ዓርብ 14 ፌብሩዋሪ 2014

ዋሊያዎቹ


የከሳቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ዋሊያ የሚለዉን ቃል በሁለት መልኩ ይፈታዋል፤

1ኛ. መጠንዋ ከወፍ ላቅ ከዶሮ ዝቅ ያለች ላባዋ ቡላ ሆድዋ ነጭ መብልዋ ማሽላ አዳርዋ ከዛፍ ላይ ነዉ፡፡

2ኛ. የበረሐ እንስሳ በእያንዳንዱ ቀንድ ላይ ብዙ ቀንድ የሚያበቅል፡

በማለት ይገልፁታል፡፡

ወክፒድያ የተባለዉ ደግሞ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ የአይቤክስ ዝርያ ይለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ወክሎ በእግር ዃስ የሚጫወተዉም ቡድን ስያሜዉን ያገኘዉ ከዚህ ብርቅዬ እንስሳ በመነሳት ዋሊያ ብርቅዬዉ በሰሜናዊዉ በረሐማ እና ተራራማ ስፍራ የሚኖር የኢትዮጵያ ኩራት እንደመሆኑ እነዚህም ተጫዋቾች ተራራ ሸለቆ ሜዳ ገደል ሳይሉ በየብስ እና በአየር ላይ እየተጓዙ አገርንና ህዝብ ስም የሚያስጠሩ የኢትዮጵያ ኩራቶች ናቸዉ፡፡

በአካለ መጠን ያልገዘፉ ከማንም ግን የማያንሱ በጥበብ የተካኑ እለት እለት በብቃት እየበለፀጉ ያሉ ከ31 ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያን ታሪክ ለመቀየር የበቁ ጀግኖች መጠሪያ ነዉ፤ ለዓለምም ሆነ ለወገኖቻቸዉ ብርቅ የሆኑ ታሪክ የማይዘነጋቸዉ ድልን የተቀናጁ ታሪክን የፃፉ ናቸዉ፤ ዋሊያዎቹ፡፡

ዋሊያዎቹ ከዚህ ቀደም ለ20ኛዉ ዓለም ዋንጫ ዝግጅት የተለያዩ ፍልሚያዎችን ማድረጋቸዉን መዘገባችን የሚዘነጋ አይደለም፤ ከአፍሪካ ምርጥ 10 አገሮች አንዷ ሆና በስተ መጨረሻ ደግሞ ለዓለም ዋንጫዉ ፍጥጫ ለመሳተፍ ከአቻዋ ከናይጄሪያ ጋር ተመድባ በደርሶ መልስ ጨዋታ በጨዋታና በተለያዩ ምክንያቶች ከዉድድሩ በሽንፈት ተገላለች፡፡ ይህንንም የመጀመሪያዉን ግጥሚያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደጋፊዉ ፊት በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ስታድየም ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ መካሄዱ ግድ ቢለንም ሽንፈቱ ተስፋችንን አላሟጠጠዉም ነበር እዛዉ ናይጀሪያ ላይ ተስፋ ይኖረናል የሚል ዕድል ነበርና እስከዚያች ቀን ድረስ ኢትዮጵያዉያን በመላዉ ዓለም እንደ ድር አብረን ዋልያዎቹን ስንደግፍ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ዉጤቱ አስደንጋጭ ቢሆንም … …

ዋሊያዎቹ ለ20ኛዉ የዓለም ዋንጫ የመጨረሻዉን የማጣሪያ ጨዋታ ከአቻዉ የናይጀርያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ደርሶ መልስ ጨዋታን በማድረግ ድል ከቀናዉ ለዓለም ዋንጫዉ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዉን ጉዞ ወደ አዘጋጅ አገርዋ ብራዚል ያደርግ ነበር ግን አልሆነም፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአቻዉ ከናይጄሪያ ቡድን ጋር ወደ ሰባት ጊዜ ተገናኝተዉ አምስቱን ድል በመደረግ አንዱን አቻ በመዉጣት አንዱን በበላይነት ተለያተዋል፡፡ ያ ሁሉ አልፎ በዘመናችን ያላየነዉን ድል ያሳየን፣ እግር ኳስን እንደምንችልና አይደለም ለአፍሪካ ለዓለም ዋንጫ መቅረብ እንደሚቻል ያሳየን እና ያሳመነን የዘመናችን የእግር ኳስ ጀግና የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ዋልያዎቹ ከዓለም ዋንጫ መሰናበትን ተከትሎ እና ከዚያም በኃላ በተደረጉት ዉድድሮች ሰበብ ጨዋነት በጎደለዉ ስርአት፣ ዉለታዉን በዘነጋ ድርጊት፣ የርሱንም ሆነ የስፖርት ቤተሰቡን ልብ በሚሰብር ሁናቴ በጨዋ ደንብ ቁጭ ብለዉ ሳይነጋገሩ እና ሳይመካከሩ ከአሰልጣኝነት እንደሸኙት እሱም እኛም ከሚዲያ ሰማን (አቶ ሰዉነት እንዳለዉ)፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ህዝብ መርጦ እስካስቀመጣቸዉ ድረስ ያለ ህዝብ ተሳትፎ እና ዉይይት ምንም እንኳን ቢደክም ዉጤቱ ባያምር የትላንትናዉን አንበሳችንን ጀግናችንን እንዲህ እንደ ደሃ መቃብር ለማሰናበት ፈጠኑ? ሰዉነት እኮ እኛን ብቻ አልነበረም ያስደሰተዉና ያስፈነደቀዉ ዓለማችንን ያሳየን ከሰዉ እኩል በኣለም መድረክ እንድንጣወቅ ባንዲራችን እንዲዉለበለብ ያደረገዉ እነሱንም ጭምር እንጂ (የፌዴሬሽኑን ሰዎች ጨምሮ)፡፡  

በእዉነት ሰዉ ሳያዘጋጁ እሱን ማባረር ያስፈለጋቸዉ ምስጢሩ ምን ይሆን?

ያኔ አይዞህ በርታ ከጎንህ ነን ድል ይቅናህ  ጀግናችን ነህ ያሉት ባለስልጣኖቻችን ዛሬ ሲባረር ወዴት ይሆኑ?

እንደሆነ ከጥቁር አበሻ እስከ ነጭ ፈረንጅ ድረስ ቀያይረን አሰልጣኝ አምጥተን ነበረ ነገ ደግሞ ማን ይመጣ ይሆን?

የሰዉነታችንስ መድረሻስ ወዴት ይሆን?

እኛንማ ቅስማችንን ሰብረዉ ጥለዉናል፤ ሰዉነት ለምን ተነሳ ዘለዓለሙን ይቀመጥ የሚል ከንቱ አመለካከት የለኝም አቶ ሰዉነት ራሱም እንዲህ አይነት አቋም እንደሌለዉ ለዉጥ እንደሚያስፈልገን በአደባባይ ተናግሯልና እኔም እንዲሁ ለዉጥ እፈልጋለሁ፡፡ የሚመጣዉ ግን የሚበላ እና የማያበላ ለዉጥ ለማምጣት ብቻ ይሁን፡፡ ቸር ይገጠመን ለእግር ኳሳችን ዳግም ትንሳኤ ይሁንለት፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...