እሑድ 8 ማርች 2020

ሴቶች ተቋምን ለመፍጠር ያላቸዉ ብቃት March 8

ሴቶች ይችላሉ።

ከዚህ ቀደም ስለ ተቋም ስኬት እየተነጋገርን እንደነበረ ይታወሳል ለዛሬ ከዚያው ቀጣይ ክፍል የተቀነጨበ ስለሴት ልጅ ችሎታ የሚያረጋግጥልን ጽሑፉ መታሰቢያነቱ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ላሉ ሴቶች እና ህልማቸውን እንዳያሳኩ በማይረቡ ጭንጋፍ ወንዶች የተሳናከለባቸው የታገቱ እህት ተማሪዎች ይሁንልኝ።

$$$$$$$$$$$$$$$$$

2. ሰው መሥራት

የአንድ ሰው ዋጋ እጅግ ውድ እና በምንም የመገበያያ ገንዘብ ሊተመን የማይችል ነው፤ በአንድ ተቋም ውስጥ ከሰው የሚበልጥ ነገር የለም።
ስለዚህ የሰራተኛን አመለካከት፣ የሰራተኛን ችሎታ፣ የሰራተኛውን አቅም ማሳደግ ከሁሉ ነገር መቅደም ይገባዋል።
ለውጤታማነቱ ተከታታይነት ያለው ክትትል በጥንቃቄ ሊተገበር ይገባል።
እርስ በርስ ፍሬያማ የሆነ ውድድር እንዲኖር አዎንታዊ የእርስ በርስ ተቋማዊ ውድድር እንዲኖር ማድረግ አንዱ ሰው የምንሰራበት መሣሪያ ነው።
ሰው በዚህ መልኩ በጥሩ ሁኔታ ከተገነባ ጠንካራ የሰው ሃይል ስኬታማ ተቋምንም ሆነ አገርን መገንባት ይቻላል።
አገርንም ሆነ ተቋምን በጠንካራ መሠረት ላይ ለመመስረት የሴቶች ተሳትፎ ትልቅ ድርሻ አለው፤ ሴቶች ትውልድን በመቅረጽ ላይ ትልቁን ሚና ስለሚጫወቱ።
አገራትም ሆኑ ተቋማት የሴቶችን ቁጥር በመጨመር ለዘላቂ ስኬት መትጋት ይኖርባቸዋል።
በምሳሌ ላስረዳ:- ሴት ከሁሉም የሰው ፍጥረት ጋር ቀዳሚ እና ዘላቂ ቁርኝነት ስላላት ሚናዋ ከፍ ያለ ነው። ምክንያቱም ሴት ልጅ የወንድ ልጅ የተፈጥሮ አጋር ከመሆኗ ባሻገር እናት ነች፣ (ልጇን በስነምግባር አንጻ ለስኬት ብቁ አድርጋ መቅረጽ ትችልበታለች) ሞግዚት ናት፣ (ጤናማ እና በአካል የዳበረ ለትምህርት እና ለሥራ ዝግጁ የሆነ ዜጋ መፍጠር ትችላለች)፣ የሥራ ሃላፊ ነች፣( በቅርበት በእናትነት እና በእህትነት ጸጋ የሥራ ባልደረቦቿን የተጣመመውን አቃንታ የተበላሸውን አስተካክላ ለመጓዝ የሚያክላት እና ከርሷ የተሻለ ልምድ ያለው የለም)፣ ሚስት ናት፣( ባለቤቷን ለተሳካ ውሎ በደስታ እና በተነቃቃ መንፈስ ከቤት መሸኘት የምትችል በውሎው ደስተኛና ስኬታማ እንዲሆን የምታስችል መግነጢሳዊ ጸጋ የተላበሰች ነች) እህት ናት፣( ትንሽ ሆና ትልቅ በእድሜ አንሳ አስተሳሰቧ ትልቅና ሐላፊነትን መሸከም የሚችል ነው።)
ይህ ሁሉ ሴትን ልጅ የዚህ አለም ማጣፈጫ ጨው ናት ብንል ማጋነን አይሆንብንም ሰው መሥራት ትችላለችና።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...