ማክሰኞ 18 ሴፕቴምበር 2018

COMPETENCY/ብቃት

ብቃት


መግቢያ

ብቃት የሚለዉ ፅንሰ ሃሳብ ዘርዘር አድርገን ስንመለከተዉ በማንኛዉም የሥራ ዘርፍ እና ሙያ በየትኛዉም የሀላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኝ መሪ እና ሰራተኛ ሊኖረዉ የሚገባ ዕዉቀት ፣ክህሎት እና አስተሳሰብ ወይም አመለካከትን አጣምሮ የያዘ ድምር ዉጤት ነዉ፡፡አንድ ሰራተኛ ወይም የሥራ ኃላፊ/መሪ ብቃት አለዉ ለማለት ሦስቱንም በአንድ ላይ አሟልቶ መገኘት ግድ ይለዋል፡፡አንዱ ባልተሟለበት ሁኔታ ይቅርና የላቀ ዉጤት ማሰመዝገብ የተሰጠን ኃላፊነት በተሟላ መንገድ ለመፈፀም አይቻልም፡፡አንዱ ለሌላዉ መጋቢ ብቻም ሳይሆን ተደጋጋፊም ናቸዉ፡፡ አንዱ በጎደለበት ሌላዉ የተሟላ ሊሆን ስለማይችል ብቃት ብሎ ነገር የለም ማለት ነዉ፡፡ስለዚህ አንባቢ ስለብቃት ሲያስብ ሶስቱንም ማሟላት ግድ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡
ይህንን ፅሑፍ ከኮሎኔል ፈቃደ ገብረየስ መፅሐፍ "የአመራር ሳይንስና ጥበብ" መካከል ሳገኝ ስለተጠቀምኩበት ለሌሎችም ባጋራዉ ትዉልዱ በየሄደበት የአገልግሎት ቦታ ሁሉ ስለሚያገለግሉት አገልጋዬች ብቃት ማነስ እያነሳ ሲተች እና ሲማረር ባይ እኛም በያለንበት ሥፍራ ጥራት እና እርካታ ያለዉ አገልግሎት ብንሰጥ ይህንን ቅሬታ መቅረፍ የተሻለ አገልጎሎት ለመስጠት ያስችለናል ብዬ በማሰብ ነዉ፡፡ አንባቢ በዚህ ብቻ ሳይገደብ ማንበብ ሙሉ ሰዉ ያደርጋልና የኚህን ምሁር መፅሐፍ ሙሉዉን ብናነብ እኔ ያልዳሰስኳቸዉ መፅሐፉ የሚዳስሳቸዉ ጥልቀት ያለዉ እዉቀት እንደሚያገኙ ለማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
ዕዉቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ለሥራችን ብቻ ሳይሆን ለህይወታችንም እጅግ ጠቃሚ ነዉና አትኩሮት ሰጥተን በማንበብ ወደ ተግባር እንድንቀይረዉ እያሳሰብኩ በዚህ አጭር ፅሑፍ ብቻ ሳንወሰን ሌሎችንም መፅሐፎች በመመርመር የተሻለ ሥራ እንድትሰሩ የተሻለ ህይወት እንድተመሩ እመኝላችኋለሁ፡፡
መልካም ንባብ፡፡

1.      ዕዉቀት
ዕዉቀት ማለት ማንኛዉም ሰዉ በመደበኛ ትምህርት ቤት ገብቶ የተማረዉን ትምህርት እና ለመማሩም ተገቢዉን ማስረጃ ያገኘበት ሲሆን በትምህርት ቤት ዉስጥ ገብቶ ከሚያገኘዉ በተጨማሪ መደበኛ ባልሆነ መንገድ በልምድ ፣ በማንበብ፣ በተሞክሮ ወዘተ ሊገኝ ይችላል፡፡
ዕዉቀት መሪዉ ወይም ሰራተኛዉ ሥራዉን ለማከናወን የሚፈልግ ልዩ ችሎታ ነዉ፡፡
ሂሳብ ሥራ ለማከናወን …….. አካዉንቲንግ
የህክምና ሙያ ለማከናወን ……..የሃኪም ዕዉቀት
ዳኛ ለመሆን……….. የሕግ ዕዉቀት፡፡ በመስኩ የተወሰነ ዕዉቀት ሊኖራቸዉና ይህንንም በየጊዜዉ እያዳበሩት ሊሄዱ ይገባል፡፡
በብዙ ተቋማት ሰራተኞችን እንደ ጀማሪ ሲቀጥሩም ይሁን የዉስጥ እድገቶችን ማስታወቂያ ሲያወጡ መስፈርቶቹ እዉቀትን እንዲሁም በቀጣይነት የምንመለከተዉን (ክህሎት) ከግምት ዉስጥ ያስገባሉ፡፡ ምክንያቱም ዕዉቀትን መገብየት ለብቻዉ ብቃት እንዲኖረን ስለማያደርግ ይህ ማለት ግን እዉቀት ድርሻ የለዉም ማለት አይደለም፡፡ አዳዲስ ምርቃን እኔ ከእንደዚህ ዩኒቨርስቲ በእንደዚህ አይነት የትምህርት መስክ በድግሪ / በማስተርስ ተመርቄያለሁ ለምን ስራ አላገኝም ለምን እድገት አላገኘሁም ብለዉ ቅሬታ ሲያሰሙ ይደመጣል፡፡ ስለዚህ ይህንን ግምት ዉስጥ በማስገባት የምንፈልገዉን ያላገኘንበት ምክንያት ተቋሙ የራሱ ግብ እንዳለሁ ሁሉ በምን አይነት ባለሙያዎች ያንን ግብ ማሳካት እንዳለበት የቀረፀዉ መንገድ ስላለ ለዚያ ነገር ተገዢ መሆን ይኖርብናል፡፡ በዚሁ ማዕቀፍም እኛም የብቃት ልካችንን ልንለካ እና ብቃታችን የሚያስቀምጠን ቦታ ላይ ብቻ ብንቀመጥ ዉጤታማ እንደምንሆን ልብ ልንል ይገባል፡፡ ለአገርም ለወገንም የሚጠቅመዉ ይህ እንደሆነ ልብ ልንለ ይገባል፤ ጥቅምን ብቻ ያማከለ አካሄድ ባንጓዝ የአገልግሎት ጥራታችንን አንድ ደረጃ ወደፊት ያራምደዋልና፡፡

2.     ክህሎት
2.1.     የመሪነት ክህሎት
መሪዎች ስኬታማ አመራር ለመስጠት ስትራቴጂካዊና የዕለት ተዕለት ተግባራትን በተሟላ መልኩ ለመምራት እንዲያስችላቸዉ የተለያየ ክህሎት ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ ቴክኒካዊ ክህሎትን በተመለከተ ዝቅተኛዉ አመራር በስራ መስኩ ሰፋ ያለ ዕዉቀት ሊኖረዉ ይገባል፡፡ወደ ከፍተኛዉ አመራር ስንመጣ ግን ቴክኒካዊ ክህሎቱ መጠነኛና ጠበብ ያለመሆኑን ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡የንድፈ ሃሳብ ክህሎት ላይ ግን የከፍተኛዉ አመራር ሰፋ ያለ ሲሆን የዝቅተኛ አመራር ደግሞ ጠበብ ያለ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡
2.2.    የንድፈ ሃሳብ ክህሎት
የንድፈ ሃሳብ ክህሎት ሲባል የተለያዩ ሃሳቦችን የመረዳት ፣ መረጃ የማግኘት፣ የመተንተንና የመተርጎም ችሎታዎችን ያጠቃልላል፡፡ይህ ክህሎት የመሪዉ ተቋሙን እንደ አንድ አድርጎ የማየትና የመተርጎም ችሎታ ነዉ፡፡እንዲሁም ሁሉም ክፍሎች በአንድነት ለአንድ ግብ እዉን መሆን እንዲጥሩ አድርጎ ዋናዉ የተቋሙን ዓላማ እንዲሳካ ማስቻል ነዉ፡፡ይህ እንዳለ ሆኖ የንድፈ ሃሳብ ችሎታ መሪዉ ስለተቋሙ ያለዉ አጠቃላይ ስትራቴጂካል አመለካከት ሁሉ ያካትታል፡፡
2.3.    የችግር አፈታትና የዉሳኔ አሰጣጥ ክህሎት
መሪነት ብዙ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ዉሳኔ በመስጠት የተሞላ ነዉ፤ መምራት ትክክለኛ ዉሳኔ መስጠት መቻል እንደሆነ ይታመናል፡፡ እንዲሁም መሪዎች ብቃታቸዉ የሚለካዉ በሚሰጡት የዉሳኔ ትክክለኛነትና ወቅታዊነት ነዉ፡፡ ሰራተኛዉም ለሚያከናዉናቸዉ የዕለት ተዕለት ተግባሩ ጥንቃቄ የተሞላዉ ችግር የመፍታት ችሎታዉ እና እንደደረጃዉ ዉሳኔ ሰጪነቱ ዓላማዉን ከግብ ለማድረስ ያግዘዋል፡፡
የመሪ ዉሳኔ በማቀድ፣ በማደራጀት፣ በመምራትና በመቆጣጠር ሂደቶች ስለሚከሰቱ አማራጭ ዘዴዎችን መጠቀም ይኖርበታል፡-
2.3.1.   በቅድሚያ ችግሩን መለየት (ግልፅ የሆኑ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣ ከመረጃዉ ዉስጥ መላምቶችን ፣አደናጋሪ ነገሮችን ፣ ግምታዊ ሁኔታዎችን እና ምናባዊ ጉዳዮችን ማዉጣት)
2.3.2.  አማራጭ የመፍትሔ ሃሳቦችን ማቅረብ ፣ የመፍትሔዎቹን የችግር ፈቺነት አቅም፣ ጠቀሜታ ፣ ፍትሃዊነት እና አስተማማኝነት ሁኔታ ግንዛቤ ዉስጥ ማስገባት
2.3.3.  የተሻለዉን አማራጭ የመፍትሔ ሃሳብ መምረጥ
2.3.4.  የማስፈፀሚያ መርሃ ግብር ማዘጋጀት ፣ ዉሳኔዉን ተግባራዊ ማድረግ
2.3.5.  የዉሳኔዉ ዉጤት ያስገኘዉን ጠቀሜታ እና ያስከተለዉን ጉዳት በመለየት ችግሩን ለማስወገድ ክትትል ማድረግ ፣ ደጋግመን መከለስ፣ እንደ አስፈላጊነቱ ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡ (አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦችን ማቅረብ፣ የተሻለዉን አማራጭ በማመላከት እና በቀጣይም ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡)

2.4.    ዉጤታማ የሥራ ቡድን የመገንባት ክህሎት
ሲተጋገዝ እንጂ ፍጡር የሚድነዉ፤
ምንም ብርቱ ቢሆን አንድ ሰዉ አንድ ነዉ፡፡
ሰራተኞች በአግባቡ ሊተዋወቁ እና የህብረት ስሜት ሊኖር የሚችልበትን ስልት መቀየስና መተግበር ይጠበቅባቸዋል፤ መሪዉም ይህንን የማመቻቸት እና የመከታተል የሃላፊነት ድርሻዉ ትልቅ ነዉ፡፡ ቡድኖች ከመቋቋማቸዉ በፊት ፡-
·         ለምን ዓላማ እንደሚቋቋሙ፣
·         ምን ምን ስራዎች እንደሚከናወኑ፣
·         የሚጠበቀዉ ዉጤት ምን እንደሆነ፣
·         ስራዎቹን ለመስራት የሚያስፈልገዉ ዕዉቀትና ክህሎት እንዲሁም የሙያ ስብጥር እና የሰዎች ብዛት ምን መሆን እንዳለበት … አስቀድሞ መታወቅ አለበት፡፡ 
የቡድን አባላት ባሕሪይ
በቡድን አሰራር ዉስጥ የተለያዩ ባሕሪያት ሊንፀባረቁ ይችላሉ፡፡ከነዚህም ዉስጥ አብዛኛዉን ጊዜ
Ø  ግራ አጋቢዎች
Ø  ዘባራቂዎች
Ø  ሃሳበ ግትሮች
Ø  ለፍላፊዎች
Ø  በሆነ ባልሆነ ተበሳጮች … ወዘተ ሊኖሩ እንደሚችሉ በቅድሚያ ማወቅ ይበጃል፡፡
የቡድን መሪዎችም እነዚህን ባህሪያት ለማስተናገድና ዝግጁ በመሆን እነዚህን ሰዎች በዘዴ መያዝ ይጠበቅበታል፡፡ከላይ ያሉትን ባህሪያት ከታች ለማጣመርና ለማያያዝ ተሞክሯል፡፡ እነርሱም፡-
2.4.1.  አምራችና አዳዲስ ነገሮችን የሚፈጥር ሚና/ባሕሪይ
ይህ ባህሪ ያለዉ ሰዉ አዳዲስ ሃሳቦችን ያፈልቃል፣ይቸኩላል፣ይፈጥናል፣ማንም አይደርስበትም፡፡ዉጤታማ መሆን በጣም ይሻል፣ትጉ ነዉ፣ቡድኑ በአጀንዳዉ መሰረት መስራቱን ይከታተላል፤ እንዲሁም ያበረታታል፡፡ ጊዜ እንዲባክን አይፈቅድም፡፡
2.4.2.  ገንቢ ጠጋኝ ሚና
ይህ ባህሪይ ያለዉ ሰዉ እጅግ መልካም ሰዉ ነዉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ሁሉን ያበረታታል፣ ያፅናናል፣ዕርቅ እንዲመጣ ሰላም እንዲሰፍን ይጥራል፣የቡድኑን ህብረት ይጠብቃል፡፡የአገልጋይ ባህሪይ ያለዉና ሁሉን ሊረዳ የሚፈልግ ሰዉ ነዉ፡፡ቀና እና ግልፅ ባህሪይ አለዉ፡፡በመከፋፈል አያምንም፤ዝምተኞች እንዳይረሱ ያግዛቸዋል፡፡
2.4.3.  የተጓዥና የአግበስባሽ ሚና
Ø  እንዲህ አይነት ሰዉ / ቡድን ሳያመርጥና ሳያጣራ ይቀበላል፡፡
Ø  ወዴት እንሄዳለን እንኳን ብሎ አይጠይቅም፡፡
Ø  ሁሉም ይስማማዋል፤ የሚቆረቁረዉ ነገር የለም፡፡
Ø  ትንሽ ስልጣን ያለዉ ሰዉ ሃሳብ ካቀረበ እንዳሳቡ አድርጎ ይሟገታል፡፡በሌሎች ሃሳብ ባለቤት ይሆንና ይሟገታል፡፡
Ø  በስብሰባ ወቅት የራሱን ሥራ ይሰራል፤ የሚነሱ አጀንዳዎች ጉዳዩ አይደሉም፡፡
Ø  ድንገት ለየት ያለ ሃሳብ ያቀርባል፤ … የቡድኑ አባላትም ይህን ሰዉ የተሻለ ሃሳብ ያቀርባል ብለዉ አይጠብቁትም፡፡
Ø  እንደዚህ አይነት ሰዉ ቡድኑን ሊጎዳ ይችላል፡፡

2.4.4. አስቂኝና አስደሳች ባህሪይ
ü  እንደዚህ አይነት ሰዉ በቡድኑ አባላት የሚወደድ እና ቀልደኛ ሰዉ ነዉ፡፡
ü  ምንም ስብሰባ አይደብረዉም፡፡
ü  በሰዉ ላይ ክፋት አያስብም፡፡
ü  አባላት መስማማት ሲሳናቸዉ ያስማማል፣ ያስታርቃል፣ ልዩነቶችን ያጠባል፡፡
ü  ለችግሮች መፍትሄ ይፈልጋል እንጂ አያባብስም፡፡

2.4.5.  አፍራሽ እና አደፍራሽ ባህሪይ

Ø  በቡድን ዉስጥ ይህን ሚና የሚጫወት ሰዉ ብዙ ደጋፊዎች የሌሉት ሰዉ ነዉ፡፡
Ø  አልፎ አልፎ አባላቱ ይፈሩታል፡፡
Ø  በግሉ ደግሞ በጣም ተደማጭ ለመሆን ይሻል፡፡
Ø  ተደማጭነትን እስከሚያገኝ ስብሰባዉን ያዉካል፣ ብዙ ይናገራል፣ ራሱ ግን ብዙ አያዳምጥም፡፡ በድምፁ ማንነቱን ለማሳወቅ ይጥራል፡፡
የቡድን አባላት ሚና
Ø  ለቡድኑ ስኬት ወይም ዉድቀት የቡድኑ አባላት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ቡድኑ አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ሚና አለዉ፡፡
Ø  በአዎንታዊ ገፅታዉ የምርታማነትና የእንክብካቤ ሚና፡፡
Ø  በአሉታዊ ገፅታዉ ደግሞ የፀረ ቡድን ሚና ይካሄዳል፡፡
Ø  የምርታማነት ሚናዎች በስራዉ ላይ ሲያተኩር የእንክብካቤ ሚናዎች ደግሞ በቡድኑ ዉስጥ ባሉት ሌሎች አባላት ላይ ያተኩራሉ፡፡
ሀ. አደራጅ
ለ. ቀስቃሽ
ሐ. መረጃ ሰብሳቢ
መ. አግባቢ
ሰ. ገምጋሚ
ወዘተ
ቀሪዉን በክፍል ሁለት ለማቅረብ ሞክራለሁ መልካም ንባብ

for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...