እሑድ 7 ጁን 2020

«ደስተኛ ሕይወት»

ከጭንቀት ነፃ የሆነ «ደስተኛ ሕይወት» ለመኖር ወሳኝ የሆኑ #አሥር_የሕይወት_መርሆች

1. እራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦ ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው እራስን ከሰው ጋር ማፎካከር ነው።

2. አትኩሮትህ በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ ይሁን፡- ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

3. እራስህን ሁን፦ በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከበድ ነገር ምን አለ? እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር፡፡

4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦ አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።

5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦ በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ ሲሆን እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፣ አላማችንና ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበትም ነው፡፡

6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦ ሰዎችን አትና፤ በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ፡፡

7. መለወጥ የማትቻለውን ነገሮችን ተቀበላቸው፦ ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ/ለፈጣሪህ ስጠው።

8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦ ራስህን መውደድ ተለማመድ፤ የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። እራስህን ሲያጠፋ ይቅር በማለት፣ ሲደክም በማበርታት፤ ሲሳካለት በማሞካሠት ተንከባከበው፡፡

9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦ በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት ያመለካከታችን እና ያስተሳሰባቸን ውጤት ነው። ይህን ካወቅክ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።

10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦ ህይወት ማለት የተሰጠህን ሃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ሃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምትፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለህይወት ያለህ አመለካከት ይቀየራል፡፡

📌❇️ ደስተኛ ህይወትን ለሁላችንም ይስጠን ! መልካም የጤና ጊዜ!!!

ምንጭ - (ቶማስ እንደፃፈዉ፣ ፅሁፉ ከዶክተር አለ የተወሰደ)

እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች አሉት

እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች አሉት

ተፈጥሮ በኡደት (Process) የተመላች ናት፡፡ ዘመናትን በጊዜ ቀመር አስልታ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላኛው ታሻግራለች፡፡ የኡደት ስሌትዋ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትናንሽ ወደ ትላልቅ የሚያመራ ነው፡፡

የሰው ልጅ የዕድገት ለውጥ ዓላማ በተፈጥሮ የወረሰውን እምቅ ኃይል ከከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው፡፡ ኤልሳቤጥ ሃርሎክ የተባለች የሳይኮሎጂ ምሁር እንደገለጸችው ሰዎች በአእምሮ ፤ በአካል ከሌሎች የተሻሉ ሆነው ለመገኘት የሚያደርጉት ጥረት ወደ ዕድገት ለውጥ ግብ ለመድረስ የሚደርጉት ጥረት ስለሆነ እነዚህን ጥረቶቻቸውን እውን ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ሰዎች እራሳቸውን ለማሻሻል እምቅ አቅምና ችሎታ ካላቸው ከወዴት ነው የሚጀሚሩት የሚለው ነው፡፡ ብዙዎቻችን በስራችንና በህይወታችን የምንፈልገውንና የምንሻውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻልነው ዕቅዶቻችንንና ስኬቶቻችንን ከታች ከትንንሽ ነገሮች ስለማንጀምራቸው ነው፡፡ ቀድሞ የሚታየን ትልቁ ስዕል እንጂ ወደ ትልቁ የስኬት ጎዳና ለመድረስ ከትንሽ ነገር መጀመር እንዳለብን አንገነዘብም፡፡ ከዚህ በታች ከትንንሽ ነገር ተነስተን ወደ ትልቁ ስኬት ለመጓዝ የሚረዱንን ነጥቦች እንመለከታለን፡፡

ዸራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ)


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖታዊ ሥርዓት መሠረት የዛሬዋ እሁድ በዓለ ጰራቅሊጦስ ይባላል።

 "ወላጆች_እንደሌላቸው_ልጆች_አልተዋችሁም" (ዮ.ሐ14፥18)

✍️ጰራቅሊጦስ፡- ቃሉ ግሪክ ነው፡፡ ጰራቅሊጦስ ማለት

#መጽንኢ በእምነት የሚያጸና፣
#መንጽሒ ከኃጢአት የሚያነጻ፣
#ናዛዚ ያዘኑትን የሚያረጋጋ፣
#መስተፍስሒ፣ የተጨነቁትን የሚያስደስት፣
#ከሣቲ ምስጢርን የሚገልጽ ማለት ነው፡፡

#ጰራቅሊጦስ፡- መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የጰራቅሊጦስ በዓል ታሪክም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም የሚሠራውን ሥራ ከጨረሰ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያትን ወደ አባቴ እሄዳለሁ (አርጋለሁ) ሲላቸው ደነገጡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም መደንገጣቸውን አይቶ👉 (ልባችሁ አይደንግጥባችሁ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም እመኑ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ማለት ባባቴ ቤት በመንግሥተ ሰማያት ብዙ ማዕርገ ሀብታት አለ)

ዓርብ 5 ጁን 2020

ሕይወትን እንደ ንሥር አሞራ ኑር!


ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው ፍጡር ነው። ሌሎች ቁራዎችና ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሆነው ከበው ሲጮሁበት ወደ ፀሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል። ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ፀሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋባቸዋል!!
- ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል፣
- ንስር ከ 2.30-3 ሜ ይረዝማል፣
- ንስር ከ5-7 ኪሎሜትር ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣
- ንስር ለአደን እስከ 120 ኪሎሜትር አካሎ ይበራል፣
- ንስር መጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሆኖ ኃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በመምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣
- ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣
- ንስር ሲታመም ፀሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣
- ንስር 340° ማየት ይችላል። ከ360° በአንድ እይታ 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣
- ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ። ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል።
የመጀመሪያው ፤
ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል፣
ሁለተኛው ፤
አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ (መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል፣
ሶስተኛው፤
ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።
እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።
1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?
2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?
የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።
ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።
፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።
፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።
፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡
፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።
፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡
ንስር እጅግ ግዙፍ፣ እጅግ ጠንካራ፣ በሰማይ ከሚበሩ ሁሉ እጅግ የተለየ ባህርይ ያለው፣ ረጅም እድሜ መኖር የሚችል ሲሆን ድንቢጥ ግን ይህን ልዩ ፍጥረት ትፈታተነዋለች። ድንቢጥ ንስርን ፈተና የምትሆንበት ክንፎቹ ሥር በመግባት በመንከስ ነው።
ንስር ምንም እንኳን ድንቢጥ ፈተና ብትሆንበትም በቀላሉ እጅ አይሰጥም፤ በከፍታ በመብረር ብቃቱ ተጠቅሞ ወደ ላይ ይበራል። ድንቢጥ ንስር ሊደርስበት የሚችለው ክልል መብረር አቅሙ የላትምና ትወድቃለች። ድንቢጥም ፈተና ከመሆን አልፋ ትፈተናለች ትወድቃለችም።
ወዳጄ ሆይ:
ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ...ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡ.ኡ.. አትበል ፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የተሻለ ነገር ለመስራት ጣርና ሕይወትህን ቀይር!
ሰው ነህና የሥነፍጥረት ሁሉ ገዥ ተደርገህ ተፈጥረሃልና ሃይልህን፣ ጥበብህን ተጠቀም።
እንደ ድንቢጥ የሚፈታተንህ ዘረኝነት፣ ብሔርተኝነት፣ ፖለቲካ፣ የእምነት ጽንፈኝነት፣ አክራሪነት፣ ሙስና ወዘተ ሊጥልህ ከክብርህ ዝቅ ሊያደርግህ ይጥራልና በከፍታ ብረር፣ በአስተዋይነት ተንቀሳቀስ፣ የዘረኝነት መንደር፣ የብሔርተኝነት የፖለቲካ ጎጥ ውስጥ አትርመጥመጥ፣በሙስና ለመበልጸግ በእምነትህ ልትከፋፈል እጅ አትስጥ።
ለነዚህ ሥትል ከሰውነት ክብርህ ዝቅ አትበል። ሰው ሆነህ እንደተፈጠርክ ሰው ሆነህ ኖረህ ሰው ሆነህ እለፍ።
ፈተናዎችን እንደ ንስር በጥበብ እለፍ።

"አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሞተ"

"አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሞተ"

መምህር ዘለአለም ወንድሙ
፪ቆሮንቶስ 5: 14
አንዱ:- ማን ነው? አካላዊ ቃል ወልድን ነው። ከሶስቱ አካል አንዱ ወልደ እግዚአብሔር ነው
በምን ሞተ:- ለባህሪው ሞት የማይስማማው ጌታ በፈቃዱ ሞተ። ነፍሱን ሊጥላት እና ሊያነሳት ስልጣን አለውና ዮሐንስ 10: 17
የሞተው በፍቅሩ ነው ሮሜ 5: 8 ሐጢያተኞች ሳለን
ፍቅር ኋያል ወልድን ከመንበሩ ሳበው እንዲል
በግፍ ተሰቅሎ ሞተ
ዮሐንስ15: 22
ድንቅ ተአምራትን እያደረገ፣ ብዙ የመጽናኛ ቃል እየተናገረ፣ ድውያንን በተአምራት፣
መዝሙር 68: 4 በከንቱ የሚጠሉት በዙ፣ በረቱ
በስጋ ሞተ
፩ ጴጥሮስ 3: 18 ሞት በሚስማማው በስጋ ሞተ በባህሪው/በመንፈስ ህያው ነው
ለምን እንደሞተ:-
ጠላችን ዲያብሎስን ሊሽርልን ነው ለ5ሺ 5 መቶ ዘመን ወደ ሲኦል ስንጋዝ የነበርነውን የሰው ልጅ ነጻ ያወጣ ዘንድ ሞተልን
እብራዊያን 2: 14- በሞቱ በሞት ላይ አለቃ የነበረውን ከስልጣኑ ሰይጣንን ሊሽረው ሞተልን።
በሥጋ ምክንያት የሞተውን አዳምን በስጋ ማርያም አድሮ ከርሷ ተወልዶ፣ መከራ ተቀብሎ ፣ ሞቶ አዳነን።
ዮሐ3: 16 የዘለአለም ህይወት እንዲሰጠን ሞተ
ከሲኦል ባርነት ሊያወጣን ሞተ
ቆላሲስ 2: 14 በመከራ ሳለን የሚቃወመንን የእዳ ደብዳቤ ሊሽር፣ ነጻ ሊያወጣን፣ ሞትን በመስቀል ላይ ሊጠርቀው እኛን ነጻ ሊያወጣን፣ ህይወት ሊሰጠን፣ ሞተልን።
በህገ ልቡና የነበሩ ሌዋውያን ካህናት፣ ቅዱሳን፣ የተሰውት የእንስሳት መስዋእት ሊያድነን አሌቻለም። ይህ አልተቻላቸውም።
ትንቢተ ሆሴእ 13: 14 በትንቢት እንደተናገረ የሞትን መውግያ ሠበረ፣ ድል ነሳው።
ሞታችንን በሞቱ ሊያስወግድልን ሞተ
ሮሜ 15
ከርሱ አስቀድሞ አንዳችም ሃይል አልነበረም።
ዮሐንስ 11: እኔ ትንሣኤ እና ህይወት ነኝ እንዳለ ከሞት ቀስቅሶ በስጋ ሞቶ ህይወት ሰጠን።
፩ ቆሮንቶስ15: 3 ስለኛ ሃጢያት በሥጋ ሞተ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ፤ ሞቶ አልቀረም። መቃብሩን ባዶ አድርጎታል። ሞት ሊያስቀረው፣ ሊያሸንፈው አልቻለም።
ኢሣይያስ 25 :8 - ሞትን ለዘለዓለም ይውጣል፣ይሽረዋል፣ ያስወግዳል ተብሎ እንደተጻፈ
እንባችንን አበሰ፣ ስድባችንን ያስቀር ዘንድ ተሰደበ፣ መከራችሁን በቃችሁ ሊል መከራ ተቀበለ፣ ሞተልን፣ የትንሣኤ በኩራት ይሆን ዘንድ ተነሳ።
፩ቆሮ15: 20
እኛም የማይቀረውን ሞት ስንሞት ምተን አንቀርም እንነሳለን። ከሞት በኋላ መቃብር እንዳለው ከመቃብር በኋላ ትንሣኤ አለ።
ለእርሱ ክብር እንድንነሳ ሞተልን ፩ ቆሮንቶስ ፭: 14
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንድንኖር ሞተልን የአይናችንን አምሮት የሥጋችንን ፍላጎት እንዳንኖር ውድ ዋጋ ከፈለልን።
፩ ቆሮንቶስ 6: 19
ስለዚህ በሥጋችን እንድናከብረው የሞት ዋጋ ከፈለልን
ሮሜ 8: 12 የሥጋና የደሙ እዳ አለብን።
የምንሰማው ቃሉ፣ የምንጠራበት ሥሙ፣ የተቀበልነው ሥጋና ደሙ፣ እዳ አለብን።
በፈቃዳችን ፈቃደ ሥጋችንን ለፈቃደ ነፍሳችንን አስገዝተን ልንኖር ይገባል። ሐብታችን፣ እውቀታችን፣ ሠውነታችን ጣኦት ሊሆንብን አይገባም። ከዚህ እስር
ኤፌሶን 5: 14 አንተ በሐጢያት አለም መካከል የምትተኛ በንሰሐ ንቃ ከአእምሮ ሞት ንቃ የእግዚአብሔር ፍቅር ልብህን ይግዛው።
ከእርሱ ጋራ ለዘለዓለም እንድንኖር ስለኛ ሞተ።
፩ ተሰሎንቄ 5: 9
የህይወትን አክሊል እንድንቀዳኝ ሞተ
እግዚአብሔር ለምን ወደክ ሳይሆን ለምን አትነሳም ነው አለማው። ንሰሐ አዘጋጅቶልናል። በንሰሐ እንድንነሳ፣ በሕይወት አብረን እንድንኖር ሞተ።
በሞት እንድንመስለው እንዲሁ ደግሞ በትንሣኤው ልንመስለው ይገባናል።
ስለዚህ የተከፈለልንን ዋጋ አስበን ወልድ ወደዚህ አለም የመጣበትን አላማ እያሰብን በንሰሐ ሁላችንም ከወደቅንበት ኃጢአት እንነሳ፣ በህይወት እንመላለስ፣ በክብር ለዘለዓለም የተከፈለልንን ዋጋ የሚመጠን የጽድቅ ኑሮ እንኑር።

ወዴት ነን?


*. ብዙዎች ስለ ዘራቸው እምነታቸውን ዘንግተዋል፣
*. ብዙዎች ስለ ፖለቲካ ሲሉ እምነታቸው ላልቷል፣
*. ብዙዎች ስለ ጥቂት ብዙ ነገር አጥተዋል፣
*. ብዙዎች የእምነት ጥንካሬያቸውን ስለ እምነት ተቋም ይዞታቸው ገብረዋል፣
*. ብዙዎቹ በየቡድናቸው ስለ መደጋገፍ እውነትን፣ እምነትን፣ ሐቅን፣ በቁሟ ቀብረዋታል፣
*. ብዙዎች ስለ እኔን ይድላኝ፣ የኔ ይቅደም፣ የኔ ይብለጥ አገርን ወደኋላ አስቀርተዋል፣
*. ብዙዎች ስለ ምድራዊው ነገር ሰማያዊ ነገራቸውን በጥቅም አስይዘዋል፣
*. ብዙ የእምነት አባቶች የምእመኖቿ መሪ ሣይሆን የምድር ርስት ጉልት ይጨነቃሉ፣
*. ብዙዎች የሚሰባሰቡት ከአንድ ሁለት ስለሚሻል ሳይሆን ከዘርህ ዘሬ፣ ከባህልህ ባህሌ፣ ከሐይማኖትህ ሐይማኖቴ፣ ከፖለቲካህ ፖለቲካዬ፣ ከድርጅትህ ድርጅቴ ይበልጣል ብለው ነው፣
*. ብዙዎች ስለውጫዊ ልዩነታቸው ውስጣዊ አንድነታቸውን ክደዋል፣
*. ብዙዎች ብዙ በጎ ነገርህን ቀብረው በጥቂቱ ስተትህ ሐዘን ተቀምጠዋል፣
*. ብዙውች ለመከባበር ቦታ ነፍገው መቻቻል አንግሰዋል፣
*. ብዙዎች በራስ መንገድ ከማሰብ በቡድን ማሰብ ተጸናውቷቸዋል፣
*. ብዙዎች እውነትን ሳይሆን ሰወችን በመከተል ዘመናቸውን ይጨርሳሉ፣
*. ብዙዎች በጋራ መውደድ እና በጋራ በመጥላት ተጠልፈዋል፣

ሥጋ በል እጽዋት


ከላይ ባለ ገጽታቸው እጽዋት መስለው እጽዋት ናቸው ብለው ነፍሳት ሲጠጓቸው/ሲቀርቧቸው በውስጣዊ ማንነታቸው ሥጋ በል እጽዋት ናቸው። 
 
ሰወችም ዘመድ እጽዋት ናቸው ሥንል ሥጋ ዘመድ፣ ልጅ፣ እህት፣ ሚስት፣ አዛውንት፣ መነኮሳት፣ የሚበሉ የሚደፍሩ ሥጋ በል እጽዋት አመንዝራና ቅንዝራም ናቸው።
 
በአለም ላይ በወረርሽኝ የተከሰተው COVID19 ባስከተለው በቤት መቀመጥ #stayhome ብዙዎች የውሻ ባህሪ ያላቸው ወንዶች ወንድም፣ አባት፣ አጎት፣ ዘመድ መስለው የዋሃን ሴቶችን ያለ እድሜ ገደብ በመድፈር ከክብር አነውረዋቸዋል።
 
ሰው ስንላቸው እንስሳ እየሆኑ ጨቅላ ሴቶችን የበሉ እንስሳ ወንዶች ተበራክተዋል፤ በየሚዲያው ከሰማናቸው ከመቶ በላይ ሴቶች በዚህ ጥቃት የስነልቦና ስብራት፣ የሞራል ውድቀት፣ የሥጋ ጉዳት ቤት ይቁጠራቸው።
 
ይህ ክስተት እየተነሳን ማውገዝ የከፋ ነገር ባይሆንም ችግሩ በዚህ ብቻ አይፈታም።ልጆቻችንን ወንድሞቻችንን በቤት ስናሳድግ ሴቶችን አክባሪ፣ ወንጀልን የሚከላከል፣ ዝሙትን የሚጸየፍ አድርገን ልንቀርጻቸው ይገባል።
 
ሴቶቻችንም እያንዳንዷ ድርጊታችሁን ዝሙትን ቀስቃሽ ከሆነ ተግባራት ልትጠበቁ፣ ልጆቻችሁን እና እህቶቻችሁን ከዚህ ተግባር ልትገድቡ ይገባል። 
 
መንግሥትም አገርንና ትውልድን አንገት የሚያስደፋ ተግባራትን በሚያከነረውኑት ላይ ከሌሎች አገራት ህግ ተሞክሮ በመውሰድ ጠንካራ ህግ በማውጣት የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የሴቶችን የመኖር መብት ከሥጋ በል እጽዋት ወንዶች ሥጋት ነጻ ሊያደርግ ይገባል።
 
ደፋሪዎችን አወግዛለሁ፤ ከተጎዱ ሴቶች ጉን እቆማለሁ።

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...