ክፍል አንድን ለመዳሰስ
እንደሞከርነዉ ሁሉ ክፍል ሁለትን እንዲህ እንቃኘዋለን፤ መልካም ንባብ፡፡
2.5. የሰብአዊ
ግንኙነት ክህሎት #
አንድ ተቋም
የሚፈጠረዉ እና የሚንቀሳቀሰዉ በሰዉ ነዉ፤ በእርግጥ ለሰዉ ሥራ ማቀላጠፊያ የሚሆኑ ቁሳቁሶች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶች
ሰወችን ይደግፉ ይሆናል እንጂ በራሳቸዉ ሰዉን አይተኩም፡፡ ስለሆነም በየትኛዉም የስልጣን እርከን ይሁን በየትኛዉ የስራ መስክ
ላይ የሚሰራ ሰራተኛ የሰብአዊ ግንኙነት (የሰዉ ለሰዉ ግንኙነት) ክህሎት አካል የሆነዉን የስሜት ብልህት (Emotional Intelligence/Quotient) ሊያዳብር ይገባዋል፡፡
Øአንድ መሪ የግሉንና የሌሎች ሰዎችን ስሜት የማወቅና
የመቆጣጠር እንዲሁም ለራሱና ለሌሎች ሰዎች ስሜት ሊሰጥ የሚገባዉን ትክክለኛ ምላሽ ለይቶ የማወቅ ግላዊ እና
ማኅበረሰባዊ ብልሀት ችሎታ ሊኖረዉ ይገባል፡፡
የሰብአዊ
ግኙነት ማለት መሪዉ የሚመራዉን ሰራተኛ በአግባቡ ስሜቱን የማወቅ እና የመረዳት ችሎታ ሲሆን ሰራተኛዉ ደግሞ የሚያስተናግደዉን
ደንበኛ፣ አብሮት የሚሰራዉን ሰራተኛ፣ እንዲሁም የሚመራዉን የቅርብ አለቃዉን ስሜት የመረዳት ችሎታ ማለት ነዉ፡፡ ይህ ካለ መሪዉ ሰራተኛዉን የማበረታታት፣
ለስራ የማነሳሳትን፣
የማትጋት፣
የቅሬታ አፈታትን፣ የግጭት አፈታትን ችሎታ ወዘተ … እያዳበረ ይሄዳል፡፡ ሠራተኛዉም እርስ በእርስ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር
ተደማምጦ፣ ተከባብሮ፣ በጋራ መስራትን እያዳበረ ይሄዳል ማለት ነዉ፡፡
ለዚህም የሚያግዙ ሁለት ነገሮች አሉት
2.5.1. የግንኙነት
ክህሎት
አንድ መሪ በስራ ገበታዉ ላይ በመሆን
ከብዙ አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፤ ለምሳሌ ከሚመራቸዉ ሰራተኞች፣ ከደንበኞች፣ ከአቅራቢዎች፣ ከመንግስት አካላት፣ … ወዘተ
ግንኙነቱም በስብሰባ፣ በቃል በመነጋገር፣ በደብዳቤ፣ በስልክና በኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎች ሊሆን ይችላል፡፡ መልካም ኮሙኒኬሽን የጥሩ አመራር ክህሎት
ነፀብራቅ ነዉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ብዙ
አለመግባባቶች የሚፈጠሩት በሚያግባባ መልኩ ግንኙነት ካለማድረግ የተነሳ ነዉ፡፡
ኮሙኒኬሽን ክህሎት ነዉ፡፡
ሰዎችን
ለማሳመንና ለማግባባት መሪዉ ምን መስራት እንዳለበት? በምን ዓይነት ግንኙነት የተቋሙን ዓላማ ማሳካት እንዳለበት ጠንቅቆ
ለማወቅ ያስችለዋል፡፡ በስሩ ያሉትንም ሰራተኞች አስተባብሮ በማነቃቃት ዉጤት ለማስመዝገብ ያስችለዋል፡፡
2.5.2. የማዳመጥ
ክህሎት/ጥሩ አዳማጭ መሆን
" ብዙ የምታስካካ ዶሮ ብዙ እንቁላል አትጥልም፡፡ "
vየንግግር ችሎታ አስፈላጊ
እንደመሆኑ መጠን የሰዎችን መሠረታዊ ችግር ተረድቶ ተገቢዉን መፍትሄ መስጠት የሚችለዉ ጥሩ የማዳመጥ ችሎታ ሲኖር ነዉ፡፡
vየምናዳምጠዉ ከፈራጅነት ወይም
ከትችት ነፃ በሆነ ልቦና መሆን ይኖርበታል፡፡
vሰዎች ችግራቸዉን እንዲናገሩ
ነፃነት እንዲሰማቸዉ የሚያደርግ አሳብ ለመረዳት በተዘጋጀ ልብ የሚያዳምጥ ሰዉ እዉነትም የተባረከ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ይህ ነዉ
የሚባል ትልቅ ለዉጥ ባያመጣም አዳማጭ ለሚፈልጉት ሰዎች ትልቅ መፍትሔ ነዉ፤ ከዚያም ባሻገር ከፊል መፍትሔዎችን ማግኘት
የምንችለዉ ከምናዳምጠዉ ንግግር ዉስጥ ነዉና፡፡
vጥሩ የማዳመጥ ችሎታ የጎደለዉ
መሪ ነዉ፤ በዉሳኔ አሰጣጡም ዉስጥ ላይ ችግር ማስከተሉ አይቀርም፡፡
2.6. የጊዜ አጠቃቀም
ክህሎት
በስንፍና በቀልድ-የተጫወቱበት፣
የልጅነት ዕድሜ-አፍላ ወጣትነት፤
ኋላ በስተርጅና-ከጊዜ ጋር በኖ፣
በፀፀት ያፍናል-ቁልል አመድ ሆኖ፡፡
• ጊዜ ምትክ የሌለዉ
ረቂቅ ሃብት (intangible
asset) ነዉ፡፡
• ጊዜ አንዴ ካመለጠ
የማይመለስና ካልተጠቀምንበት ባክኖ የሚጠፋ ነዉ፡፡
• የአንድ መሪ/ሠራተኛ ችሎታ ከሚመዘንባቸዉ
ነገሮች አንዱ ጊዜዉን የሚጠቀምበት ሁኔታ ነዉ፡፡
• ጊዜ
የለኝም የሚለዉ ሰበብ ተቀባይነት የሌለዉና ቢሆን እንኳን አልፎ አልፎ ብቻ ነዉ መሆን ያለበት፤ ከዚያ
ባለፈ የድክመት መሸፈኛ ነዉ የሚሆነዉ፡፡
• ጊዜ በጊዜዉ
ካልተጠቀምንበት ተመልሶ የማናገኘዉ እና አቆይተን እንደሌላ ሃብት በኋላ የምንጠቀምበት አይደለም፡፡ ካለፈ አለፈ ነዉ፡፡
• ሥራን በኋላ
እሰራዋለሁ አንበል፤ ቀጠሮ ጊዜን ይሰርቃልና፡፡ እንዲሁም ነገሮችን ዛሬ ማከናወን ስንችል ለነገ መቅጠር ለዉድቀት እንጂ ለስኬት
አይሆንምና፡፡
• በአንድ ጊዜ ብዙ
መስራት አይገባም በአንደኛዉም ዉጤታማ አይኮንምና፡፡
ጊዜአችንን እንዴት እንጠቀም?
ሀ. እለታዊ ዉሎን በጥንቃቄ ማቀድ፤
ለ. ቅድሚያ ለሚገባዉ ቅድሚያ መስጠት፤
ሐ. ትኩረትን አስፈላጊ በሆነ ጉዳይ ላይ
ማድረግ፤
መ. የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ መጠቀም፤
ሰ. ሚዛን የማይደፉትን ወደ ጎን መተዉ/
ለሌላ ጊዜ ማሸጋገር፡፡
2.7. የተቋምን ጤንነት
የመመርመር ክህሎት
የሰዉ ልጅ
ጤናዉን ተመርምሮ እንደሚታከም ሁሉ ተቋምም እንደሰዉ ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ያረጃል፣ ብሎም ይሞታልና
በዚህ ሂደት በየደረጃዉ የሚገኝበት የጤንነት ደረጃ በመፈተሸ ተገቢዉን ህክምና መዉሰድ ይጠበቅበታል፡፡ የተቋምን ጤንነት
በተመረጡ መመዘኛ ላይ ተንተርሰን ልንመረምር ይገባል፤ አፋጣኝ ህክምናም ልንሰጠዉ ይገባል፡፡
2.8. የስትራቴጂካዊ
ዕቅድ የማዘጋጀት ክህሎት #
አንድ ተቋም የተቋሙን ስትራቴጂክ ዕቅድ
ሲያዘጋጅ የሚሄድበትን አቅጣጫ ግልፅ ያደርግበታል፡፡
qአሁን የት እንደአለ?
qየት ሊደርስ እንዳሰበ?
qወደፊትን እንዴት
እንደሚደርስበት?
ወዘተ … ይዳሰስበታል፤ መልኩን
ያሳይበታል፡፡
ችግሮች ሲያጋጥሙ ስጋቶችን
ይመረምርበታል፡፡ ዕቅዱ እንደማይሳካ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን ቢከሰቱ አማራጭ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፡፡
ስትራተጂክ ዕቅድ የሚከተሉትን ጥያቄዎች
መመለስ አለበት
•የዉጫዊ ዳሰሳ ምን ያህል
ያመለክታል?
•ያለዉን የተገልጋይ ፍላጎት ምን
ያህል ተደርተናል?
•ድርጅቱን ዉጤታማ አድርጎ ለማሳደግ
የሚያስችል የተሻለ ዘዴዎች ምንድን ናቸዉ? እንቅፋቶችስ?
•ተፎካካሪዎች እነማን ናቸዉ?
•ድርጅቱ ስትራቴጂዉን ማስፈፀም
ይችላልን?
•የእጭርና የረጅም ጊዜ ትኩረት
ሚዛናዊነታቸዉን የጠበቁ ናቸዉ?
•እቅዱ ሲተገበር በየደረጃዉ የሚጠበቁ
ጠቃሚ ዉጤቶች ምንድን ናቸዉ?
•ድርጅቱን ያጋጠመ ፈታኝ ሁኔታዎች
ምንድን ናቸዉ?
•ድርጅቱ ዘላቂነቱን ማረጋገጥ
የሚችለዉ እንዴት ነዉ?
üብቃት ሊመጣ የሚችለዉ እዉቀትና
ክህሎት ስላለን ብቻ አይደለም አንዱና ዋነኛዉ ነገር አመለካከት /አስተሳሰብ / ሲጨመርበት ነዉ፡፡
üአመለካከት / አስተሳሰብ ስንል አዎንታዊ
(Positive) ማለታችን እንደሆነ አንባቢ ልብ ሊለዉ ይገባል፡፡
üአመለካከታችን / አስተሳሰባችን ዳግም
መርጠን የምንይዘዉ ጉዳይ እንጂ የዕድል ጉዳይ አይደለም፡፡
üለዚህ ነዉ የምንኖረዉ የአስተሳሰባችን
/የአመለካከታችን ያህል ነዉ የሚባለዉ፡፡
üበመሪነት ጥበብ እንኳን ብንመለከት
ተሰጥኦ ክህሎት እና ቴክኒካዊ እዉቀት 20 በመቶ ብቻ ሲይዙ አስተሳሰብ / አመለካከት 80 በመቶ እንደሚይዝ ጥናቶች
የሚያረጋግጡት፤
üአስተሳሰባችን ለጠቅላላዉ ስኬታችንም
ይሁን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ላይ ከሌሎች ጉዳዮች የበለጠ አስተዋፅኦ አለዉ፡፡
üበአስተሳሰብ ያልተለወጠ ሰዉ ኑሮዉን
ብትቀይርለትም አኗኗርን ግን ልትለዉጠዉ አትችልም የሚባለዉ ሃሳብ በሚሄድበት ሰዉየዉ ተከትሎ ይጓዛልና፡፡ አስተሳሰቡ ድሃ ከሆነ
ሰዉየዉ ምንም ሀብታም ቢሆን በድህነት ዉስጥ ሲንቦጫረቅ እናገኘዋለንና፡፡
üስኬት የሚጀምረዉ በሃሳብ ነዉ ፤
አመለካከትም የሚጀምረዉ እንደዚሁ በሀሳብ ነዉ፡፡
üአስተሳሰብህ የከፍታህን መጠን
ይወስነዋል፤ ትልቅ ቦታ እንድትደርስ እና ስኬታማ እንድትሆን አስተሳሰብህን ከፍ አድርግ፡፡
üለስኬት የመጨረሻዉ አትሁን ከኋላም
አትቅር ብትችል ቀድመህ ተገኝ፡፡
vመጥፎ አመለካከት ስኬትን ያጨናግፋል::
ማጠቃለያ
የዚህ ፅሑፍ
አንባቢያን ይህን ብቃት ለማምጣት ባለን ብቃትም አገራችንን ኢትዮጵያን በታማኝነት እና በቅንነት ለማገልገል በተሰማራንበት መስክ
በምንሰራበት ተቋም ፍሬ ያለዉ ተግባር ለማከናወን በምን መልኩ፣
ምን በማየት፣
ምን በመስማት፣
ምን በማንበብ … ዕዉቀታችንን ክህሎታችንን እና
አመለካከታችንን/ አስተሳሰባችንን እንቀርፃለን? ወይንስ
ምን አሉ?
እያልን ቀናችንን
ከወረኞች እና አሉባልተኞች መንደር ጆሮአችንን ደግነን ቀናችንን
እናባክናለን? ወይንስ የክፋት መርዛቸዉን ይህቺ የተቀደሰች ዓለም ላይ ከሚረጩት ጋር ተደምረን
የአገራችንን/የተቋማችንን ዕድገትና ለዉጥ ወደ ኋላ እንጎትታለን?
የትኛዉ ይሻለናል?
ብቃታችን ለመሪነት አዘጋጅቶናል? ወይንስ ሁሌም በመመራት እንኖራለን?
የ ብቃት ን ጉዞ
ከሞላ ጎደል በሁለት ክፍል በዚህ መልኩ አጠናቀቅን፡፡
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ