ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች “ ጠላትን
” ስለመዉደድ ጥቂት ነገር ብለናል በዛሬዉ ፅሁፋችን ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመጨረሻዉን ክፍል እንመለከታለን፤ እግዚአብሔር
“ጠላቶቻችን” እንድንወድ ያስችለን፡፡
ጠላቴን ለመዉደድ የሚያስችለኝ ነገር ምን ላድርግ?
(ምን መደረግ አለበት?)
ጠላትህን ለመዉደድ እነዚህን ነገሮች ሳታወላዉል አድርግ!
ምናልባት
እነዚህን የተዘረዘሩትን ነገሮች በሙሉ በአንዴ ለማድረግ ይከብዱ ይሆናል፤ ይከብዳሉም፡፡ ነገር ግን የሚከብደዉን ሁሉ እንተወዋለን
፣ እንሸሸዋለን ማለት አይደለም፡፡ ማንኛዉም የዓለማችን ነገሮች የመለማመድ ዉጤት ናቸዉና ዘወትር በድርጊታችን ዉስጥ እንለማመዳቸዉ፡፡
በእርግጠኝነት ለዉጥ እናመጣባቸዋለን … ለዚያዉም በጣም የሚያስደንቅ … ነገር ግን ብዙ መንገድ ያስጉዙናል፡፡ቢሆንም ግን ጥቂቶች
ለእኔ እስከ አሁን ጠቅመዉኛል በእርግጠኝነት አንተንም ይጠቅማሉና ሞክራቸዉ፤ ከታች በዝርዝር የተቀመጡትን ፈፅማቸዉ፡፡
i.
ጠላቴ ስለምትለዉ ሰዉ ከዚህ ቀደም የሚሰማህን ነገር ማሰብ
አቁም፡ በፊት ስለሚሰማህ ስሜት ደጋግመህ አስብ ( አስር ጊዜ
)፤ አሁን ደግሞ የሚሰማህን አስብ እዉነት ያንን ነገር ማቆምህን ራስህን ገምግመዉ እርግጥ ነዉ በአንዴ ሃሳብህን መቆጣጠር ሊከብድህ
ይችላል ነገር ግን ደጋግመህ አድርገዉ ( እርሳዉ )
ii.
ራስህን በእርሱ ቦታ አድርገህ አስብ፡ ያኔ በዉስጥህ የሚመጣዉን ጥላቻ ታስወግደዋለህ፤ እርሱ ያደረገዉን ድርጊት አንተም እርሱ
ቦታ ብትሆን ታደርገዋለህና፡፡በቃ አሁን ያ ሰዉ ማለት አንተ ነህ፡፡ ያ ሰዉ እንደ አንተ ትክክለኛ ሰዉ የነበረ ነዉ ያ አጋጣሚ
በርሱ ላይ ይህን ክፉ ድርጊት አመጣበት እንጂ፤ ስለዚህ ይህን ሰዉ ከመጥላት ያንን ክፉ ድርጊት ጥላ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የለጠልህ
ጥሩ ሰዉ ሁን፡፡ የሰዉ ልጅ በጠቅላላ ጥሩ ነገር ለማድረግ ይጥራል ነገር ግን ስህተት ይሰራል፡፡ ስህተት እና ጥፋት ይለያያል፡፡
እንኳን ለተሳሳተ ላጠፋም ይቅርታ ማድረግ ግድ ይለናል፡፡ አለበለዚያ በድርጊቶች ላይ የተለያየ አመለካከት አለዉ፡፡ አንድን ነገር
ከተለያየ ቦታ ላይ መመልከት እጅግ ይከብዳል ግን እጅግ ይጠቅማል “ 6 ” ይህን ቁጥር አንተ ስትፅፈዉ ስድስት ስትለዉ ከፊት ለፊትህ
ለተቀመጠዉ ደግሞ “ 9 ” ሆኖ ስለሚታየዉ ዘጠኝ ሊለዉ ይችላል፡፡ ችግሩ ከቁጥሩ ወይንም ከሰዉየዉ ሳይሆን ሰዉየዉ ከተቀመጠበት ቦታ ነዉ፤ ስለዚህ አንድን
ነገር ከመወሰናችን በፊት ራሳችንን ከሰዉየዉ ቦታ አድርገን ብንመለከተዉ መልካም ነዉ፡፡
iii.
ልትረዳዉ ሞክር፡ በርሱ ቦታ ራስህን የማስቀመጥ ዋና ዓላማዉ ይህ ነዉ፤ እርሱ ያደረገዉን ነገር ለምን እንዳደረገዉ
ከተረዳኸዉ ቀጣዩ ድርጊትህ መረዳት ይሆናል፡፡ እዉነት እልሃለዉ ጠላቴ የምትለዉን ሰዉ ከምንም በፊት ችግሩን ልትረዳዉ ሞክር እዉነቱን
ታገኛለህ፤ ምናልባት ይህ ሃሳብ ላይዋጥልህ ይችላል ነገር ግን አድርገዉ፡፡
iv.
ልትቀበለዉ ሞክር፡ ስለተፈጠረዉ ነገር አንቧጓሮ ከመፍጠር እና ለግጭት ከመዳረግ ይህ ሰዉ ማንም ይሁን ማንም
ልትቀበለዉ ሞክር፣ ልትሰማዉ ⁄ ልታዳምጠዉ ሞክር፣ እድል ስጠዉ፣ እስከ ማንነቱ ተቀበለዉ፡፡ በልዩነት ተስማሙ ምክንያቱም ድርጊቱ
አንዴ ተፈፅሟልና፡፡ ሰዉየዉ እንዳንተ ሰዉ ነዉ በሃሳብ ነዉ እንጂ የተለያያችሁት ምናልባት እጅግ ፈታኝ እና ከባድ ሊሆን ይችላል፤
ነገር ግን ተቀበለዉ፡፡ ካልተቀበልከዉ በፍፁም ልትወደዉ አትችልምና፡፡
v.
ላለፈዉ ነገር ሁሉ ይቅርታ አድርግለት፡ ይህ ደግሞ እስካሁን ካሉት እጅግ እንደሚከብድ አዉቃለሁ በጣም እርግጠኛ ሆኜ የምነግርህ
ነገር በቅርቡ ዉጤቱን ታያለህ፡፡ጥሩ ዉጤት ለማየት ከፈለክ ወይም የድካምህን ፍሬ ለማየት ከፈለክ ይህ ሰዉ ያደረገብህን ነገር በልብህ
ሳጥን ⁄ ሰሌዳ የተቀመጠዉን እዉን ልታደርገዉ ትችላለህን? በእዉነት ከልብህ ይቅር ብለኸዉ ከሆነ በቀላሉ ስትረዳዉ ታያለህ፣ ሃሳቦቹን
ትቀበላለህ፣ ይቅርም ልትለዉ ቀሎህ ታገኘዋለህ፡፡ ይህን ነገር ደጋግመህ አስበዉ፡፡ ትናንት የተፈጠረዉን ዛሬ ላይ ሆነህ አስበዉ፤
በፍፁም ፍቅር ዛሬን ቀይረህ ወደፊት መጓዝ ትችላለህ፡፡ ወደ ኋላ ተመልሰህ ነገር ብትበላ፣ ብትብሰለሰል ምንም የምታመጣዉ አዲስ
ነገር አይኖርም፡፡ ይቅርም እንድትባል፣ ይቅር የማለትንም ፍሬ እንድትበላ የበደሉህን አንድ ጊዜ አይደለም፣ ሰባት ጊዜ አይደለም፣
ሰባት ጊዜ ሰባ ያህል ( ብዙ ) ጊዜ ይቕር በላቸዉ፡፡
vi.
ለመዉደድ ምክንያት ፈልግ፡ ይቅር ካልከዉ እና ከዚህ ክፉ ሃሳብ ከተላቀቅክ … ከዚህ ከነፍስ እና ከስጋ የምትገጥመዉን
ጦርነት ተገላገልክ ማለት ነዉ፡፡ ያንን አስከፊ ጊዜ በፍቅር ⁄ በመዋደድ ⁄ ተካዉ፡፡ ይህንን እንዴት ነዉ የምታደርገዉ? በዚህ
ሰዉ ላይ የሚታይ የሚወደድ ነገር ፈልግበት፤ ምንም ነገር ሊሆን ይችላል ብቻ ልትወድለት የምትችለዉን … የግድ ከባድ ነገር መሆን
የለበትም፡፡ ከፈለክ ሳቁን ሊሆን ይችላል፣ ቅንነቱን ሊሆን ይችላል፡፡ ብቻ የሆነ የሚደንቅ ነገር ፈልግና ዉደድለት፡፡ ይህ ድርጊት
ምናልባት እርሱን የበለጠ እንድታዉቀዉ እና እንድትወደዉም ምክንያት ሊሆንህ ይችላል፡፡ ይህ ነገር በራሱ ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡
ነገር ግን ሳታወላዉል አድርገዉ፡፡
vii.
ልክ እንደራስህ አድርገህ እየዉ ( ዉደደዉ )፡ ከላይ የዘረዘርናቸዉ ነገሮች ባይሳኩልህ ይህንንም ሰዉ ጠንቅቀህ ማወቅ ከተሳነህ
ተስፋ አትቁረጥ ፣ ለክፋት እጅ አትስጥ ፣ አትሸነፍ …. ሌላ አማራጭ
አለና፤ ራስህን በእርሱ ቦታ እንዳለህ ሆነህ አስብ፤ ከአንተ ጋር ተመሳሳይ እንደሆነም ተመልከት፡፡ አለበለዚያም እጅግ በጣም እንደምትወደዉ
አንድ ሰዉ አድርገህ ዉደደዉ፡፡ ( ወዳጄ ሰዉን መዉደድ ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ ልብ ብለኸዋል? ሰዉንስ መጥላት ምን ያህል ቀላል
እንደሆነ? “ ጠላትህን ”መዉደድ ዋጋዉም ምን ያህል እጥፍ ድርብ እንደሆነ ልብ በል፤)
viii.
በጋራ የምትስማሙበትን ነገር ፈልግ፡ ከማንኛዉም ሰዉ ጋር አንድ የሚያደርገን ነገር በፍፁም አይጠፋም፡፡ ያንን ነገር በጣም
አጠንክረህ ( አፅንኦት ሰጥተህ ) ከተመለከትክ ምናልባት ያ ነገር በጋራ የሚያግባባችሁ እና የሚያስደስታችሁ ጉዳይ ነዉ፡፡ የምትጋሩት
እና አንድ የሚያደርጋችሁም ጉዳይ ነዉ፡፡ በዉስጣችሁ እያደገ የሚሄድና ትልቅ ነገር የሚያደርግ ምናልባት አንድ ሰዉ በጋራ ታዉቁታላችሁ
አለበለዚያም ትወዱታላችሁ፡፡ ስብዕናዉን ወይም የዚያን ሰዉ ባህሪ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ነገር ይህን ሰዉ ከራስሀ ጋር በደንብ እንድታነፃፅረዉ
ሊረዳህ ይችላል፤ እንድትወደዉም ያደርግሃል፡፡
ix.
ልብህን ክፍት አርገዉ፡ ይህም ሌላኛዉ ከባድ ነገር ነዉ፤ልባችን በብዙ ሰወች ላይ ዝግ የመሆን አዝማምያ ያሳያል፡፡
ልንጎዳ እንችላለን በሚል ስጋት ልባችንን እንዘጋለን አለበለዚያም እንጠላለን እንደ መከላከያነት እየተጠቀምን፡፡ ይህ ልቡናችንን
ዝግ ማድረግ ብዙ ጊዜ ደስታንም አሳጥቶናል፣ ከምንፈልገዉ የፍቅር ግንኙነትም አግዶናል፡፡ ከማፍቀርም ከመፈቀርም ዉጭ አድርጎናል፡፡
ምናልባት አንድ ጊዜ ለምናፈቅረዉ ሰዉ እንከፍተዉ ይሆናል እንደአጋጣሚ ሆኖ መጥፎ ነገር ሲገጥመን በድጋሜ ክፍት ለማድረግ እጅግ
ያዳግተናል፡፡ከሁሉ ነገር እንታቀባለን ራሳችንንም ከሁሉም ነገር እንገደባለን፡፡ይህ ትልቅ የሚገጥመን ፈተና ነዉ፤ ልብን መክፈት
እንዲሁ በአንድ ጊዜ የሚመጣ እና የሚደረግ በቀላሉ የሚታዘዝ ሳይሆን የብዙ ጊዜ ልምምድ ይጠይቃል፡፡ አሁን “ ጠላታችንን ” ለመዉደድ
ልባችንን ክፍት በማድረግ እንጀምር ፤ እስኪ ትንሽ ከፈት በማድረግ እንለማመድ ይህንን ሰዉ ለመዉደድ ከዚህ የተሻለ አማራጭ የለምና፡፡
x.
እጅህን ዘርግተህ ተቀበለዉ፡ ይህንን ካደረክ ትልቁን የህይወት ፈተና ድል ነስተሃል፤ በቃ አሁን ስለዚህ ሰዉ ፍቅር
⁄መዉደድ⁄ ማሰብ ትችላለህ፡፡ ማድረግም ትችላለህ፡፡ፍቅርህን በአንድም መግለፅ ትችላለህ፡፡ መዉደድህን ለመግለፅ አሁን ብዙ አማራጮች
አሉህ፤ አሁን ጥላቻ ተወግዷልና፡፡ እንደምትወደዉ በምትፈልገዉ ቃላት ልትገልፅለት በምትፈልገዉ ድርጊት ልታሳየዉ ትችላለህ፡፡ እጅግ
ደስ የሚሉ ነገሮችን በፍፁም ልብህ በፍፁም ፍቅር ልታወራዉ ትችላለህ፡፡ በግልፅ ልትመካከሩ ልትወያዩ ትችላላችሁ፡፡ምን እንደሚሰማህ
ምን እንደሆነ አንዳች ሳትደብቅ ትነግረዋለህ፡፡ ትልቅ ግምት እና ቦታ በዉስጥህ ትሰጠዋለህ፣ እጅግ በጣም ጥሩ እና የተወደደ ነገር
ታደርግለታለህ፣ እጅግ ደስተኛ ነህ፣ ቀልዶችህ ሁሉ ደስ ይላሉ፤ ነፍስህም እጅግ ሐሴት ታደርጋለች፡፡
አሁንም
ደግሜ እላለሁ ጠላትህን ዉደድ፤ ስለሚጠሉህ ሰወች አብዝተህ ፀልይ፡፡
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
Great post and success for you..
ምላሽ ይስጡሰርዝKontraktor Pameran
Jasa Pembuatan Booth Pameran
Kontraktor Booth Pameran
Jasa Pembuatan Booth