ስኬታማ ተቋም
ተቋም ፡- ማለት የብዙ ግብአት ዉህደት ሲሆን አንድን ተቋም ስኬታማ ለማድረግ አለበለዚያም
በመቋቋም ላይ ያለን ተቋም ከግንባታዉ ጀምሮ ስኬታማ ለማድረግ ከታሰበ እያንዳንዱ ግብአቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በእኩል በልዩ አትኩሮት
መገንባት ግድ ይላል፡፡
ለዛሬዉ
አንድን ተቋም ስኬታማ አድርጎ ከጅምሩ ለመፍጠር ጠቃሚ ከሆኑት ዉስጥ ጥቂቱን እንመለከታለን፡፡
1)
የሥራ አከባቢን ምቹ
ማድረግ፡- በተለያዩ ቁሳቁስ ማሟላት/ ማደራጀት፤
2)
ሰዉ መፍጠር፡- ሰዋዊ ባህሪ ያለዉና ሰዉ ሰዉ የሚሸት ማንነት የተላበሰ ሰራተኛ በእዉቀት፣ በክህሎት
እና በቀና አመለካከት የዳበረ መገንባት፤
3)
የሚተገበር ራእይ ማዘጋጀት፡- ራእይ የሌለዉ ተቋም በዉሃ ላይ እንደሚንሳፈፍ ኩበት አለበለዚያም ወንዝ ዳር እንደበቀለ
ሸንበቆ ነፋስ ወደ ነፈሰበት የሚሄድ መሆን ነዉ፤
4)
የሚያሰራ መዋቅር መዘርጋት/መፍጠር፡- ወጥነት ያለዉ፣ መነሻና መድረሻ ያለዉ መዋቅር ወሳኝ ነዉ፤
5)
መፈተሸ፡- ከላይ የተጠቀስናቸዉ ነገሮች ወደምንፈልገዉ ግብ(ስኬታማነት) ያደርሱናል አያደርሱንም?
እስከ ዛሬ በመጣነዉ ለምንፈልገዉ ግብ እየቀረብን ነዉ? ወይንስ ገና በብዙ ርቀት ላይ ነን?
6)
እርምት መዉሰድ፡- ጉዞአችን ወደ ግባችን የማያደርሰን ከሆነ ፈትሾ ማስተካከያ መስራት ግድ ነዉ፤ ሁሌም
በአንድ መንገድ / አካሄድ መጓዝ አግባብ ስላልሆነ፡፡
ስኬት ምንድን ነዉ?
ስኬት
ማለት የአንድ ዓላማ አፈፃፀም ማለት ነዉ፡፡አንድ አላማ አፈፃፀም በስኬትም በዉድቀትም ሊጠናቀቅ ይችላል፤ ለዛሬ የምንዳስሰዉ ስለ
ስኬት ስለሆነ እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል እና ስለ ስኬት እንዳስሳለን፡፡
ፀሐፍት
የስኬትን ምሥጢራት እንዲህ አስቀምጠዉልናል፡-
I.
ተነሳሽነቱን መዉሰድ/ስኬታማ
ለመሆን ሃላፊነቱን ለራስ መዉሰድ
II.
የመጨረሻዉን/መድረሻችንን
በአእምሮአችን ይዘን /አስቀምጠን መጀመር
III.
ቀዳሚ ነገሮችን ማስቀደም
(ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት)
IV.
ሁለቱም ወገን አሸናፊ ስለሚሆንበት
ማሰብ
V.
ቅድሚያ ሌሎች እርስዎን እንዲረዳዎት
ሳይሆን እነርሱን ለመረዳት ጊዜ ይስጡ
VI.
ቅንጅትን /አብሮነትን መፍጠር/ከአንድ
ሁለት ይሻላልና/
VII.
መጋዙን መሳል/ ዘወትር ለመቁረጥ
ስለት ያለዉ ለመሆን መዘጋጀት
እንግዲህ
እነዚህ ምሥጢራት በአግባቡ ከተገበርን ስኬት የምርጫ ጉዳይ ነዉ፡፡
ስኬት
አጥብቆ የመፈለግ እንጂ የምኞት ዉጤት አይደለምና አጥብቀዉ ይፈልጉ፤
ጠንክረዉ ይስሩ፡፡
ስኬት
የህልምም ዉጤት ስለሆነ ህልምዎ እንዳይደናቀፍ ህልምዎን አጋርዎ ካልሆነ ሰዉ ዘንድ ያርቁት፡፡ ( ህልምና ፅንስ መሬት እስኪይዝ
ድረስ ሊጨናገፍ ይችላልና፡፡ እንደዉም እናቶች ሲያረግዙ ፅንሱ ሶስት ወር እስኪሞላዉ ለማንም አይናገሩም)
̎ ስኬት የቀና አመለካከት ፅንስ የጠንካራ ተግባር ልጅ ነዉ፡፡ ̎
1.
የሥራ
አከባቢን ምቹ ማድረግ
የሥራ
አከባቢ ሥንል ሥራን ለማከናወን ብቻ መሆን የለበትም ምክንያቱም በየዕለት ተዕለት ህይወታችን ዉስጥ ከ37% በላይ ጊዜያችንን የምንኖረዉ
የመኖሪያ ሥፍራችን መስሪያ ቤታችን አከባቢ ነዉና፡፡ ስለዚህ የመስርያ ከባቢያችን ለመኖር ምቹ መሆን ይኖርበታል፡፡
ምቹ፡- ፅዱ፣ አረንጓዴ፣ ማራኪ፣ ሰላማዊ፣ ከክፋት፣ ከተንኮል፣ ከቂም፣ ከጥላቻ፣ ከአላስፈላጊ
አለመግባባት፣ ወዘተ በአንፃራዊነት የፀዳ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
1.1.
ለሠራተኛ ምቹ፡- ለመስራት የሚጋብዝ
መሰረተ ልማት የተሟላለት፡- ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ኮምፒዉተር፣ ኔትወርክ፣
የጽህፈት መሳሪያ ቁሳቁስ፣ ወዘተ
የመስርያ ቁሳቁስ፡- በስምና በቁጥር ኮምፒዉተር፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ … አንድ፣
ሁለት፣ ብለን የምንጠራቸዉ ሳይሆን በትክክል የሚሰሩ፣ የሚያገለግሉ፣ ተገልጋይን የማያጉላሉ፣ አገልጋይን ላሰበዉ ስኬት መንገድ ጠራጊ
የሚሆን እንጂ እንቅፋት የሚሆኑ መሆን የለባቸዉም፡፡
እንደዚህ
ዓይነት ቁሳቁስ ከመኖራቸዉ ይልቅ አለመኖራቸዉ ይጠቅማልና፤ ምክንያቱም ባለሙያዉ አለመኖራቸዉን አዉቆ ይሟላልኛል ብሎ በሥራ ተነሳሽነት
እና በትልቅ ተስፋ ይጠብቃልና፡፡ አንድም በተቋማት ዉስጥ ትልቅ ትኩረት የሚያገኘዉ አንድን ያረጀ ነገር ከመቀየር የሌለን ነገር
ማሟላት ስለሚቀላቸዉ፡፡ የለዉም ከሚለዉ ይልቅ ይቀየር ለሚለዉ ጆሮ ስለማይሰጡ፡፡
1.2.
ለሥራዉ ደህንነት፡- ምሥጢሩ ተጠብቆ ተኣማኒነት ተረጋግጦ መስራት አለበት፤
ደህንነቱ የተጠበቀ፡- ፋይል ማስቀመጫ፣ ለአደጋ ተጋላጭ ያልሆነ
አከባቢ፣ ለዝርፍያ ተጋላጭ እና ሰነዶች ለመሰወር፣ ለመሰረዝ፣ ለመደለዝ፣ ተጋላጭ የማይሆን ሥፍራ ወዘተ
2.
ሰዉ መፍጠር
ሰዉ
ማለት ሰባቱ ባሕርያት የተሟሉለት ቆሞ የሚሄድ ፣ ሮጦ የሚያመልጥ፣ አባሮ የሚይዝ፣ ወጥቶ የሚገባ፣ ሰርቶ የሚበላ፣ ወዘተ የሚለዉ
እንዳለ ሆኖ ከዚህ ባሻገር ጭንቅላቱን ፣ አስተሳሰቡን፣ እዉቀቱን፣ ጉልበቱን፣ ሃብቱን፣ ወዘተ ተጠቅሞ ዓለምን መለወጥ የሚችል ፍጡር
ነዉ፡፡
ይቀጥላል ...
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta