አይነጋ የለ ነጋ ጊዜው 11፡30 ሰዓት ነው የሞላኋት የግድግዳ ሰዓቴ ድምፅ አሰማች እኔም ከእንቅልፌ ነቃሁ ሲረፍድብኝ እንዳላደርኩ ሳይረፍድብኝ ወደ ቅዳሴ ሄድኩ የቀን መዘውሩ ተገባዶ ሌሊቱ ለንጋት ስፍራውን መልቀቁን የተገነዘበ ሕዝበ አዳም ታጥቆ ተነስቷል ፀሐይ የንጋት ብርሃኗን ለመፈንጠቅ ሰማዩን ፏ አድርጋዋለች ነጭ ነጠላ የለበሱ ምዕመን መንገዱን ሞልቶታል አብያተ ክርስቲያናት የጥሪ ደውላቸውን (ድምፃቸውን) እያሰሙ ነው ሱቆችም የአሁኗን ንጋት በጥዋፍና ሻማ ዕጣን ሽያጭ ጀምረዋል ነዳያን ቤተክርስቲያን ጌጥ መስለው ከደጇ በረድፍ ተቀምጠዋል አስቀዳሹ እኔም አላረፈድኩም በሚል ስሜት በርጋታ እየተራመድኩ የደጃፉን በር ተሳልሜ ከግቢው ከመግባቴ ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ …›› የሚለውን የካህኑ ድምፅ በዜማ ተሰማኝ ተፈጥሮ ካስዋበው ከቤተክርስቲያኑ አጸድ ሥር ተጠንቅቄ በመቆም እጆቼን ከላይ ሆኖ ወደሚያየኝ አምላክ በማንጋጠጥ ዘረጋሁ ዙሪያው ጭር ያለው ግቢ በምዕመናን እየተጨናነቀ መጣ የቅዳሴው ‹የተሰጥኦ› ዜማ ሥፍራውን የመላዕክት ከተማ ኢዮር፣ ኤረር፣ ራማን አስመስሎታል የዕጣን የሽታ መአዛ ግቢውን አውዶታል ነፍሳችን እጅግ ተደስታለች ቅዳሴውን የሰማይ አዕዋፍ በድምፃቸው አብረው ሲያጅቡት የበለጠውን ውበት ሰጥተውታል የዕጣን ጢስ ወደላይ ማረግ የተመለከተ ልቡናችን አብሮ ከመንበረ ፀባኦት ደርሷል
የዕለት የዓመት ስሜቱን ከአምላኩ ፊት ቆሞ ልቡናችን ያነበንብ ጀመር በዚህን ሰዓት ነበር ባላገሯ ሴትዮ በቅዳሴው መካከል እንደ ወፍ በረው ከሴቶች በር ፊት ለፊት መጥተው ፍግም ብለው የሰገዱት ‹‹አንተ ገብርኤል ፣ አንተ እውነተኛ ታቦት ልብ ትላለህ ትመለከተኛለህ …›› አሉ በምሬት ቃል የሰው ሁሉ ልቡና ከተጓዘበት ከዕጣን ጎዳና ከመንበረ ጸባኦት ከእግዚአብሔር ፊት ከመቀጽበት ቁልቁል ወረደ በሴትዮዋ አነጋገር ሁሉም ድንጋጤ መንፈሱን ወረሰው አብዛኛው ሠው ከላይ ወደታች ከግራ ወደቀኝ አማተበ ሴትዮዋ እንባ ይተናነቃቸዋል ቀዩ ፊታቸው እየገረጣ መጥቷል በእልክ ከንፈራቸውን ነክሰው ፊታቸውን ወደ ሕዝቡ ዞር አድርገው ከጭንቅላታቸው ላይ ያደረጓትን የቆሸሸች ነጠላ ደልደል አደረጓት ቁና ቁና እየተነፈሱ ወደ ሕዝቡ መካከል ጠጋ ብለው ቆሙ የሚናገሩት ነገር ባይኖርም ከራሳቸው ጋር በውስጣቸው ትግል እንደገጠሙ ሳያቸው ከሰው ፊት እያጋለጣቸው ነው እጃቸውን ሲያወራጩ ቆዩና ሆዳቸውን የዝምበል ያህል ጥብቅ አድርገው ያዙት ሰው ወደቅዳሴው ተመልሶ ተሰጥኦውን እየተቀበለ በተመስጦ ከእግዚአብሔር ጋር ንግግሩን ቀጥሏል ዲያቆኑ ‹‹ጸልዩ››ን በዜማ ሲል ምዕመኑን አቡነ ዘበሰማያትን በለሆሳስ ይፀልይ ጀመር ሆድ የባሳቸው ሴትዮ ብቻ ብሶታቸውን ለገብርኤል ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ያሰማሉ ‹‹… ገብርኤል! አንተ ገብርኤል በእውነት ከሌላው እኩል ቆሜ የምሄድ እኩል አንድ ሰው ነኝ ከሞቱት ሰው እኔ በምንድን ነው የምሻለው እስኪንገረኝ?...›› እያሉ ከፊቱ ቆመው ያነባሉ ምዕመኑ በድጋሜ ልቡ ተሰረቀ ከፊሉ የሴትዮዋን ሁኔታ ተመልክቶ ከንፈር ይመጥላቸው ጀመር ነገሩ ምንም እንኳን አዲስ ባይሆንብኝና ቤተክርስቲያን የችግረኞች የችግራቸው ማሳሰቢያ መሆኗን ባልዘነጋም በቅዳሴ መካከል እንዲህ አይነት ትዕንግርት ማየቴ ገረመኝ የሴትዮዋ ሁኔታ ልቡናዬን ሰረቀውና አልመልስ አለኝ ምን ሆነው ይሆን በሚል ሁኔታ እንድጨነቅ አደረገኝ ሴትየዋ አሁንም መነጋገራቸውን አላቆሙም ይልቁንም ብሶታቸው እየጨመረ መጣ ስሜታቸው እየተቀጣጠለ ‹‹… ያቃጥላት ስታቃጥለኝ አደረች አንተ ገብርኤል አንተ እውነተኛው ታቦት …. አንቺ ማርያም እንደው በዕለተ ቀንሽ አንድ ነገር ካላሳየሽኝ መቸሽ …›› አሉና በመገረም ዘና ብላ በመዳፋቻ አገጫቸውን በአንድ እጃቸው ወገባቸውን ይዘው ተከዝ ማለት ጀመሩየሆነው ነገር ምንም ባይገባኝ የጎረቤታሞች ጣጣ ይሆናል ብዬ ገመትኩ መቸስ የአንዳንድ ጎረቤታሞች ፀባይ ከአጋሞ የተጠጋ ቁልቋል መሆን ነው እንደሆነ፤ ሴትየዋ ራመድ አሉና ከምስለ ፍቁር ወልዷ ፊት ቆሙና ድምፅ ሳያሰሙ ተነጋገሩና ሰገዱ ደግሞ አለፍ ብሎ ካለው ከመድኃኔዓለም ሥዕል ፊት ለፊት ደግመው ሰገዱ ቅዳሴ ይሁን ምን ይሁን ሰው እንዳለም ማየታቸውን እንጃ ‹‹… እንቅልፌን አስትተሽ በሌሊት ብን አድርገሽ ከቤቴ እንዳስወጣሽኝ አንቺንም የአባቴ አምላክ ከሐገር ብን ያርግሽ … ቤቴን ሰላም እንዳነሳሽው ሰላም ይንሳሽ … መውጫ መግቢያ እንዳሳጣሽኝ መግቢያ መውጫሽን ይድፈንብሽ የሰማዩ ደጃፍ ይዘጋብሽ…›› አሉና የደከመው ሰው ያህል አብዝተው ተነፈሱ ከበፊቱ ይልቅ እግራቸው ፈርከክ አድርገው እጃቸውን ወደ ኋላ በማድረግ ቆዝመው ለረጅም ሰዓት ቆሙ ምን ሲያስቡ እንደቆዩ እንጃ በጣም ተናደው ከመስኮት ላይ ሰዎች ለኩሰው ያቆሙትን ሦስት ሻማ አተኩረው ተመልክተው ጥርሳቸውን በመንከስ ‹‹እኸ….›› አሉ ‹‹አንተ ገብርኤል …. አንቺ ማርያም … የእኔን ቤት ድፍንፍን ጭልምልም አድርጋችሁ ለእናንተ እዚህ ሻማ ይብራላችሁ አሉና፤ አጥፍተውት እግራቸውን አጣጥፈው ትንሽ ልጅ መሰለው ግርግዳውን ተጠግተው ቁጭ አሉና ስቅ ስቅ ብለው አለቀሱ ሆዴን ባርባር አለው እጅግ አሳዘኑኝ በጣም ገረመኝ ተጠግቼ ምን እንደነካቸው ልጠይቅ አስብ አዳረኩና ሰው ምን ነካው ቢለኝስ አልኩ ደግሞም ቅዳሴ ላይ ነን ሴትየዋ አሁንም ጎንበስ እሉ መሬት መሳሙንና እጃቸውን እያወራጩ ማውራቱን አላቋረጡም፡፡ መለስ ብዬ ቅዳሴውን ሳዳምጥ ዲያቆኑ ቅዳሴውን አጋምሶት ‹‹ጸልዩ በእንተ ወንጌል ቅዱስ››ን በዜማ ብሎ የዕለቱን ምስባክ ከመዝሙረ ዳዊት ከሰበከ በኋላ ‹‹ሃሌ ሉያ ቁሙ ወአጽምዑ ወንጌለ ቅዱስ ዜናሁ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ›› እያለ ነበር ከሴትዮዋ የኔ ሁኔታ ግርም አለኝ በየሳምንቱ በሥርዓት ሳላስቀድስ መግባቴ ባለፈው ሣምንት ከቅዳሴ ላይ ተጠርቼ ሔድኩ አሥራ አምስት ቀን አክፍዬ ርቦኝ ሳዛጋ ዋልኩ በቅዳሴ ሰዓትም ወድቄ ስተኛ በእንቅልፍ የትንሣኤን ቅዳሴ አጋመስኩ ዛሬ ደግሞ የሠው ገበና ሣዳምጥ ልዋል አዬ የኔ ነገር …›› የእመቤታችን ዕለት በመሆኑና እሁድ በመሆኑ ሠው ይጎርፋል ቤተክርስቲያን እጣን ጥዋፍ ብቻ የቸገራት ይመስል ቅዳሴውን እያቋረጠ እየገባ የ0.25 ሣንቲም ጠዋፍና እጣን እየወረወሩ ወደ ቤቱ የሚመለስም ሞልቷል ተቸግራለችና ሮጥ በልና አድርስህላት ና የተባለ ይመስል ከነጋ ጀምሮም እዚያው ቆሞ ያነጋውም እንቅልፉን ተኝቶ የሚጨርስ ይመስል ከሥፍራው ቆሞ የሌለም አለ፡፡ የውስጡን ችግር ቤት ይቁጠረው፡፡ ካህኑ የዕለቱን ወንጌል አንብበው ሲጨረሱ ገረመኝ የሴትዮ ከጎረቤቷ ተጣልታ መምጣት የወንጌሉ መልዕክት ገርሞኝ የእግዚአብሔርን ሥራ አደንቅ ጀመር ሴትየዋ ከተቀመጡበት ተነስተው ቆሙ ዲያቆኑ ቅዱስ ወንጌልን እያዞረ ሲያሳልም ሲሰግዱ ሲያወሩ ከቆዩ በኋላ ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ በስጨት ብለው በ በቃ ተወው አይነት ሁኔታ እጃቸውን ወንጨፍ አድርገው ቅዳሴውን ጥለው የብዙ ሰው ልቡና አስከትለው ከየጓዳቸው ከየብሶታቸው ጨምረው ሄዱ እያንዳንዱ ሠው ሴትዮዋን ይመስል ለየግሉ በየራሱ መንገድ እየተጓዘ በሐሳብ ይነጎድ ጀመር አልፎ አልፎ ከንፈሩን የሚመጥ በረጅሙ የሚተነፍስ በዛ ግቢው በሐሳቡ ታወከ ሴትዮዋ የሐሳብና የጭንቀት መንፈስን ዘርተው የሄዱ መሰለ፡፡
ይቆየን!

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ