ከሳጥናኤል ማስታወቂያ ሚኒስተር የወጣ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ድርጅታችን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ክፍት የሥራ ቦታዎች ሠራተኞችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
1. ለክፋት
ማበልፀጊያ
ማዕከል፡- በዕውቀቱ ወይም በጉልበቱ በማጭበርበር ወይም በመጭበርበር ዲግሪ የተመረቀ ዕውቀትን የዛቀ በተንኮል ጥበብ የመጠቀ ከአጉል ሱሶች ማለትም፡- ከፍቅር፣ ከደግነት ከእውነትና ከጋራ ዕድገት የራቀ ከሚኖርበት ክልል በማንኛውም የማኅበራዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ ያልተሳተፈ መሆኑን መረጃ ማቅረብ የሚችል፡-
·
ዕድሜ፡- በዚህች ዓለም ላይ ቢያንስ ለግማሽ ቀን የኖረ
·
የሥራው ዓይነት፡- ነገር ጉንጎና
·
ደሞዝ፡- እንደሌብነት
·
የሥራው ቦታ፡- ሥራ ከማይሠራባቸው ከተሞች ባንዱ
2. ለዕብዶች
ተራድኦ
ድርጅት፡- አንድ ካልታወቀ ዩኒቨርስቲ በማስትሬት ድግሪ ተመርቆ በ‹‹ኑሮኝነት›› ሙያ ፒ.ኤች.ዲ ያለው ከሰው ልጅ ጋር በመኖር ቢያንስ የአምስት ደቂቃ ልምድ ያለው፡-
·
ዕድሜው፡- ያልታወቀ
·
የሥራ ዓይነት፡- ገላጋይነት
·
ደሞዝ፡- የአንድ ሺህ ብር ጫት
·
የሥራው ቦታ፡- መንጨቆረር
3. የሽርደዳና
የአቃቂር
ማምረቻ
ፋብሪካ፡- አንድ እንደ ዘንድሮ ሰው ‹‹ምላሱ መንታ አንዱ ለፍቅር አንዱ ላሜታ›› የሆነ ‹‹ሄደ ተናገሩ መጣ ዝም በሉ››ን ጠንቅቆ የሚያውቅ የነገርን ፊደል የለየ ሆኖ ቢያንስ የአምስት ዓመት የቅናት ልምድ ያለው የመላዕክት ሆነ የዲያብሎስን ቋንቋ አሳምሮ መናገር የሚችል፡-
·
ዕድሜ፡- እንደምላሱ
·
የሥራ ዓይነት፡- ጥሬ የሠው ሥጋ ዘልዛይነት
·
ደሞዝ፡- በንትርክ
·
የሥራ ቦታ፡- አዲሱ የነገር ቄራ
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ