እሑድ 19 ጃንዋሪ 2020

"ዳንኤልን" እንኳን ሰው ሠይጣንም ይፈራዋል (ክፍል 3)


በክፍል ሁለት ትዝታችን ነቢዩ ዳንኤልን የሥራ ባልደረቦቹ የሆኑ ሹማምንት በስልጣን ጥማት እና በሹመት ቅናት ከንጉሡ ጋር መክረዉ ህግ አዉጥተዉ ለርሱ ለመገዛት ወስነዉ ነገር ሸረቡ ዳንኤልም እንደጠበቁት ከወጥመዳቸዉ ገባላቸዉ፤ እዉን ንጉሥ ዳርዮስ እና ንግስተቱ ዳንኤልን እንደተባለዉ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ይከቱት ይሆን? አናብስቱስ ይበሉት ይሆንን?
‘’ ንጉሡም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ በጣም አዘነ ያድነዉም ዘንድ ልቡን ወደ ዳንኤል አደረገ፤ ሊያድነዉም ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ደከመ፡፡ ‘’ ዳንኤል 6÷14
ዳርዮስ ያስብ እንጂ አልተሳካለትም፤ አጣብቂኝ ዉስጥ አስገብተዉታልና፡፡
ዳንኤል ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣለ፡፡
በስተመጨረሻ ንጉሡም ዳንኤልን  የሚያመልከዉ አምላኩ እንደሚያድነዉ ያምናልና
‘’ሁል ጊዜ የምታመልከዉ አምላክህ እርሱ ያድንህ አለዉ’’
ሹማምንቱም ጉድጓዱን እንዳይከፈት የሚቻላቸዉን ሁሉ አደረጉ፤ ንጉሡም እያዘነ ወደ ቤቱ ሄደ እራትም ሳይበላ እንቅልፍም በአይኑ ሳይዞር አደረ፡፡

እሑድ 12 ጃንዋሪ 2020

ዳንኤልን እንኳን ሰዉ ሰይጣንም ይፈራዋል፤(special)


ነብዩ ዳንኤል ላይ ሹማምንቱ ለምን አሴሩበት?
ሹማምንቱ ንጉሡን ወጥመድ ዉስጥ ማስገባት ለምን ፈለጉ?
ዳንኤል ለምን ከነሱ የተለየ አቋም ኖረዉ?
የዳንኤል ከሹማምንቱ የተለየ አላማዉ ምንድን ነዉ?
ነብዩ ዳንኤል እዉን በሹማምንቱ ወጥመድ ይወድቅ ይሆን?
ንጉሡሥ በነብዩ ዳንኤል ላይ ዉሳኔዉ ምን ይሆን?
ዳንኤል መጨረሻዉ ምንድን ነዉ?
ዳንኤል ያቺ ሰላሳ ቀን እስክታልፍ ድረስ የልቡን እግዚአብሔር ስለሚያዉቀዉ እነሱ ያሉትን ለምን አይፈፅምም?
ዳንኤል ሹማምንቱ እንዳሉት በእጃቸዉ ቢወድቅ ሕጉ ቢፀናበት እንዴት ያልፈዋል?
እነዚህንና ሌሎችን ጥያቄዎች ቀጣይ ክፍል ይመልሰዋልና ይጠብቁን፡፡

ሐሙስ 2 ጃንዋሪ 2020

ዳንኤልን እንኳን ሰዉ ሰይጣንም ይፈራዋል፤ (ክፍል ሁለት)


መፅሐፍ ስለምርኮ በሚናገረዉ በዘመኑ ስለተደረጉት ዋና ዋና ድርጊቶች ሲተርክ በባቢሎን በስደት መኖርን ሲያነሳ ታላላቅ ሰዎች ብሎ ካነሳቸዉ መካከል ሕዝቅኤልና ዳንኤል ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡

ብልጣሶር፡- ትርጉሙ ቤል (የባቢሎን ጣኦት) ንጉሥን ይጠብቀዉ ማለት ነዉ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 46÷1
1)    የናቡከደነፆር የልጅ ልጅ የናቡናዲስ ልጅ፡፡ የአዲሲቱ ባቢሎን መንግሥት የመጨረሻ ንጉሥ፡፡
በመጠጥ ግብዣ ጊዜ በቤቱ ግንብ ላይ ፅሕፈት የምትፅፍ እጅ ታያቸዉ ፅሕፈቱም ፡- ̎ማኔ ቴቄል ፋሬስ̎ የሚልነበረ፡፡
ንጉሡም ደንግጦ ትርጉሙን ሲፈልግ ዳንኤል እንዲህ ብሎ ተረጎመለት፡፡
̎ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቆጠረዉ፣ ፈፀመዉ፣ በሚዛን ተመዝነህ ቀለህ ተገኘህ፤ መንግሥትህም ተከፈለ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ፡፡̎ ዳንኤል 5÷25-28
በዚያ ሌሊት የባቢሎን መንግሥት በፋርስ እጅ ወደቀ፡፡ ይህም የሆነዉ በ539 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነዉ፡፡ ዳንኤል 5÷1-30፣ 8÷1
  
2)    ለዳንኤልም የተሰጠ ሥም ነዉ፡፡ ዳንኤል 1÷7 በሥም እኩል በግብር ሥንኩል ማለት እንዲህ ነዉ፡፡

ዳንኤል ማን ነዉ?
የስሙ ትርጓሜ ፡- ̎ እግዚአብሔር ፈራጅ ነዉ̎ ማለት ሲሆን
ትዉልዱ፡- መጻሕፍት እንደሚሉት የተወለደዉ በ618 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ትዉልዱም ከይሁዳ ነገድ  ስለሆነ ከንጉሳዊ/ከመሳፍንት ቤተሰብ እንደሆነ ይገመታል፤ የዮናኪር የልጅ ልጅ ነዉና፡፡ ምነዉ ቢሉ ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም (የእስራኤል ንጉሥ) ልጅ ስለሆነ፡፡ የኢዮአቄም ዘመነ ንግሥናዉም ከ609 እስከ 598 ከክርስቶስ ልደት በፊት ማለት ሲሆን የነገሠዉም በ18 አመቱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አንዳንዶችም በ25 አመቱ እንደነገሠ ይናገራሉ፡፡ ዳንኤል ግን መሾሙን መጽሐፍ ይናገራል፡፡  ዳንኤል 1÷6

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...