በክፍል
አንድ እንዴት ስኬታማ ተቋም መፍጠር እንደሚቻል በጥቂቱ መዳሰስ ጀምረን በይደር ማቆየታችን ይታወቃል ክፍል ሁለትን እነሆ፡-
ሰዉን
እንዴት መፍጠር ይቻላል?
ሰዉ
በእግዚአብሔር በአርአያዉ እና በምሳሌዉ የተፈጠረ ሆኖ እንዴት ድጋሜ መፍጠር ይቻላል? የሚሉ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ አዎ! ጥያቄዉ
ጤናማ ነዉ፡፡
ሰዉ
በፆታ ወንድ እና ሴት ተብሎ በሁለት እንደተከፈለ ሁሉ ሰዉ ሆኖ በእኩልነት አንድ ሆኖ ሊያስቀጥለዉ የሚችለዉን ማንነት መፍጠር ይቻላል፡፡
እንዴት?
ሰዉን
መፍጠር የሚቻለዉ በሶስት ነገር ነዉ፤
1.
በእዉቀት፡- አከባቢዉ ላይ በሚገኘዉ የትምህርት ተቋም በማስገባት ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ
የትምህርት ተቋም በሚፈለገዉ መስክ በማስገባት ማሰልጠንና እዉቀት እንዲገበይ እና በዚህ መንገድ በተለያየ የሙያ መስክ መፍጠር ይቻላል፡፡
2.
በክህሎት፡- ከትምህርት ባሻገር በተሰማራበት የሙያ መስክ ከተቀጠረበት ተቋም የሥራ ባልደረቦች ጋር
በመሆን ክህሎት (experiance) ማዳበር ይቻላል፤ በዚህም ራስን የሙያ ባለቤት ማድረግ ሌሎችንም ክህሎቶቻችንን በማጋራት ሌሎችን
መፍጠር ይቻላል፡፡ ስለዚህ ሁለተኛዉ ሰዉን የምንፈጥርበት መንገድ ክህሎትን በማዳበር ይሆናል ማለት ነዉ፡፡
3.
በአመለካከት፡- አመለካከትን በሁለት እንከፍለዋለን፡፡ አዎንታዊ (positive) እና አሉታዊ (Negative)
ብለን፡፡ ለጊዜዉ አሉታዊዉን ወደ ጎን በመተዉ ከላይ ከጠቀስናቸዉ ሰዉን የመፍጠሪያ መንገዶች ጋር ተጣጥሞ ሊሄድልን የሚችለዉ አዎንታዊዉን
/ቀና/ አመለካከቱን እንዳስሳለን፡፡
ቀና
አመለካከት ስንል አንድ ሰዉ እንዲሁ በቀላሉ ቀና ሁን ስለተባለ ብቻ ከመሬት ተነስቶ ቀና የሚሆንበት አጋጣሚ የለም፡፡ ጥረት ፣
ልማድ፣ ተሞክሮ፣ ሊኖር ግድ ይላል፡፡ እንዲህ ቀላል ቢሆን ኖሮ አለም በጠቅላላ መንገዷ አልጋ በአልጋ በሆነ ነበር ነገር ግን አይደለችም፡፡
አመለካከት/አስተሳሰብ
መርጠን የምንይዘዉ/ የምንለማመደዉ እንጂ የዕድል ጉዳይ አይደለም፡፡
(የመሪነት ጥበብ አጥኚዎች ተሰጥኦ / ክህሎት እና ቴክኒካዊ እዉቀት አንድ ላይ 20 በመቶ ድርሻ ሲይዙ
አስተሳሰብ /አመለካከት ለብቻ 80 በመቶ እንደሚይዝ ያረጋግጣሉ፡፡)
ለዚህም
ነዉ አስተሳሰቡ ያልተለወጠ ሰዉ ኑሮዉን ብትቀይርለትም አኗኗሩን ግን ልትለዉጠዉ አትችልም የሚባለዉ ሃሳብ በሚሄድበት ሰዉየዉ ተከትሎ
ይጓዛልና፡፡ አስተሳሰቡ ደሃ ከሆነ ሰዉየዉ ምንም ሐብታም ቢሆን በድህነት ዉስጥ ሲንቦጫረቅ እናገኘዋለንና፡፡
ስለዚህ
እነዚህን ሶስት መሰረታዊ የሰዉን ልጅ እንደ አዲስ ለመፍጠር የምንጠቀምበትን ግብአት በተናጠል ካየናቸዉ እንዴት አድርገን ነዉ አዲስ
ሰዉ የምንፈጥረዉ የሚለዉ ቀጣይ ጥያቄ ነዉ? እንዴት? የሚለዉ የሁላችንም ድርሻ ሆኖ ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ ብዬ ወደ ሌላ
ርእሰ ጉዳይ አልፋለሁ፡፡
የሰዉ
ልጅ የምንለዉ ፍጡር ሶስቱን (እዉቀት፣ ክህሎት፣ አመለካከት) በአንድ ላይ፣ ከሶስቱ ሁለቱን፣ አንዱን፣ ሊኖረዉ ይችላል፤ ነገር
ግን አንድን ተቋም ስኬታማ አድርጎ ለመፍጠር አለበለዚያም የመጨረሻ ግባችን ስኬታማነት እንዲሆን ከተፈለገ አንዱን ወይም ሁለቱን
አሟልቶ ወይም አጓድሎ ስኬታማ መሆን እንደማይቻል ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ ስለዚህ?
ስለዚህ
ሰዉን መፍጠር የምንችለዉ እነዚህን ሶስት ግብአቶች (እዉቀትን፣ ክህሎትና ቀና አመለካከትን) በአንድ እናዋህድለታለን
ማለት ነዉ፡፡ ይህ ነዉ ሰዉ መፍጠር የሚባለዉ የሸማ ጥበበኛ ድርና ማጉን አዋዱ ጥሩ እና ዉብ ልብስ እንዲሰራ፡፡
ሌላኛዉ
ጥያቄ እንዴት አድርገን ነዉ ሶስቱን በአንድ ማዋሃድ የምንችለዉ? የሚለዉ ነዉ፡- በዝርዝር እንመለስበታለን፡፡
የአንድ
መሪ ስኬት የሚወሰነዉ በመሪዉ ችሎታ ብቻ ሳይሆን በሚመራቸዉ ሰዎች ባህሪያት ፣ ዲሲፒሊን/ሥነ ሥርዓት እና ችሎታ መኖር ለመሪዉ
ስኬት ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ጥሩና መጥፎ መሪ እንዳለ ሁሉ ጥሩና መጥፎ ተመሪ አለና፡፡
1.
የለዉጥ አመራር
2.
የለዉጥ ሃይል/ሰራዊት/
ከላይ
የተቀመጡትን ሁለት የተቋም የማእዘን ድንጋይ (ሰራተኛ እና አመራር) እንዲኖረን የሚከተሉት ተግባራት በጥንቃቄ ልንከዉን ይገባል፡፡
i.
ሰዉ መምረጥ
ii.
ሰዉ መስራት/መፍጠር/
iii.
ሰዉ ማመን/ አመኔታ
መጣል/
iv.
ሰዉ መጠቀም
3. የሚተገበር ራእይ መኖር
ራእይ
ከተቋም ምስረታ ጋር አንዳንዴም ቀድሞ የሚቀመጥ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ራእይ የሚለዉን ከህልም ለይተን ማየት ይጠበቅብናል፡፡ ራእይ
በእንግሊዝኛ ቋንቋ Revelation ወይም Vision የሚል ፍቺ የሚሰጠን ስለሆነ አሁን የምንነጋገርበትን ራእይ ከ Revelation
ነጥለን Vision ላይ አትኩሮታችንን እናደርጋለን፡፡
አንድ
ተቋም እንደምናዉቀዉ ከሁለት ያልበለጠ ከአንድ ያላነሰ ራእይ ይኖሩታል እንደ ምሳሌ
ብንወስድ የኢትዮ ቴሌኮም ራእይ የነበረዉ ‹‹ ዓለም አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ
የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋም ሆኖ ማየት ነዉ፡፡ ››
ሌሎችንም ተቋማት ብንመለከት እንዲሁ ሊደረስበት ከሚፈልጉት የግብ አቅጣጫ ራዕይ ያስቀመጣሉ ማለት ነዉ፡፡ እነዚህን ራዕይ የጊዜ ገደብ እና ሌሎች ተያያዥ ነገሮች ይኖራቸዋል ማለት ነዉ፡፡
ራዕያችን
ሊኖሩት ከሚገቡ ባህርያት ዉስጥ በዋነኛነት ሊተገበር የሚችል ባህሪያት ሊኖሩት ይገባዋል፡፡ ለምሳሌ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ‹‹ የእናቶችን
ሞት መቀነስ ›› በሚለዉ ፈንታ ‹‹ የእናቶችን ሞት ማስቀረት ›› ቢል ቃሉ ምንም እንኳን ያማረ ፣ ደስ የሚያሰኝ
ቢሆንም ተግባር ላይ ግን ብዙ ተግዳሮቶች ይኖሩታል፡፡ ስለዚህ ራዕያችን
የሚተገበር መሆን አለበት፡፡
ከዚህ
ጎን ለጎን ልንመለከተዉ የሚገባዉ ጉዳይ ከበላይ አካል በትእዛዝ መልክ ስለወረደ ብቻ ሳይሆን የመተግበር አቅሙንና ባህሉን መፈተሸ
ግድ የሚለዉ አመታዊ እቅዶቻችንም መሆን ይገባቸዋል፡፡ በስሜት 100% ለማቀድ መነሳት ጤናማነት አይመስለኝም፡፡ ፈፅሞም አይታቀድም
ማለት አይደለም እቅዶቻችን ዉስጥ በተናጠል ሊተገበሩ የሚችሉ አሉና ይካተታሉ፡፡ ከዚህም ባሸገር ሥናቅድ ነባራዊ እዉነታዎችን ግምት
ዉስጥ አስገብተን ሳይሆን ስሜታዊ ሆነን ይመስለኛል፡፡
4. የሚያሰራ መዋቅር/Structure/ መዘርጋት/መፍጠር
የአንድ
ተቋም መዋቅር ከመሬት ተነስቶ በተፈለገ ጊዜ የሚቀየር እና የሚተገበር ሳይሆን በባለሙያ በደንብ ተጠንቶ ለረጅም ጊዜ እንደሚያገለግል
ተደርጎ የሚዘጋጅ ነዉ፡፡ ስለዚህ በጥልቀት የምንዳስሰዉ ሳይሆን መዋቅር የሚያሰራ ሆኖ ሲዘጋጅ ያለዉን ጥቅም እንዳስሳለን፡፡ ከዚያ
በፊት ስለተቋም መዋቅር የተፃፈዉን ብንመለከት ጥሩ ይመስለኛል፡፡
‹‹ organizational structure helps a company assign a hierarchy
that defines roles, responsibility, & supervision. It’s the plan that
outlines who reports to whom & who is responsible for what. It’s usually
recorded & shared as an organizational chart that includes job titles &
the reporting structure. ››
ስለዚህ ከዚህ ፅሑፍ እንደምንረዳዉ አንድ መዋቅር የተቋሙ ማሕበረሰብ ያለዉን
ሚና፣ ሃላፊነት፣ ቁጥጥር ከዚያም ባለፈ አንድ እቅድ ሲታቀድ አፈፃፀሙን ማን ለማን ሪፖርት እንደሚያደርግ፣ ማን ለምን ኃላፊ እንደሆነ
ይተነትናል፡፡ በመቀጠልም የሪፖርት ማቅረቢያ አወቃቀሩን የሚያካትት ሰነድ ይኖረዋል ማለት ነዉ፡፡
እንዲህ ሲሆን አሰሪዉም ሰራተኛዉም አይቸገርም፡፡ እያንዳንዱን ተግባሩን ለማከናወንም
የተሳለጠ ይሆንለታል ማለት ነዉ፡፡ ያለዉ መዋቅር ዘመኑን ያልዋጀና ተቋሙ ከደረሰበት አቅም ጋር የማይሄድ ሆኖ ሲገኝ ተፈትሾ እርምት
እንዲወሰድበት ለሚመለከተዉ የበላይ ሃላፊ ቀርቦ በመፅደቅ ወደ ትግበራ ሊገባ ይገባል፡፡ የተቋም መዋቅር የሃይማኖት ዶግማ አይደለምና፡፡
5. መፈተሸ
ከላይ
ከተራ ቁጥር አንድ እስከ አራት የተዘረዘሩት እንደ ጊዜዉ ሁኔታ ያስኬዳል?
የታቀደዉን
እቅድ ያሳካል?
የታሰበዉን
ስኬት ያመጣል?
ከዘመኑ
ጋር ይሄዳል? ወዘተ የሚሉትን መፈተሸ ተገቢ ነዉ፡፡
የሚያስኬድ
ከሆነ አጠንክሮ መቀጠል የማያስኬድ እና ጉድለት ካለበት እርማት የሚያስፈልገዉ ቦታ ተፈትሾ ማረም ተገቢ ነዉ፡፡
6. እርምት መዉሰድ
እንዴት
ነዉ እርምት የምንወስደዉ? የሚለዉ ከተግባር ይልቅ ሙያ ይጠይቃል፡፡ ስለዚህ ባለሙያዎች አጥንተዉ ትክክለኛዉን አካሄድ ሃሳባቸዉን
ለሚያፀድቀዉ ክፍል ማቅረብ እና ማፀደቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ደረጃ ተቋምን ከዉድቀት መታደጊያ ደረጃ ነዉ፡፡
በመቀጠል
ከዚህ ቀደም በተራ ቁጥር ሁለት ላይ በጥቂቱ የዳሰስነዉ ሰዉን መምረጥ/መፍጠር (የለዉጥ አመራር ማብቃት) በሚለዉ በጥልቀት እንፈትሻለን፡፡
የሰዉ
ልጅ የለዉጥ ሃይል መሆኑ እሙን ነዉ ተቋማት ካላቸዉ ሃብት ዋናዉን ድርሻ የሚይዘዉና መተኪያ የሌለዉ (የሰዉን ቦታ ተክቶ የሚሰራዉን
ቴክኖሎጂ እንኳን የፈጠረዉ ሰዉ ነዉና) ሃብት የሰዉ ልጅ ነዉ፡፡
ስለዚህ
የለዉጥ አመራር፣ የለዉጥ ሃይል፣ የተቋም ሃብት … ‹‹ ሰዉ ›› ስለተባለዉ ትልቅ ፍጡር እንዳስሳለን፡፡
የሁሉንም
ነገር መዉደቅም ሆነ መነሳት የሚወስነዉ ሰዉ ነዉና፡፡
ይቀጥላል፡፡
ይቆየን፡፡
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ