ክርስቲያን ሆንን አልሆንን፣ወደድንም ጠላንም፣በየትኛዉም
የእምነት አስተምህሮ ዉስጥ ብንሆንም በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርተ ወንጌል ዉስጥ ለማንኛዉም የሰዉ ልጅ ጥሩ
የመሆን ፍላጎት ሊሆን ከወደደ የሚገደደዉ ወይም ሊቀበለዉ ግድ የሚለዉ መሰረታዊ ነገር አለ፤ (ፀሐፊዉ ሊዮ ባኩታ በገፀ ድሩ እንዳሰፈረዉ)
ü
በአቅራቢያችን የሚገኙ ጎረቤቶችን
መዉደድ አይደለም፣
ü
የሚወዱንን ስለሚወዱን አፀፋ
ለመመለስ መዉደድ አይደለም፤ ነገር ግን
v
ጠላቶቻችንን፣ የሚጠሉንን፣ በህይወት መኖራችንን የማይፈልጉትን፣ የእኛን ማግኘት
፣የእኛን ጤና መሆን፣ ወጥቶ መግባት ፣ ሰርቶ ማግኘት ፣ ነግዶ ማትረፍ፣ ዘርቶ መቃም፣ ወልዶ መሳም፣… በጭራሽ የማይፈልጉትን መዉደድ፡፡
ይህ አባባል ፣ ይህ ድርጊት፤ የዚህ ፅሑፍ ዋና
መልዕክት ነዉ “ ጠላትህን ዉደድ ” የህይወታችንም ትልቁ ፈተና ፣ ሰዉ የመሆናችን እና የእምነታችን መለኪያዉ ነዉ፡፡
ይህ መልዕክት ትልቅነቱ ∕ ጥቅሙ ⁄ ለምን አስፈለገ?
ይልቁንም ሃይማኖተኛ ለሆነዉም ላልሆነዉም ለምን
መልዕክቱ መተላለፍ አስፈለገዉ?
( የዚህ ፅሑፍ ዋና ዓላማ የእምነት ትምህርት
ማስተማር ላይ ያዘነበለ አይደልም፤ ምንም እንኳን የሃይማኖት ትምህርት ማስተማር ችግር ባይኖረዉም እና ይልቁንም ክብር ያለዉ እና
ዋጋዉም እጅግ እጥፍ ድርብ ክፍያዉም በሰማይ የሆነ ቢሆንም ) ዋናዉ
መነሻዬ በመላዉ ዓለም እና በሁሉም የሰዉ ዘር መካከል የጠፋ ትልቅ ቁምነገር (ሀብት) ከመሆኑ የተነሳ እንጂ፡፡“ ጠላትህን መዉደድ
” እምነት ቢኖርህም ባይኖርህም ችግር የሌለዉና ልታደርገዉ የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ ነዉ፡፡ ( ነገር ግን በዓለም ላይ ትልቁ ችግር
፣ ዓለምም ያጣችዉ እና የጎደላት ጉዳይ ቢኖር ጠላትን መዉደድ ነዉ፡፡)
Ø
የሰዉ ልጅ ሰዉን የሚጠላበት
Ø
ከመጥላትችንም ባሻገር ለመጉዳዳት
የምንነሳበት
Ø
እኛንም ሊያጠቁንና ሊያጠፉን
ለሚፈልጉ
Ø
ይህ ሁሉ ሲሆን የሰዉ ልጅ
ያለሰዉ መኖር የማይችልበት ሁኔታ እያለ፤ … ( ለዚህ እኮ ነዉ የምንኖርበትን ሥፍራ ‘ በረሃ ’ ፣ ‘የማይረባ ’፣ ‘ ያለማ ‘
፣ ‘ ሰዉ በፍፁም ሊኖርበት የማይገባ ’ ወዘተ … ) ብለን የምናማርረዉ ‘ ሰዉ ’ በብዛት ስላልሰፈረበት ፣ የሰዉ ልጅ በመልክዐ
ምድራዊ አቀማመጥ ተራርቆ ስለተቀመጠ ነዉ፤ ሌላ ምክንያት የለዉም፡፡ ሰዉ ቦታን ቦታም ሰዉን ይቀድሰዋልና፤ ሰብእ ይቀድሶ ለመካን
መካን ይቀድሶ ለመካን እንዲሉ አበዉ፡፡ የአንድ ስፍራ ዉበቱም ድምቀቱም ሰዉ ነዉና ነዉ፡፡ ለዚህም ነዉ ሰወች በልማት ምክንያት
ከአንድ ስፍራ (ለዘመናት ሲኖሩ ከነበሩበት ) ተነሱ እና ሌላ ቦታ ሥፈሩ ሲባሉ እምቢኝ አሻፈረኝ ማለታቸዉ ለሰዉ እንጂ አፈሩ ስላለዉ
ልምላሜ እና በአፈሩ ዉስጥ ስላለዉ ንጥረ እና የከበረ ማዕድን አይደለም ፤ ‘የለማ’ ሲባል ሰዉ ያለበት ማለት ነዉ፡፡
“ ጠላትህን ዉደድ ” አይደለም በክርስትናዉ በሌሎችም
ቤተእምነቶች (በእስልምና ፣በቡዳህ፣ እና በሌሎችም ) ታላላቅ ማህበረሰቦች እና እምነቶች ትልቅ የትምህርታቸዉ ክፍል ነዉ፡፡ይሁን
እንጂ ይህ ትምህርት ( መልዕክት ) ይህንን ያህል ተፅዕኖ ሊያመጣ እንዳልቻለ ብዙ ምልክቶች እየታዩ ናቸዉ፡፡ ለማሳያነትም በዚህ
በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን እራሱን በዓለም ላይ አለሁ ያለ የአሸባሪ ቡድን ISIS (አይሲስ) ማየት ይቻላል፡፡ከዚህ አስተምህሮ ያፈነገጠ
አይደለም ጠላቱን ሊወድ ይቅርና ለወዳጁ የማይመለስ በሺዎች የሚቆጠሩ ነፍሳትን በሚዘገንን መልኩ የሰዋ ( ለክብር መስዋዕትነት ያበቃ፣
የተኛነዉን እኛን የእምነታችንን ጥንካሬ የፈተሸ እና ያነቃ) የሺዎችን ቤት ሃዘን እንዲያጠላበት ያደረገ ቡድን ትልቅ ማሳያ ነዉ፡፡ሌሎቹስ
ቢሆኑ? በአገራት መካከል ያለዉ ፍጥጫ፣ በዜጎች መካከል ያለዉ ሽኩቻ፣ በየቤተሰቡ ፣ በየጎረቤቱ ያለዉ አለመስማማት የምን ፍሬ ናቸዉ?
ይህ እንዲህ ከሆነ እዉነቱ እንዲህ ካፈጠጠ ይህንን
“ ጠላትህን ዉደድ ” የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ወደ ዕለት ተዕለት ትምህርት፣ ምክክር፣ ዉይይት ፣ተግባር ልናመጣዉ ግድ ይለናል፡፡ይህን
ለማስተማር ሰባኪ ወንጌል መሆን ግድ አይልም፤ ፓስተር ፣ሼክ ፣ ወይንም ሌላ መሆን አይጠበቅም ጥሩ ሰዉ ( ሰዉ ) መሆን ብቻ በቂ
ነዉ፡፡ ይህንን ተፈፃሚ ለማድረግ የሚጠላ ፣ የማይመቸዉ፣ ከዚህ ዓላማ ጎን የማይቆም ሰዉ ይኖራል? አይኖርም ብሎ መጠበቅ ምንም
እንኳን የዋህነት ቢሆንም ወደዚህ እናምጣቸዉ፤ ፈጣሪም ልቡናቸዉን እንዲያበራላቸዉ እና ጠላቶቻቸዉን እንዲወዱ እንዲያነሳሳቸዉ በትህትና
በፍፁም ፍቅር እንፀልይላቸዉ፡፡ እንደ ቀላል ነገር አንየዉ እጅግ ከባድ ነገር ነዉ ለምንቀበለዉ እንደማር እንደ ወተት የምንወደዉ
እና የሚጣፍጠን ቢሆንም የዚያኑ ያህል ደግሞ ለማይቀበሉት እና መልዕክቱ ላልገባቸዉ እንደ ሬት እንደ ኮምጣጤ ይመራቸዋልና፡፡
እስኪ ወደራሳችን እንምጣ እና የዚህ መልዕክት
አንባቢ በዚህ ሃሳብ ከተስማሙ ፣ ዓላማዉንም ከደገፉ ፣ በዚህ ሁኔታ ልብዎት ከተነካ እና ለመልዕክቱ ከተማረኩ “ ጠላትን መዉደድ
” ለሚለዉ ዓላማ የክብር አንባሳደር ይሁኑ፡፡ ድጋፍዎትን ለማሳየት ፅሑፉን በመጀመሪያ ለሌሎች ያጋሩት ፣ በመቀጠልም ከአጠገብዎት
በማንኛዉም ሰዓት ፣ሁኔታ እና አጋጣሚ የቆመዉን ፣ የተቀመጠዉን ፣ በሥራ ገበታዎ አብረዉት የሚሰሩትን፣ በትራንስፖርት ላይ አብሮት
የተሳፈረዉን፣ የቤተሰብዎን አባል ( ይልቁንም ህፃናት እነሱ ቀጥ ብለዉ ካደጉ ቀሪዉ ዓለም ቀጣዩ ዘመን የመጣመም ዕድሉ የመነመነ
ነዉና ) የዚህን መልዕክት መንፈስ ማጋራት የዕለት ተዕለት ሥራዎ ይሁን ይህንን በዕዉነት ካደረጉ
ይህ መልዕክት ዞሮ አንድ ቀን ከራሳችን ጆሮ ይደርሳል፡፡ ያኔ ስራችንን በአግባቡ መስራታችንን ልብ እንለዋለን ዋጋችንን በደስታችን
እና በእርካታችን እንወስዳለን ማለት ነዉ፡፡( እባክዎ ተግባራዊ ሲያደርጉ በጥንቃቄ እና በፍቅር ይሁን በሃይል በጭቅጭቅ አያድርጉት
ስለሚያጋጥምዎት ማንኛዉም ፈተና ትዕግሥት እና ጸሎትን ብቻ እንደ መሳሪያ ይጠቀሙ፡፡ ) ለመስጠት መሰጠት እንደሚያስፈልገዉ ሁሉ
ተናግሮ ለማሳመን የተናገሩትንም በሰዉ ልብ ዉስጥ ለማስረፅ መሰጠት ስለሚያስፈልግ በተለያየ መንገድ የማሳወቅ እና መልዕክቱን ያስተላልፉ፡፡
እኛንም ጨምሮ ትናንት ሰወች ብዙ በደሎችን በድለናል ብዙ ጥፋቶችን አዉቀንም ይሁን
ሳናዉቅ ፈፅመናል፣ ብዙ በደሎች ተፈፅሞብናል፣ በዚህ በደል ብዙዎች ለስደት ፣ ለርሃብ፣ ለበሽታ ፣ ለሞት ፣ ለእርዛት፤… ወዘተ
ተዳርገዋል፡፡ በዚህ የተነሳ በዓለም ላይ ብዙ ንቅናቄዎች ተቀስቅሰዋል፣ ብዙ ጠርነቶች ተደርገዋል(የ1ኛ እና 2ኛዉ የዓለም ጦርነተኖች፣በአገራችን
የጣሊያን ጦርነት፣ የደርግ ከሻቢያ እና ከወያኔ ጋር )፣ በጠረጴዛ ዙሪያ ሰላም ለማምጣት ድርድሮች ተካሄደዋል፡፡ በጣም በእርግጠኝነት
አንዳቸዉ “ ጠላትህን ዉደድ ” የሚለዉን አልሰበኩትም ምናልባት ክፎዎችን አዉግዘዉት ይሆናል፡፡ ዉግዘት ብቻዉን በቂ ነገር አይደለም
ለሰዎች ፍቅርን መስጠት እንጂ ከዚያም ባሻገር ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ እና ማስረፅ እንጂ፡፡ ክፉን ነገር ሳይጠሉ እና መልካም
ነገርን ሳያደርጉ ሰላምን ማምጣት አይቻልምና፡፡የሚገርመዉ አገራት ስለሰላም ሲነጋገሩ እና ለእርቅ ሲደራደሩ አስቂ ነገራቸዉ ድንበር
ላይ ጦር አሰልፈዉ የስብሰባዉ በር ላይ ከጠላት የሚጠብቃቸዉን ሰዉ አቁመዉ ነዉ፤ እንግዲህ በዚህ አይነት እንዴት ሰላም ወደ ዓለማችን
ይግባ?
ከላይ እንደጠቀስነዉ ምንም እንኳን ጠላትን መዉደድ የሚችል ልቡና እጅግ ደስ የሚያሰኝ ሲሆን የዚያኑ ያህል ምሬቱን
ሊግቱን የሚያስቡ እንዳሉ ማሰብ ሥነልቡናችንን ዝግጁ ያደርገናል፤ እንዲህ አይነት ክፉ አስተሳሰብ ያላቸዉ ሰወች የሉም ብለን ልናስብ
አይገባም፡፡በእነዚህ ሰወች ያንን ያህል ልንደነቅ አይገባም፤ ከብስል ዉስጥ ጥሬ እንዳለ ሁሉ እንዲሁ ጥሬ ሰዉም አለና፡፡ይልቅስ
የእኛን አስተሳሰብ ጤናማነት ለመለካት
“ ክፋት ” እኔ ያስደስተኛል?
የጨመረልኝስ ነገር አለ? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፡፡
አንዳንዴም ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜ ክፉ ሰወች ራሳቸዉን በሚያገኙት ነገር
ሳይሆን ወገኖቻቸዉ በሚያጡት ይደሰታሉ፤ እኛስ ምን ያህል ከዚህ አስተሳሰብ እና ድርጊት ( አኗኗር ) የጸዳን ነን? ይሄኔ ነዉ ጠላትን መዉደድ
የሚችል ልቡና ሊኖረን የሚችለዉ፤ ትልቁንም የህይወት ፈተና ማለፍ የምንችለዉ፡፡
ለመግቢያ ያህል ይህንን
ያህል ካልን በቀጣዩ ክፍል በሰፊዉ
ü
ጠላትህን
ዉደድ ምን ማለት ነዉ?
ü
ጠላቶቻችን
እነማን ናቸዉ?
ü
ጠላቴን
የምወደዉ ለምንድን ነዉ?
ü
ጠላቴን
ለመዉደድ የሚያስችለኝ ነገር ምን ላድርግ (ምን መደረግ አለበት)? የሚሉትን እና ሌሎችንም እንዳስሳለን ፤ ቸር ይግጠመን፡፡ ይቆየን፡፡
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ