ዛሬ ሰኞ መጋቢት 9/2005 ዓ.ም. ነዉ፤ ሰኔና
ሰኞን አለመሆን እንዳለ ሆኖ ለሰራተኛና ለተማሪ ደሞ የባሰዉን ነዉ፡፡
የትራንስፖርት ችግር ደግሞ ሰኞ አያዉቅ ማክሰኞ
የለ ሁሌ ችግር ነዉ ለነገሩ ለእናንተ መንገር ለቀባሪዉ አረዱት ይሆንብኛል፡፡
አሁን ስለትረንስፖርት ችግር ላወራ አይደለም፤እንዲያዉም
እናቴ በአፍ ይሄዳል ትል ነበርና … … መተዉ ሳይሻል አይቀርም፡፡
……….. ነገሩ እንዲህ ነዉ፡- በጠዋት ተነስቼ
ወደ ሥራ ገበታዬ እያመራሁ ነበር ፤ መኪናዉ ጉዞዉን ጀምሯል እንሄዳለን፣ እንሄዳለን … መንገዱ
አያልቅም ወይ አያስኬድም፡፡
አንዳንድ ሰዎች የትራንስፖርት
መዘጋጋቱን ምክንያት(ተገን) በማድረግ ትዉዉቅ ይጀምራሉ (በአራዳ ቋንቋ ይጀናጀናሉ!) ፡-
በተለይ የከተማ አዉቶቡስ ላይ፤