ማክሰኞ 18 ማርች 2014

ጊዜና ዘመን

ጊዜ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ይታሰባል ይከወናል ትናንት ዛሬን እየሆነ ይቆጠራል፤ ትናንትናና ዛሬ ተደማምሮ ሳምንት ሳምንታትና ቀናት ተደማምረው ወራትና ዓመታትን /ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀናትን/ ይሰጣሉ፡፡ ከአዳም ጀምሮ ዓመት ይቆጠራል፡፡ የዓመታት ጥርቅም ዘመን ተብሎ ይጠራል ዘመን ረጅም ጊዜ ነው ወይም አንድ አይነት አገዛዝ አምልኮ ሌላም የተደረገበት ጊዜ መጠሪያ ነው፡፡
       ዘመን የተፈጠርንበት /የተወለድንበት/ ትምህርት የጀመርንበት፣ ሥራ የያዝንበት፣ መከራን ያየንበት፣ ከውድቀታችን የተነሳንበት፣ የተማመንበት፣ የተፈወስንበትወቅት ማስታወሻ /መጠሪያ/ ሊሆን ይችላል፡፡
       ወደ ፍሬ ነገሩ ልምጣና ከብዙ ሰዎች አንደበት ስሰማና ከብዕራቸው የዕምባ ጠብቃ ሳነብ ብዙዎች ዘመንና ጊዜን ሲደግፉ በከንቱ ስሙን ሲያጠፉ ሲኮንኑ አዳምጣለሁ አነባለሁ ‹‹አይ ዘመን፣ አይ ጊዜ›› ‹‹ጊዜው ነው፣ ዘመኑ ነው›› ሲሉ ነገር ግን ጊዜና ዘመን ምን አደረገ ምንስ በደለ ጊዜና ዘመን በራሱ ምን ያመጣው ለውጥ ምንስ ያደረሰው ተፅዕኖ አለ? አንዳንድ ፀሐፍት እንደሚሉት ዘመንና አህያ አንድ ነው ይላሉ አህያ እንዳሸከሟትና የጫኑባትን ይዛ እንደምትገኝ ዘመንም
የምንተገብርባትና መልካሙንም ክፉውንም እስከነኛው ይዛ ትገኛለች ይህ ደግሞ ዘመን ወይም ጊዜ እንዳመጣው ጊዜና ዘመንን ልንወቅስ አይገባም፡፡
       ወላጆች የልጆቻቸው ፀባይ ሲበላሽ ሥርዓት አልባዎች ሲሆኑ ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጭ ሲሆኑ አለመታዘዝ ምግባራቸው ሲሆን ዘላንነት መለያቸው እየሆነ ሲመጣ ወላጆች ‹‹አይ ጊዜ አይ ዘመን›› ሲሉ ይደመጣል ሌሎችም ሰዎች ለተፈጠሩት ችግሮች በሙሉ ምክንያትና ሰበብ የሚያደርጉት የሚወቅሱት ጊዜና ዘመንን ነው፡፡
       በአንድ ወቅት በምሽት ሰዓት ከአንድ አዛውንት ጋር ተቀምጠን እራት እየበላን ሳለን የገጠመኝን ማንሳት አንዱ መረጃ መግለፅ ደስ ይለኛል፤ እየበላን ሳለን አንዲት ዝብ መጥታ አላስበላ አላስጠጣ አለች አንዴ ከሚበላው አንዴ ደግሞ ከሚጠጣው መግባት ጀመር ከአጠገቤ የነበሩት አዛውንት ‹‹አይ ጊዜ አይ ዘመን›› አሉ ምነው? ጊዜና ዘመን ደግሞ ምን አደረጎት አልኳቸው ቆጣ በማለት ‹‹እንዴት ምን! ምን! ያላደረገኝ ነገር አለ›› አሉ በመቆጣት ‹‹አታየውም እንዴ ድሮ በኛ ጊዜ እንኳን ዝንብ ስንበላ ልጅ ራሱ ወደጓዳ ነበር አሁን አትመለከትም ዝንቡ ራሱ አላስበላ ሲለኝ›› አሉና ገላመጡኝ እያረጋጋኋቸው አቤት ይኼኮ ጊዜ ወይም ዘመኑ ያመጣው ነገር አይደለም ዝንብ ድሮም ያለ አሁንም ያለ ነው አላስበላ ብላ መረበሻE ደግሞ ዋና ሥራዋ ነው አልኳቸው ‹‹በፍፁም! የድሮ ዝንብ እኮ ቢያስቸግረን ቀን ቀን ነው ለዚያውም ግንቦት ውስጥ እስኪ ከመች ወዲህ ነው ዝንብ በማታ የምታስቸግረው በምንስ አይኗ አይታ ነው ‹‹ጊዜው ነው እንጂ›› ዘመን ያመጣብን ነው እንጂ›› አሉ በጣም እየተማረሩ በውኑ ጊዜና ዘመኑ ያመጣው ችግር ነው? ጊዜው ያደረገው ነገር ምን አለ? ሌሎቻችንም ከዚህ ባልተናነሰ ሁኔታ ጊዜና ዘመንን ስንወቅስ እንታያለን እንዳመጣልን ትክክለኛ ምክንያት ይዘን ይሆን?
       ጊዜና ዘመንኮ ዛሬ ዛሬ እንደምንወቅሰው ሳይሆን ለኛ ይልቁንም ታላቅ ባለውለታችን ነው ያላደረገልን ነገር የለም ሰው የሆንበት፣ ከወደቅንበት የተነሳንበት፣ የተዋረድን ከፍ ከፍ ያልንበት፣ አላዋቂዎች የነበርን ተምረን አዋቂዎች የሆንበትወደፊትም ደግሞ ልንተገብርበት ብዙ ዕቅዶችን የያዝንበት ወቅት ነው፡፡ ጊዜና ዘመን እግዚአብሔር ቢፈቅድ በሕይወት ብንኖር ዛሬ እያደረግን ያለነውን /ይህን/ ያቀድነውን ወደፊትም የምናደርግበት /ያንን/ ነው፡፡
       ጊዜና ዘመን ሰማይና ምድር በውስጧም ያሉ ነገሮች የተፈጠረበት፣ የበደልን እኛ ሰዎች ይቅርታን ያገኘንበት፣ ወደፊትም ከኃጢአት ተጠብቀን የምንኖርበት ነው፡፡
       እስራኤላውያን ፀሐይ ወጥታ እስክትጠልቅ ቀኑን ለብቻ ገብታም እስክትወጣ ሌሊቱን ለብቻው በሰዓት ይቁጠሩ ነበር ሮማውያን ደግሞ ከእኩለ ሌሊት እስከ እኩለ ቀን በእኩለ ቀን እስከ እኩለ ሌሊት ቀንና ሌሊቱን አያይዘው በሰዓት ይቆጥብ ነበር፡፡ ሰዓት የተወሰነ ጊዜን አጭር ጊዜን ሊያመለክት ይችላል ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያ አሥራሁለት ሰዓት ከምሽቱ እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት በአንድ ላይ ተደምሮ አንድ ቀን ይባላል የቀናት ድምር በሂሳብ ቀመር ተጠቅመን ዓመት /ዘመንን/ እናገኛለን፡፡
       በእስራኤል የዓመት አቆጣጠር እስራኤላውያን ከግብፅ የወጡበት የኒሳን ወር መጀመሪያ ተብሎ ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ሕዝቡ ግብርና ስለሚኖሩ አጨዳ ሲጨርሱ የዓመት መለወጫን ያከብሩ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ በወሩ ሳይሆን በግብርና ሥራ ጊዜው ይገለጣል፡፡ በጥንት ዘመናት እንደ ከተማ መቆርቆር እንደ ምድር መናወጥ ከመሳሰሉ ከታወቁ ሁኔታዎች በመነሣት ዓመታት ይቆጠሩ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት በየጊዜው የተፈፀሙትን ድርጊቶች ከክርስቶስ ልደት ወዲህ ካለው አቆጣጠር ጋር ማዛመድ ያዳግታል፡፡ ከክርስቶስ ልደት ጀምሮ የተፈፀሙትን ነገሮች በዓመት ለመውሰድ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከረ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ዲዮናስዩስ ኤክስጉአስ የተባለ መነኩሴ ነው፡፡ ሌላውም 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ አቡሻክር እብን አራሂብ (ወልዳ መነኮስ) ነው፡፡ ከዚያም ወዲህ ብዙ ሰዎች የመንግሥታትን ታሪኮች እየመረመሩ ዘመናትን መቁጠር ሞክረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በቂ የጥናት መሠረትና ማስረጃ ስላልነበራቸው ዘመኑን በትክክል አልገመቱም ስለዚህም በሊቃውንት መካከል ብዙ መለያየት ተፈጥሯል፡፡

       ስለጊዜና ዘመን ብዙዎች ብዙ ይላሉ እኔም ጊዜና ዘመን በመኖሩ ወጥተን ውለን እንገባለን፣ ጥረን ግረን ያልፍልናል ሰው እንሆናለን፣ የሕልውናችን ዋና መሠረት ነው፣ እንለወጥበታለን፣ ብዙ ድርጊቶችን እንተገብርበታለን፣ በጊዜ ደጉ በዘመን ደጉ የሠራው ያድግበታል ያልሠራው በከንቱ የሚኩራራው ይወድቅበታልናባለውለታ ስለሆነ እኛ የምንተገብረውን የሚያሳይ የኑሮና የሕይወታችን በአጠቃላይ የማንነታችን ሙሉ ገፅታ ነውና ሊወቀስ አይገባውም ‹‹አይ ጊዜ አይ ዘመን ሊባልና ሊታዘንበት ልንቆጭበት አይገባም እላለሁ፡፡

5 አስተያየቶች:

  1. ሚስተር ቤንጃሚን የኢሜል ዝርዝሮችን እነሆ ፣ Lfdsloans@outlook.com ፡፡ / ወይም ደግሞ ንግዴን ለመጀመር በ 90,000.00 ዩሮ ብድር የረዳኝ WhatsApp + 1-989-394-3740 እና እኔ በጣም አመስጋኝ ነኝ ፣ እዚህ አንድ ነጠላ እናት ነገሮች እንዳላደረጉ መንገድ ለመፍጠር እየሞከርኩ ነው ፡፡ ከእኔ ጋር ቀላል ይሁኑ ግን ንግዴ እየጠነከረ ሲመጣ እና እያሰፋ ሲሄድ እያየሁ በሚስተር ሚስተር እርዳታ ፊቴ ላይ ፈገግታ አሳየኝ ፡፡ የገንዘብ ድጋፍን መፈለግ ወይም በዚያ ንግድ ውስጥ መከራን ማለፍ ወይም የመነሻ የንግድ ሥራ ፕሮጀክት መጀመር መፈለግ ይህንን ማየት እና ከችግራቸው ለመውጣት ተስፋ ሊኖረው ይችላል ... እናመሰግናለን ፡፡

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...