ለሰው ልጆች በዚህ ምድር ላይ የምንኖበት ሰዓት መስራታዊና
አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በታችኞቹ የትምህርት ቤት ክፍሎች በደንብ
ስምተናል፤ ዛሬ ዛሬ ግን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይልቁንም ለተማሪዎችና ለመንግሥትም ሆነ ለግል ድርጅት ተቀጣሪ ሠራተኞች መሠራታዊ
እየሆኑ ካ ነገሮች መካከል ትራንስፖርት ቅድሚያውን ሥፍራ ከያዘ ሠነባበቱ ነገር ግን “አባከና” የሚለውም ካጣ በመስነባበቱ ምክንት
ችግሩ ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል “መፍትሔ” እየተባሉ የሚወሰዱትም ተጠቃሚ ህብረተሰብን ያላማከለ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ከዚህም ጎን ለጎን በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የተሰማሩት እንዲሁ ተበደልን ከገበያው ልንወጣ ነው በማት ሮሮዋቸውን የነዳጁን በየጊጊዌውመጨመር፤
የመለዋወጫ ዕቃ መናገር፤ እንዲሁ ከአሥር ዓመት በፊት ለሙሉ ጥገና የምናወጣው ወጪ ከእጥፍ በላይ መጨ መርን….ቀዘተ ዋቢ በማድረግ
ያቀርባ፡፡ ይኽ ሁሉ እውነታ ካለ ታዲያ መፍትሔው ምን ይሁን? ባለድርሻ አካላት፤ ባለሃበት፤ መንግሥት፤ ህብረተሰብ፤ ወዘተ ማት
የሚገባውን ከተግባ ጋር እንደያደርጉት አደራዬን አሠማለሁ በበኩሌ ግን አንድ ነገር ጠይቄ በዚየው ማት ያብኝን ማት አውዳለሁ፡፡
ጎልቶ በሚታየው የትራንስፖርት ችግር ላይ መፍትሔ ለመሥጠት
እብጠቱን ለማስተንፈስ ከችግር ይልቅ ወደመፍትሄነት ለማሸጋገር የአንበሳው ደርሻ ምን ይወስድ?
ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ይጫኑ
ይህ አንኳር ጥያቄ እንዳለ ሆኖ አንዳንድ ነገሮችን ለማንሳት
ወደድኩ፤ በአሁኑ ሰዓት የትራንስፖትን አብይ ችግር ለመፍታት ደፋቀና ከሚሉት መካከል ጥቄቶቹን ብንጠቅስ ታክሲዎች፤ ሐይገር (ሚዲባስ)፤
“ላዳዎች”፤ የመሳሪያ ቤቶች ሰርቪስ፤ እንዲሁም በዋነኛነት አንበሳ የከተማ አውቶብሶች ወዘተ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ብቻቸው
መፍትሔውን ለማምጣት ደፋ ቀና ሲሉ ትከሻቸ ው የጐበጠ የትራንስፖርት አገልግሎት በመሥጠት ላይ ያሉ ዘርፎች ምን እያደረጉ ነው?
ምን እያጠፉ ነው? እንዴት መሥራት አለባቸው? ምን ማስተካያ ማድረግ አለባቸው? ቀዘተ የሚሉትን ብንመለከት የተሸለ ይመስለኛል፡፡
ለአንባቢዎቼ “ማስጠንቀቅ” ወይም ማሳሰብ የምፈልገው ፅሑፌን
ስታነቡ በማብዛት ሳይሆን በማሳነስ በማስረዘም ሳይሆን በማሳጠር እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ የኔንም ፅሑፍ እንደዛው ልብ ልቻሉልኝ
እንደሚገባ በአደራ ጭምር እፅፋለሁ፡፡
እስኪ እየተወሰዱ ካሉት መፍትሔዎች እንጀምር፡-
አንደኛ በታክሲዎች ላይ የተወሰዱ የታፔላ ሥምሪቶች ከቀድሞው የታክሲ የትራንስፖርት አገልግሎት በተለይ “ጥናት” ተደርጎበት በታፔላ
መሠማራት ከተጀመረ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው፤ መፍትሔው ምን ይህል አመርቂ ነው? ምንስ ችግር አለበት? የታዘብኩትን ላካፍላችሁ ሲጀመር
ካልተሳሳትኩ “ጥረቱ” መሰረታዊ ችግሩን ያገኘ አይመስለኝም የዚህ ዘርፍ ሊቃውንት ችግሩን ማግኘት የመፍትሔውን አጋማሽ ማግኘት ነው
ይላሉና፡፡ በመቀጠል የተሳሳትኩ እኔ ካልሆንኩ በቀር ውጤታማ የሆነ ጊዜ ያልተወሰደበት እና በትራንስፖርቱ ዘረፍ ላይ ብስለት ያነሳቸው ሰዎች በይድረስ ይድረስ ያጠኑትና
መፍትሔውን ሳይሆን ችግሩ ምን ያልደረሱበት ይመስለኛል፡፡ ይኽ ችግር ደግሞ ተደራራቢ ችግር በመሆኑ የተጠቃሚውን ትከሻ ያጉበጠ የመማር
ማስተማሩ ሂደት ላይ ጠባሳ የጣለ፤መንግሥት ለተያያዘዉ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ሰራተኛው በሰዓቱ ገብቶ ግዴታውን እንዳይወጣ
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኗል፡፡ ይኸ ብቻ አይደለም በታክሲዎች ላይ የሚታየው ችግር የወለደው ችግር ዛሬ ዛሬማ ችግሩ ሳይፈታ
በችግር ላይ ችግር ፤ በኑሮ ወድነት ላይ ሌላ ውድነት ህብረተሰቡ እንዲሸከመው የታሪፍ ማሻሻያ ይጨመራል የሚያሳዝነው ግን ጭማሪው
በተደረገ ጊዜ በዜና ሲነገር አንድንድ የዜና ማስራጫዎች የዋጋውን መጨመር በማስመለክት ያዘጋጁትን “ የህብረተሰቡን የመክፈል አቅም
ባገናዘበ መልኩ ብለው መዘገባቸው በጣሙን የሚያሳዝን ነበር፤ የሚገርመው ነገር እንኳንስ የታሪፍ ጭማሪዉ የደመወዝ ጭማሪውም የህብረተሰቡን
አቅም ያላገናዘበ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነበር፡፡
ከነዚህ ሁሉ ባሻገር ደግሞ ሁሉ ነገር ሆኖ የተከፈለው
ተከፍሎ ታፔላውም አሰማርቶ ወደ ምንፈልገው በሠዓቱ በሰላምና በጤና ያለስጋት ብንደርስ መልካም ነበር ማቆራረጡ ጨምሯል፤ አብዛኛው
የታክሲ መቀመጫ ወንበሮች ጨርቃቸው የቆሸሸ ፤ ወንበሩ የተሰበረ፤ የመስኮቶቹ መስታወት የማይዘጋና የማይከፍት፤ ……ወዘተ በአጠቃለይ
ከይቅርታ ጋር ቆሻሻ ማለት ይቀላል፡፡ ይኸ ከመሆኑ የተነሳ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት እያገኘ አይደለም እስኪ በታክሲ ላይ
ከሚያጋጥመን መካከል ያጋጠመኝን ልንገራችሁ ብዙ ቀን /ሁሌም ማለት ይቻላል/ ያለፍላጎት ጠጋ በል ተብዬ ተጭኜ አውቃለሁ፤ አንድ
ቀን ከማዘጋጃ ቤት ልደታ ለመሄድ ስጋፋ ከላውንደሪ ከወጣ በመጀመሪያው ቀኑ የለበስኩት ሙሉ ልብ ታክሲ ላይ ስጋፋ አውቀው በድፍረት
(በተንኮል) ሳያውቁም በስህተት (በቸልተኝነት) የቀቡት ግሪስ ልብሴን አበላሽቶታል፤ አንድ ቀን እንዲሁ የለበስኩት ከተገዛ ላውንደሪ
ያልገባ ልብስ ከወንበሩ መቀመጫ የወጣ ብረት ሱሪዬን ቀዶብኝ አዝኛለሁ፡፡ ያለአግባብ ክፍያን ተው ባይ በመጥፋቱ ልከፍል ተገድጃለሁ
ለምሳሌ ከሰሜን ማዘጋጀ ፒያሳ ሂሳብ በአጭር ጉዞ ሲከፈል፡ ከፒያሳ /ጊዮርጊስ/ እስከ ሾላ ግን በዚህ ታሪፍ መጓዝ አይቻልም እንደዚሁ
ከአምባሳደር ሲኒማ ቤት እስከ ቱሪስት ሆቴል በረጅም ጉዞ ሲከፈል ከቱሪስት ሆቴል እስከ አምባሳደር ድረስ ግን በአጭር ጉዞ ይከፈላል፡፡
እኔ ደግሞ ያላየኃቸው አንባቢ/ተጓዥ/ የታዘበው ብዙ ይኖራል ታዲያ ይህንን ጉዳይ ባለድርሻ አካል ወይም የሚመለከተው ክፍል ምን
ይላል?
ሰሚ ካገኘሁ ታሪፍ ላይ ትኩረት ይሰጥ በኪሎ ሜትር ክፍያ
ላይ፤ ሲጫን አይቆራረጥ፤ ታፔላውን እየተመለከትን በሥርዓት የምንጓዝ ተጓዦ እንሁን፤ በትራንስፖርት አገልግሎት ፅዳት ይኑረው፤ የአገልግሎት
ዘመናቸው ያለፈባቸው መኪኖች መፍትሔ ይሰጣቸው (የአግልግሎት ማብቂያ ዘመን ይኑራቸው)፤ ነዳጅ ለመቅዳት ህብረተሰቡን ይዞ ማደያ
ውስጥ አይግባ፤ ነዳጅ አለቀ በሚል ሰበብ በየመንገዱ አንጉላላ፤ ወዘተ….ጆሮ ያለው ይስማ፡፡
እስኪ ደግሞ ወደ ሚዲ ባስ /ሐይገር ባስ/ አለበዚያም
“የአገር ባስ” ወደሚባሉት እንምጣ እንደሚታወቀው እነኚህ ሚዲባሶች አመጣጣቸው የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት ካደረጋቸው
ጥረቶች ዋና ማመላከቻ በመሆኑ የሚቀርቡ ናቸው ነገር ግን የሚጠበቀውን
ያህል መፍትሄ ባይሰጡም የሚቻላቸዉን ያህል ጥረት እያደረጉ በአንዳንድ መስመሮችም ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን
በአንዳንድ መስመሮች ላይ በጭራሽ እንዳትደርሱ የተባሉ ይመስላሉ፤ምነው መፍትሔውን እየሰጠ የሚገኘው የሥራ ክፍል እነዚህን መኪኖች
በታፔላ አላሰማራቸውም?
ሌላኛው ለረጅም ዓመታት የአንበሳን ድርሻ ይዞ የዘለቀው
የህብረተሰቡ “አጋር” የሆንን ዛሬ ግን ምንም አይንት የታዳሽ ሃይል ቢጠቀም የህብተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት አቅም ያጠረውና ችገሩ
መፍትሔ ያጣለት የሚመስለው አንበሳ የከተማ አውቶብስ ነው፡፡
ይህ ድርጅት ለዓመታት በትራንስፖርት አገልግሎት እንደ ሥሙ አንበሳ ነበር አሁን
አሁን ግን ከህዝብ መባዛት የተነሳ አቅም አንሶታልና መታደስ ያለበት አለበለዚያም የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ክፍል ሊያስፈልግ
ግድ ነው፡፡ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ/ አንበሳውን የሚያግዝ፤ አንበሳውን የሚመራ…… ወዘተ ካለ አቤት ይበል፤ ለችግራችን ዘላቂ
መፍትሔ ይስጥ፡፡ ጥቂቶች አፋጣኝ መፍትሔ ለመስጠት በአክሲዮን ተደራጅተው ገንዘብ አሰባስበው በተለያየ ስም መምጣታቸው የቅርብ ጊዜ
ትውስታ ነበር ነገርግን የደረሱበትን እግዚአብሔር ይወቀው የውኃ ሽታ ሆነዋል፡፡
ለምንድን ነው የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ያስፈለገው?
በአጨሩ አንበሳው ችግር ስላለበት መታደስ፤ መለወጥ፤ መተካት፤ ስላለበት ነው፡፡ አቅም ማጣት ስለታበት፡፡
የአንበሳ የከተማ አውቶብስ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ
አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አድማሱንም በማስፋት ቁጥሩንም በመጨመር ከ450 እስከ
500 እና ከዛ በላይ የሚሆኑ መኪኖችን በዕለት በማሰማራት መጠነ ሰፊ አገልግሎት በመስጠቱ የሚያክለው የለም፡፡ ይህ ድርጅት ሊመሰገኑ
ከሚገባቸው አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ካልተሳሳትኩ በመመስገን ቀዳሚ ሥፍራውን ሳይዝ አይቀርም፡፡
ይሁን እንጂ ይኸ ዕድሜ ጠገብ ተቋም “አንበሳ ሲያረጅ
…” እንደሚባለው በማርጀቱ ምክንያት ብዙ ለውጥ ያስፈልገዋል ልንዘነጋው የማይገባ ጉዳይ ይህንን ተቋም ለማሻሻል መንግሥት ያላሰለሰ
ጥረት አድርጓል መዋዕል ንዋያትንም አፍስሷል ማናጅመንቱን አስተካክሏል፤ መኪኖችን አድሷል አሮጌውን በአዲስ ተክቷል፤ ቁጥራቸውን
ጨምሯል …… ነገር ግን “ለውጥ የለውም” ወይም የሚጠበቀውን ያህል
አልተገኘም ምነው ቢባል የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ አስፈልጎታል፡፡የአንበሳ ችግር እንዲህ ጥቂት አይደለምና፤
ጠንካራ ጎኖቹ እንዳሉ ሆነው እስኪ ጎልተው የሚታዩትን
ችግሮች በወፍ በረር እንያቸው ከሚሰጣቸው አገልግሎቶችና መሰመሮች ለምሳሌነት በሰሜን በር መግቢያ ከአዲሱ ገበያ ፤ ፒያሳ ካሳንችስ፤
ሃያሁለት መገናኛ ተርሚናል የሚገባውን 80 ቁጥረን ከዚያው ከአዲሱ ገበያ፤ ፒያሳ፤ ሸበሌ፤ቄራ፤ የሚጓዘውን 6 ቁጥር የአንበሳ አውቶብስ
በንፅፅር እንመልከት ስድስት ቁትር ሰዓቷን ጠብቆ ከመምጣቷ ባሻገር በበቂ ሁኔታ ተደራጅቶ ብዙ ጊዜ ልዩ በመሆን ከአዲሱ ገበያ ጊዮርጊስ
ሚኒልከ አደባባይ ድርስ በቅናሽ ዋጋ አገልግሎቱን ይሰጣል ፤ ሰማንያ ቁጥር ለምሳሌ ጠዋት የመጀመሪያዋ 12፡45 ሰዓት ከሄደች ሁለተኛዋ
ለሰራተኛም ለተማሪም ሳትሆን በሄደችበት እየለመደች ለዚያውም ካልተበላሸች መጥታም ልዩ ብላ ካልሄደች አልፎ አልፎ ምክንያቱ ይህ
ነው በማይባል ሁኔታ ዘግታ ካልሄደች 1፡45 ሰዓት ወይም 2፡00 ሰዓት ጥመጣለች ይኸ ማለት ለ0.30 ሰዓት ወይም ለ1፡00 ሰዓት
በመቆም ከተጠበቀች በኋላ መሆኑ ነው፡፡ ከዚያም ካለፈ እንደቸርነቷ ካላደረገች 2፡30 ሠዓት 3፡00 ሰዓትም ይሆናል ከልካይ የላትማ
በነገራችሁ ላይ አንድ የሚገርመኝ ነገር አለ ተቆጣጣሪ ወይም ስምሪት ተብለው የሚመደቡት ወይም አይቆጣጠሩ ወይ አያሰማሩ ብቻ ቦታውን
የያዙት ሰዎች የባህርይ አንድነታቸው የአስተሳሰብ አድማሳቸው አንድ መሆን የሚገረም ነገር ነው፡፡
ይህንን ያህል ካልን አንበሳ የከተማ አውቶብስ ሌላኛው
ችግሩ ምንድን ነው? እጠቡኝ አፅዱኝ የሚለው ንፅህናው አሁንማ ይባስ ብሎ ከተገጣጠመው ወራትን ያስቆጠሩት ቢሸፍቱ ባስ እንኳን ሳይቀር
አቧራ እየለበሱ ይገኛሉ፡፡ የከተማ አውቶብስ መሆኑ ቀርቶ የክፍለ ሀገር መኪና ይመስል ከክረምት እስከ በጋ ጭቃ ለብሷል ከዚህም
ባሻገር ከንፅህናው ጉድለት የተነሳ የአንዳንድ መስመሮች አውቶብስ “ሽታዬ” የሚል ቅፅል ስም እየወጣላቸው ይገኛሉ፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ጥንቃቄ ማድረግ ረጋ ብሎ ማሽከርከር የሚበረታታ
ትልቅ ነገር ሲሆን ከዚህ ባሻገር ግን ከፍጥነት በታች በሆነ መልኩ በመጠበቅ ብዛት ጨጓራዉ የተመለጠውን ተሳፋሪ በየመንገድ የሚያሳርሩ
አሽከርካሪዎች አይታጡም፡፡ ጥሩዎችንም እዚጋ ልንዘነጋ አይገባም፡፡
ሦስተኛ ቅድም ከመዘግየት ጋር ተያይዞ እንደተነሳው ወጥተው
ሰው የስራ ሰዓት እየረፈደበት ጸሐይ እየመታው /ክረምት ሲሆን ዝናብ እየደበደበው/ ለረጅም ሰዓት ሳይጭኑ መቆም ከመጡም በኋላ ቲኬት
ቆራጮች የማስተናገድ ፍላጎት አለመታየት በዝርዝር አማካይነት ማመናጨቅና ማጉላላት (ህብረተሰቡም በዝርዝር በኩል አስፈላጊውን ትብብርና
ቅድመ ዝግጅት ያደርግ ዘንድ መልዕክቴን አስተላልፋሁ)
በአራተኛነት ረገድ መስመሮችን እየዘለለሉ መሄድ (መቆም
የሚገባቸው ቦታ አለመቆም) ተጠቃሚው በአግባቡ እንዳይስተናገድ በሮችን በአግባቡ አለመክፈት አንዳንዴ እንዲውም ለሚያዉቁት ሰው ብቻ
የፊተኛውን በር መክፈት ተከትሎ የገባውንም ማመናጨቅ፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሊታይ የሚገቡ ጉዳዮች በብልሽት ምክንያት ህብረተሰቡን
በየመንገዱ የሚያጉላሉ ተበላሽተዋል ተብሎ መሥመር እየዘጉ መመለስ የተከፋለም ሂሳብ እንደ ቴሌ የህዝብ ሥልክ ዋጥ አድርጎ ማስቀረት
ቋሚ ተግባሩ ሆኗል፤ ቲኬት ቆራጮችም መበላሸቱን እየተመለከቱ ትኬት እየቆረጡ መልስ መልሽ አትመልሽ በመባባል አምቧጓሮ የሚፈጥሩም
እየታዩ ይገኛሉ፡፡
በአምስተኝነት ተራ ቁጥር ላየው የወደድኩት ነገር ቢኖር
ድርጅቱም አፋጣኝ መፍቴ ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ የመስመሩን አመልካች ቁጥር በጉልህ አለማሳየት ይልቁንም በአዳዲሶቹ መኪኖች ላይ
ጉልቶ የሚታየው የቁጥር አፃፃፍ ነው ምን ተብሎ ነው(በሰለጠነ ሲስተም ላይ ችግር እንቅፋት መፍጠር) የተለያዩ የማየት አቅም ባላቸው
በተለያየ የትምህርት ደረጃ ላይ ላሉ ላለማንበብ በቋፍ ላይ ላለ ማኀበረሰብ በእስክሪብቶ መፃፍ ከዚህም ባሻገር በጀርባው በኩል ጽሑፍ
አለመኖር የድሮዎቹም ቢሆኑ ሲጀምሩ አይታዩ ከፊት ለፊት ካመለጠ በኋላ ለማየት በአቧራ መሸፈኑ የሚገረም ሆኖ ሳለ አፋጣኝ መፍትሔ
የሚያስፈልገውና አፅንኦት የሚያሻው ጉዳይ ነው፡፡
ጐበዝ ታዲያ የትራንሰፖርት ዘርፉን ችግር ስንመለከት የአንበሳውን ድርሻ በኑሮአችን ውስጥ ይዘው ለዘመናት ሲያገለግሉን
ቆይተው ዛሬ ከተኙበት አልነቃ ያሉትን እነዚህን ክፍሎ የሚተካ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ አያሻውም ትላላችሁ? ታዲያ ማን የአንባሳውን
ደርሻ ይውሰድ?
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ