ሟችና መልዐከ ሞት
እስኪ ይፍረዱ፤
እርስዎ እያሉ እነማን ይሂዱ?
ታሪኩ እንዲህ ነዉ ሰዉየዉ በዕድሜ እጅግ በጣም
እጅግ የገፉ ናቸዉ ከዕለታት አንድ ቀን አጅሬ ሞት በድንገት ከተፍ ይልባቸዉና "ይነሱ ልወስድዎት
ነዉ ተልኬ የመጣሁት "ብሎ በሰዉኛ ያናግራቸዋል፤ ሰዉየዉም እስከዛሬ ባላዩት እንግዳ ሰዉ እና እንዲህ አይነት
አስደንጋጭ መልዕክተኛ ግራ በመጋባትም በመደናገጥም "አንተ ማነህ? ከወደየትስ ነዉ የመጣኸዉ? የላከህስ ማነዉ?" ይሉታል፡፡
መልዕክተኛዉም "እኔ መላከሞት ነኝ! የላከኝ ፈጣሪ ነዉ" ብሎ አሳጥሮ ይነግራቸዋል፤
"እህሳ ለምን መጣህ?"
"ልወስዶት ተልኬ"
"ለምን ቢባል?"
"የመሔጃ ጊዜዎት ስለደረሰ ልወስዶት… "
"በል እንግዲህ ይህን መልዕክት ይዘህ መጥተህ የለም፤ መልዕክቴንም አድርስልኝ መሔጃዬ ሲደርስ
እኔ ራሴ ሰዉ እልክብሃለዉ በልልኝ"
ብለዉ መልአከ ሞትን ሸኙት፤ ሞትም ተመልሶ ሄደ፡፡
ከዓመታት በኋላ ብዙ ሰዉ ከሞተ በኋላ እንዲሁ
እንደከዚህ በፊቱ የነፍሳቸዉን ደጅ ይጠፋል(ያንኳኳል)
"ማነህ?"
"እኔ ነኝ!"
"አንተ ማን …. ስም የለህም?"
"መልዐከ ሞት ባለፈዉ መጥቼ የመለሱኝ"
"ታድያ ለምን መጣህ? አትምጣ እኔ ራሴ ሰዓቴ ሲደርስ መልዕክተኛ እልክብሃለዉ ብዩህ የለ?"
"አይ ይበቃዎታል፤ እርሶ እድሜ ልክዎትን ቢጠበቁ ጊዜዬ ደርሷል ብለዉ ሰዉ አይሰዱም ይልቅስ
አሁን ይነሱ እና እንሂድ አላቸዉ"
እሳቸዉ ግን በፍፁም ሊሄዱ ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡
መልዕክተኛዉም መልአከ ሞት እንደምንም ሊያግባባቸዉ ሞከረ፤ እሳቸዉ ግን አሻፈረኝ አሉት፡፡ ሞትም ቀረብ ብሏቸዉ
"
እስኪ ይፍረዱ ፤
እርስዎ እያሉ እነማን ይሂዱ?" አላቸዉ ይባላል፡፡
አሁንም ስልጣንን መልቀቅ እና ሞትን የሚፈሩ ብዙዎች ናቸዉ፤ ሆኖም ግን መልዐከ ሞት እንዳለዉ እናንተ እያላችሁ እነማን ይሙቱ? እነማንስ ከስልጣን
ይዉረዱ?
ጆሮ ያለዉ ይስማ! ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ