የጊዜ አጠቃቀም
መግቢያ
ስኬታማ
የጊዜ አጠቃቀም ያዳበረ ሰራተኛም ሆነ ግለሰብ ጊዜዉን በመርሃግብር እና በዕቅድ ይመራል፤ ይህ ሰዉ ህይወቱን የሚመራዉ በዕድል ሳይሆን ራሱ ነዉ፡፡ ስለዚህ ይህንን ዶክመንት ማዘጋጀት ግድ ሆኗል፡፡
ጊዜ
፡-
በቀን
24 ሰዓት
በሳምንት
7 ቀን
በወር
30 ቀን
በዓመት
52 ሳምንት/
365 ቀናት/ ብለን የምንጠራዉ ማለት ነዉ፤
“ ጊዜ
ከሁሉ ነገር በላይ እጅግ የሚያስፈልገን ነገር ሆኖ ሳለ ከሁሉ ነገር በላይ በተበላሸ ሁኔታ የምንጠቀምበት ነገር ነዉ፤”
ዊሊያም
ፔን
ዓላማ ፡-
v የተቋማትን
፣አልያም የአገራችንን፣ ከዚያም አልፎ የየራሳችንን፣ ወዘተ … “የተለጠጠ” እቅድ ለማሳካት ዋነኛ ሃብት ጊዜ በመሆኑ ጊዜያችንን በመጠቀም ዉጤትን እንድናመጣ ግብን እንድናሳካ ግንዛቤ ለመፍጠር ነዉ፡፡
የጊዜ አስፈላጊነት (ጥቅም)
Ø ለመዉጣት ለመግባታችን የምንጠቀምበት
Ø በመዉጣት በመግባታችን ዉስጥ የምናከናዉናቸዉን ነገሮች የምንፈፅምበት መሣሪያ
” የአንድ
ዓመት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ክፍሉን የደገመን ተማሪ ጠይቀዉ“
“የአንድን ሰዓት ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ለመገናኘት የተቀጣጠሩ ትኩስ ፍቅረኞችን ጠይቃቸዉ”
” የአንድን
ደቂቃ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ አዉቶቡስ ለትንሽ ያመለጠዉን ሰዉ ጠይቀዉ“
v ያለ በቂ ምክንያት፣ ከአቅማችን በታች በሆነ ጉዳይ ከሥራ ላይ የቀረንባቸዉ ቀናት ምን ያህል ግባችን ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠሩ እንመልከት፤
“ የአንድን
ሰከንድ ዋጋ ለማወቅ ከፈለግህ ከአደጋ ለጥቂት ያመለጠን ሰዉ ጠይቀዉ”