የደህንነት ቀበቶ
በምድር
ላይ ህጎች በአራቱም አቅጣጫ ይወጣሉ፤ ህግ አዉጭ፣ ህግ ተንታኝ፣ ህግ አስፈጻሚ፣ ህግ ፈፃሚ፣ ዳኛ፣ አቃቢ ህግ፣ ጠበቃ፣ከሳሽ፣ተከሳሽ፣
ምስክር፣ዋስ፣ … ወዘተ ይኖሩታል፡፡ ህጎች ከህገ ልቡና ዛሬ በየመንደሩ እና በየቤቱ በየፌስቡኩ እስከ ሚወጡት እንሰማለን እናያለን
እንተዳደርበታለን እናስተዳድርበታለን ሌሎችን እንዳኝበታለን እራሳችንም እንዳኝበታለን፡፡ከሚሻር ህግ እስከማይሻር ለዘለዓለም የሚፀና
ከኦሪት ህግ (ብሉይ ኪዳን) እስከ አዲስ ኪዳን (የወንጌል ህግ ) ድረስ ይዘልቃል፤ ከዚሁ ጋርም የህግን መሰረት ያለቀቁ ዘመናትን
ያስቆጠሩ በህብረተሰብ ዘንድ የተከበሩ ብዙ ስርዓቶችም አሉን ለምሳሌ ያህል ለመጥቀስ (የገዳ ስርዓትን የመሰለ ብዙ ሚሊዮኖች የሚተዳደሩበት
ዘመን ያስቆጠረ) በቤተሰብ ዘንድ እና በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከልም እንዲሁ ለዘመናት ህዝቡን ከሰንሰለት በጠነከረ አስተሳስሮ
ያለ ስርዓት በሁሉም ብሄር ብሔረሰብ ዘንድ አለን ቱባ ባህልን ጨምሮ፡፡
ለዛሬ
ከዚህ ወጣ ብለን አንድ ህግን መዘን አጠር አድርገን እንወያያለን ስለ ደህንነት ቀበቶ ህግ፤ በኢትዮጵያ ህግ ወጥቶለት በመተግበርና
ባለመተግበር በመቀጣትና በማስተማር እንዲሁም ላለመማር በማስተባበል ዉስጥ የዘለቀ ህግ አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለም አላት፡፡
የደህንነት ቀበቶ/ ሴፍቲ ቤልት/ ጥቅሙ በዋናነት ለባለቤቱ ሲሆን
ለሌላዉም እግረኛ መንገደኛም ሆነ አሽከርካሪ ጥቅሙ አንድ እና ሁለት የሚባል አይደለም፡፡
ለሌላዉም እግረኛ መንገደኛም ሆነ አሽከርካሪ ጥቅሙ አንድ እና ሁለት የሚባል አይደለም፡፡
የደህንነት
ቀበቶ ያላጠለቀ አሽከርካሪ አለማጥለቁን ባወቀበት ቅፅበት ከጉዞዉ ተገቶ ቀበቶዉን ለማድረግ ይገደዳል፤ ነፍሱን/አካሉን እና ንብረቱን
ከአደጋ ለመታደግ ፣ ንብረት ከማዉደም እና አካልን/ነፍስን ከማጥፋት ሌላዉን ለመታደግ ፣ አልፎ ተርፎም ከመቀጣት እና የቅጣት ቁጥሩን
ላለማብዛት እና ለመቀነስ፡፡
ዛሬም
ለሚያሽከረክሩትም ሆነ ለማናሽከረክረዉ፣ ህጉን ጠብቀን በእግረኛ መንገድ ለምንጓዘዉም ሆነ ለማንጓዘዉ፣ የእግረኛ ማቋረጫ (ዜብራ)
ለምንጠቀመዉም ሆነ ለማንጠቀመዉ ሁሉን በአንድ ስለሚገዛ እና ልብ ልንለዉ ስለሚገባ ነገር እየጋለብን ካለንበት ከአዉሎ ንፋስ ከፈጠነ
ዝቅጠታችን ማንሳት ወደድኩ ሆላችንም ቆም ብለን የደህንነት ቀበቶአችንን ጠበቅ እንድናደርግ አደራዬ የበረታ ነዉ፡፡ ይኸዉም ስለ
ብሄር ያለን የተንሸዋረረ እይታ እያሰጋኝ ስለሆነ ነዉ፤ ለምን? ካለችሁ ትዉልድ የተሻገረ አብሮነታችን ዛሬ ደብዛዉ እየጠፋ ነዉ፣
ጉረቤታሞች እና አበልጃሞች በዚህ ጠባብነት እየተቃቃሩ እየተነጣጠሉ ነዉ፣ ይህ የብሄር ድንበር ሳይገድባቸዉ ትናንት ጋብቻን መስርተዉ
ፍሬ አፍርተዉ ቤተሰብ የመሰረቱ ኢትዮጵያዊነትን ያፀኑ ብሔረሰቦች አንሶ ለመለየት የትዳርን አጥር ለመነቅነቅ የአገርን ዳር ድንበር
ለማናጋት ዳር ደርሰዋል፣ የተማረ ሰዉ መፍለቂያ የሆኑ የዕዉቀት ገበታዎቻችን ዩኒቨርሲዎቻችን ከትላንት በባሰ መልኩ ብሄር ብሄረሰቦች
እንዳይማሩባት ጥቂት የማይባሉ ስጋቶች እንደባህር ዛፍ ችግኝ ፈልተዉባታል፣ሃዘን እና ደስታችንን እንኳን የምንካፈለዉ በብሄር መሆን
ከጀመረ ሰነበተ፣ ወንዞች ተራሮች ኮረብቶች ቅርሶች ወዘተ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊያን መሆናቸዉ ቀርቶ የብሄሮች ብቻ እየሆኑ
መጥተዋል፣ ስለ አንዲት ኢትዮጵያ መሆኑ ቀርቶ ስለ አንድ ብሄር ግለሰብ ሲባል አንድነት ትንቀጠቀጣለች የሶሻል ሚዲያዎች ማዕበል
ህዝብን ይንጣል ኢትዮጵያ ትታመማለች (ኢትዮጵያዊነት አንድም ሰዉ ራሱን እንዲያመዉ ሆዱን እንዲቆርጠዉ የማንሻበት ማንነት ነዉ)፣
በብሄር ሽኩቻ የተነሳ ትክክል ያልሆነዉ ትክክል የሞሆንበት ትክክል የሆነዉ ደግሞ ትክክል የማይሆንበት ፍርድ የተዛባባት ጊዜ ላይ
ደርሰናል፣ ብዙ ምሁራን የዘረኝነት እንቦጭ ወሮአቸዉ ቢጨምቋቸዉ ብሄርተኝነት ብቻ ስለሚያቀነቅኑ ተተኪ ዜጋን ማፍራት ከተሳነን አስርት
ዓመታት አንድ ሁለት እያሉ ነዉ፣ …
ስለዚህ ትዉልድ ሊቀጣ ነዉና፣አደጋ እየደረሰ ነዉና፣ ንብረት እየወደመ ነዉና፣
አንድነት/ህብረት እየተናጋ ነዉና ቆም ብለን እናስብ፤መልዕክቴ ነዉ፡፡
ቆም
ብለን ማሰብ ካልቻልን ከኛ ጀርባ ያሉ ይጎዳሉ፣ ከኛ ጀርባ ያሉ ይጎዳሉ፣ ከኛ ማህፀን ያሉ ይጎዳሉ፣ በአዕምሮአችን የሚመላለሱ የሃገር
እና የህብረተሰብ ተስፋ ጨቅላ ሃሳቦች ይነጥፋሉ፣ የእጅ ስራዎቻችን ይመክናሉ፣ ተስፋዎቻችን ይጨልማሉ፣ እኛም አልፈን ትናንት የሚባል
ይጠፋል፣ ነገም ይጨልማል፤ …
ዘረኝነት
የልሂቃን እንዳልሆነ ይታወቃል፤ እዉነት ይህ ሁሉ ጨዋ እና ከእዉቀት ነፃ ከሆነ አገር ባዶዋን ነች፡፡ 100 ሚሊዮን ህዝብ ባለባት
አገር እንዲህ አይነት ዜማ የህዝብ መዝሙር ሊሆን አይገባም፣ ሸምጋይ እና ገላጋይ ከጠፋ እሳት ሲቀጣጠል ቢንዚን የምናቀብል ከሆነ
በዚህ ዘመን ዉስጥ ማለፍ በራሱ እፍረት ነዉ፡፡
የሰዉነታችን
ክፍል ሁሉም እድገቱ ሲገታ ሁሌም እያደገ የሚሄድና እድገቱ የማይገታዉ አዕምሮ ብቻ ነዉ አድገን እዚህ ደርሰን ከሆነ አንገት ያስደፋል፤
እስኪ ዘወር ብለን እናስብ፡፡ ተሰብስበን ስለ እንደዚህ አይነት ኪሳራ ከምናወራ ስለ ኢትዮጵያ ትንሳኤ እንስራ፤ ጠባብነትን እናስወግድ
ሃላፊነትን ሌሎች ላይ ጣታችንን አንቀስር፡፡
መጋቢ
ምሥጢር አባ ወርቅነህ የሚባሉ የሃይማኖት መምህሬ በረካተቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን እና ስራፈት አዕምሮ የሰይጣን ወርክሾፕ ይሆናል
ይሉ ነበር ዛሬም የስራ ፈትነታችን ጥግ የፅንፈኞች መጫወቻ አድርጎናል፡፡ በኳስ ሲባክን የነበረ ጭንቅላታችን ዛሬ ደግሞ በሶሻል
ሚዲያ ክፉ ወሬ አንድነታችን ተናግቷል፡፡
የደህንነት
ቀበቶ ፡-
በአደገኛ
የስራ ገበታ ላይ ያለዉን ከአደጋ ይታደጋል፣
ልጆችን
በመኪና ዉስጥ አሳፍረን ስንጓዝ ከአደጋ ከመታደጉ/ከመቀነሱ ባሻገር ነፃነት እንዲሰማን ያደርጋል፣
ከቅጣት
ያድነናል፣
ከፍታን
ለመዉጣት ወደ ጥልቁም በቀላሉ ለመዝለቅ ያስችለናል፣
ስጋትን
ይቀንሳል፣
ስለዚህ
ለህይወታችን፣ ለአንደበታችን፣ ለአዕምሮአችን፣ ለእጃችን (ለስሜት ህዋሳቶቻችን) የደህንነት ቀበቶ እንጠቀም፤ " አንደበትህን
ጠብቅ … " ተብለናልና፡፡ የትምህርት ቤት መምህራን በየደረጃዉ አንድነትን ስበኩ፣ የሃይማኖት መምህራን በመድረክም በህይወትም
አንድነትን /ፍቅርን/ ይቅርታን/ ትዕግስትን/ … ስበኩ፣ የአገር ሽማግሌዎች የተጣሉትን አስታርቁ/ የተራራቁትን አቀራርቡ፣ ወላጆች
ነገር ተረካቢ ጥሩ ዜጋ አፍሩ፣ ወጣቶች ስሜቶቻችሁን በመግዛት / አንደበታችሁን በመጠበቅ/ እሳትን በቅጠል እንጂ በማቀጠል ነገ
አገር ወገን አትጡ/ በገንዘብም ልብ ግዙ እንጂ ስሜቶቻችሁን ለማብረድ እህቶቻችሁን አትግዙ፣ ህፃናትም እግዚአብሔርን በመፍራት ባህላችሁን
በመጠበቅ እደጉ፡፡
ምላስ
ቁጣን ታበርዳለች እሳትም ታስነሳለችና ያላያችሁትን እንዳያችሁ የወደቀዉን ተሰበረ፣ በሬ ወለደ እያልን ከማዉራት ተጠብቀን አይቶ
እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ በመሆን ክፉ ዘመን እስኪያልፍ በአርምሞ እና በፀሎት አገራችንን ከዉስጥ ሆነ ከዉጭ ጠላት በመጠበቅ አባቶቻችን
ያቆዩልንን ሰላማዊት የሆነች እንኳንስ የተወልድንባት ለመጡባትም የምትመቸዋን ለልጆቻችን ለማዉረስ እንትጋ፡፡ አንድነታችንን አጠንክረን
እንጠብቅ፡፡
መልካም
ዘመን!
አንዲት
ኢትዮጵያ!
የብሄር
ብሄረሰብ እኩልነት ይለምልም፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ