“ወአንሰ ሐሰ ሊተ ኢይዜኋር ዘእንበለ በመስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ”
“እኔስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንጂ በሌላ አልመካም፡፡ በሌላ የምመካ ከሆነስ ሐሰት ነዉ፡፡” ገላትያ 6፡14
ከጌታችን ከአምላካችን ከመድኋኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በፊት መስቀል የመቅጫ መሣሪያ ነበር፡፡ሰዉን በመስቀል ላይ መቅጣት የተጀመረዉ በፋርስ ነዉ፡፡ ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ናት፤የፋርስ ሰዎች “ኦርሙዝድ” የተባለ “የመሬት አምላክ” ያመልኩ ነበር፡፡ ከዚህም የተነሳ “ወንጀለኛዉ” ቅጣቱን በመሬት ላይ የተቀበለ እንደሆነ አምላካችን ይረክሳል ብለዉ ስለሚያምኑ ወንጀለኛዉን ከመሬት ከፍ አድርገዉ በመስቀል ላይ ይቀጡት ነበር፡፡ ይህ ቅጣት ቀስ በቀስ በሮማ ግዛት ሁሉ የተለመደ ሆነ፡፡
ከዚህም ሌላ በኦሪት ስርዓት ቅጣታቸዉን በመስቀል ላይ የሚቀበሉ ሰወች ርጉማንና ዉጉዛን ነበሩ፡፡ይኸንንም፡- እግዚአብሔር ለሙሴ “ ማንም ሰዉ ለሞት የሚያበቃዉን ኋጠያት ቢሰራ እንዳይሞትም ቢፈረድበት በእንጨትም ላይ ብትሰቅለዉ በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነዉና ሬሳዉ በእንጨት ላይ አይደር” ሲል ነግሮታል፡፡
ኦሪት ዘዳግም 21፡22-23
እዚህ ላይ “በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሚሞት የተረገመ” ከሆነ ለምን ጌታችን መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ? እንል ይሆናል ለሁሉም ግን አባቶቻችን “ነገር ከስሩ ዉሃ ከጥሩ” ይላሉና ነገረ መስቀሉን ከሥር መሰረቱ ማየቱ የበለጠ ጠቃሚ ይሆናልና ነገረ መስቀሉን ከስር ለመቃኘት በተለይም እኛ ወጣቱ ትዉልድ ስለመስቀል መጠነኛ ግንዛቤ መጨበጥ ሊኖርብን ስለሚገባ እነሆ፡-
1ኛ. መስቀል በሥርዓተ ኦሪት
2ኛ. መስቀል ከቀራንዮ በኋላ
3ኛ. ቅድስት እሌኒና መስቀለ ክርስቶስ የሚሉትን እናያለን፡፡
1ኛ. መስቀል በሥርዓተ ኦሪት
መስቀልን በኦሪት መነፅር ስንመለከተዉ አበሳ፣ጌጋይ፣ ኩነኔ፣ መርገም፣ስቅላትና ሞት በሚሉ አስፈሪና አስደንጋጭ የአደጋ ምልክቶች ተከቦ እናየዋለን፡፡ኦሪት: “እስመ ርጉም ዉእቱ በኋበ እግዚአብሔር ዘስቁል ዲበ ዕፅ፤” በእንጨት የተሰቀለ ሰዉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነዉ ማለትዋ ለምህረትና ለይቅርታ የሚያበቃ አመለካከት ፈፅሞ እንዳልነበረበት ያመለክታል፡፡
ኦሪት “ርጉም” ያላቸዉን ለማየት ስንሞክርም ሞት የተባለዉ በደለኛ፣ዓመፀኛ፣ወንጀለኛ፣ጥፋተኛ፣ነዉረኛ፣ በሚሉት በተመሳሳይ አሳፋሪ ቃላት የሚገልፅ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ሚዛን ላይ የተገኘ በደለኛ ሰዉ እድል ፈንታዉ ሞት ብቻ ሳይሆን የሞት ሞት ነበር፡፡ ያዉም መስቀል፡፡
ኦሪት ርጉም ያለችዉን የሚቀጣባቸዉ የመስቀል ዓይነቶች ልዩ ልዩ ቅርፅ ያላቸዉ ብዙ እንደሆኑ የሚገመት ቢሆንም እስከአሁን ድረስ የሚታወቁትን ግን ሦስት ናቸዉ አራተኛዉ ደግሞ ዛፍ ነዉ፡፡ እነዚህ ሦስት ዓይነቶች ፡-1ኛ. ተ 2ኛ. ፐ 3ኛ.x የመሰለ ቅርፅ እንደነበራቸዉ ተጽፎአል፡፡
በሶስተኛዉ ተራ ቁጥር የተገለፀዉ የመስቀል ቅርፅ መስቀል ቅዱስ እንድሪያስ በመባል የሚታወቅ ሆኖ በሁለተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰዉ የመስቀል ቅርፅ ደግሞ የላቲን መስቀል በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት መድኋኒዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል የላቲኑ መስቀል መሆኑን በብዙ አርቲስቶች የተደገፈ ጥናታዊ አባባል ነዉ፡፡ አራተኛዉ የመስቀል ዓይነት ግን ማንኛዉም ለአፈፃፀም ምቹ የሆነ ዛፍ እንደሆነ በመፅሐፍ ቅዱስ ተፅፏል፡፡ አስቴር 2፡21-23
በመስቀል እንዲሞት የተፈረደበት ሰዉ እጅ እግሩን በማሰር ወይም አሰቃቂና አስፈሪ በሆነ ችንካር በመቸንከር እኔን ያየህ ተቀጣ ለማሰኘት በሚፈፀም አስፈሪ የቅጣት ዓይነት ይቀጣ ነበር፡፡ በዚህ መሰረት ታላቁ እስክንድር ከአንድ ሺህ በላይ ብዛት ያላቸዉ ሰዎችን በስቅላት እንዲቀጣና አይሁድ በባቢሎን በባርነት በነበሩበት ዘመንም በስቅላት ይቀጡ እንደነበር ዮሲፎስ የተባለ ዕዉቅ የታሪክ ፀሓፊ ዮሴፍ ወልደኮሪያ ጽፏል፡፡
የፋርስ ንጉስ ዳርዮስም ትዕዛዙን የሚተላለፍን ሰዉ በስቅላት ሲቀጣ መኖሩን ለማስገንዘብ፣ …. …. ይህንም ትእዛዝ የሚለዉጥ ሁሉ ምሰሶዉ ከቤቱ ተነቅሎ እርሱ ይሰቀልበታል፡፡ ቤቱም የጉድፍ መጣያ ይደረግ ብዬ አዝዣለሁ፡፡ በማለት ያስተላለፈዉ አዋጅ በመፅሃፍ ዕዝራ ተፅፎ ይገኛል፡፡ ዕዝራ 6፡11
መስቀል ወዲያዉኑ እየተሰራ በደለኛዉ እንዲስቀልበት ከማድረግ ይልቅ በአብዛኛዉ ጊዜ ተዘጋጅቶ ይቀመጥ እንደነበር መገመት የሚያስችል ፅሑፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎአል፤ ለምሳሌ ጨካኙና ተንኮለኛዉ ሐማ የተሰቀለበት መስቀል ራሱ ለመርዶክዮስ መሰቀያ ይሆናል ተብሎ የተዘጋጀዉ ላይ እንደነበር እንገነዘባለን፡፡ መጽሐፈ አስቴር 7፡6-10
እዚህ ላይ ግን ባለ አራቱ ዕብራዊና ባለጣኦቱ አረማዊ የመስቀልን ሕግ እኩል ተግባራዊ ሲያደርጉ ስንመለከት የመስቀልን ታሪካዊ መነሻና ምንጭ ኦሪት ነበረች ከማለት ይልቅ ፣ በእህዛብ ዘንድም ቀደም ብሎ የተለመደ ማህበራዊ ሥርዓት ወይም ፖለቲካዊ ሕግ ሆኖ ሲሰራበትየኖረ ነበረ፤ማለቱ የቀለለ ሆኖ እናየዋለን፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አይሁዳዊም ሆነ አረማዊ ለሞት የሚያበቃዉን በደል ፈጽሞ ሲገኝ በመስቀል የመቀጣቱ ነገር አማራጭ ያልነበረዉ ጉዳይ ሆኖ እያለ፣ ሮማዊዉ ዜጋ ግን ምንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም እንዃ፣ በመስቀል እንዳይቀጣ ሮማዊቷ ህግ ነፃ አዉጥታዋለችና በመስቀል አይቀጣም፡፡በሮማ ግዛት በስቅላት እንዲቀጣ የሚፈረድበት ሰዉ ፣ሮማዊ ዜግነት የሌለዉ በሮማ ግዛት ክልል ሮማዊዉን ከበርቴ እያገለገለ በባርነት የሚኖር ኢ-ሮማዊ ዜጋ ብቻ ነበር፡፡
እንግዲህ ኦሪት «በእንጨት የተሰቀለ ሰዉ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነዉ፡፡» ብላ ነበርና መስቀል እስከ ሞተ ክርስቶስ ድረስ የመርገም፣የበደል፣የነዉርና የርኩሰት ምልክት፣ሟቹ የሚረክስበት፣የሟቹ ወገንም የሚያፈርበት ነበር ማለት ነዉ፡፡
2ኛ.መስቀል ከቀራንዮ በኋላ
ብዙ ሰዎች መስቀልን የማክበራችን ምሥጢር ማወቁ ይሳናቸዋል፣ይከብዳቸዋል ፣ይፀናባቸዋል፡፡ እኛ ግን መስቀልን የምናከብረዉ ስላከበረን ነዉ፡፡ክብር ምስጋና ይግባዉና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀልን ታግሶ በደሙ ክሶ፣ በቀራንዮ ዉሎ ዓለምን ከቀደሰልን በኋላ፣ መስቀል የርግማን፣ የኋፍረትና የኋጢያት ምልክት መሆኑ ቀርቶ መስቀል መርገመ ኦሪት የተሸረበት፣ ሰላምና ነጻነት የታወጀበት፣የኛ ድህነት ፣ የበረከትና የነፃነት አርማ፣ የወለወደ እግዚአብሔር ክርስቶስ የሰለም ዙፋን ሆኖ ዓመተ ፍዳ እና ዓመተ ኩነኔ ተሸሮ ዓመተ ምህረት የታወጀበት የነፃነት ዋስትናችን ነዉ፡፡ ለዚህም ቅዱስ ጳዉሎስ፡- «ወለነሰ ተሣየጠነ ክርስቶስ እመርገመ ለኦሪት በዘወጽአ በእንቲአነ ወጾረ መርገማ፣እኛንስ ክርስቶስ በኦሪት መርገም ዋጅቶናል፡፡ ስለኛ ሕግን በመፈጸሙና የኦሪትን መርገም በመሸከሙ፡፡» ብሏል፡፡ ገላትያ 3፡13
እንቀጥላለን!

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ