ሕዝብ
፡ በቋንቋ:በሃይማኖት፡በሕገ መንግሥት፡በታሪክ፡በልማድ፡በኑሮ አንድነት ኅብረት ያንድ መንግሥት አጽቅነት ማለት ነዉ፡፡ከሣቴ ብርሃን
ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት እንደሚለዉ፤
የኢትዮጵያ
ህዝብ የራሱ የሆነ ቋንቋ ፣ሃይማኖት፣ሕገ መንግሥት ፣ታሪክ ፣ልማድ፣ኑሮ፣ባህል፣ያለዉ ቢሆንም ለረጅም አሥርት ዓመታት እየተፈራረቁ
ሲገዙት ወይም ሲያስተዳድሩት ከነበሩት መንግሥታት ( ነገሥታት ) ክፋት እና በጎ አሳቢነት ከማጣት ፣ከልማት ይልቅ “ ረሃብ ” ሲጫወትበት ኖሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር አገሪቱ በዉስጥም
ሆነ በዉጭ ጠላቶቿ ሠላም በማጣት ልጁን ለጦርነት እየማገደ ፣ ራሱም በረሃብና በበሽታ አለንጋ እየነደደ 21ኛዉ መቶ ክ⁄ዘመን ላይ
ደርሷል፡፡ይሁን እንጂ ኑሮዉ ያልተሻሻለ ፣ ስላሙ ያልተረጋጋለት የህብረተሰብ ክፍል በሃገሪቱ ላይ በብዛት ይገኛል፡፡ እንኳን የገጠሩ
የከተማዉ ነዋሪ የተሻለ ኑሮ ይኖራል፣ የተሟላ ነገር አለዉ፣ ለዕድገት እና ለለዉጥ ቅርብ ነዉ፣ … ወዘተ የተባለዉ ህይወቱ የሃዘን
እንጉርጉሮ የበዛበት ነዉ፡፡ መፈጠሩን እስኪጠላ ይማረራል፡፡እንደ ትናንቱ ለመሬት ከበርቴዉ እና ለወኪሉ የጉልበት አገልግሎት አይስጥ
እንጂ ዛሬም ህብረተሰቡን ሙስና አቅሙን አሳጥቶታል፡፡ አጥር ማጠር፣ቤት ማደስ፣የወር ተራ ገብቶ በዘበኝነት ማገልገሉ፣ በእርሻ መሳተፉ
ቢቀርለትም በየቢሮዉ ጉዳዩን ለማስፈፀም ደፋ ቀና ማለት፣ነገ ተመለስ፣ ጉዳዩን የሚያከናዉንልህ አለቃ ስብሰባ ላይ ነዉ፣ ማኅተም
የምታደርገዋ ፀሐፊ ዛሬ ስራ አልገባችም፣ እገሌ የሚባሉት ሰዉ ዛሬ ⁄ ሰሞኑን የሉም፣ … ወዘተ የሚሉ ምክንያቶች ደሃዉን ሆነ ሃብታሙን
የህብረተሰብ ክፍል ቀና ብሎ እንዳይሄድ አድርገዉታል፤ ከትላንት የተሻለ ቀንም እንዳይወጣለት አድርገዉታል፡፡ከዚህም ባሻገር በየተቋማቱ
ያሉ ( የተንሰራፉ ) ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ በፖለቲካ የልዩነት ፍጭት፣ ትልቅ የራስ ምታት እና ሰፊዉ ህብረተሰብ አገልግሎት ለማግኘት
ሁለተኛ እዚህ ስፍራ ብደርስ ብሎ እንዲማረር አድርጎታል፡፡ ( ዝሆኖች ሲራገጡ ሳሩ ይጎዳልና ህብረተሰቡ ትልቅ በደል እና ጉዳት
ደርሶበታል ) ከትናንት በስትያ ፣ ትናንት እና ዛሬም ድረስ የዘለቀዉ ዘመን ተሻጋሪ ነቀርሳ ኢትዮጵያ ሰፊ መሬት ያጣች ይመስል
በልማት ሰበብ የህዝቡ ለዓመታት ይኖርበት ከነበረ ፣ ተወልዶ ካደገበት ማፈናቀልና በየሄደበት ቦታ ከነባር ነዋሪዉ ጋር ግጭት መፍጠር፣
አልነሳም ትነሳለህ በሚል ክርክር ከገዢዉ ጋር እሰጣገባ ዉስጥ መግባት፣ ሃብት ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ድበደባ ፣ እስር ፣ እንግልት፣
ጤናዉን ማጣት፣ሰደት፣ አልፎ ተርፎም ሞት ይደርስበት ነበር፡፡
በቀደሙት
ስርዓት አርሶ አደሩ ካረሰዉ እና ከሚያረባዉ ለከበርቴዎች እንደሚገብረዉ ሁሉ ዛሬም ህብረተሰቡ ትናንት በወጣዉ የግብር ተመን መሠረት
( ህብረተሰቡን ለሞት ለእስር ለእንግልት ) የዳረገዉን የተለያየ ቁጣ ያስነሳዉን የግብር ተመን አሁንም ያለምንም ማሻሻያ ገበሬዉም ነጋዴዉም የመንግሥት ሠራተኛዉም የቀን ሠራተኛዉም ሁሉም እኩል እንደ ገቢዉ መጠን እስከ 35% ድረስ
ይገብራል ( ይበዘበዛል)፡፡
ዛሬም እንደ ትናንቱ በሰፊዉ
ህዝብ የሚበላ እንጂ ሠፊዉ ህዝብ ሠርቶ እንዲበላ ያስቻለዉ የለም፡፡ የህዝብ ጫንቃ ያልቻለዉ ቀንበር ያልቻለዉ አለንጋ የለም፡፡
ትናንት የገበሬዉ ልጅ ወላጆቹ
ዓመት ሙሉ ለፍተዉ ያገኙትን ለከበርቴዎች ሲገብሩ የደከሙበትና የለፉበት በማለቁ የተመጣጠነ ምግብ ባለማግኘታቸዉ ለረሃብ፣ ለበሽታ
አልፎ ተርፎም እጅግ ብዙ ቁጥር ያለዉ ለሞት ይዳረግ ነበር፡፡የቀሩትም ደግሞ የመማር እና የተሻለ ኑሮን የመምራት ዕድል ስለሌላቸዉ
መሃይምነት እና በሽታ ሲፈራረቅባቸዉ ዘመናቸዉ አልቆ ከዚህ አይነት አሰቃቂ ህይወት ሞት ይገላግላቸዉ ነበር፡፡
የሠራተኛዉ ዕጣ ፈንታ የጉልበቱን
እንጥፍጣፊ ሳይቀር ከመበዝበዝ በቀር ምንም የተረፈዉ አልነበረም፡፡ መንግሥትም ቢሆን የሠራተኛዉን ክፍል ጥቅም የማስጠበቅ፣ መብቱን
የማስከበር መንግሥታዊ ሃላፊነቱን አልተወጣም፡፡ አሰሪዉም ክፍል የሠራተኛዉን የላቡን የድካሙን ዋጋ አስቦ ተምኖ እንደመክፈል ጉልበቱን
መበዝበዝ ያሰኘዉን መክፈል አንዱ የትርፍ ምንጭ አደረገዉ፡፡
ከሁሉም የከፋዉ ደግሞ በሴቶች
ላይ ይደርስ የነበረዉ ግፍ እና መከራ በፈርኦን ቤተመንግሥት በራሄል ላይ ከደረሰዉ ምንም አይተናነስም ነበር፤ በስራ ገበታቸዉ ላይ
እያሉ ምጣቸዉ የሚመጣባቸዉ፣ ሥራቸዉን በአግባቡ ሠርተዉ አጠናቀዉ ከወንዶች ያነሰ የሚከፈላቸዉ ጥቂት አልነበሩም፡፡
ወታደሩም ቢሆን ለአገር ለወገን
ዳር ድንበሩን እያስከበረ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ነገር ግን የላቡ የደሙ ዋጋ አይደለም ቤተሰቡን ሊያስተዳድር ራሱንም ሳምንት
የማያደርስ ክፍያ ነበር የሚከፈለዉ ሆኖም ወታደሩ የራሱን በደል ወደጎን በመተዉ የአገር ሉዓላዊነት ለማስከበር፣ የህዝቡን አንድነት
ለማናጋት የሚነሱትን ጠላቶች ይመክት ነበር፡፡
ይህ ህዝብ እንዲህ ዓይነት በደሎች
በየደረጃዉ ሲደርስበት የነበረዉ አማራጭ አንድ እና አንድ ነበር “ ቁጣ ” ከመቆጣት የዘለለ መብትም አቅምም ስላልነበረዉ፡፡
ህዝብ ለምን ይቆጣል?
ህዝብን የሚያስቆጣዉ ምክንያት
እጅግ ብዙ እና እዚህ ጋር ተዘርዝሮ ስለማያልቅ እንዲሁ በጥቅሉ ካየነዉ ግን ህዝብን የሚያስቆጣዉ በደል ነዉ፤ ህዝብ ሲበደል በደልን
መቋቋም ሲያቅተዉ፣ መፍትሔ ሲያጣ፣ ሰሚ ሲሻ፣ ለዉጥ ሲናፍቀዉ፣ ይሰማኛል ወደሚለዉ አለበለዚያም ሊሰማኝ ይገባል ብሎ ወደሚያስበዉ
መልዕክቱን በቁጣ መልክ ይገልፃል፡፡
ህዝቡ ቁጣዉን እንዴት ይገልፃል?
የህዝቡ ቁጣ መገለጫዉ በተለያየ
ዓለም እንደመለያየቱ መጠን በአገራችን በኢትዮጵያም ህዝቡ ቁጣዉን የሚገልፅበት መንገድ እንደየዘመኑ ይለያያል፡፡ ከነዚህም መካከል፡
Ø
አደባባይ ይወጣል
Ø
በስብሰባዎች ላይ በሃይለቃል
መልዕክቱን ይገልፃል
Ø
የተባለዉን ( የታዘዘዉን
) እምቢኝ አሻፈረኝ አላደርግም ⁄ እጅ መንሻ አላመጣም ይላል
Ø
የሥራ ማቆም አድማ ያደርጋል
Ø
ተማሪ ትምህርቱን አልማርም
ይላል
Ø
ከባሰበት ጦር ይመዛል ( ጫካ
ይገባል )
Ø
ግብር አልገብርም ይላል
Ø
ህዝባዊ ግዴታዉን አይወጣም
እነዚህ
ጥቂቶች ናቸዉ፤ ብሶቴን ይገልፁልኛል ያላቸዉን ከመጠቀም ወደ ኋላ አይልም፡፡
መንግሥት ምን ማድረግ ይጠበቅበታል?
ምንም
እንኳን አንድ ላይ ያለፉትን መንግሥታት ብንወቅስ እና የህብረተሰቡ ችግሮች ናቸዉ ብንልም የህዝቡን የልብ ትርታ የሚያዳምጡ አይደለም
ቁጣዉን ዘፈን እና እንጉርጉሮዉን የሚያዳምጡ፣ አይደለም አደባባይ የወጣዉን በዱር ያለዉን እረኛዉን ሳይቀር የሚያዳምጡ መሪዎች ነበሩን፡፡
ሹማምንቱን ዛሬስ እረኛዉ ምን አለ ብለዉ የሚጠይቁ የህዝቡን ብሶት የሚሰሙ ነበሩ፤ እነዚህ መሪዎች የህዝቡ መናገር ስጋታቸዉ አልነበረም
ዝምታዉ እንጂ፡፡ እዉነትም ህዝብ ከተናገር ብሶቱን በቃላት ካወጣ ችግር የለዉም ዝም ካለ ግን ትልቅ ችግር አለ ማለት ነዉ፡፡ በአገራችን
ኢትዮጵያ ብዙ መሪዎች እንደመፈራረቃቸዉ መጠን ብዙ ችግሮች አይተናል፤ የቅርቡን እንኳን ብንመለከት አገራዊ ምርጫን ተከትሎ በ1997
ዓ.ም. የምርጫ ቅስቀሳን ለመደገፍ በነቂስ እንደመዉጣቱ መጠን የምርጫዉንም “ መጭበርበር ” ተከትሎ እንዲሁ አደባባይ ወጣ ቁጣዉን
ገለፀ፤ 2002 ዓ.ም. ላይ መንግስት ምንም እንኳን ከአዕምሮ በላይ በሆነ ዉጤት ዲሞክራሲ እና ዕድገት በሰፈነበት አገረ አሜሪካ
እንኳን እንዲህ አይነት ዉጤት ባልተመዘገበበት ሁኔታ አሸነፍኩ ቢልም ህዝቡ ዝምታን መረጠ፡፡ አሁንም በ2007 ዓ.ም. አገራዊ ምርጫ
ህዝቡ ዝምታን ነዉ የመረጠዉ ለምንድን ነዉ? ያ የደጋፊነት እና ተቃዋሚነት መንፈሱ ወዴት ሄደ? ትልቅ ጥናት ይጠይቃል፤
አሁን
ማየት ያለብን ነገር እንደከዚህ ቀደም የህዝቡ ልማድ የህዝቡን ቁጣ እና ዝምታ መንግሥት እንዲሁ ዝም ብሎ ማየት አለበት ወይ? ዝም
ማለት የለበትም፤ ህዝቡ ሲቆጣ ቁጣዉን ማዳመጥ ዝም ሲል ዝምታዉ ምን እንደሆነ ሊመረምር ይገባዋል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ጥቃቅኑን ቀበሮዎች
አጥምዳችሁ ያዙልን እንዳለዉ ሁሉ መንግሥትም ጥቃቅኖቹን ባለስልጣናት አጥብቆ ሊቆጣጠራቸዉ ይገባል እነሱ ናቸዉና ህዝቡን እየበደሉ
የሚገኙት፡፡ አደባባይ ወጥቶ ሲቆጣ የማይሰሙትና ብሶቱንም እንዳይናገር እና ዝምታን እንዲመርጥ ያደረጉት፡፡
አይደልም
ህዝብን ማስተዳደር ቤተሰብን መምራት ከባድ በሆነበት በዚህ ዘመን ህዝብን መምራት እንዲህ ቀላል ባልሆነበት ሰዓት መንግሥት እንደ
ጠቢቡ ሰሎሞን በጥበብ ህዝቡን ለማስተዳደር ጥበበኛ ሊሆን የህዝቡን በሃይል ፀጥ ከማድረግ ይልቅ ሊሰማ እና እርምጃ ከመዉሰድ እና
አላስፈላጊ ፍረጃ ከመፈረጅ ተቆጥቦ አስፈላጊዉን መፍትሔ ለህዝቡ ቢሰጥ ይሻላል፡፡ የህብረተሰቡንም ዝምታ በጥሞና ሊመረምር ይገባል፡፡
ከስልጣን ከወረደ በኋላ ከሚፈርዱበት አሁን ስልጣን ላይ እያለ ቁጣቸዉን ቢሰማ የተሻለ ነዉ፡፡
ለምንድን
ነበር በ1997ዓ.ም. ህዝቡ መንግሥትን የተቃወመዉ ተቃዋሚዎችንስ የመረጠዉ? ለዉጥ ስለሚፈልግ ነዉ፡፡ ህዝቡ መንግሥትን በምርጫ
ካርድ መሾም መሻር እንደሚቻል አዉቋል ሰልጥኗልና፤ መንግሥትም እንደ ህዝቡ ሊሰለጥን በምርጫ ካርድ ማመን ለህዝብም ድምፅ መገዛት
ሊለማመድ ግድ ይለዋል፡፡ አሁን ያለዉም ወደፊት ለሚመጣዉም መንግሥት ይህ ፅኑ መልዕክታችን ነዉ፡፡ለምን ነበር በ2002 ዓ.ም.
የምርጫ ወረቀቶች ላይ ስድብ እና አላስፈላጊ ነገሮች ህዝቡ ሲናገር የነበረዉ? ባዶዉንስ ካርድ ወደ ምርጫ ኮረጆ የከተተዉ? የምርጫ
ካርዱንስ ተጠቅሞ ላለመምረጥ ቤቱ በዝምታ የተቀመጠዉ? በ2007 ዓ.ም. ምርጫ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን (ማኅበራዊ ድረ ገጾች )
እንዳየነዉ ካርዱን ለምን ቀዶ ጣለዉ? መንግሥት ይህን ነገር ጣቱን ወደ ዉጭ ከመቀሰር ዉስጡን ለመፈተሽ ቢገለገልበት፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ