ባለፈዉ በመግቢያችን ላይ
ጠላትን ስለመዉደድ አንስተን በቀጣዩ ክፍል በሰፊዉ ቀሪዎቹን እንደምንዳስስ
ተቀጣጥረን ነበር በቀጠሮአችን መሰረት እነሆ በክፍል ሁለት ተገናኘን፤
ü
ጠላትህን ዉደድ ምን ማለት ነዉ?
ደስ የሚልና ጥሩ ጥያቄ ነዉ፤ ነገር ግን እንደየሰወች አስተሳሰብ እና አተረጓጎም ይለያያል፡፡ ትንሽ ገለፃ ለማድረግ
ያህል “ ጠላት ” የሚለዉን አስቀድመን ማየት ይጠበቅብናል፡፡ጠላት
ማለት ለዚህ ምንባብ አንባቢ ልብ እንዲለዉ የሚፈለገዉ የአገር ጠላት
ማለት እንዳልሆነ ላሳስብ ወዳለሁ፡፡ስለአሸባሪዎች ማዉራት እንዳልፈለኩ አንባቢ ልብ ይለዋል፡፡ በመሰረታዊነት በፅሑፍ ለማንሳት የተፈለገዉ
ስለሰዉ ልጅ ሲሆን በማንኛዉም መንገድ አንወዳቸዉም ብለን ስለፈረጅናቸዉ ሰወች ነዉ፤እንደዚህ ዓይነት ሰወች በሁላችንም ሕይወት ዉስጥ
አሉና፡፡ የኛንም ሰላም የሚነሱን ከእግዚአብሔር ጋርም የሚያጋጩን ፤…
ü
ጠላቶቻችን እነማን ናቸዉ?
1) ምናልባት ገና ስማቸዉ ሲጠራ የሚያበሳጨን
፣ ወይንም ስማችንን ሲጠሩን ሊያመን የሚደርስ፣ በዚያም ሆነ በዚህ የነርሱ ነገር የሚያሳምመን ዓይነት ሰወች ፣ መጠኑ ይለያይ እንጂ
በነርሱ ነገር ላይ ቅሬታ ያለን ዓይነት ሰወች፤ ( እነዚህ ሰወች ፍቅረኛችን የነበሩ ሊሆኑም ይችላሉ አንድ ያልተጠበቀ አጋጣሚ ጠላት
ያሰኛቸዉ ጠላት ያደረጋቸዉ)
2) ምናልባትም የቤተሰብ አባል የሆኑና
በመካከላችን ትልቅ ቅራኔ ያለን፣ ወይንም በአንድ ወቅት በማይረባ ጉዳይ ተጋጭተን የነበርን፤
3) ምናልባትም በምናዉቃቸዉ ወይም በምንወዳቸዉ
ሰወች ላይ ከህሊናችን አልጠፋ ያለ በደል ያደረሱ ሰወች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡( ከአካል ጉዳት እስከ ያላቸዉን ግንኙነት ሊጎዳ የሚችል
ድረስ )
4) ምናልባትም መምህራኖቻችን (የፈተና
ዉጤት አበላሽተዉብን፣ የማይሆን ነገር ጠይቀዉን ፣ ዉጤት ስጡን ብለናቸዉ እምቢ ብለዉን )፣ የሥራ ባልደረቦቻችን ፣ የፍቅር ወይንም
የትዳር አጋሮቻችን፣ አለቆቻችን ወይንም አሰሪዎቻችን፣የአገር መሪዎች፤
ታዲያ እነዚህን ሰወች “ ጠላትህን ዉደድ ” ማለት ምን ማለት ነዉ?
ዉደድ ሲል በግልፅ ማስቀመጥ የምፈልገዉ ነገር የተለያዩ ፆታዎች የፍቅር ስሜት ያለበት ለማለት እንዳልተፈለገ በግልፅ
ማስቀመጥ ነዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ማያያዝ የምፈልገዉ ሌላኛዉ ነገር ልጆቻችንን፣ ወንድሞቻችንን፣ የቤተሰብ አባላቶቻችንን፣ የልብ ጓደኞቻችንን፣
… የምንወደዉ መዉደድ እንደሚለያየዉ ሁሉ ይህም ከዚያ ይለያል፡፡ (መቸስ የትዳር አጋራችንን እና የልብ ጓደኛችንን የምንወደዉ ምን
ያህል እንደሚለያይ አንባቢ ይለየዋልና ) ስለዚህ በጎ ያደረጉልንን ሰወች ፍቅር⁄መዉደድ ፣ የምናዉቃቸዉን ወይም በፍፁም የማናዉቃቸዉ
ሰወች መልካም ነገር ሲያደርጉ ስናያቸዉ የምንወዳቸዉ ፣ አለበለዚያ ለትናንሽ ህፃናት የምናሳየዉ ፍቅር፣ ይህንን መዉደድ⁄ ፍቅር
ነዉ እንግዲህ ለነዚህም ከላይ ለዘረዘርናቸዉ በደል ፈፃሚያን የምንሰጣቸዉ ፡፡
v ወሲባዊ ⁄ የፍቅር ስሜት የሌለዉ
መዉደድ ለሌላ ሰዉ ከቤተሰባችን አባል ⁄የቅርብ ጓደኞቻችን ለምንላቸዉ ⁄ ዉጭ እናደርጋለን?
v ይህንን መፈፀም ያለምንም ጥርጥር
ዋጋ አያሳጣንም ፣ ምንም አያጎድልብንም፤ እንዲሁ ለሌላዉም ቢሆን
v በእርግጠኝነት ይህንን የሚተገብሩ
ከሆነ ስለሰዉ ልጅ ያለዎት አስተሳሰብ መልካም ይሆናል ( ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን )
v ከዚህ የላቀዉ ደግሞ ይህንን ማድረግ
ላቃታቸዉ ማገዝ የበለጠ የሚደነቅ እና በሁላችንም ዉስጥ ከሰረፀ በዓለም ላይ የሰፈነዉ እልቂት ⁄ መጠፋፋት በእርግጠኝነት ይቀየራል፡፡
መሪዎች ተፎካካሪዎቻቸዉን እስር ቤት አያጉሩም ፣ ሊያጠፉ አይሯሯጡም ፣ተቃዋሚዎች ለአመፅ አይነሱም ሰይፍ አይመዙም፣ በየምክንያቱ
አይጠላለፉም ይልቅስ ተነጋግረዉ ለአገር እና ለህዝብ የሚበጀዉን ይሰራሉ እንጂ፡፡
ነገር ግን ጠላትን መዉደድ ወዳጅን የመዉደድ ያህል ቀላል ነገር ባይሆንም ያንን ስሜት ግን ማምጣት ይቻላል፤ ፀብን ፣
ጥላቻን የለመደ አብሮ አደግ ማንነታችን እንዲሁ በቀላሉ ባይቀየርም ጥረት ግን ይቀይረዋል፡፡ ስለዚህ ጠላታችንን ለመዉደድ ምን ማድረግ
አለብን ⁄ ይጠበቅብናል?