2ኛ.መስቀል ከቀራንዮ በኋላ
ብዙ ሰዎች መስቀልን የማክበራችን ምሥጢር ማወቁ ይሳናቸዋል፣ይከብዳቸዋል ፣ይፀናባቸዋል፡፡ እኛ ግን መስቀልን የምናከብረዉ ስላከበረን ነዉ፡፡ክብር ምስጋና ይግባዉና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀልን ታግሶ በደሙ ክሶ፣ በቀራንዮ ዉሎ ዓለምን ከቀደሰልን በኋላ፣ መስቀል የርግማን፣ የኋፍረትና የኋጢያት ምልክት መሆኑ ቀርቶ
መስቀል መርገመ ኦሪት የተሸረበት፣ ሰላምና ነጻነት የታወጀበት፣የኛ ድህነት ፣ የበረከትና የነፃነት አርማ፣ የወለወደ እግዚአብሔር ክርስቶስ የሰለም ዙፋን ሆኖ ዓመተ ፍዳ እና ዓመተ ኩነኔ ተሸሮ ዓመተ ምህረት የታወጀበት የነፃነት ዋስትናችን ነዉ፡፡ ለዚህም ቅዱስ ጳዉሎስ፡- «ወለነሰ ተሣየጠነ ክርስቶስ እመርገመ ለኦሪት በዘወጽአ በእንቲአነ ወጾረ መርገማ፣እኛንስ ክርስቶስ በኦሪት መርገም ዋጅቶናል፡፡ ስለኛ ሕግን በመፈጸሙና የኦሪትን መርገም በመሸከሙ፡፡» ብሏል፡፡ ገላትያ 3፡13
በነብዩ « ዉእቱ ነስኣ ደዌነ ወፆረ ሕማማነ በእንቲአነ ሓመ፣ወንሕነኒ ርኢናሁ ሕሙመ ወዉእቱሰ ቈሰለ በእንተ ኋጢአትነ ወሐመ በእንተ ጌጋይነ ፤ ትእምርተ ሰላምነ፤ ወበቁስለ ዚአሁ ሐየወነ ቁኢስለነ፡፡»
እሱ ደዌያችንን ገንዘብ አደረገ፣ ሕማማችንንም ተሸከመ ስለ እኛም ታመመ እኛ ታሞ በመከራም ተጨንቆ አየነዉ፡፡ እሱ ግን ስለ ኋጢያታችን ቈሰለ ስለበዳላችንም ታመመ፣የፍቅር የአንድነታችንም (የሰላማችንም) ምልክት እሱ ነዉ፡፡ በእሱ ቁስልም ከቁስላችን ዳንን … …፡፡ ተብሎ ተጽፎ ነበርና ትንቢት እንዲሁም ኦሪታዊ መርገመ መስቀል እንዲያከትም አምላክ ወልደ አምላክ ደዌያችንን ተሸክሞ በቀራንዮ ዋለልን፡፡ት.ኢሳይያስ53፡4-5 ዮሓንስ 19፡1-42
ቅዱስ ጳዉሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈዉ መልዕክቱ ምዕራፍ 8፡3 ላይ «ወኮነና ለይእቲ ኋጢያት በነፍሰቱ ኋጢአትን በሰዉነቱ ቀጣት፡፡»ያለዉን እንደነ ቅዱስ አትናትዎስ የመሰሉ አበዉ ሊቃዉንት ደግሞ
«ወአስተሐፈረ ኋጢአት በዲበ ምድር፤ ወአበ ጠለ ሞተ በዉስተ ሲኦል ወሰዐረ መርገመ በዲበ ዕፀ መስቀል ወነሰተ ሙስና በዉስተ መቃብር፡፡ወዘኢየሐምም ሐመ በሥጋ ሐማሚ ተዋህዶ ቃል ምስለ ሥጋ ወገብረ ዘንተ ከመይፁር ሕማመ ዚአነ ወያእትቶ እምኔነ ወየሀበነ ዘዚአሁ ሕይወተ፤ ወአዕረገ ርእሶ መሥዋዕተ በእንቲአነ»
በምድር ላይ ኋጢአትን አሰፈረ፤ በሲኦልም ሞትን አጠፋ፤በመስቀል ላይ መርገምን ሻረ፤ በመቃብር ዉስጥም ሙስና መቃብርን አጠፋ፡፡ የማይታመመዉ በሚታመምዉ ሥጋ ታመመ ቃል ከሐማሚ ሥጋ ጋር ተዋሐዶ ሕማምን ከሥጋ ያርቅ ዘንድ፣ ከእኛም ያርቀዉ ዘንድ የርሱንም ሕያወት ይሰጠን ዘንድ ይህን አደረገ፡፡ስለኛም ራሱን መሥዋእት አድርጎ አቀረበ በማለት ይገልጹታል፡፡
ሃይማኖተ አበዉ ዘቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 30፡40 ንፁሐ ባህርይ ክርስቶስ ከሥራዉ ስህተት ከአንደበቱ ሐሰት ሳይገኝበት፣ በኋጢአተኞች ዘንድ፣ ኋጥእ በደለኛ ተብሎ መስቀል ላይ ዋለ መባሉ እዉነት ነዉ፡፡ሆኖም ክርስቶስ መስቀል ላይ የዋለበት አንድ ዐብይ ምክንያት እንዳለ ግን መዘንጋት የለበትም፡፡ይኸዉም ዕዳ በደላችንን ደዌ ኋጢአታችንን ተሸክሞ በደሙ ካሣ መርገማችንን ሽሮ ከኋጢአት ባርነት ነፃ ያወጣን ዘንድ መሆኑን ነዉ፡፡ ስለዚህም፤
«እስመ ዘኢየአምር ኋጢአተ ረስየ ርእሰ ኀጥአ ከመ ኪያነ ያጽ ድቀነ»
«ለእግዚአብሔር ኋጢአት የሌለበት ንጹሐ ባህርይ ክርስቶስ እሱ እኛን የእግዚአብሔር ማደሪያ ለመሆን ያበቃንና ያከብረን ዘንድ፣ ራሱን እንደ በደለኛ አድርጎ በመስቀል ላይ ዋለ፡፡» ተብሎ እንደ ተጽፎአል፡፡ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21
መስቀል ብርሃናችንና የቤተክርስትያናችን መሠረት ነዉ፡፡ለዚህም ታላቁ አባት ቅዱስ ያሬድ «መስቀል ብርሃን ለኩሉ ዓለም መሠረተ ቤተክርስትያን፡፡» በማለት መስቀል በጨለማ ግርዶሽ ይኖር ለነበረ ዓለም ሁሉ ብርሃን፣ ለቤተክርስቲያንም መሠረት መሆኑን አስተምሮናል፡፡
የሰዉ ልጅ በ5ሺ5መቶ የታሪክ ዘመኑ፣ሞት በላዩ ላይ ሰልጥኖበት የዲያቢሎስ የባርነት ቀንበር ተጭኖት ለችግሩ መፍትሔ ለሕመሙ መድኋኒት አጥቶ ዘመነ ፍዳዉን በመቁጠር ሲባዝን ከኖረበት በኋላ የእግዚአብሔር የይቅርታና የምህረት ቀን (እለተ አድኀኖ) በደረሰ ጊዜ ግን ሰላሙንና ነፃነቱን ያገኘዉ በመስቀል ነዉ፡፡
በዚህ መሰረት መስቀል ነፃነታችን ነዉና እናከብረዋለን፡፡
«እስመ ክርስቶስኒ ምዕረ ሞተ በእንተ ኋጣዉአ ሰብዕ፡፡ ክርስቶስ ስለ ሰዉ ኋጢአት ጊዜ ሞቶአል፤ ኋጢአት የሌለበት ክርስቶስ ስለኛ ሞተ፡፡ … ነፍሳቸዉ ታስራ ወደ ነበረችበት ሄዶ ነፃነትን ሰበከላቸዉ፡፡» እንዳለ መጽሃፍ 2ኛ ጴጥሮስ 3፡18-19፤ 2፡24 አዎ! እኛ መክፈል የማንችለዉ ካሣ ተከፍሎልን ዕርቅ ያገኘነዉ በመስቀል ነዉ፡፡
«ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ ለዘበሰማይ ወለዘ በምድር» ተሰቅሎ ባፈሰሰዉ ደሙ በሰማይ ያሉ መላዕክትንና በምድር ያለን እኛን አስታርቆ ሰላሙን ሰጠን እንዲል፡፡ ቈላስያስ2፡20
መስቀል ሰላማችንና ነፃነታችን ብቻ ሳይሆን ክብራችንም ቅድስናችንም ነዉ፤ በመስቀሉ ተቀድሰናል፣ በመስቀሉ ከብረናል፡፡
«ወበእንተዝ ኢየሱስኒ ከመ ይቀድሶሙ ለሕዝብ በደመ መስቀሉ በአፍኣ እምትዕይንት ተቀትለ»
ሕዝቡን በደመ መስቀሉያከብራቸዉ ይቀድሳቸዉ ዘንድ ከከተማ በአፍኣ (በዉጭ) ተሰቀለ፡፡ እንዲሁም ከሆነ እሱ የተቀበለዉን መከራ መስቀል እየተቀበልን ከዚህ ዓለም ልዩ ሆነን፤ እሱ ወዳለበት እንገሥግሥ፡፡ ዕብራዉያን 13፡12-13 ካለ መስቀሉ ሰላም ፣ ካለ መስቀሉ እርቅና አንድነት፣ ካለ መስቀል ፍቅርና ሰላም አልተገኘምና፣ መስቀል ክብራችን ነዉ የምንለዉ ለዚህ ነዉ፡፡ አካላዊ ቃል እግዚአብሐየር ወልድ በሥጋዉ ክሶ ኋጢአትን ደምስሶ ዲያቢሎስን ድል ነስቶ የቸርነት ሥራዉን
በመስራት የሰዉን በደል ይቅር ብሎ ሰዉን ከአምላክነቱ ያስታረቀ፣ ሰማያዉያንንና ምድራዊያንን አንድ ያደረገ አስታራቂያችን እሱ ነዉ፡፡
«እስመ ዉእቱ ሰላምነ ዘረሰዮሙ አሐደ ለክሌሆሙ፡፡» ኤፌሶን 2፡13-17 ቈላስያስ1፡20
መስቀል ተስፋችንና ምርኩዛችን መሆኑንም ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ በማለት ይገልፃል፡- «ተስፋየ እምን እሰየ ምርጉዝ ለርስዐንየ ዝንቱ ዉእቱ መስቀል» ከህፃንነቴ (ከታናሽነቴ) ጀምሮ ተስፋዬና አለኝታዬ በሽምግልናዬ ወይም በድካሜ ጊዜም ምርኩዜ ይኸዉ መስቀል ነዉ፡፡ ዋዜማ ዘመጋቢት መስቀል፡፡
ለሰዉ ልጅ ክብርና መመኪያ ከመስቀል የበለጠ ሌላ ነገር አለመገኘቱን በግልፅ የተረዳ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስም « ወአንሰ ሐሰ ሊተ ይዜኋር ዘእንበለ በመስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአነ፡» እኔስ በጌታችን በኢየሱስ ክረስቶስ መስቀል እንጂ በሌላ አልመካም፤ ሌላ መመኪያ አለኝ ብል ሐሰት ነዉ፡፡ በማለት ክብረ መስቀልን በሚገባ ያስገነዝባል፡፡ ገላትያ 6፡14
የመስቀሉ ነገር ሰላም፣ነፃነት፣ዕርቅና ድህነት ሆኖ እያለ ግን አንዳንድ ሰዎች የመስቀሉ ጠላቶች ሆነዉ መታየታቸዉ አስገራሚ ነገር ነዉ፡፡ በእርግጥ የመስቀሉ ምሥጢር አይታያቸዉምና ስንፍና ይመስላቸዉ ይሆናል፤ ያላዋቂ ትችትም ለመሰንዘር ይሞክራሉ፤ እኛ ትርጉሙን ሳናዉቅ መስቀልን እንደምናከብረዉ መስሎ ይታያቸዋል፤ ይህ የተሳሳተ ግምታቸዉና አመለካከታቸዉም መስቀሉን እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ለዚህም የመስቀሉ መሰረታዊ ጠላት የሆነ ዲያቢሎስ መስቀሉን እንዲጥሉ ያደርጋቸዉ ዘንድ ግዴታ ስለሆነ ነዉ፡፡ ዳሩ ግን በፊልጲስዩስ 3፡18-19
« ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነዉ ይነሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለነሱ እላችኋለሁ፤ አሁንም እንዃ እያለቀስሁ እላለሁ፡፡ መጨረሻቸዉ ጥፋት ነዉ፡፡ ሆዳቸዉ አምላካቸዉ ነዉ፤ ክብራቸዉ ነዉ፤ አሳባቸዉ ምድራዊ ነዉ፡፡ » ተብሎ ተፅፎአልና ጣላቻዉ የማይቀር ቢሆንም መስቀሉን መግፋት ግን ዉጤቱ ምን እንደሚሆን ማስተዋሉ ጠቃሚ ይሆናል፡፡
መስቀሉ ኋይላችን መድኋኒታችን ክብራችን ጸጋችንና በረከታችን ነዉና መስቀሉን እናከብረዋለን፤ በመስቀሉ ኋይለ አጋንንትን፣ ፀብአ አጋንንትን ድል እንነሳበታለን፤ መስቀሉን ስንሰብክ የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፤መስቀሉን ስናከብር የተሰቀለዉን ክርስቶስን እናከብራለን፡፡
« እስመ ነገረ መስቀሉሰ እበድ ዉእቱ በኀበ ሕጉላን፤ ወበኀቤነሰ ለእለ ድኀነ ኋይለ እግዚአብሔር ዉእቱ፡፡»
የመስቀሉ ነገርስ በጥፋተኞች ዘንድ ስንፍና ነዉ፤ ለእኛ ለዳነዉ ግን የእግዚአብሔር ኋይል ነዉ፡፡ … መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉና፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፤ « ወንህነሰ ንሰብክ ክርስቶስሃ ዘተሰቅለ » እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 1፡18-24
3ኛ. ቅድስት እሌኒና መስቀለ ክርስቶስ
በቀጣዩ እንዳስሰዋለን!

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ