ ገዳዮች ነን ማለት ነዉ፡፡ ከእግዚአብሔር
ሕግም ባሻገር የወንጀለኛ ሕጉን አንቀጽና ቁጥር ባልጠቅስም በየትኛዉም ዓለም ሕግ ነፍስ ማጥፋት አይፈቀድም ወንጀልም ነዉ፡፡ በነፍሳችን
ምንም እንኳን ወዲያዉ በዓይናችን አይተን በእጃችን ዳሰን የምንፈራዉ ቅጣት ባይደርስብንም ቅሉ በምድራዊ ህግ ግን ለእስርና በገንዘብ
መቀጮ ከዚያም ባሻገር የከፋ ፅኑ ቅጣት ሊኖረዉ ይችላል የተለያዩ የቅጣት ማቅለያዎች ግምት ዉስጥ ካልገቡ በቀር፡፡
ተርቤ አላበላችሁኝም!
ወቅቱ በኢ/ኦ/ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የፆም ወቅት እንደመሆኑ
መጠን ያለፉትን ሰባት ሳምንታት በፆምና በጸሎት በምፅዋትና በስግደት አሳልፈን አሁን የዐብይ ፆም የመጨረሻዉ ሳምንት ላይ እንገኛለን፤
ይህም ሳምንት ሰሙነ ኅማማት ይባላል፡፡ ሰሙነ ኅማማት ማለት የዐብይ ፆም የመጨረሻዉ ሳምንት ሲሆን የጌታን መከራና ኅማም የምናስብበት ሳምንት ነዉ፡፡ በዚህ ሳምንት ከምናስባቸዉ ኅማሞች መካከል በቀላሉ እንዲረዳን ስለመራቡ፣ መጠማቱ፣ መንገላታቱ፣ መሰደቡ፣ ምራቅ በፊቱ ስለመተፋቱ፣ ያለ አንዳች ጥፋት ለፍርድ መያዙ፣ ለፍርድ በጲላጦስ አደባባይ መቆሙ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ድረስ መስቀል ተሸክሞ መዉጣት መዉረዱ፣ በመስቀል ላይ እንደ ወንጀለኛ ከመሬት ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ በመስቀል ላይ መዋሉ፣ … ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡ ለዛሬዉ የምንመለከተዉ ‹መራቡን› ብቻ ይሆናል፤ ይህንንም ሲያጸናዉ በወንጌሉ ላይ እንዲህ ብሎ አስቀምጦታል የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 ቁጥር 42 ላይ በግራዉ ያሉትን የኃጥአን ምሳሌ ነፍሳት ‹‹ተርቤ አላበላችሁኝምና ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና ….›› እያለ በፍርድ ሰዓት ባለማድረጋቸዉ የሚያስጠይቃቸዉን ነገር ይዘረዝራል፤ ይህ ቃል አንድም የሚያጠይቀዉ በሰሞነ ሕማማት ወቅት የተራበዉን ሲሆን አንድም ደግሞ በመፅሐፍ እንዳስቀመጠዉ ለፍርድ በግራዉ ቆመዉ ያሉት ለቅጣት ማቅለያነት ‹‹ተርበህ መች አየንህ?›› ቢሉት እርሱም እንዲህ ሲል መልሶላቸዋል ‹‹ … ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁ ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል፡፡›› ይላል፡፡የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ‹‹ከእነዚህ ለአንዱ›› ብሎ የተናገረዉ በሥጋ ዓይን ከኛ አንሰዉ የሚታዩ የሚራቡና የሚጠሙ ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ ርሃባቸዉን ለማስታገስ፣ ጉድለታቸዉን ለመሙላት፣ እርቃናቸዉን ለመሸፈን ሲሉ ከየደጃችን ሲቆሙና የሳንቲም ድቃቂ የጨርቅ እላቂ እና የምግብ ትራፊ ሲለምኑ ዝምታ እና ዝንጋታዉ በቀጥታ እግዚአብሔርን ሲራብ አለማብላት እንደሆነ መፅሐፍ ያረጋግጥልናል፡፡
ይህም ሳምንት ሰሙነ ኅማማት ይባላል፡፡ ሰሙነ ኅማማት ማለት የዐብይ ፆም የመጨረሻዉ ሳምንት ሲሆን የጌታን መከራና ኅማም የምናስብበት ሳምንት ነዉ፡፡ በዚህ ሳምንት ከምናስባቸዉ ኅማሞች መካከል በቀላሉ እንዲረዳን ስለመራቡ፣ መጠማቱ፣ መንገላታቱ፣ መሰደቡ፣ ምራቅ በፊቱ ስለመተፋቱ፣ ያለ አንዳች ጥፋት ለፍርድ መያዙ፣ ለፍርድ በጲላጦስ አደባባይ መቆሙ፣ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ ድረስ መስቀል ተሸክሞ መዉጣት መዉረዱ፣ በመስቀል ላይ እንደ ወንጀለኛ ከመሬት ከፍ ከሰማይ ዝቅ ብሎ በመስቀል ላይ መዋሉ፣ … ጥቂቶቹ ናቸዉ፡፡ ለዛሬዉ የምንመለከተዉ ‹መራቡን› ብቻ ይሆናል፤ ይህንንም ሲያጸናዉ በወንጌሉ ላይ እንዲህ ብሎ አስቀምጦታል የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 ቁጥር 42 ላይ በግራዉ ያሉትን የኃጥአን ምሳሌ ነፍሳት ‹‹ተርቤ አላበላችሁኝምና ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና ….›› እያለ በፍርድ ሰዓት ባለማድረጋቸዉ የሚያስጠይቃቸዉን ነገር ይዘረዝራል፤ ይህ ቃል አንድም የሚያጠይቀዉ በሰሞነ ሕማማት ወቅት የተራበዉን ሲሆን አንድም ደግሞ በመፅሐፍ እንዳስቀመጠዉ ለፍርድ በግራዉ ቆመዉ ያሉት ለቅጣት ማቅለያነት ‹‹ተርበህ መች አየንህ?›› ቢሉት እርሱም እንዲህ ሲል መልሶላቸዋል ‹‹ … ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁ ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል፡፡›› ይላል፡፡የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ‹‹ከእነዚህ ለአንዱ›› ብሎ የተናገረዉ በሥጋ ዓይን ከኛ አንሰዉ የሚታዩ የሚራቡና የሚጠሙ ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ ርሃባቸዉን ለማስታገስ፣ ጉድለታቸዉን ለመሙላት፣ እርቃናቸዉን ለመሸፈን ሲሉ ከየደጃችን ሲቆሙና የሳንቲም ድቃቂ የጨርቅ እላቂ እና የምግብ ትራፊ ሲለምኑ ዝምታ እና ዝንጋታዉ በቀጥታ እግዚአብሔርን ሲራብ አለማብላት እንደሆነ መፅሐፍ ያረጋግጥልናል፡፡
የማናችንም ነፍስ በፍርድ ሰዓት መልካምም ትስራ መጥፎ ነገር በግራዉ
ከኃጥአን ጋር ለመቆም ብርታቱ ሆነ ፍላጎቱ የለንም፤ ነገር ግን ዛሬ በቁማችን ሳለን ታሪካችንን መቀየር የምንችልበት የንስሐ ዕድሜ
ያለመልካም ስራ እንዲሁ ማንቀላፋቱና ያኔ ማልቀሱ እንደማይበጅና ዛሬ ግን መልካም ሥራን ልንሰራበት የተሰጠንን ሰዓት በአግባቡ በመጠቀም
ኃጥያታችንን አስቀርተን ጽድቅን ለመጎናፀፍ ዛሬ የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ አንዱና ዋነኛዉም ነገር የተራበን ማብላት
ነዉ፡፡ ለድሆችም በመስጠት በደላችን እንደሚሰረዝልን መጽሐፍም ይናገራል፤ ት.ዳንኤል 4፡27 ‹‹ … በደልህንም ለድሆች በመመጽወት
አስቀር፡፡›› ይላልና፡፡ ከጥቅሙ ባሻገርም ድሆችንም በልግስና መርዳት እንዲገባ ተቀምጧል፡- ‹‹ … በአገርህ ዉስጥ ላለዉ ድሃ
ለተቸገረዉም ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ፡፡›› ኦሪት ዘዳግም 15፡11
ለዚያዉም ከድህነት ወለል በታች ባለች አገር ለምንኖርና ኢኮኖሚዋ በጥቂት
ባለሃብቶች እጅ በወደቀበት አገር ዉስጥ እያለን የተቸገረ ወንድማችንን መርዳት ትልቅ ሃላፊነት ነዉ፡፡ ምንም እንኳን እኛም የሌለን
ሰዎች ብንሆንም ህጉ ጥብቅ ስለሆነ ካለን ለማካፈል እንገደዳለን ‹‹ሁለት ያለዉ አንድ ይስጥ›› ይላልና፡፡ አንድም ፍፁም ነኝ ብሎ
እግዚአብሔርን መከተል ቢፈልግ በመጨረሻ ሊያደርግ የሚቀረዉ ነገር ቢኖር ያለዉን ሸጦ ለድሆች መስጠትና እግዚአብሔርን መከተል ነዉ፡፡
ማቴዎስ 19፡21
ኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነት ባህላችን
ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሔር ብሔረስብ ያላት፣ ከ80 ሚሊዮን ህዝብ
በላይ ያላት፣ ብዙ ዉብ የሆኑ ባህሎች ያሏት ድንቅ አገር ናት፤ከነዚህም መካከል እንግዳ ተቀባይነታችን በየትኛዉም ዓለም የማይታይና
ምናልባትም በዓለም ላይ በብቸኝነት የምንጠራበት ባህላችን ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ከአገራት በላይ እምዬ ኢትዮጵያን በመላዉ ዓለም
የሚያስጠራትና የሚያኮራን ባህላችን በአንድም ሆነ በሌላ የተራበን ማብላት ይመለከታል፤ ይህን ከጥንት ይዘነዉ የመጣነዉ ከአባቶቻችን
የወረስነዉ ባህላችን አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ የሚያስችለን ባህል ነዉ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ዓለም የሚያዉቀንም የተራብን ህዝቦች እንዶሆንን
ነዉ ይህ ደግሞ የሚያሳየዉ ባህላችንና ማንነታችን መጣረሳቸዉን ነዉ፡፡‹‹እንግዳ›› ማለት ከሩቅ አገር ባህር ተሻግሮ የመጣን ብቻ
አይደለም፣ የሩቅ ዘመዳችንም ድንገት ባላሰብነዉ ሰዓት ከደጃፋችን ቆሞ በር ሲያንኳኳ ብቻ ማለት አይደለም፣… እንደዚህ አስበን ከሆነ
ተሳስተናል፤ በዓለም ርሃብ የማንነታችን ገጽታ ሆኖ እንዲታይ ያደረገዉ በእርግጠኝነት እንድናገር በሚያስደፍረኝ መልኩ እንግዳ ተቀባይነት
ባህላችንን ባግባቡ አለመተግበራችንና ትርጉሙን ጠንቅቀን አለማወቃችን ነዉ፡፡
እንግዳ ተቀባይነታችንን ከዉጭ ለመጣ፣ ቆዳዉ ለነጣ፣ኪሱ ላበጠ ብቻ
ባይሆንና ተርቦና ተጠምቶ ከደጃችን ለሚቆመዉ ወንድማችን ብንተገብረዉ ሲራብ ብናበላዉ፣ ሲጠማ ብናጠጣዉ፣ ሲታረዝ ብናለብሰዉ በነፍሳችን
ዋጋ ከማግኘት ባሻገር የአገራችንንም ገበና ከዓለም ሚድያ ፊት ባላጋለጥንና ገመናችንን በሸፈንን ነበር፡፡
እንግዳ ብለን ተቀብለን የምንሸኘዉ ይህን ያህል ለነፍሳችን ዋጋ የሚያስከፍል፣
በደላችንን የሚያስደመስስልን ሳይሆን እንዲሁ ስላበላነዉ አብልቶ፣ ስላጠጣነዉ አጠጥቶ፣ብድር የሚመልስልን ነዉ፤ በየደጃፋችን በራችንን
የሚጠፉ ወንድሞቻችን ግን ብድራቱን ከእግዚአብሔር የሚያሰጡ እንጂ አቅም ኖሮአቸዉ ብድሩን የሚመልሱ አይደሉም፡፡ ከላይ የጠቀስናቸዉ
እንግዶች እኛን ያስደስቱን እንደሆነ እንጂ በእግዚአብሔርም ዘንድ ይሁን በማንም ዘንድ ለአገርም ቢሆን ፋይዳቸዉ እስከዚህም ነዉ፤
የተራበን ማብላት ግን ዋጋን ከማሰጠቱም አልፎ ተርፎ በሌላዉ አለም ተመጽዋች ከመሆን ይልቅ ተደጋግፈን እኛዉ በእኛዉ ክፉ ቀንን
አልፈን ወዳጅነታችን ይጠነክርና ስማችንም ይታደስ ነበር፡፡
የምፅዋት አፈፃፀሙ
ምፅዋት/መስጠት ዋጋ ያለዉ ነገር እንደሆነ ከላይ በጥቂቱም ቢሆን ያየነዉ
ነገር ሲሆን የአፈፃፀም ስርዓት እንዳለዉ ግልጽ ነዉ፤ ሥርዓቱንም ለማሳያነት አንድ ምሳሌ አንስተን እንመለከታለን፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ዮሐንስ ለጸሎት ወደ ቤተመቅደስ በሚመላለሱበት
ሰዓት ከእለታት በአንደኛዉ ቀን ከቤተክርስቲያን ደጅ ተቀምጦ ይለምን የነበረ አንድ ሰዉ ከቀኑ በዘጠነኛዉ ሰዓት ላይ አገኛቸዉ ከእነሱም
አንዳች ነገር (ምጽዋት) አገኝ እንደሆነ ብሎ ተመለከተ፤ ‹‹ ጴጥሮስ ግን …›› ይላል መጽሐፍ ጴጥሮስ ግን ለዚህ በእግዚአብሔር ደጅ ተቀምጦ ዘወትር ለሚለምን
‹የኔ ቢጤ› አንዳች ነገር ሊሰጠዉ እንደሚገባ ልቡ አመነ፡ ነገር ግን አንዳቸዉም ምንም ሊሰጡት የሚችሉት ነገር እንደሌለ አወቀ፡
እንዲህም ሲል ተናገረዉ ‹‹ ብርና ወርቅ የለኝም ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለዉ፡ …›› ቅዱስ ጴጥሮስ የሚሰጠዉ ነገር ባይኖርም
ይህ ዓይኖቹ ወደሱ ተተክለዉ የነበሩትን ዓይኖች ዝም ብሎ ምን ያፈጥብኛል ‹‹በቃ የለኝማ! የሌለዉ ሰዉ አያዉቅም እንዴ?›› በማለት
አላለፈዉም፤ ወይም ‹‹ እዚህ ቁጭ ብለህ ከምትለምን ሰርተህ አትበላም፣ እንደ ጓደኞችን ተደራጅተህ ከመንግስት ተበድረህ ለምን አትሰራም?
፣ ለምን አትሸከምም? … ›› ክፉ ቃል አልተናገረዉም፡፡ ያለዉ ሲሰጥ የሌለዉም ለምፅዋት እጁን ወደ እኛ ለሚዘረጋ በስርአት መመለስም
ከምፅዋት አይተናነስምና፤ ካለ ይሰጡታል ከሌለ ደግሞ ካለበት ያድርስህ፣ እግዚአብሔር ይስጥህ … ይሉታል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹
ያለኝን እሰጥሃለዉ፡በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለዉ፡፡›› የሐይማኖት አባቶቻችንና የእምነት አስተማሪዎቻችን
ከቅዱስ ጴጥሮስ ሊማሩት የሚገባ መንፈሳዊነት ሥነ ምግባር እንዳለ ይሰማኛል፤ ሁላችንም ብንሆን ከቅዱስ ጴጥሮስ የምንወርሰዉ ሕይወት
ነዉ ፡፡ በቃ ቅዱስ ጴጥሮስ የለዉማ ያለዉ ከእግዚአብሔር የተሰጠዉ ፀጋ ብቻ ነዉ ያለዉ፤ ይህ ሰዉም ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ አንካሳ
ስለነበር መራመድ አይችልም የዘወትር ጸሎቱ እንደ ሰዉ መራመድ አባሮ መያዝ ሮጦ ማምለጥ እለት እለት የሚመኘዉ ምኞቱ ነበር ልቡ
በደስታ ተሞላ አግባብነት ያለዉ ስጦታዉን ለመቀበል ድሃዉ ሰዉ አላቅማማም እጁን ለቅዱስ ጴጥሮስ ሰጠ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ በቀኝ
እጁም ይዞ አስነሳዉ በዚያን ጊዜም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጸና ወደ ላይ ዘሎም ቆመ ይመላለስም ጀመር …. ከእነርሱም ጋር ወደ መቅደስ
ገባ፡፡ ›› የሐዋርያት ሥራ 3፡1-8
እስኪ
ወደ እኛ እንመለስ ምጽዋት ለምንሰጣቸዉ ሰዎች እንዴት አድርገን ነዉ የምንሰጣቸዉ? ቅዱስ ጴጥሮስ እጁን ይዞ አስነሳዉ ይላል በቀኝ
እጁ በግራዉ አይደለም፤ አልተፀየፈዉም ‹‹ ከፍትፍቱ ፊቱ ›› አይደል የሚባለዉ አንዳንዴ የሚጠቅም ነገርም ቢሆን ሰጥተን አሰጣጣችን
ግን ልብ የሚሰብር ነዉ፡፡ አንዳንዴም ለምጽዋት በምንሰጠዉ ደረቅ ዳቦ ወይም የሻገተ እንጀራ ምጽዋተኛዉን ልንፈነክት ይቃጣናል፡፡
የሆነዉስ ሆነና ለማን ነዉ የምንሰጠዉ? አትታዘቡኝና አንዳንዴ በቤተክርስቲያን ደጅ ሆነዉ ለሚለምኑ ወንድሞቻችን ለምጽዋት ስንዘረጋ
ፊት የምናይበት ጊዜ አለ፤ ‹‹እከልዬ … ›› እያልን በመላመድ ያወቅናቸዉን ሰዎች ጠቀም የማድረግ፣ የማናዉቃቸዉን በማለፍ የምንመጸዉትበት
ሁኔታ አለ፡፡ ከዚህም በማለፍ ደግሞ በቤታችንም ስመ እግዚአብሔርን እየጠሩ ምጽዋት ለሚለምኑት ለአንዳንዶቹ ቆረስ አርገን ስንሰጥ
ለአንዳንዶቹ እንኳን ወደ ጉረሮ ለመግባት ወደ አፍንጫችንም ስናስጠጋዉ የሚሰነፍጥ የተበላሸ ትርፍራፊ ምግብ እንሰጣለን፡፡ ላልመሰለንም
ደግሞ አድርሰናል፤ ብለን እናባርራለን፡ ኧረ እንዲያዉም ዉሻ የሚሰድበት አለ፤ እስኪ ‹‹ እግዚአብሔር ይስጥህን ›› ማን ገደለዉ?
ከዚህም ባሻገር ደግሞ ዛሬ ዛሬ ደግሞ ምጽዋትን በሃይማኖትና፣በብሔር፣
ከፋፍለን ለመስጠት እየቃጣን ይገኛል፤ እንዲያዉም አንዳንዶቹም ተመጽዋቾች ይህ ነገር አስቀድሞ ስለገባቸዉ ሲለምኑ እንኳን በአከባቢያቸዉ
የሚታወቀዉን ጻድቅ ስም እየጠሩ መለመን አዋጭ እንደሆነ ገብቷቸዋል፡፡ አህያዉን ፈርቶ ዳዉላዉን እንደሚባለዉ ምጽዋት የፖለቲካ መቃወሚያ
እስኪመስል ድረስ በስልጣን ላይ ያሉ መሪዎችን ብሔር ያላቸዉን ወንድሞች አግባብነት በሌለዉ ቃላት ልብ ስንሰብር እንገኛለን፡፡
እኛ ክርስቲያኖች ነን የምንል እንኳን ክርስትና ገብቶን ስመ እግዚአብሔርን
ለሚጠራ ሰዉ ምጽዋት ለምንሰጥ ሰዎች አንድ እንደ ማሳሰቢያም ጭምር የሚሆን መልዕክት ላስተላልፍ እወዳለሁ፡፡አህዛብ የምንላቸዉ በእግዚአብሔር
የማያምኑ ሰወች እንኳን በሚበልጡን ሁኔታ እኛ በክርስትናዉ ሕይወት ለሌሉ ተመጽዋቾች ምጽዋት መስጠት የማንፈልግ ብዙዎች ነን! ከማያምኑትም
በበለጠ ሁኔታ የአህዛብ ስራ የምናሳይበት አጋጣሚ ቢኖር ምጽዋት ላይ ነዉ፤ ምጽዋትን ፖለቲካ አድርገነዋል፣ በዘር እየተከፋፈልንበት
እንገኛለን፣በሃይማኖት ተከፋፍለናል፣ በወንዝ ተከፋፍለናል፣…
ጌታ ለፍርድ ሲመጣ ሃጥአንን በግራ አቁሞ ተርቤ አላበላችሁኝም ሲል
የፖለቲካ ተፅዕኖ ስለነበረብኝ ነዉ ብንል ሰሚ አናገኝምና ከመንፈሳዊነት ቅኝት የወጣንና ወደ ፖለቲካዉ ዘወር ያልን ሜዳዉን እንለይ፡፡
የፖለቲካና የመንፈሳዊነት አዉድማዉ ይለያያልና መልካም ፍሬን ለመቃረም ይቻለን ዘንድ ከነዚህ መስመር ወጣ እንበል፡፡ በፖለቲካዉም
ቢሆን የተራቡትን ለማብላት በምርጫ ወቅት የደገፈዉን፣ በጦርነት ወቅት ያልተቃወመዉን፣ አሁንም አብሮት ያለዉን ብቻ መመገብ አይደለም
ስራዉ፡፡
ወንድሙ ተርቦ ዳቦ ሲለምነዉ ድንጋይ የሚሰጥ ማንም የለምና ወንድማችን
ተርቦ ከደጃችን ቆሞ ዳቦ ሲለምን ድንጋይ አናቀብለዉ፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ