“የህዳር ሚካኤል ካለፈ አንድ ወር ሆኖታል ታህሳስ ከገባ ደግሞ 11ኛ ቀኑ ነዉ እንደከዚህ በፊቱ በፌስ ቡክ እናወራለን፣
ምሥጢሬን ሁሉ ነዉ የምነግረዉ አንድም የምደብቀዉ ነገር አልነበረኝም፤ እህቴ እቤት ዉስጥ የጤና ባለሙያ ሆና ሳለ ትንሽም ራሴን
ሲያመኝ በጣምም ምቅቅ ብዬ ጨጓራዬ ሲያሰቃየኝ የማወራዉ ለሱ ነበር፡፡
በጣም እጅግ ሲበዛ በ…ጣ ም ይመክረኛል፣ ያፅናናኛል እኔም ምን እንደሆነ አላዉቅም እፅናናለሁ፣ ወዲያዉ የማላዉቀዉ
ጤንነት ይሰማኛል፡፡ በነበረን ጊዜያት አንዴ ብቻ ነዉ የማደርገዉን ነገር ያልነገርኩት እሱንም አስቤዉ አልነበረም በዚያን ጊዜ ሲጠፋብኝ
በጣም ቅር አለኝ፤ በነጋ ቁጥር የፀሐይ ብርሃን ሳይሆን የርሱ ድምጽ ነበር የሚናፍቀኝ፣ ስልኬን ስሰጠዉ ምንም ቅሬታ አልነበረኝም
፣ የመኖሪያ ቤቴን ሰፈር ሁሉ ስነግረዉ ደስ እያለኝ ነበር፣ አሁን ግን እነዛ ድምጾቹ የሉም ርቀዉኛል፤ የሚገርመዉ ድምፁን የምናፍቀዉ
ኔትወርክ በሌለበት ስፍራ ነዉ፡፡ ተራራ ባየሁ ቁጥር ሞባይሌን እንደ አቅጣጫ መጠቆሚያ ከመዳፌ አላርቃትም ነበር፤አሁንም አሁንም
ደጋግሜ አያታለሁ ቻርጅ ባየሁ ቁጥር መሰካት ነዉ ከሞባይሌ ርቄ መሄድ ጥሩ ስሜት ከማይሰሙኝ ነገሮች መካከል ዋነኛዉ ነበር፡፡ ቀናቶች
እየነጎዱ ጤናዬም መለስ እያለ ስለመጣ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ፈለኩኝ እንድመለስ ያደረገኝ የጤናዬ ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ እሱን
የማግኘት ፍላጎቴ ካቅሜ በላይ ስለሆነብኝም ጭምር እንጂ ፡፡ ለነገሩ ወደዚህ ስመጣ ስራዬን ለቅቄ ነበር የመጣሁት ልቤ ግን ክፍል
ለማለት ወደኃላ አልል አለኝና አስጨነቀኝ፡፡ደብረ ብርሃን ስደርስ ጭንቀቴ እየጨመረ ሄደ፣ መንገዱ ራቀብኝ፣