https://www.facebook.com/alex.abreham.31/posts/1607429286206948
ማህደር የእኛን ማህደር ስትከፍተው !!
(አሌክስ አብርሃም) ለተፃፈዉ ምላሽ ...
ማህደር የእኛን ማህደር ስትከፍተው !!
(አሌክስ አብርሃም) ለተፃፈዉ ምላሽ ...
“ የተኛዉን በሬ ቆስቁሰዉ አደረጉት አዉሬ ” ይላል የአገሬ ሰዉ፤ ሰምቼ መፃፍ ያላሰኘኝ ነገር ቢኖር የቢግ ብራዘሩ የሃና
ጉዳይ፣ ሊቢያ ላይ የተፈፀመዉ የንፁሐን ዜጎች ደም በከንቱ በኤሲስ መፍሰስ እና መሰዋት፣ አሁን ደግሞ ከግራ ወደ ቀኝ እንደመሰለን
ትንሽ ነገር አንጠልጥለን የነፈስንበት የአርቲስት ማኅደር አሰፋ ጉዳይ ናቸዉ፡፡ አሁን ግን የማደንቀዉ ጸሐፊ (ጦማሪ) አሌክስ አብርሃም
ፅንፈኛ ሆኖ የፃፈዉ እና ህዝቡን የዘለፈበት ጉዳይ ዝምታን እንዳልመርጥ አድርጎኛል፡፡
1ኛ. ይህ ወዳጄ መጽሐፍ ቅዱስን ደስ ሲለን ብቻ የምንጠቀምበት፣ ሐብታሞች
የማይነቀፉበት እና የማይገሰፁበት፣ እሱ ብቻ ሲፈቅድ ለአዕምሮዉ የሚመቸዉ ተግሣፅ ሲሆን ይለፍ የሚለዉ ጉዳይ አስመስሎታል፣ ተግሣፆችንም
እንደሱ ፅሑፍ እኔ ካላረምኳቸዉ አይነት ነገር አይቼበታለሁ፣ ሌላዉ ለአሌክስ አብርሃም አክብሮቴ እና አድናቆቴ እንዳለ ሆኖ መጽሐፍ
ቅዱስን እንደ አንድ ተራ ጥራዝ ባያየዉ እመርጣለሁ፡፡
2ኛ.እንደ አንዳንድ የሥነ ፅሑፍ ስነምግባር ያልገባቸዉ የኔ ቢጤዎች ዘለፋ
የበዛበት ነገር ባይፅፍ ለዚያዉም አግባብነት የጎደለዉ እንዲህ ስል ግን ተጨባጭነት ያለዉ ተግሳፅ አይገባም ማለቴ አይደለም፡፡
3ኛ. ሰዉየዉ ሃብታም ስለሆኑ ብቻ የሳቸዉ ጉዳይ በክፉ አይነሳ ብሎ አግባብነት
የጎደለዉ ሙገሳ ቢያቆም፤ እኚህ ሰዉ በአንድም በሌላም ምክንያት ለዚህ ህዝብ ባለዉለታ መሆናቸዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚነገረዉ አይደለም፡፡
ገንዘብ ሰጡ ማለት ንፁህ በኩለሄ (ሁሉም ቦታ ንፁህ ) ናቸዉ ማለት እንዳይደለ ልብ ቢል ሰብአዊነታችን በሳንቲም ድቃቂ ሲገዛ ዝም
የምንል ህዝቦች መሆን የለብንም እና፡፡
4ኛ. ሌሎች ሃብታሞች በየጓዳ ጎድጓዳዉ ያሻቸዉን ስለሚሰሩ እሳቸዉን ዝም
ማለት ከየት የመጣ የበደል ማጣፊያ ነዉ? አልገባኝም
5ኛ. አዎ ማኅደር አገር የሚያደንቃት ባለሙያ ነች ይህ ማለት ግን እንዳሻት
እንድትሆን ማካካሻ አይደለም፤ እርሷ ስታጠፋም ዝም እንድንላት ይህን ያህል የወረደ ሞራል እንደሌለን ልብ በል፡፡ ይህ ህዝብ እንኳንስ
በቴሌቭዢን መስኮት ያያትን ማኅደርን ይቅርና አንተን የሚያደንቁ አድናቂዎችህ ፅሑፍህን ታዝበዉ እንዴት አስተያየት እንደሚሰጡህ ልብ
በል፡፡
6ኛ. እዛዉ ማኅደር ላይ ባለህ አቋም እርሷ ለዚህ መጪ ትዉልድ (ህፃናት)
አርአያ ካልሆነች ማን ሊሆን ነዉ ሲጀመር እኮ አንተ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ጥፋቷ እንደወደድካት ህዝቡም (ህጻናትም) እንደዚያዉ
ማድረግ እንዲችሉ ማድረግ አይቻልም፡፡
ሳጠቃልለዉ እንደጦማሪነትህ ሃላፉነትህ ይህ ነዉ? እንዲህ ሽንጥህን ገትረህ
የተከራከርከዉ፣ አርቲስት መሐሙድን፣ ባለፀጋዉ የለገሱትን ገንዘብ እያጣቀስክ የፃፍከዉ እንደ አርቲስቶቹ የብር ሽልማቶችን ሽተህ
ይሆን? ሰዉየዉ እንኳን ፅፈህ … ካልፈለጉ አይሰሙም፤ ህዝቡን ያዝ …
እኔ እና እኔን ለምትመስሉት፡
በሰዉ በደል ሆያ ሆዬ ለምንል እስኪ የሌሎችን ጉድፍ ትተን የራሳችን ምሰሶ
ዞር ብለን እንመልከት፤ አሌክስን ባስቆጣዉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዳለዉ ታሪክ ( አንዲት ሴት ስታመነዝር ቢያገኙዋት ጌታ ጋር ይዘዋት
በመሄድ ከሰሱዋት እንዲህ በማለት “ ስታመነዝር አገኘናት ስለዚህ
እንደ ስርአታችን በድንጋይ ወግረን እንድንገድላት ፍቀድልን ” በማለት ጌታም “ በአጭሩ ከእናንተ ንጹሕ የሆነ ይዉገራት … ) በደላቸዉን ያዉቀዉ
ነበር እና እንዲህ አለ፡፡ አሁንም እኔም እላለሁ ከማኅደር ንጹሕ የሆነ ፌስ ቡክ ላይ ይፃፍ፣ ይተቻት፣ ይማት፣ ይስደባት፣ ….
የተሻለ ነገር አለን የምንል ደግሞ ለዚህ ትዉልድ በጎዉን ቃል እንፃፍ
፣ በጎዉን ነገር እናሳይ፣ በጎዉን እንኑር፣ …
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ