ማክሰኞ 31 ዲሴምበር 2019

ከትናንት እስከ ዛሬ …

በነገራችን ላይ   ከ ፈረንጆቹ Thursday, March 22, 2012 እስከ ዛሬይቱ ቀን ድረስ ………. 


https://deressereta.blogspot.com/

የደረሰ ረታ እይታዎች የፀሐፊዉ ያላሰለሰ ስንፍና እንዳለ ሆኖ በአገራት ኢትዮጵያና አሜሪካ እንደ ቅደም ተከተላቸዉ ብዙ አንባቢያን ያሉበት ሲሆን በመቀጠል ኬንያ፣ ሩሲያ እና ኢንዶኔዥያ ከ1 እስከ 3 ያለዉን ተራ ይይዛሉ፡፡
ከሚለጠፉት ፅሑፎች ደግሞ ትልቁን የቀዳሚነት ድርሻ የያዘዉ ፍቅር በፌስቡክ ክፍል ሁለት ሲሆን አጋጣሚ ክፍል አራት እና ለመጪዉ ትዉልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም የሚሉት ሁለተኛ እና ሶስተኝነትን ይይዛሉ፤ እኔን በስነ ፅሑፍ ዘመኔ እጅግ ዋጋ ያስከፈለኝ እና በወቅቱ ከ1500 በላይ ኢ-ሜይል የተቀበልኩበት እና አንባቢ ያገኘዉ ብዙ ጊዜም ሲመራ የቆየዉ ዋጋ የሚያስከፍሉ ጥፋቶች
አራተኛዉን ረድፍ ይዟል አምስተኛዉ እና ለኔ ሁሌም አንደኛዉ ስለሴቶች (እናቶች ፣ ሚስቶች፣ እህቶች፣ ልጆች፣ጓደኞች … ) የተፃፈዉ እናት የተሰኘዉ ፅሑፌ ነዉ፡፡
 ምን ለማለት ነዉ

ይህንን ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ እድል ለሰጠኝ ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ለማቅረብ እንዲሁም በአንድ ወቅት ፅሑፌን ተመልክቶ በመገምገምና እና እንድበረታ ለረዳኝ ከሁሉም ጎን መቆም ለማይሰለቸዉ ሲረዳህ ፊቱን የሸፈኑት ፂሞቹ ደስታዉን የማይከልሉት ታላቅ ወንድሜን ነፃነት ተስፋዬ አበበን እንድታመሰግኑልኝ ጭምር ነዉ፡፡


በመቀጠልም ፍቅር በፌስቡክ አንደኛ ተነባቢ ያደረጋችሁት ክፍል አንድን ዘላችሁታልና መለስ ብላችሁ አንቡት የሚለዉን ጥቆማዬን ለመሰንዘር ነዉ፤ ከዚሁ ከጥቆማ ሳልወጣ አጋጣሚ የተሰኘዉ በሁለተኛ ደረጃም የተቀመጠዉ ሶስት ክፍሎቹን (አጋጣሚ ክፍል አንድ፣ ሁለት፣ ሶስትን ) ዘላችሁታል እላችኋለዉ፡፡

ሳጠናቅቅ ሌሎችም አንደኛ ሊሆኑ የሚችሉ ይቅርታን የመሰለ፣ የሕይወት ታላቁ ፈተና ጠላትህን ዉደድ፣ የመለስ ሌጋሲ፣ ፖሊስና ሕብረተሰብ፣ ኑሮ በአሜሪካ፣ የማለዳ ጀንበር (ከእናት ጋር የሚተካከል)፣ ዛሬን የሚመጥኑ ናቸዉና ይነበቡ፡፡

በሌሎችም እመጣለሁ፡፡
በፌስ ቡክ ‘’ደረሰ ረታ አስቴር’’ የኔ ነዉ ፌስቡክ የለኝም ብይ አልቦተልክም፡፡
Deresse Reta fugeraandnekora.com የተሰኙ ሁለት ገፆች (Page) ላይ በሽ ነኝ፡፡
ጊዜዉ የቴሌግራም ነዉ ካላችሁም telegram t.me/deressereta  ላይ ታገኙኛላችሁ፡፡



ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...