ማክሰኞ 31 ዲሴምበር 2019

"ዳንኤልን" እንኳን ሰው ሠይጣንም ይፈራዋል ( ክፍል አንድ )

"ዳንኤልን" እንኳን ሰው ሠይጣንም ይፈራዋል
12 ምእራፍ እያንዳንዳቸው ትንሹ 13 ቁጥር ሲኖረው ትልቁ 49 ቁጥር አለው። በአማካይ አንድ ምእራፍ 30 ቁጥር ይኖረዋል።
የመጽሐፉ ክፍል "የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በነገሠ በሶስተኛው አመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት።" ብሎ ይጀምርና። " አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ አንተም ታርፋለህ: በቀኑም መጨረሻ በእጣ ክፍልህ ትቆማለህ።" በማለት ይዘጋዋል።
የሥሙ ትርጓሜ " እግዚአብሔር ፈራጅ ነው " ማለት ሲሆን የተረጎማቸው ሕልሞችና ያያቸውን ራእዮች ብዙ ምሥጢር ያለባቸው ከመሆኑ የተነሣ ብዙዎች አይስማሙበትም።
አላማው እኔ ልግነን፣ ልታወቅ፣ ብዙ ተከታዮች ይኑሩኝ፣ አድናቆትን ላትርፍ፣ ወዘተ ... አይደለም። እግዚአብሔር እና ሕዝቡ እንደሚያሸንፍ ለመግለጥ እንጂ።
የመጽሐፉ ክፍሎች በአሥር የተከፈሉ ሲሆኑ በአብዛኛው የሚያወሩት ስለ ምርኮ፣ ሕልም፣ ትርጉም፣ አራት መንግሥት፣ ጦርነት፣ ስለ እግዚአብሔርም ሕዝብ መከራ ... ወዘተ ነው።
"ዳንኤልን" እንኳን ሰው ሠይጣንም ይፈራዋል::
በይፋ ተጀመረ።
ይቆየን።

ከትናንት እስከ ዛሬ …

በነገራችን ላይ   ከ ፈረንጆቹ Thursday, March 22, 2012 እስከ ዛሬይቱ ቀን ድረስ ………. 


https://deressereta.blogspot.com/

የደረሰ ረታ እይታዎች የፀሐፊዉ ያላሰለሰ ስንፍና እንዳለ ሆኖ በአገራት ኢትዮጵያና አሜሪካ እንደ ቅደም ተከተላቸዉ ብዙ አንባቢያን ያሉበት ሲሆን በመቀጠል ኬንያ፣ ሩሲያ እና ኢንዶኔዥያ ከ1 እስከ 3 ያለዉን ተራ ይይዛሉ፡፡
ከሚለጠፉት ፅሑፎች ደግሞ ትልቁን የቀዳሚነት ድርሻ የያዘዉ ፍቅር በፌስቡክ ክፍል ሁለት ሲሆን አጋጣሚ ክፍል አራት እና ለመጪዉ ትዉልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም የሚሉት ሁለተኛ እና ሶስተኝነትን ይይዛሉ፤ እኔን በስነ ፅሑፍ ዘመኔ እጅግ ዋጋ ያስከፈለኝ እና በወቅቱ ከ1500 በላይ ኢ-ሜይል የተቀበልኩበት እና አንባቢ ያገኘዉ ብዙ ጊዜም ሲመራ የቆየዉ ዋጋ የሚያስከፍሉ ጥፋቶች

ሰኞ 16 ዲሴምበር 2019

የጊዜ አጠቃቀም


የጊዜ አጠቃቀም


መግቢያ

ስኬታማ የጊዜ አጠቃቀም ያዳበረ ሰራተኛም ሆነ ግለሰብ ጊዜዉን በመርሃግብር እና በዕቅድ ይመራል፤ ይህ ሰዉ ህይወቱን የሚመራዉ በዕድል ሳይሆን ራሱ ነዉ፡፡ ስለዚህ ይህንን ዶክመንት ማዘጋጀት ግድ ሆኗል፡፡

ጊዜ -

በቀን 24 ሰዓት

በሳምንት 7 ቀን

በወር 30 ቀን

በዓመት 52 ሳምንት/ 365 ቀናት/ ብለን የምንጠራዉ ማለት ነዉ፤

ጊዜ ከሁሉ ነገር በላይ እጅግ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ በተበላሸ ሁኔታ የምንጠቀምበት ነገር ነዉ፤

ዊሊያም ፔን

                                    ዓላማ -

v የተቋማትን ፣አልያም የአገራችንን፣ ከዚያም አልፎ የየራሳችንን፣ ወዘተ … “የተለጠጠእቅድ ለማሳካት ዋነኛ ሃብት ጊዜ በመሆኑ ጊዜያችንን በመጠቀም ዉጤትን እንድናመጣ ግብን እንድናሳካ ግንዛቤ ለመፍጠር ነዉ፡፡


 የጊዜ አስፈላጊነት (ጥቅም)


Ø  ለመዉጣት ለመግባታችን የምንጠቀምበት

Ø  በመዉጣት በመግባታችን ዉስጥ የምናከናዉናቸዉን ነገሮች የምንፈፅምበት መሣሪያ

የአንድ ዓመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀዉ

 የአንድን ሰዓት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸዉ

የአንድን ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ አዉቶቡስ ለትንሽ ያመለጠዉን ሰዉ ጠይቀዉ

v  ያለ በቂ ምክንያት፣ ከአቅማችን በታች በሆነ ጉዳይ ከሥራ ላይ የቀረንባቸዉ ቀናት ምን ያህል ግባችን ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠሩ እንመልከት፤

የአንድን ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰዉ ጠይቀዉ

ረቡዕ 31 ጁላይ 2019

ስኬት/Success/


ስኬታማ መሆን ይፈልጋሉ?
Believe That Success Is Your Birth Right
የስኬት ህጎች
መጀመሪያ ሊያዉቋቸዉ የሚገባዎትን ጠንቅቀዉ ሳያዉቁ ስኬታማ ለመሆን አስበዉ ያዉቃሉ?
ስለስኬት ህጎች ሳያዉቁ ስኬታማነትን ማሰብ ፡- ስለማሽከርከር ህግ ሳያዉቁ እና የመንገድ ደህንነት ህጎችን ሳይረዱ መኪና እንደማሽከርከር ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ስኬት የምርጫ ጉዳይ እንጂ በሌላ ሰዉ የሚጫኑት አይደለም፡፡
የስኬትን ህግ ካወቁና ከተገበሩ ስኬታማነትን ባይፈልጉ እንኳን የተሳካለት ሰዉ ነዎት፡፡ የተለያዩ የሰዉን ልጅ ለስኬት የሚያበቁ ክንዉኖች አሉ የእርስዎ ስኬት የትኛዉ እንዲሆን ይፈልጋሉ?
Ø  ሃብት ፡- የገንዘብ ብዛት ከአስተሳስብ ድኅነት አያድንምና የእርስዎ ሃብት ምን እንዲሆን ይሻሉ?
Ø  ዕዉቀት፡- ወደ ተግባር የማይለወጥ ዕዉቀት የጋን ዉስጥ መብራት ነዉና የእርስዎ እዉቀት ለርስዎ እና በዙሪያዎ ላለዉ ምንድን አደረገ?
Ø  ጥበብ፡- ጥበብን መፈለግ እንቁን ከመፈለግ በእጥፍ ይሻላል እርስዎ ጥበብን ለመፈለግ ምን ያህል ዋጋ ይከፍላሉ?
Ø  ትዳር/ቤተሰብ፡- ቤተሰብ የአገር መሰረት ነዉና ትዳሮትን ምንድን ላይ ነዉ የመሰረቱት አለት ላይ ወይንስ አሸዋ ላይ?
Ø  ስራ፡- ዕለት ተዕለት ጥሮ ግሮ የሰዉ ልጅ ህይወቱን እንዲመራ የአምላክ ትዕዛዝ ነዉ እርስዎ ስራዎን ሲሰሩ ዉጤታማ ለመሆን ነዉ ስራዎን ለማጠናቀቅ ብቻ ነዉ የሚሰሩት …
Ø  ወዘተ …

1.    የመፈለግ ህግ
"አንድን ነገር እጅግ ጠንካራ በሆነ ፍላጎት ከፈለጉት እንደሚያገኙት አይጠራጠሩ ፤"
Ø   ንካራ ፍላጎት የስኬት መነሻ ሲሆን እንዲሁም ግብን ያሳያል አንድ ሰዉ ጠንካራ ፍላጎት ካለዉ በልቡ የሞላዉን ፍላጎቱን ለማሳካት ይጥራል፤ ያሳካዋልም፡፡
Ø  ንካራ ፍላጎት ነገሮችን በድል ለመስራት ትልቅ ሃይል ነዉ፤ (እኤአ 2000 ላይ ኃይሌ ገብረ ስላሴ በሲዲኒ ኦሎምፒክ ህመሙን ታግሶ አንደኛ በመዉጣት ያሸነፈዉ ፖልቴርጋት ቀሽም ስለሆነ ወይንም ተወዳዳሪ ስላልነበረ ሳይሆን ኃይሌ የማሸነፍ ጠንካራ ፍላጎት ስለነበረዉ ነዉ፡፡ለኃይሌ መሸነፍ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ አማራጭ አልነበረም / አይደለምም) ፤ ለጊዜዉ ስሙን የማላስታዉሰው የጦር ጀነራል የነበረ አንድ ሰዉም የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ተልዕኮዉን ለመወጣት ሰራዊቶቹን ይዞ ባህር አቋርጦ በሄደ ጊዜ የተሻገረበትን መርከብ በማቃጠል እና ድልድዩን በመስበር ነበር ጦርነቱን የጀመረዉ ምክንያቱም ጠላትን ድል ሳያደርግ የሃገርን ዳር ድንበር ሳያስከብር ወደ ኋላ የመመለስ ህልም አልነበረዉምና፤ ጠንካራ ፍላጎቱ ድል እንጂ ወደ ኋላ መሸሽ/መመለስ አልነበረምና ነዉ፡፡ መርከቡ እና መሸጋገሪያዉ ድልድይ ቢኖር ፈሪዎች ወደ ኋላ መመለስን እንደ አማራጭ ይጠቀሙበት ነበርና ነዉ፡፡ ስለዚህ እኛም ወደ ኋላ የሚመልሱንን ከስኬት ከተሻለ ለዉጥ ወደ ኋላ የሚያሰቀሩ መንገዶችን ልናቃጥል አዉጥተን ልንጥል ይገባናል፡፡
Ø  ኞትና ተራ ፍላጎት ስኬትን አያስገኙም፤ ምኞት ማለት የቀረበን እንጀራ

ማክሰኞ 30 ጁላይ 2019

COMPETENCY/ ብቃት/ክፍል ሁለት/


ክፍል አንድን ለመዳሰስ እንደሞከርነዉ ሁሉ ክፍል ሁለትን እንዲህ እንቃኘዋለን፤ መልካም ንባብ፡፡
2.5.  የሰብአዊ ግንኙነት ክህሎት #
አንድ ተቋም የሚፈጠረዉ እና የሚንቀሳቀሰዉ በሰዉ ነዉ፤ በእርግጥ ለሰዉ ሥራ ማቀላጠፊያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶች ሰወችን ይደግፉ ይሆናል እንጂ በራሳቸዉ ሰዉን አይተኩም፡፡ ስለሆነም በየትኛዉም የስልጣን እርከን ይሁን በየትኛዉ የስራ መስክ ላይ የሚሰራ ሰራተኛ የሰብአዊ ግንኙነት (የሰዉ ለሰዉ ግንኙነት) ክህሎት አካል የሆነዉን የስሜት ብልህት (Emotional Intelligence/Quotient) ሊያዳብር ይገባዋል፡፡
  Øአንድ መሪ የግሉንና የሌሎች ሰዎችን ስሜት የማወቅና የመቆጣጠር እንዲሁም ለራሱና ለሌሎች ሰዎች ስሜት ሊሰጥ የሚገባዉን ትክክለኛ ምላሽ ለይቶ የማወቅ ግላዊ እና ማኅበረሰባዊ ብልት ችሎታ ሊኖረዉ ይገባል፡፡
የሰብአዊ ግኙነት ማለት መሪዉ የሚመራዉን ሰራተኛ በአግባቡ ስሜቱን የማወቅ እና የመረዳት ችሎታ ሲሆን ሰራተኛዉ ደግሞ የሚያስተናግደዉን ደንበኛ፣ አብሮት የሚሰራዉን ሰራተኛ፣ እንዲሁም የሚመራዉን የቅርብ አለቃዉን ስሜት የመረዳት ችሎታ ማለት ነዉ፡፡ ይህ ካለ መሪዉ ሰራተኛዉን የማበረታታት፣ ለስራ የማነሳሳትን፣

ማክሰኞ 18 ሴፕቴምበር 2018

COMPETENCY/ብቃት

ብቃት


መግቢያ

ብቃት የሚለዉ ፅንሰ ሃሳብ ዘርዘር አድርገን ስንመለከተዉ በማንኛዉም የሥራ ዘርፍ እና ሙያ በየትኛዉም የሀላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኝ መሪ እና ሰራተኛ ሊኖረዉ የሚገባ ዕዉቀት ፣ክህሎት እና አስተሳሰብ ወይም አመለካከትን አጣምሮ የያዘ ድምር ዉጤት ነዉ፡፡አንድ ሰራተኛ ወይም የሥራ ኃላፊ/መሪ ብቃት አለዉ ለማለት ሦስቱንም በአንድ ላይ አሟልቶ መገኘት ግድ ይለዋል፡፡አንዱ ባልተሟለበት ሁኔታ ይቅርና የላቀ ዉጤት ማሰመዝገብ የተሰጠን ኃላፊነት በተሟላ መንገድ ለመፈፀም አይቻልም፡፡አንዱ ለሌላዉ መጋቢ ብቻም ሳይሆን ተደጋጋፊም ናቸዉ፡፡ አንዱ በጎደለበት ሌላዉ የተሟላ ሊሆን ስለማይችል ብቃት ብሎ ነገር የለም ማለት ነዉ፡፡ስለዚህ አንባቢ ስለብቃት ሲያስብ ሶስቱንም ማሟላት ግድ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
ይህንን ፅሑፍ ከኮሎኔል ፈቃደ ገብረየስ መፅሐፍ "የአመራር ሳይንስና ጥበብ" መካከል ሳገኝ ስለተጠቀምኩበት ለሌሎችም ባጋራዉ ትዉልዱ በየሄደበት የአገልግሎት ቦታ ሁሉ ስለሚያገለግሉት አገልጋዬች ብቃት ማነስ እያነሳ ሲተች እና ሲማረር ባይ እኛም በያለንበት ሥፍራ ጥራት እና እርካታ ያለዉ አገልግሎት ብንሰጥ ይህንን ቅሬታ መቅረፍ የተሻለ አገልጎሎት ለመስጠት ያስችለናል ብዬ በማሰብ ነዉ፡፡ አንባቢ በዚህ ብቻ ሳይገደብ ማንበብ ሙሉ ሰዉ ያደርጋልና የኚህን ምሁር መፅሐፍ ሙሉዉን ብናነብ እኔ ያልዳሰስኳቸዉ መፅሐፉ የሚዳስሳቸዉ ጥልቀት ያለዉ እዉቀት እንደሚያገኙ ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
ዕዉቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ለሥራችን ብቻ ሳይሆን ለህይወታችንም እጅግ ጠቃሚ ነዉና አትኩሮት ሰጥተን በማንበብ ወደ ተግባር እንድንቀይረዉ እያሳሰብኩ በዚህ አጭር ፅሑፍ ብቻ ሳንወሰን ሌሎችንም መፅሐፎች በመመርመር የተሻለ ሥራ እንድትሰሩ የተሻለ ህይወት እንድተመሩ እመኝላችኋለሁ፡፡
መልካም ንባብ፡፡

ረቡዕ 22 ኖቬምበር 2017

የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta's Views : የህይወት ታላቁ ፈተና “ጠላትህን ዉደድ”

የደረሰ ረታ እይታዎች Deresse Reta's Views : የህይወት ታላቁ ፈተና “ጠላትህን ዉደድ”: ክርስቲያን ሆንን አልሆንን፣ወደድንም ጠላንም፣በየትኛዉም የእምነት አስተምህሮ ዉስጥ ብንሆንም በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርተ ወንጌል ዉስጥ ለማንኛዉም የሰዉ ልጅ ጥሩ የመሆን ፍላጎት ሊሆን ከወደ...

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...