ቤተክርስትያን በክርስቶስ ኢየሱስ ደም የተመሰረተች መሰረቶቿ
ከዐለት እጅግ የጠነከሩ፡ ሐዋርያት ከዳር ዳር ተዘዋዉረዉ ወንጌልን በማስተማር ያፀኗት፡ ሰማዕታት ደማቸዉን አፍሰዉ አጥንታቸዉን
ከስክሰዉ ያቆዩዋት፡ ደናግላን÷ መናኞች÷ባህታዉያን በገዳም ጤዛ ልሰዉ ድንጋይ ተንተርሰዉ ድምፀ አራዊቱን ፀበ አጋንንቱን ታግሰዉ
በፆምና በጸሎት ያቆዩዋት ቅድስት ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔር ደጅ
ነች፡፡ ከነዚህ ቤተክርስትያንን ለዛሬ ካደረሱት መካከል ሴቶች ከፊሉን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ሴቶች (እናት፡ ሚስት፡ እህት፡ … ከመሆን
ባሻገር ይልቁንም በአገራችን በኢትዮጵያ ትልቅ ተሳትፎ በሁሉም ስፍራ ሲያበረክቱ ይታያሉ፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ የገጠሯ ሴት በብዙ
ቦታ ጉልህ ድርሻ አላት፡ ልጅ ወልዳ አሳድጋ እድሜዉ ለአቅመ ትምህርት ሲደርስ እርሷ ሳትማር ልጇን ለትምህርት ያላትን ቋጥራ ከየኔታ
ጋር ሰዳ ፊደል ቆጥሮ፡ መዝሙረ ዳዊት ደግሞ፡ ቅዳሴ ተምሮ፡ ቅኔ ተቀኝቶ፡ … ቤተክርስትያንን እንዲያገለግል ወይም እርሱም መፅሓፍ
ዘርግቶ እንዲያስተምርና ተተኪ እንዲያፈራ የምታደርግ የቤተክርስትያን ባለዉለታ እና መከታ የሆነች ሴት ናት፤ ከዚህም ባሻገር የበረቱት
እንደ እማሆይ ጀማነሽ ያሉቱ መፅሃፍ ዘርግተዉ ደቀመዛሙርት ሰብስበዉ አስተምረዉ የሚያስመረቁ ሴቶች አልታጡም ይህ ሰማአዕትነት፡
ሐዋርያነት ነዉ፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስም ብዙ መልካም ስራን የሰሩ ለቤተክርስትያን ማገር ዋልታ የሆኑ ብዙ ተጠቃሽ ሴቶች አሉ፡ የሐዋርያትን
ፍኖት ተከትለዉ ከጌታ እግር ስር የተማሩ 36ቱ ቅዱሳን እንስት ሌላ
ተጠቃሽ ሴቶች ናቸዉ፡፡
ዛሬም ቤተክርስቲያን ልጆቿን የእግዚአብሔር መንግሥት የምታስወርስ የሴት
ሐዋርያ ትፈልጋለች /ያስፈልጋታል/፡፡
ሴት፡- ስንል ሌላ ተዓምር ማለታችን አይደለም እግዚአብሔር
በመልኩና በአርአያው በመጀመሪያ ከወንድ የፈጠራት ፍጥረት ማለት ነው፡፡ ሴት /ሔዋን/ የህያዋን ሁሉ እናት ከአባታችን ከአዳም የግራ
ጎን በተፈጠረች ጊዜ የቤተክርስቲያን መጽሐፍት /ታሪክ/ እንደሚነግረን ስላሴ የሰውን ልጅ እንፍጠር ብለው በተመካከሩ ሰዓት አብና
መንፈስ ቅዱስ አዳም ደካማ ባህርይ /የሚሳሳት/ ስለሆነ አንፈጥርም ሲሉ ወልድ እዋሰዋለሁ ብሎ ሊፈጠር ችሏል፤ ለዚህ ድካሙ ረዳት
አጋዥ ትሆነው ዘንድ የተፈጠረችለት የመዳን የብርታት የጥንካሬ ሐዋርያ ሌላ ወንድ አልነበረም ሴት /ሔዋን/ እንጂ፤
ዛሬም
ደካማውን መሳት ያለበትን አዳም ልትጥለው ልትገረስሰው ምክንያተ ስህተት የምትሆንበት ሳይሆን