ሰኞ 30 ሴፕቴምበር 2013

መስቀል ክፍል 3



ባለፈዉ በሁለት ተከታታይ ክፍል ስለ ቅዱስ መስቀል ተመልክተን በክፍል ሦስት እንደምንገናኝ ተቀጣጠረን ተለያይተን ነበር እግዚአብሔር ፈቅዶ አባቶቻችን እና ወንድሞቻችን በቃልና በመጽሐፍ ያቆዩልንን ትምህርት ሳልጨምር ሳልቀንስ ለንባብ እንዲመች በክፍል በክፍል አቅርቤላችኋለሁ፤ ክፍል ሦስት እነሆ! በክፍል አራት ያገናኘን፡፡

3ኛ. ቅድስት እሌኒና መስቀለ ክርስቶስ
ጌታችን መድሓኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ካረገ በኋላ በሐዋርያት ስብከት የወንጌሉ ፋና ለዓለም ሲበራ በዕፀ መስቀሉ ልዩ ልዩ ተአምራት ይደረጉ ነበር፡፡ አስቀድመዉ ጌታን የሰቀሉ አይሁድ አሁን ደግሞ በሰቀሉበት መስቀል ተአምራት ሲደረግ በማየታቸዉ በቅንአት መስቀሉን ከኢየሩሳሌም አጠገብ ቀብረዉ በአዋጅ ቆሻሻ በየእለቱ እንዲደፋበት አደረጉ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ሥራዉን የሚሰራበት የራሱ ጊዜ አለዉና በ327ዓ.ም. የታላቁ ንጉስ የደጉ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት እሌኒን አስነሣ፡፡ እርሷም አስቀድማ ከአረማዊዉ ንጉስ ቁንስጣ የወለደችዉ ልጅዋ ክርስቲያን ከሆነላት ከቁስጥንጥንያ ወደ ኢየሩሳሌም ተሻግራ የጌታችንን ዕፀ መስቀል ልታወጣ ብፅዐት ገብታ ነበር፡፡ በልዑል እግዚአብሔርም ፈቃድ ልጅዋ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ስለሆነላት በመስከረም 17 ቀን ቁፋሮዉን አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን አወጣችዉ፡፡
መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ለ300 ዓመታት ያህል ቆሻሻ እየተደፋ ስለተከመረበት ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ነገር ግን በወቅቱ በኢየሩሳሌም በነበረዉ አበዉ መሪነት ደመራ አስደምራ፣ ዕጣን አስጨምራ፣ ጸሎት ስታስደርግ የዕጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ መስቀሉ በተቀበረበት ቦታ ላይ ሰገደ፡፡ በጢሱ ምልክትነትም ቦታዉ ስለታወቀ ለሰባት ወራት ያህል ተራራዉ ተቆፍሮ ሊወጣ በቅቷል፡፡ ዛሬ በክርስቲያኖች ዘንድ ደመራ የሚደመረዉም ይህንኑ ለማስታወስ ነዉ፡፡
መስከረም 17 ቀን ወይም በዋዜማ፣ በዓለ መስቀሉን ስናከብር ከመስቀሉ ቀጥለን የምናስባት ቅድስት እሌኒ ናት፡፡ ቅድስት ዕሌኒ የመስቀሉ ጥበብ ተገልጾላት ክብሩና ሞገሱ በግልጽ ታይቶአት፣ መድኋኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ቅዱስ መስቀል የት ባገኘሁት እያለች ለብዙ ጊዜ ታስብና ትመኝ ነበር፡፡ በተለይም ልጄ መምለኬ እግዚአብሔር ንጉስ ቈስጠንጢኖስ፣ መክስምያኖስ ከሚባል ጠላቱ ጋር ሲዋጋ፣ …

ዓርብ 27 ሴፕቴምበር 2013

መስቀል ክፍል ሁለት

2ኛ.መስቀል ከቀራንዮ በኋላ


ብዙ ሰዎች መስቀልን የማክበራችን ምሥጢር ማወቁ ይሳናቸዋል፣ይከብዳቸዋል ፣ይፀናባቸዋል፡፡ እኛ ግን መስቀልን የምናከብረዉ ስላከበረን ነዉ፡፡ክብር ምስጋና ይግባዉና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀልን ታግሶ በደሙ ክሶ፣ በቀራንዮ ዉሎ ዓለምን ከቀደሰልን በኋላ፣ መስቀል የርግማን፣ የኋፍረትና የኋጢያት ምልክት መሆኑ ቀርቶ
መስቀል መርገመ ኦሪት የተሸረበት፣ ሰላምና ነጻነት የታወጀበት፣የኛ ድህነት ፣ የበረከትና የነፃነት አርማ፣ የወለወደ እግዚአብሔር ክርስቶስ የሰለም ዙፋን ሆኖ ዓመተ ፍዳ እና ዓመተ ኩነኔ ተሸሮ ዓመተ ምህረት የታወጀበት የነፃነት ዋስትናችን ነዉ፡፡ ለዚህም ቅዱስ ጳዉሎስ፡- «ወለነሰ ተሣየጠነ ክርስቶስ እመርገመ ለኦሪት በዘወጽአ በእንቲአነ ወጾረ መርገማ፣እኛንስ ክርስቶስ በኦሪት መርገም ዋጅቶናል፡፡ ስለኛ ሕግን በመፈጸሙና የኦሪትን መርገም በመሸከሙ፡፡» ብሏል፡፡ ገላትያ 3፡13
በነብዩ « ዉእቱ ነስኣ ደዌነ ወፆረ ሕማማነ በእንቲአነ ሓመ፣ወንሕነኒ ርኢናሁ ሕሙመ ወዉእቱሰ ቈሰለ በእንተ ኋጢአትነ ወሐመ በእንተ ጌጋይነ ፤ ትእምርተ ሰላምነ፤ ወበቁስለ ዚአሁ ሐየወነ ቁኢስለነ፡፡»
እሱ ደዌያችንን ገንዘብ አደረገ፣ ሕማማችንንም ተሸከመ ስለ እኛም ታመመ እኛ ታሞ በመከራም ተጨንቆ አየነዉ፡፡ እሱ ግን ስለ ኋጢያታችን ቈሰለ ስለበዳላችንም ታመመ፣የፍቅር የአንድነታችንም (የሰላማችንም) ምልክት እሱ ነዉ፡፡ በእሱ ቁስልም ከቁስላችን ዳንን … …፡፡ ተብሎ ተጽፎ ነበርና ትንቢት እንዲሁም ኦሪታዊ መርገመ መስቀል እንዲያከትም አምላክ ወልደ አምላክ ደዌያችንን ተሸክሞ በቀራንዮ ዋለልን፡፡ት.ኢሳይያስ53፡4-5 ዮሓንስ 19፡1-42
ቅዱስ ጳዉሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈዉ መልዕክቱ ምዕራፍ 8፡3 ላይ «ወኮነና ለይእቲ ኋጢያት በነፍሰቱ ኋጢአትን በሰዉነቱ ቀጣት፡፡»ያለዉን እንደነ ቅዱስ አትናትዎስ የመሰሉ አበዉ ሊቃዉንት ደግሞ
«ወአስተሐፈረ ኋጢአት በዲበ ምድር፤ ወአበ ጠለ ሞተ በዉስተ ሲኦል ወሰዐረ መርገመ በዲበ ዕፀ መስቀል ወነሰተ ሙስና በዉስተ መቃብር፡፡ወዘኢየሐምም ሐመ በሥጋ ሐማሚ ተዋህዶ ቃል ምስለ ሥጋ ወገብረ ዘንተ ከመይፁር ሕማመ ዚአነ ወያእትቶ እምኔነ ወየሀበነ ዘዚአሁ ሕይወተ፤ ወአዕረገ ርእሶ መሥዋዕተ በእንቲአነ»
በምድር ላይ ኋጢአትን አሰፈረ፤ በሲኦልም ሞትን አጠፋ፤በመስቀል ላይ መርገምን ሻረ፤ በመቃብር ዉስጥም ሙስና መቃብርን አጠፋ፡፡ የማይታመመዉ በሚታመምዉ ሥጋ ታመመ ቃል ከሐማሚ ሥጋ ጋር ተዋሐዶ ሕማምን ከሥጋ ያርቅ ዘንድ፣ ከእኛም ያርቀዉ ዘንድ የርሱንም ሕያወት ይሰጠን ዘንድ ይህን አደረገ፡፡ስለኛም ራሱን መሥዋእት አድርጎ አቀረበ በማለት ይገልጹታል፡፡
ሃይማኖተ አበዉ ዘቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 30፡40 ንፁሐ ባህርይ ክርስቶስ ከሥራዉ ስህተት ከአንደበቱ ሐሰት ሳይገኝበት፣ በኋጢአተኞች ዘንድ፣ ኋጥእ በደለኛ ተብሎ መስቀል ላይ ዋለ መባሉ እዉነት ነዉ፡፡ሆኖም ክርስቶስ መስቀል ላይ የዋለበት አንድ ዐብይ ምክንያት እንዳለ ግን መዘንጋት የለበትም፡፡ይኸዉም ዕዳ በደላችንን ደዌ ኋጢአታችንን ተሸክሞ በደሙ ካሣ መርገማችንን ሽሮ ከኋጢአት ባርነት ነፃ ያወጣን ዘንድ መሆኑን ነዉ፡፡ ስለዚህም፤

ሐሙስ 26 ሴፕቴምበር 2013

መስቀል

“ወአንሰ ሐሰ ሊተ ኢይዜኋር ዘእንበለ በመስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ”
“እኔስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንጂ በሌላ አልመካም፡፡ በሌላ የምመካ ከሆነስ ሐሰት ነዉ፡፡” ገላትያ 6፡14
ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኋኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በፊት መስቀል የመቅጫ መሣሪያ ነበር፡፡ሰዉን በመስቀል ላይ መቅጣት የተጀመረዉ በፋርስ ነዉ፡፡ ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ናት፤የፋርስ ሰዎች “ኦርሙዝድ” የተባለ “የመሬት አምላክ” ያመልኩ ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ “ወንጀለኛዉ” ቅጣቱን በመሬት ላይ የተቀበለ እንደሆነ አምላካችን ይረክሳል ብለዉ ስለሚያምኑ ወንጀለኛዉን ከመሬት ከፍ አድርገዉ በመስቀል ላይ ይቀጡት ነበር፡፡ ይህ ቅጣት ቀስ በቀስ በሮማ ግዛት ሁሉ የተለመደ ሆነ፡፡
ከዚህም ሌላ በኦሪት ስርዓት ቅጣታቸዉን በመስቀል ላይ የሚቀበሉ ሰወች ርጉማንና ዉጉዛን ነበሩ፡፡ይኸንንም፡- እግዚአብሔር ለሙሴ “ ማንም ሰዉ ለሞት የሚያበቃዉን ኋጠያት ቢሰራ እንዳይሞትም ቢፈረድበት በእንጨትም ላይ ብትሰቅለዉ በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነዉና ሬሳዉ በእንጨት ላይ አይደር” ሲል ነግሮታል፡፡
ኦሪት ዘዳግም 21፡22-23
እዚህ ላይ “በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሚሞት የተረገመ” ከሆነ ለምን ጌታችን መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ? እንል ይሆናል ለሁሉም ግን አባቶቻችን “ነገር ከስሩ ዉሃ ከጥሩ” ይላሉና ነገረ መስቀሉን ከሥር መሰረቱ ማየቱ የበለጠ ጠቃሚ ይሆናልና ነገረ መስቀሉን ከስር ለመቃኘት በተለይም እኛ ወጣቱ ትዉልድ ስለመስቀል መጠነኛ ግንዛቤ መጨበጥ ሊኖርብን ስለሚገባ እነሆ፡-
1ኛ. መስቀል በሥርዓተ ኦሪት
2ኛ. መስቀል ከቀራንዮ በኋላ
3ኛ. ቅድስት እሌኒና መስቀለ ክርስቶስ የሚሉትን እናያለን፡፡
1ኛ. መስቀል በሥርዓተ ኦሪት
መስቀልን በኦሪት መነፅር ስንመለከተዉ አበሳ፣ጌጋይ፣ ኩነኔ፣ መርገም፣ስቅላትና ሞት በሚሉ አስፈሪና አስደንጋጭ የአደጋ ምልክቶች ተከቦ እናየዋለን፡፡ኦሪት: “እስመ ርጉም ዉእቱ በኋበ እግዚአብሔር ዘስቁል ዲበ ዕፅ፤” በእንጨት የተሰቀለ ሰዉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነዉ ማለትዋ ለምህረትና ለይቅርታ የሚያበቃ አመለካከት ፈፅሞ እንዳልነበረበት ያመለክታል፡፡
ኦሪት “ርጉም” ያላቸዉን ለማየት ስንሞክርም ሞት የተባለዉ በደለኛ፣ዓመፀኛ፣ወንጀለኛ፣ጥፋተኛ፣ነዉረኛ፣ በሚሉት በተመሳሳይ አሳፋሪ ቃላት የሚገልፅ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ሚዛን ላይ የተገኘ በደለኛ ሰዉ እድል ፈንታዉ ሞት ብቻ ሳይሆን የሞት ሞት ነበር፡፡ ያዉም መስቀል፡፡

ዓርብ 3 ሜይ 2013

“እንሞታለን ገና” ጋዜጠኞች




            UNESCO ባወጣዉ ዘገባ አማካይነት በሳምንት አንድ ጋዜጠኛ እንደሚሞት ይፋ አድርጓል፡፡ የዚህ አንድ ጋዜጠኛ ህይወት የሚቀጠፈዉ ወይም ለመስዋዕትነት የሚቀርበዉ ለአድባር ወይም ለአምልኮ ጣዖት አይደለም፤
ለሙያዉ ክብር ሲል እንጂ፡፡ ይህ ጋዜጠኛ ሥራን ለመስራት ላይ ታች ሲል ህይወቱ በአንባገነኖች መዳፍ ዉስጥ ትወድቃለች፡፡
             በአለም አቀፉ ደረጃ የፕሬስ ነፃነት በሚከበርበት ዕለት በወጣዉ መረጃ መሰረት በፈረንጆች ዘመን አቆጣጠር ከ2006 እስከ 2012 ድረስ 502 ጋዜጠኞች የተገደሉ ሲሆን አሟሟታቸዉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡መረጃዉም ከዚህ እንደሚከተለዉ ተቀምጧል፡-
ዘመን
የሟች ቁጥር
2006
70
2007
59
2008
48
2009
77
2010
65
2011
62
2012
121
  
          ይህ ድርጊት እየተፈፀመ ያለዉ በታዳጊ አገራት እና ዲሞክራሲ ባልተስፋፋባቸዉ አገሮች ብቻ አይደለም፡ ባደጉት አገሮችና ዲሞክራሲ ጥርሱን በነቀለባቸዉም አገራት ጭምር እንጂ፤ ይህ ደግሞ ለእንደ እኛ አገር  እጅግ ትልቅ ስጋት ነዉ፡፡
           ይህ መረጃ የሚያሳየን ይህቺ ዓለም ለጋዜጠኞችና ለኢየሱስ ክርስቶስ (አንዳች ሀሰት ያልተገኘበት) እንዳልተመቸች ነዉ

ሐሙስ 2 ሜይ 2013

‹‹እንደተናገረ ተነስቷል››



የዮሐንስ ወንጌል 20

1
ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች።


2
እየሮጠችም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ወደ ሌላው ደቀ መዝሙር መጥታ። ጌታን ከመቃብር ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አናውቅም አለቻቸው።


3
ስለዚህ ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙር ወጥተው ወደ መቃብሩ ሄዱ።


4
ሁለቱም አብረው ሮጡ፤ ሌላው ደቀ መዝሙርም ከጴጥሮስ ይልቅ ፈጥኖ ወደ ፊት ሮጠና አስቀድሞ ከመቃብሩ ደረሰ፤


5
ዝቅም ብሎ ቢመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ነገር ግን አልገባም።


6
ስምዖን ጴጥሮስም ተከትሎት መጣ ወደ መቃብሩም ገባ፤ የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥


7
ደግሞም በራሱ የነበረውን ጨርቅ ለብቻው በአንድ ስፍራ ተጠምጥሞ እንደ ነበረ እንጂ ከተልባ እግሩ ልብስ ጋር ተቀምጦ እንዳልነበረ አየ።


8
በዚያን ጊዜ አስቀድሞ ወደ መቃብር የመጣውም ሌላው ደቀ መዝሙር ደግሞ ገባ፥ አየም፥ አመነም፤


9
ከሙታን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው የሚለውን የመጽሐፉን ቃል ገና አላወቁም ነበርና።


ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቤታቸው ደግሞ ሄዱ።


ማርያም ግን እያለቀሰች ከመቃብሩ በስተ ውጭ ቆማ ነበር። ስታለቅስም ወደ መቃብር ዝቅ ብላ ተመለከተች፤


ሁለት መላእክትም ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ ሥጋ ተኝቶበት በነበረው አንዱ በራስጌ ሌላውም በእግርጌ ተቀምጠው አየች።


እርሱም፦ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? አሉአት። እርስዋም፦ ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው።


ይህንም ብላ ወደ ኋላ ዘወር ስትል ኢየሱስን ቆሞ አየችው፤ ኢየሱስም እንደ ሆነ አላወቀችም።


ኢየሱስም፦ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? ማንንስ ትፈልጊያለሽ? አላት። እርስዋም የአትክልት ጠባቂ መስሎአት። ጌታ ሆይ፥ አንተ ወስደኸው እንደ ሆንህ ወዴት እንዳኖርኸው ንገረኝ እኔም እወስደዋለሁ አለችው።


ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ በዕብራይስጥ።

ማክሰኞ 30 ኤፕሪል 2013

አንድ ሠው እንሁን

አንድ ሠው እንሁን

ለቤተክርስቲያን ዋልታ ጥላ ከለለዋ፣
ለክፉ ቀን ደራሽ ጋሻ መከታዋ፡፡
እንድንሆን አንድ ቀን ብዙም ሳንዘገይ፣
ቆመን እንገኝ የወደቀውን ሳናይ፡፡
በልጆቿ መጥፋት በጣሙን ተማራ፣
ቤተክርስቲያን "ሰው ሆይ" ብላ ስትጣራ፡፡
ልጆቿ ሆይ ሥሙ አድምጧት ድምⶑን፣
አለን እማ በሉ አሰሙ ድምፃችሁን፡፡
አጋር ሲያስፈልጋት ከጎኗ የሚቆም፤
ክርስቲያን ነኝ የሚል ጠበሏን የሚጠጣ፣
መስቀሏን የሚሳለም፣
ከለላ አጥር ሲያስፈልጋት ድንበር፤
በርቀት ሳንሆን በቅርበት ከጎኗ እንኑር፡፡
ብዙ ሰው ሲያስፈልጋት ተገን፤
እኛም ለእርዳታው አንድ ሰው እንሁን፡፡
ለቤተክርስቲያን ዋልታ ጥላ ከለለዋ፣
ለክፉ ቀን ደራሽ ጋሻ መከታዋ፡፡
እንድንሆን አንድ ቀን ብዙም ሳንዘገይ፣
ቆመን እንገኝ የወደቀውን ሳናይ፡፡
በልጆቿ መጥፋት በጣሙን ተማራ፣
ቤተክርስቲያን "ሰው ሆይ" ብላ ስትጣራ፡፡
ልጆቿ ሆይ ሥሙ አድምጧት ድምⶑን፣
አለን እማ በሉ አሰሙ ድምፃችሁን፡፡
አጋር ሲያስፈልጋት ከጎኗ የሚቆም፤
ክርስቲያን ነኝ የሚል ጠበሏን የሚጠጣ፣
መስቀሏን የሚሳለም፣
ከለላ አጥር ሲያስፈልጋት ድንበር፤
በርቀት ሳንሆን በቅርበት ከጎኗ እንኑር፡፡
ብዙ ሰው ሲያስፈልጋት ተገን፤
እኛም ለእርዳታው አንድ ሰው እንሁን፡፡

ሰኞ 29 ኤፕሪል 2013

ቃለ መጠይቅ


የሰዉ ልጅ መሰረታዊ የተባሉትን አስፈላጊ ነገሮችም ሆነ የቅንጦት ነገሮች ለማሟላት ገንዘብ አስፈላጊ እንደመሆኑ መጠን ሥራን መስራት ግድ ይላል፤
ሥራ ስንል የቀን ስራ ፣ የመንግስት ስራ፣ የግል ድርጅት ስራ፣ የዓለም አቀፍ መስሪያ ቤቶች ስራ፣ ተደራጅቶ የሚሰራ ስራ፣በግል የሚሰራ ስራ፣ … ወዘተ ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡
እነዚህን ስራ ለመስራት መቀጠር ቀዳሚ ተግባር እንደሆነ የታመነ ነዉ፤ ለመቀጠር ደግሞ ሊያሟሉ የሚገባዎት መሰረታዊ ነገሮች እንዳለ ሆነዉ ዘመድ ወይም ቃለመጠይቅ ከነርሱ ዉስጥ የሚጠቀስ ነዉ፡፡ ለዛሬዉ ቃለመጠይቁን እንመለከታለን፡፡
(ለቃለመጠይቅ ፈተና እድሉን ያገኙ ተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝራቸዉ ተለጥፈዋል ሁሉም ለጀማሪ ሰራተኝነት ሳይሆን ለዉስጥ ዕድገት የሚወዳደሩ ይመስላሉ አለባበሳቸዉን ለተመለከተ ሴተም አጭር ቀሚስ ረጅም መጫሚያ ወንዱም ሙሉ ልብሱን ከነከረቫቱ ለብሷል )
(ለቃለመጠይቁ በፈታኝነት የተመደቡት ቦታ ቦታቸዉን ይዘዉ ፈተናዉን ጀምረዋል ተፈታኞችም አንድ በአንድ እየገቡ ደቂቃዎችን እያሳለፉ ሲወጡ ሲገረፉ የቆዩ ፣አቧራቸዉ ቡን ብሎ፣ላብ በላብ ሆነዉ፣ጠቋቁረዉ ይወጣሉ፤ አንዱ ተረኛ ገባ … )
ተጠያቂ፡- ገብቶ ከፈታኞች ፊት ለፊት ቆመ
ጠያቂ 1 ፡- እንካን ደህና መጣህ
ተጠያቂ፡- እንካን ደህና ቆያችሁኝ
ጠያቂ 2 ፡- ቁጭ በል
ተጠያቂ፡-አመሰግናለሁ( በማለት ወነበሩ ላይ ተቀመጠ)
ጠያቂ 1፡-ለምን መጣህ
ተጠያቂ፡- ድርጅታችሁ ባወጣዉ ማስታወቅያ መሰረት (የማስታወቅያ ቁጥሩን፣ የወጣበት ክፍል፣የሰዉ ብዛት፣ … ወዘተ ጠቅሶ) የፅሁፍ ፈተና በማለፌ ዛሬ ደግሞ ለቃለ መጠይቅ ተጋብዤ ነዉ የመጣሁት፤
ጠያቂ 1፡-(እንዳኮረፈ ሰዉ በመሆን) እስኪ ካሪኩለም ቪቴህን( CV ) አብራራልን
ተጠያቂ፡-እድሉን ስለሰጣችሁኝ በጣም አመሰግናለሁ፤ ሥሜ፡-(ሙሉ ስሙን ተናገረ)፣የትዉልድ ዘመን፡-(የተወለደበትን ዘመን ተናገረ)፣ትምህርት መቼ እንደጀመረ፣ የት እንደተማረ፣ የትምህርት ደረጃዉን በደንብ አስረዳ … …
ጠያቂ 2 ፡- በቃህ (ድምፃቸዉ የቁጣ ነበር )
ጠያቂ 3 ፡-የምትቀጠርበትን የስራ ክፍል ሥራ ተናገር
ተጠያቂ ፡- ገና አዲስ ምሩቅ እንደመሆኔ መጠን ምንም ዓይነት የስራ ልምድ ሥለሌለኝ በአሁኑ ሰዓት ሥለማላዉቀዉ ክፍል መናገር ይከብደኛል፤
ጠያቂ 1፡-ታድያ ምን ልትሰራልን ነዉ?(የቁጣ ፊታቸዉ ምንም አልተቀየረም )
ተጠያቂ ፡- ማስታወቂያ የወጣዉ በዜሮ የስራ ልምድ ስለሆነ (ብሎ እየተናገረ እያለ )
ጠያቂ 4፡-ስለርሱ አትነግረንም አሁን ይልቅስ ስለፕላኒንግ (Planning) የምታዉቀዉን ንገረን፤
ተጠያቂ ፡-የማኔጅመንት የማዕረግ ተመራቂ እንደመሆኑ መጠን በግልፅ እንግሊዝኛ አብጠርጥሮ ተናገረ፤
ጠያቂ 1፡- የት አገር ነዉ plan (ዕቅድ) እንዲህ አይነት ትርጉም ወይም ትንታኔ የኖረዉ?
ተጠያቂ ፡- (እየሆነ ያለዉ ነገር ከቁጥጥር ዉጭ ሆነበትና እርሱም ቆጣ በማለት) Planning & Plan has a big difference በማለት የሁለቱን ልዩነት ወደ ማስረዳት ገባ (አሁንም ጠያቂ 2 አቋረጡት)
ጠያቂ 3፡-እስኪ ስለ ሪፖርት ንገረን?
ተጠያቂ ፡- ያለማቋረጥ ለአምስት ደቂቃ ይክል ከተናገረ በኋላ በአጭሩ ይህን ይመስላል (ሁሉም ጠያቂዎች በጣም ተደመሙ ይህንን ሰዉ እንዴት ይጣሉት የሚፈለገዉ የሰዉ ብዛት አንድ ነዉ ማስታወቂያዉ ሲወጣ ሊቀጠር የታሰበ ሠዉ ግን ተዘጋጅቶበታል በጣም ተጨነቁ )
ጠያቂ 4፡-ጥያቄያችንን አጠናቀናል በመጨረሻ ከአንድ ደቂቃ ባለሰ የምትለን ነገር ካለ ተናገር፤
ተጠያቂ ፡- የምለዉ ነገር የለኝም ሁለት ጥያቄ ግን አለኝ፡ 1ኛ. የኛ ባልሆነ ቋንቋ ይህንን ያህል ሰዓት ፈጅተን በራሳችን የመግባብያ ቋንቋ ከአንድ ደቂቃ ባነሰ ምን ማለት ይቻላል?
2ኛ. የአገራችን የሥራ ቋንቋ አማርኛ (የአፍ መፍቻችን ነዉ) ወይንስ እንግሊዝኛ ነዉ? ጨርሻለሁ!

ሐሙስ 25 ኤፕሪል 2013

ተስፋዬ ማን ነው?


ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ተስፋዬ ማን /ምንድን/ ነው? ከወደየትስ ነው?
       እንደምን አደርክ እንደምን ዋልክ እንዳልልህ ባህሪህን መመራመር አይቻለኝም ስለጤንነቴም እንዳልነግርህ ሁሉን የምታውቅ ቸር አምላክ ነህ፤ እንዳለምንህ ሁሉን ነገር ሳይጠይቁህ በልግስና አውቀህ የምትሰጥ ነህ፡፡ ስላደረክልኝ ዋጋ እንዳልከፍልህ እንደምድራዊ ነገስታትና መኳንንት እጅ መንሻን የምትሻ አይደለህምና፣ ብቻ የባህርይ ገንዘብህ የሆነውን ምስጋና ላቅርብልህ፤ ዘወትር ከኔ ሳትርቅና ሳትለየኝ የረድኤት እጅህ ሳይታጠፍብኝ የምህረት ዓይንህ ከእኔ ሳይነቀል እንዲሁ የምትናፍቀኝ ከውኃ ጥማት ከእንጀራ ረሃብ ሁሉ የምትብስብኝ መለኪያ መጠን የሌለው ፍቅርህ የሚስበኝ አምላኬ ሆይ አስቀድመህ ሰማይና ምድርን በምድርም ላይ የሚመላለሱትን በእግር የሚሽከረከሩ፣ በልባቸው የሚሳቡ፣ በክንፋቸው የሚበሩ፣ በሰማይና በምድር ለኔ ፈጠርክ፤ እፅዋትንም ሳይቀር ከአዝርዕት ጋር እመገባቸው እገለገልባቸው ዘንድ ለእኔ አዘጋጀህ /አደረግህ/፡፡ ከዚያም ባሻገር ከሁሉ በላይ ራስህን በማዕከለ ምድር በቀራንዮ አደባባይ አይሁድ ምራቃቸውን እየተፉብህ እንደብርሃን የሚያበራ ፊትክን በጥፊ ተፀፋህ ቸርና ለጋስ እጆችህን የወንጀለኞች መቅጫ በነበረው (አሁን ግን ትምክህታችን በሆነው) መስቀል ቀኝና ግራ እጆችህን ቸነከሩህ ደረትክን በጦር ተወጋህ ደምህን አፍስሰህ ሥጋህን ቆርሰህ ለኔ ተሰዋህ፤
       ለእውራን ብርሃን ለአንካሶች መሄጃቸው ጤና ላጡ ጤናቸው ሰላም ላጡ ሰላማቸው የሆንክ ደግ አምላክ ሆይ ለእንደኔ አይነቱ ደካማ ፍጡር ብርታት የሆንክ አምላኬ ሆይ ባህሪህን ካላስቆጣሁና ካላስከፋሁህ አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ እባክህ አምላኬ ሆይ ተስፋዬ ምንድን ነው? ማንስ ነው? ከወደየትስ ነው? ብዬ ጥያቄ ሳቀርብልህ ዘወትር የማይለኝን አፅናኝ መልስህን ከምድር በማንጋጠጥ የምጠይቅህ የዘወትር ጠያቂህ /ለማኝህ/ ምዕመን ነኝ፡፡
ተፃፈ ለልዑል አምላክ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...