አዳም ‹‹ሴት›› ትባል ብሎ ከሰየማት አንስቶ እናት፣እህት፣ሚስት ሆና የኖረች የአዳም/የሰው ልጅ ተሰፋ/ የሆነች ይህቺ ሴት የሚደርሱባት ተጽእኖ ቀላል አይደሉም፡፡
በአላማችን ከገጠሩ ክፍለ ዓለም እስከ ዋና ዋና ከተሞች በማደግ ላይ ካሉ አገሮች አንስቶ እስከ አደጉ ከሚባሉት አገሮች ጭምር የሴት ልጅ ተጽእኖዎች እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡ ልጆችን በማኅፀኗ ከመጸነስ አንስቶ ወልዳ እስከ ማሳደግ እና ለወግ ለማዕረግ
የበለጠ ለማንበብ ከታች ይጫኑ!
እስከ ማብቃት ድረስ ያለው ድርሻ አብዛኛውና እጅጉን ውጤታማው የሴት ልጅ /የእናት/ ድርሻ ነው፡፡
በገጠሩ ያሉትን ሴቶች እህቶቻችን /እናቶታችን/ወይም ሚስቶቻችን ብንመለከታቸው በማህበረሰቡ ካሉት ተጽእኖዎ...ች ባሻገር በቤቷ/በጓዳዋ/ የሚጋጥሟት ተጽዕኖዎች እጀጉን ብዙዎች ናቸው፡፡ ምግብ ማብሰል፣ ልጆችን መንከባከብ፣ ባለቤቷን መንከባከብ ማስደሰት በሥራ ማገዝ፣ በእርሻው ሥራ በማረም፣ አልፎ አልፎም በማረስ፣ እርሻው ቦታ ድረስ ምሳ አዘጋጅቶ ይዞ በመሄድ፣ በለስ ቀንቷት ለማሳካት ደፋ ቀና ስትል ውላ ማረፍ ሲገባት አፍ ካልፈቱት ህፃናት እስከ ሊረዳት እና ሊረዳት(ረ ይጠብቃል) የሚገባው ባለቤቷ /አባወራው/ ጨምሮ ተጽእኖ ፈጣሪዎቿ ናቸው፡፡ ህጻናት አልበላም አልጠጣም በማለት በማስጨነቅ እና ህማማቸውንም ይሁን ድካማቸውን በለቅሶ በመግለጽ ስቃይዋን ያበዙባታል፡፡ከዚህም ባሻገር ባለቤትዋም ውሃ ቀጠነ በማለት በትር ሊያነሳ፣ ከቤት ሊያባርር፣ የዕረፍት ጊዜዋን (የደስታ ጊዜዋን) ተስፋ አጨልሞ ሊያስቀይማት ይችላል፡፡ የገጠሯ ሴት የሚደርስባት ችግር ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በትር ሲነሳ አካሏ ሊጎድል፣ ጥርሷ ሊረግፍ ፣ አይኗ ለጠፋ፣ ህይወቷም ሊያልፍ ይችላል፡፡
የሴት ልጅ ይልቁንም የገጠሯ የተጽእኖዎቿ መቼት ከእናቷ ማህጸን አንስቶ እስከ ግብአት መሬቷ አንደ ጥላ ይከተላታል፡፡ እስኪ ልብ ብለን እንመልከት የተወለደችው ሴት መሆኗን እንኳን በደስታ የሚቀበል የለም ምን ወለድክ ተብላችሁ ስትጠየቁ ‹‹ሴት›› ብላችሁ ስትመለሱ ጥቂቶች ናቸው በደስታ የሚቀበሉት አብዛኛው ሰው ሴትን ጨምሮ ‹‹ይሁን ግድ›› ‹‹የለም›› በሚቀጥለው ‹‹ወንድ›› ትወልዳለህ/ሽ/ በማለት ወንድ በረከት ይዞ ይመጣ ይመስል ወንድ መውለድ እንደ ጀብዱ የሚታየው መቼ ይኼ ብቻ የሴት ተጽዕኖ ገና ከፍ ሳትልና ነፍስ ሳታውቅ አለበለዚያ ገና አሥር አመት ሳይሞላት በግርዛት ሥም ሥጋዋ ይተለተላል፡፡ በዚህም የተነሳ የዛሬ ቁስሏ ለነገ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል፡፡ የመከራዋ ፍጻሜ ሳይሆን መጀመሪያ ይሆናል፡፡
እንዲህና እንዲህ የተፈጠረች ጨቅላ ህጻን ናት እንግዲህ እህት፣ እናት፣ ሚስት በመሆን የመኖራችንን ተስፋ ዘር በመተካት÷ትውልድ በማብዛት የምታለመልመዋ፣ የምትደፈረው፣ የምተደበደበው፣ ሴት ስትባል የምትናቀው፣ በወሊድ ምክንያት ረዳት አጥታ ችግሯን የሚቀርፍ መሰረተ ልማት መርሐ ግብር ጠፍቶ….. መንገድ ላይ የምትቀረው፣ ይህቺ ሴት ናት እንግዲህ የተማሪው፣ የመምህሩ፣ የወዛደሩ፣ የወታደሩ ፣ የዶክተሩ፣ የእንጂነሩ፣ የማናጀሩ፣… እናት የሰባት ቢልየን ፍጥረት እናት፣ የፈጣሪ እናት፣ የተጽእኖ አድራሹ እና ተጽእኖ የሚደርስበት ሁሉ እናት፣……
ተጽእኖ ለማሳረፍ መቼ በገጠሯ ሴት ብቻ በቃና የከተማዋስ ብትሆን በቤት፣ በቢሮ፣ በሞቀ ቤት /ትዳር/ እስከ ጎዳና፣ ካላገባችዋ እስካገባችው ….. ሥንቱ ተጠቅሶ ይዘለቃል? ምን ተብሎ ይጠናቀቃል? በምንስ ቃላት ይገለጣል? በእንባና በቁጭት ብቻ ካልተቋጨ የትኛውስ ሰው የትኛውስ መንግስት፣ የትኛውስ ዘመን፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ደስታ÷ይሰጧቸዋል? ማንስ እንባዋን ያብስላታል? የትኛው ዳኛ÷ የትኛው ህግ ይፈርድላታል? በቃሽ የሚላት፣ አይዞሽ ብሎ የሚያጽናናት? ከእንግዲህ በቃ ብሎ የተስፋ ጮራ የሚፈነጥቅላት? March 8 ነው ወይስ ከታች እስከ ላይ የተደራጀው ‹‹የሴቶች ጉዳይ›› ወይስ እንደ ሰው ተቆጥራው ‹‹ሰብዓዎ መብት ተሟጋች››? “እንባ ጠባቂ” ??? ማነው እኔ ነኝ ባይ? ማነው ለውጥ አመጭ? የለውጥ ጀግና ራሷ ሴቷ ወይስ የግራ አጥንቱን ፈልቅቆ የሰጣት ያ! ወንድ ይሆን???...
የከተማዋም ሴት የሚደርስባት ተጽእኖ የዋዛ አይደለም እንደፍጡር ፍቅር ትራባለች፣ እንክብካቤ ትከጅላለች፣ ርህራሄ ትማጸናለች፣ ‹‹ሴት›› የክብር ስሟ መሆኑ ቀርቶ ‹‹ሴት›› ተብለ ትሰደባለች፣ ትናቃለች፣ የዓለም ጀግና መሆኗ ተዘንግቶ ድንገት በጨረፍታ ጀግንነቷን ያዩ እንኳን በሴትነቷ እምነት እጥተው ‹‹ወንድ›› ብለው ያሞካሿታል፡፡ ወንድ ተብላ ከምትመሰገን ምነው ‹‹ሴት›› ተብላ በቀረች!
የትኛው ወንድ ይሆን ‹‹ወንድ›› ሆኖ በትሯን ምጧን፣ ቁስሏን፣ ምቷን፣ የቻለላት? የትኛውስ ‹‹ወንድ›› ይሆን እነሆ ትከሻዬ እንኪ ንሺ ጅርባዬን ቻይበት ያላትና ያዋሳት ‹‹ወንድ›› የሚለውን ቅጽል ስም እንደ ደህና ገጸ በረከት የሚያበረክቱላት ‹‹ወንድ›› ከሚለው የተውሶ ስም ይልቅኮ ‹‹ሴትነቷ፣እናትነቷ፣ እህትነቷ፣ሚስትነቷ›› እኮ ነው አስችሎና አስታግሶ ዘመናትን ያሻገራት
ይህንን ጹሁፍ ስሞነጫጭር አንዲት እህቴ ተመልክታ ‹‹እኛስ መች ይሆን ተጽእኖ የምናሳርፈው››? ብላ ጠየቀችኝ የዚህ ጹሁፍ ልባዊ ምኞቱ ማንም በማንም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዲያሰርፍ አይመኝም፡፡ በሰላምና በደስታ በፍቅር በዚህች በተሰጠችን ምድር ላይ በጋራ ተጋግዘን ተሳስበን እንኖር ዘንድ ከልቡ ይመኛል፡፡ አንባቢም በስሜት እየተቆጨ በክፉ
3እንዲተያይ ሳይሆን ከክፉ ተግባራችን እንድንመለስ አመለካከታችንን እንድናቃና ይልቅስ ተሳስበን እንድንኖር በመደጋገፍ ቀሪ ዘመናችንን እንድንቀጥል የሴት እህቶቻችንን፣ እናቶቻችንን፣ ሚስቶቻችንን የወደፊት ተስፋ ብሩህ አንድናደርግ ነው፡፡
ወደ ዋናው ቁም ነገር እንመለስና የከተሜዋ ሴት በየመገናኛ ብዙኀኑ፣ በየመንደሩ፣ በየካፍቴሪያው፣ በየመጠጥ ቤቱ፣ በየሆስፒታሉ፣ በሐዘንና በየደስታ ቦታው ዕለት ዕለት እንደምንሰማው በርሷ ላይ የሚደርሰው ተጽዕኖ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ መጥቷል፡፡
በበትር ትደበዳባለች አካላቶቿ ይጎድላሉ ሰላሟ ይናጋል ተስፋው ይመነምናል ዛሬ ዛሬማ በሴት ልጅ ላይ አሲድ መድፋት ቀላል ነገር፣ ዝና፣ ‹‹ህገ መንግስታዊ›› መብት፣…… እየሆነ መጥቷል እነዚያ በሥሥትና በናፍቆት የሚያዩ አይኖቿ ብርሃን ያጣሉ፣ ዘጠኝ ወር እንደ መልካም ከተማ ስታስቦርቀን የነበሩ ማኀጸኖቿ በርግጫ ይረጋገጣሉ፣ የፍቅር እናት፣ የፍቅር ተመሳሌት የሆነችዋ ሴት ትደፈራለች ከዚህም ባሻገር በአስገድዶ መደፈር የዕድሜ ልክ ጠባሳ ተሸክማ ትኖራለች/የማኀፀን ኢንፌክሽን፣ ፌስቱላ፣የተለያ የማኀጸን ችግሮች፣ በመደፈሯ ምክንያት የሚፈጠረውን እርግዝና ውርጃ የአባለዘር በሽታ ( H.I.V.አዴስን ጨምሮ) ይኼ ሁሉ ደርሶባት ወደ ህግ ቦታ እንኳን ሄዳ ፍትህ ታጣለች በደል አድራሹም ‹‹ምን ታካብዳለችሁ? ምን ሆነች?›› ስለምወዳት ነው?›› ፣ ‹‹…እምቢ ብላኝ ነው›› እያለ ምክንያት ያቀርባል ልብ በሉ እምቢ የማለት መብት እንኳን የላትም፤ አፍቅራ ማፍቀሯን ቀድማ ብትናገር ፈጣጣ፣ ደፋር፣ ባለጌ፣ ዓይነባላ፣ …… ›› ተብላ ትታማለች /ትወገዛለች/ ታዲያ ይህቺ ሴት ምን ይዋጣት? የት ትግባ? ማንስ ለመብቷ ዘብ ይቁምላት ህግ መንግስት? ህገ እግዚአብሔር?ወይስ ወንድ?
የሚገርመው ነገር በአስገድዶ መደፈር ብዙ ነገር ከደረሰባት በደል ባሻገር የሠርግዋ ዕለት ‹‹ልጃገረድ›› አይደለሽም ተብላ እንደገና ደም ይፈለግባታል፣ እንደገና ግፍ ይዋልባታል፡፡ ፍርዱን ለማን እንተወው?የተበደለችዋንና የተደፈረችዋን ሴት ቤት ይቁጠረው፤ መደፈሯ ሳያንስ ይኸንን በደልና ይኸንን ጉድ በርትታ ብትናገር ራስሽ ያመጣሽው ጣጣ ነው ተብላ ብልግናዋ ተወርቶ ዓይንሽን ላፈር ትባላለች፤ አሰዳቢ ተብላ ተረገማለች በዚህ ምክንያት ሥንቷ ህመሟን ዋጥ አድርጋ ተቀምጣለች? አቅም፣ ጉልበት፣ እውቀት፣ ጥበብ፣ እያላት እንዳትጠቀምበት ሴት በመሆኗ ተምቃና ታቅባ ተቀምጣለች፡፡ ይህ የሴት ሥራ አይደለም እየተባለች ሥነቱን የማዕረግ፣ የዕድገት፣የደረጃ፣ሥፍራ ተነፍጋለች ሴትኮ ጀግና ናት፣ወታደርናት፣ ፖሊስ ናት፣ማነው የደርግን የግፍ አገዛዝ መንግስት የገረሰሰው?ወንዱ ብቻ ነው እንዴ? ወንዱስ ብቻው በዘመተበት ዘመን በማን ሥንቅ አቀባይነት ነወ?የጠሩን ሜዳ ተኩስ፣ ፍንዳታ ፣ሞትናቁስለት፣ተቋቁሞ ድልን የተቀዳጀው የነሚኒሊክ የቴውድሮስ፣ የዮሐንስ፣ የአሉላ፣ የሐየሎም የጀግኖች አርበኞች እናት ለመሆኑ ማን ናት ‹‹ሴት›› አይደለችም?
ወንዱ ቢጀግን፣በሸፍት፣ቢያምጽ፣ቢነግስ፣ በሾም፣ ቢማር፣ ምሁር ቢሆን ቢደድብ፣ አገር የሚሸጥ ቢሆን ሥም የሚያስጠራ ቢሆን ….. መሰረቱ ማን ናት? ሴት ለዚህ ጀግና ለዚህ ምሁር የዕውቀቱ ምንጭ የጦር ሜዳው ድሉ እርሷ ናት፣ በተጓዘበት ርምጃው ሁሉ ጥላው ናት፣ የሥራው ውጤት አሻራ ናት፣ የድርሰቶቹ ነቁጥ ናት፣ የወንድ ልጅ መነሻና መድረሻው እርሷ ናት ፣…ምነው ታዲያ ይህቺን እናት፣ ይህቺን እህት ይህቺን ሚስት፣ ይህቺበን ሴት ዓለም በደፋናው ዝም አላት?ክብር ሽልማት ኒሻን ሲገባት ነፈጋት? ‹‹ወርቅ ላበደረ ጠጠር›› እንዲሉ ሕይወቷን ሰለጠችን ተጎሳቁላ ላከበራችን እንዴት ሴት ተብላ በንቀት ትጠራ እንዴትስ ትጠላ ‹‹ባል ›› መሆን ክብር ከሆነ ባል በሆነች፣ አባት መሆን ብርቅ ከሆነ እናትም አባትም ሆና ፍጥረትን ሁሉ በሥሟ በስተጠራች ያቺን ሴት እህት አርጎ ያልፈጠረላችሁ ከመውጊያ ብረት ጸብ መፍጠር /መቃወም/በእኛ ይብስብናል እንጂ ፈጣሪን ተጣሉት ባልኳችሁ ነበር፡፡ በድምሩ ያለ ሴት ልጅ ይህቺ ዓለም ባዶ እንደሆነች ልነግራችሁ ወደድኩ፡፡
እንግዲህ ወገኖቼ ስለ ሴት ካነሳንና እንጻፍ ካልን ጹሁፌ ዋና ጹሁፍ ሊሆን ይቅርና ‹‹መቅድም›› ወይም ‹‹መግቢያ›› ሊሆን አይችልምና ይቆየን ለማንኛውም ‹‹ማን እንደ እናት ማን እንደ ሐገር›› የሚለውን ዘፈን ጋብዢአችኃለሁ፡፡
ሳትማር ያስማረችን የተፈጥሮ ምሁር መማርን ብትነፈግ እውቀትን በጸጋ የተቸረች ልበ ንጹህ /ብሩህ/ አዕምሮ የሆነች (ይህ ሰው አደላ እንዳትሉ ምናልባት ዓይኖቻችን ጥቂቶችን አይቶ ሴትን አይንሽን ለአፈር ያለባት አጋጣሚ ተፈጥሮ ሊሆን ስለሚችል) በድመር ውጤት ግን ይህቺ ሴት የሌለችበት ህይወት አይጣፍጥም በአጠቃላይ የሕይወት ማጣፈጫ ቅመም/ጨው/ናት፡፡ እስኪ ባሎች /ወንድሞች/ ሴት በር ከፍታ ያልጠበቀችው ቤት፣አጣፍጣ ሰርታ ያለባለቸው ምግብና መጠጥ መርጣ አውጥታ ያለበስችው ልብስ ወዘተ ምኑ ቅጡ እርሷ የሌለችበት ሁሉ ባዶ ነው፡፡ ነገሩ እግዚአብሔርም ሲፈጥራት የወንድ ልጅ ጉድለት መሙያ ውበት ናት ድክመቱን ትሞላለት ዘንድ የተፈጠረች ልዩ ድንቅ ፍጥረት ይህቺ ሴት ናት እንግዲህ እንደ አመልኳ መከራን የምትቀበል የሰው ልጅ መድህን ናት፡፡
ይህቺ ሴት ሴትነቷም ያደረሰባት ተጽዕኖ ስታረግዝ ጀምሮ ከመጀሪያዎቹ ወራት አንስቶ የበላችው አይረጋላት፣ ልትወልድ ስትል ምጧ ያስጨንቃታል፣ሥትወልድ ማሳደጉ ይከብዳል፣ከማርገዝ ማሳደግ ይከብዳልና፣ ሰውን ለማሳደግ ከሠውንት ጎዳና ትወጣለች፣……ወዘተ
የሰው ልጆች ሁላችሁ ይልቁንም ወንዶች ታዘዟቸው፣ ተንከባከቧቸው፣ ላጠፉችሁት ለተበደሉት በደል ሁሉ ይቅርታ ጠይቋቸው፣ ትራንስፖረት ውስጥ አመቺ ቦታ ስጧቸው፣ መንገድ ላይ ቅድሚያ ስጧቸው፣ ማንኛውም ቦታ ላይ በፍቅር ታዘዟቸው፣ ውደዷቸው፣ አፍቅሯቸው፣ጥሩ ሚሰት /የልጆቻችሁ እናት/ አድርጓቸው፡፡

ይህች
ስፍስፍ እናት ናት እንግዲህ ስንት አይነት ስድብ የሚደርስባት
ክብር ለእናቴ፣ ክብር ለሚስቴ፣ ክብር ለሴቶች ልጄቼ፣ ክብር ለእህቶቼ፣ ክብር ለሴቶች!
ክብር ለወንዶች!
የሌሊትን ድቅድቅ ጨለማ የማለዳ ጀንበር ወደተደነቀ ብርሃን እንደሚያሻግረው ሴትም እንዲሁ የብቸኝነት ድቅድቅ ሕይወት ወደተደነቀ ብሩህ ተስፋ የምታሸጋግር ሕይወትን በደስታ ብርሃን የምትሞላ ብቸኛ ፍጥረት /ሴት/የማለዳ ጀንበር ናት፡፡

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ