በአንድም በሌላም እንናገራለን:ጆሮ ያለዉ ይስማ:ልብ ያለዉ ልብ ይበል፡፡ የታዘብነዉን የምንናገርበት፣ የምናዉቀዉን ለትምህርት እና ለእርምት የምናዉልበት ከወገንተኝነት ነፃ የሆነ መድረክ ነዉ፤ …ሁሌም ቢሆን አስተያየቶችን እና መልዕክቶችን ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡
ማክሰኞ 18 ማርች 2014
‹‹ቅዳሴ››
ያለው ዕለት ለንጋቱ ቦታውን ለመልቀቅ መሰናዶውን ያጠናቀቀ ይመስላል በቤቴ መስኮት ቀዳዳ የሚገባው የንጋት ብርሃን “ነግቷል ተነስ” የሚል ሰው ያህል ከፊት ለፊት በቀዳዳው እየገባ ይጎነትለኛል የጭላንጭሉን ብርሃን ተልዕኮ የሚያጨናግፈው ድብርት “አይዞህ ተኛ ገና ነው” እያለ ያዘናጋኛል፤ አሁንም በመስኮቱ የሚገባው የብርሃን ጭላንጭል ገብቶ ገብቶ ቤቱን በሰፊው ተቆጣጥሮታል፣ አካላቴ ሁሉ ሳምንቱን መንገድ ሲጓዝ እንደከረመ አንጓዎቼ በሙሉ የመዛል ስሜት ይሰማባቸዋል፡፡ ከሁለቱ አንደኛዋ አይኔ ብቻ ብርታት ይሰማታል እንጂ ሁለተኛዋ ጭራሽ የለችም ማለት ይችላል፤ አንደኛው ሲተኛ እርሷ ነቅታለች እርሱን ለመቀስቀስ ባደረገችው ጥረት እርሷም ድካም ተሰምቷት ማሸለብ ጀመረች የሌላት ልብሴን ገላልጣ ለመውጣት ጡንቻዋን ያፈረጠመችው ክንዴ ብርድ ሲያኮማትራት ተመልሳ ከብርድልብሱ ሾልካ ገባች ገና ተመኝታ የተገናኘች ይመስል እንቅልፍ ጣማት በዚያቹ በቀጫጫ ክንዷ ራሷን በራሷ እቅፍ አድርጋ ጋደም እንዳለች የእንቅልፍ ማዕበል ይዟት ጥርግ አለ፡፡ በልቦናዋ በብርቱው ምሽት ያሰበችው የዕለት ሰንበት የቅዳሴ መርሃግብርና ጠዋት በብርሃኑ ጭላንጭል መካከል ትዝ ያላት ልቡናዋን እንደብል በልቶ ጨርሷታል ሰውነቴ ለእንቅልፍ ተማርካ ከሞቀው መኝታዋ በመሆን ቅዳሴን ታስቀድስ ጀመር፤ ልክ ከመቅደሱ ፊት እንደቆመ አስቀዳሽ አሁን ለዛለችው ገላዬ ንፍቁ ዲቆኑ “ጸልዩ በእንተ ያበውኡ መባእ …” የሚለውን አዚሞ ሕዝቡም “ተወከፍ መባኦሙ ለአኃው” የሚለውን ጨርሶ ዲያቆኑ በድጋሜ “ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት” ብሏል የዛለው ገላዬም “ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ” ብላ ሰግዳለች
ይድረስ ለመንግስታችን፡
አንዲት አገር በማደግ ላይ ካለች ችግሮች እንዳሉ ይታወቃል ህብረተሰቡም ደግሞ የሚቻለዉን
ያህል ሊረዳና ችግሮችን ሊቋቋም ግድ ይላል እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ጨዋ ህዝቦች ከማንም በላይ ናቸዉ፤ ሆኖም ግን እየተካሄደ ያለዉ
ግን ከመጠን በላይ እየሆነ ስለሆነ መንግስታችን እና ባለ ድርሻ አካላት አፋጣኝ የሆነ መፍትሄ እና ተለዋጭ አቅርቦቶችን ሊያቀርቡ
ግድ ይላል፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ መብራት ሃይልም ሆኑ የኢትዮ ቴሌኮም ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም አገልግሎት ለሚሰጡት ህዝባቸዉ የገቡት
ቃል ኪዳን ሊጠበቅ ይቅርና ተጨማሪ ቃል ኪዳን የሚያስፈልገዉ ሆኖ እየተገኘ ያለ ሁኔታ ላይ እነገኛለን፡፡ የተቀሩትም እንደ ዉሃ
እና ፍሳሽ ያሉት በብርሃን ፍጥነት እየተከተሉት ይገኛሉ ከዚህ ቀደምም አልተለዩትም፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪ ቁጥር ከዕለት ወደ እለት
እየጨመረ መምጣቱ እየታወቀ ተመጣጣኝ የሆነ የዉሃ አቅርቦት ዝግጅት እንዳልተደረገበት መንግስታችንም የሚክደዉ ጉዳይ አይደለም፤ ምናልባት
የተደረገ ተጨማሪ ነገር ቢኖር ለጽዳትና ዉበት ክፍያ ተጨምሯል በዉሃ ቢል ላይ፡፡
መብራት ኃይልና ቴሌ ግን ከዕለት ወደ ዕለት ህብረተሰቡን በብርሃንና በኔትወርክ
ማጥት ከማስመረሩ ባሻገር የዕለት ከዕለት ስራዉን እያደናቀፈበት ይገኛል፡፡
መብራት ኃያሎችም ባንድ ወቅት ካሁን በኃላ ሻማ የምታበሩት ለልደት ብቻ ነዉ በማለት አላግጠዉብን ነበር፤ ቴሌዎችም ኦፕቲካል ፋይበሩን ዘርግተን ስንጨርስ
…. … … ወዘተ ወዘተ ብለዉ ያወሩት ጉዳይ ኦፕቲካል ፋይበራቸዉ አንጀት ሆኖ ይኸዉ በኔትወርካቸዉ አንጀታችንን በክፍያቸዉ ኪሳችን
እየመለጡት ይገኛሉ፡፡(ይሁን እንግዲህ እነሱን አያሳጣን ማንን እናማ ነበር አንድም ማን ላይ ቁጭብለሽ ማንን ታሚያለሽ እንዲሉ…..)
ክቡር መንግስታችን የሆነዉስ ሆነና፡-
ዓርብ 14 ፌብሩዋሪ 2014
የቤቱ ስርአት
ሰወቹ
እጅግ የተከበሩ እንዲያዉም ለምድር ለሰማይ የከበዱ ፣ የታፈሩ፣ ባእለጠጋ፣ሳርቅጠሉ አንቱ እያለ የሚያከብራቸዉ፣እነርሱን በመንገድ
እንዃን ሰዉ ቀድሞ የማይሻገራቸዉ፣በእግሩ የሚሄድ ቆሞ፣ በፈረስ ያለዉ ወርዶ እጅ ነስቶ አክብሮ የሚሸኛቸዉ፣የሰዉ ፍቅር እንደ ምድር
አሸዋ የበዛላቸዉ፣… ሁለት ሰዎች ነበሩ በትዳር ምሥጢር አንድ የሆኑ፤ መቸስ ላለዉ ይጨመርለታል ነዉና
ዋሊያዎቹ
የከሳቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት
ዋሊያ የሚለዉን ቃል በሁለት መልኩ ይፈታዋል፤
1ኛ. መጠንዋ ከወፍ ላቅ ከዶሮ ዝቅ ያለች ላባዋ
ቡላ ሆድዋ ነጭ መብልዋ ማሽላ አዳርዋ ከዛፍ ላይ ነዉ፡፡
2ኛ. የበረሐ እንስሳ በእያንዳንዱ ቀንድ ላይ
ብዙ ቀንድ የሚያበቅል፡
በማለት ይገልፁታል፡፡
ወክፒድያ የተባለዉ ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ
የአይቤክስ ዝርያ ይለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ በእግር ዃስ
የሚጫወተዉም ቡድን ስያሜዉን ያገኘዉ ከዚህ ብርቅዬ እንስሳ በመነሳት ዋሊያ ብርቅዬዉ በሰሜናዊዉ በረሐማ እና ተራራማ ስፍራ የሚኖር
የኢትዮጵያ ኩራት እንደመሆኑ እነዚህም ተጫዋቾች ተራራ ሸለቆ ሜዳ ገደል ሳይሉ በየብስ እና በአየር ላይ እየተጓዙ አገርንና ህዝብ
ስም የሚያስጠሩ የኢትዮጵያ ኩራቶች ናቸዉ፡፡
በአካለ መጠን ያልገዘፉ ከማንም ግን የማያንሱ
በጥበብ የተካኑ እለት እለት በብቃት እየበለፀጉ ያሉ ከ31 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን ታሪክ ለመቀየር የበቁ ጀግኖች መጠሪያ ነዉ፤
ለዓለምም ሆነ ለወገኖቻቸዉ ብርቅ የሆኑ ታሪክ የማይዘነጋቸዉ ድልን የተቀናጁ ታሪክን የፃፉ ናቸዉ፤ ዋሊያዎቹ፡፡
ዋሊያዎቹ ከዚህ ቀደም ለ20ኛዉ ዓለም ዋንጫ ዝግጅት
የተለያዩ ፍልሚያዎችን ማድረጋቸዉን መዘገባችን የሚዘነጋ አይደለም፤ ከአፍሪካ ምርጥ 10 አገሮች አንዷ ሆና በስተ መጨረሻ ደግሞ
ለዓለም ዋንጫዉ ፍጥጫ ለመሳተፍ ከአቻዋ ከናይጄሪያ ጋር ተመድባ በደርሶ መልስ ጨዋታ በጨዋታና በተለያዩ ምክንያቶች ከዉድድሩ በሽንፈት
ተገላለች፡፡ ይህንንም የመጀመሪያዉን ግጥሚያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደጋፊዉ ፊት በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ስታድየም ጥቅምት
3 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ መካሄዱ ግድ ቢለንም ሽንፈቱ ተስፋችንን አላሟጠጠዉም ነበር እዛዉ ናይጀሪያ
ላይ ተስፋ ይኖረናል የሚል ዕድል ነበርና እስከዚያች ቀን ድረስ ኢትዮጵያዉያን በመላዉ ዓለም እንደ ድር አብረን ዋልያዎቹን ስንደግፍ
ነበር፡፡ ምንም እንኳን ዉጤቱ አስደንጋጭ ቢሆንም … …
ዋሊያዎቹ ለ20ኛዉ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻዉን
የማጣሪያ ጨዋታ ከአቻዉ የናይጀርያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ደርሶ መልስ ጨዋታን በማድረግ ድል ከቀናዉ ለዓለም ዋንጫዉ በኢትዮጵያ ታሪክ
የመጀመሪያዉን ጉዞ ወደ አዘጋጅ አገርዋ ብራዚል ያደርግ ነበር ግን አልሆነም፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአቻዉ ከናይጄሪያ ቡድን
ጋር ወደ ሰባት ጊዜ ተገናኝተዉ አምስቱን ድል በመደረግ አንዱን አቻ በመዉጣት አንዱን በበላይነት ተለያተዋል፡፡ ያ ሁሉ አልፎ በዘመናችን
ያላየነዉን ድል ያሳየን፣ እግር ኳስን እንደምንችልና አይደለም ለአፍሪካ ለዓለም ዋንጫ መቅረብ እንደሚቻል ያሳየን እና ያሳመነን
የዘመናችን የእግር ኳስ ጀግና የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ዋልያዎቹ ከዓለም ዋንጫ መሰናበትን ተከትሎ እና ከዚያም በኃላ
በተደረጉት ዉድድሮች ሰበብ ጨዋነት በጎደለዉ ስርአት፣ ዉለታዉን በዘነጋ ድርጊት፣ የርሱንም ሆነ የስፖርት ቤተሰቡን ልብ በሚሰብር
ሁናቴ በጨዋ ደንብ ቁጭ ብለዉ ሳይነጋገሩ እና ሳይመካከሩ ከአሰልጣኝነት እንደሸኙት እሱም እኛም ከሚዲያ ሰማን (አቶ ሰዉነት እንዳለዉ)፡፡
ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ህዝብ መርጦ እስካስቀመጣቸዉ ድረስ ያለ ህዝብ ተሳትፎ እና ዉይይት ምንም እንኳን ቢደክም ዉጤቱ ባያምር የትላንትናዉን
አንበሳችንን ጀግናችንን እንዲህ እንደ ደሃ መቃብር ለማሰናበት ፈጠኑ? ሰዉነት እኮ እኛን ብቻ አልነበረም ያስደሰተዉና ያስፈነደቀዉ
ዓለማችንን ያሳየን ከሰዉ እኩል በኣለም መድረክ እንድንጣወቅ ባንዲራችን እንዲዉለበለብ ያደረገዉ እነሱንም ጭምር እንጂ (የፌዴሬሽኑን
ሰዎች ጨምሮ)፡፡
በእዉነት ሰዉ ሳያዘጋጁ እሱን ማባረር ያስፈለጋቸዉ
ምስጢሩ ምን ይሆን?
ያኔ አይዞህ በርታ ከጎንህ ነን ድል ይቅናህ ጀግናችን ነህ ያሉት ባለስልጣኖቻችን ዛሬ ሲባረር ወዴት ይሆኑ?
እንደሆነ ከጥቁር አበሻ እስከ ነጭ ፈረንጅ ድረስ ቀያይረን አሰልጣኝ አምጥተን ነበረ ነገ ደግሞ ማን ይመጣ ይሆን?
የሰዉነታችንስ መድረሻስ ወዴት ይሆን?
እኛንማ ቅስማችንን ሰብረዉ ጥለዉናል፤ ሰዉነት ለምን ተነሳ ዘለዓለሙን ይቀመጥ የሚል
ከንቱ አመለካከት የለኝም አቶ ሰዉነት ራሱም እንዲህ አይነት አቋም እንደሌለዉ ለዉጥ እንደሚያስፈልገን በአደባባይ ተናግሯልና እኔም
እንዲሁ ለዉጥ እፈልጋለሁ፡፡ የሚመጣዉ ግን የሚበላ እና የማያበላ ለዉጥ ለማምጣት ብቻ ይሁን፡፡ ቸር ይገጠመን ለእግር ኳሳችን ዳግም
ትንሳኤ ይሁንለት፡፡
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)
ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!
መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡
ትቶ እና ችሎ
ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...
-
የጊዜ አጠቃቀም መግቢያ ስኬታማ የጊዜ አጠቃቀም ያዳበረ ሰራተኛም ሆነ ግለሰብ ጊዜዉን በመርሃግብር እና በዕቅድ ይመራል፤ ይህ ሰዉ ህይወቱን የሚመራዉ በዕድል ሳይሆን ...
-
ሰሞኑን በዚች በምድራችን ‹‹ጫካው ለዛፎች ብቻ›› በሚል ዛፎች ተሰባስበው በዱር አራዊቶች እና አዕዋፎች ላይ የአቋም መግለጫ አወጡ አሉ፤ ከመግለጫው ሥር እንደ አብይ ርዕሰ ጉዳይ ያደረጉት ጫካው ለእኛ ለዛፎች ብ...
-
በክፍል አንድ “ፍቅር በFace book ” በሚለው እውነተኛ ታሪክ ላይ መሰረት ያደረገ ክፍል ማቅረባችንን ሳሙኤል በFace book ላይ የተዋወቃትንና ሳይስቡት ፍቅር ውስጥ ገብተው በኃላም ሕይወትን የመጀመር አዝማሚያ...